Africa medical students councils official page
540 subscribers
122 photos
11 videos
24 files
44 links
Dear students
This channel helps you to get Books,Videos and Pictures which are reliable to the medical courses we are taking and aid us to get credible news about our college.which also promote extra academic performance of student's
👉 @AMCstudentsbot
Download Telegram
Make a share to your friends to join this informatics medical channels
#Share #share to ur friends to join
@AMCstudents
አስማ(Asthma )
አስም ምንድን ነው?
አስም የሥርዓተ መተንፈሻ አካላት የሚያጠቃ በሽታሲሆን የአየር
ቧንቧዎች መጥበብን(constriction) በማስከተል በአተነፋፈስ ላይ
ችግር ያመጣል፡፡የአየር ቧንቧችን በተፈጥሮ ከባዕድ አካላት እራሱን የሚጠብቅበት ተፈጥሯዊ መንገድ አለው ፡፡ ጤናማ ሠው
ለባእድ ነገር የምያሳየው ግብረ መልስ በአስም በሽተኞች
ላይ የተጋነነ ነው፡፡ ስለዚህ በሌላ ጤነኛ ሰው ላይ
የማይታዮ ምልክቶች በእነሱ ላይ ይታያል፡፡ በተለይ ይሕ ወቅት የቅዝቃዜ ስለሆነ እንደ አነሳሽ ምክንያት በመሆን ይጠቀሳል፡፡ ስለዚሕ ይሕ ችግር ያለበት ቀድሞ ከአለባበስ እና አመጋገብ ጥንቃቄ ማድርግ አለባቸው ፡፡ በተጨማሪም
እንደ የአበባ ብናኝ፣ አዋራ፣ የእንስሳት
ፀጉር የመሳሰሉ ነገሮች አስም ባለባቸው ሰዎች ላይ
ከበድ ያለ ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሎ ውስጥ ተጠቃሽ፡፡ አስም
ከላይ ለተጠቀሱትና ሌሎችም ነገሮች አለርጂክ
መሆንና ለእነሱም ተገቢውን በአለርጂክ ጊዜ የሚኖር
መልስ ማሳየት ነው፡፡
እነዚህ ባእድ ነገር ሲኖር የሚኖሩ መልሶች ጊዜያዊ
የሆነ የአየር ቱቦዎች መጥበብ ፣ የትንንሽ ቱቦዎች
(bronchial tubes) ማበጥ ፣ በሰውነታችን
የሚመረተው የአየር ቱቦ ፈሳሽ(mucus)
ከተለመደው በዛ ብሎ መመረት የመሳሰሉ ክስተቶችን
ያጠቃልላል፡፡ የትንንሽ ቱቦዎች (bronchial tubes)
ማበጥ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ጉዳት ከሚያመጡት
ለውጦች ውስጥ ይመደባል፡፡ በዚህም ምክንያት
ለተወሰነ ጊዜ አየር ማስገባትና ማስወጣት አስቸጋሪ
ይሆናል፡፡ ስለዚህም ሠውነት ኦክስጅን ወደ ውስጥ
ለመሳብ ብዙ ይቸገራል በዚህም ቶሎ ቶሎ ለመተንፈስ ይገደዳል፡፡በአስም
በሽታ ጊዜ የሚከሰተው የአየር ቱቦዎች መጥበብ
ጊዜያዊ፣ዘለቀታዊ እና ወቅት እየጠበቀ የሚመጣ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች መሆኑ ይለያዋል፡፡ ነገር ግን ለረዥም ጊዜ የቆየ በሽታ
ያለበት ሰው የአየር ቧንቧው መጥበብ ጊዜያዊነቱን
ትቶ ለሁልጊዜም ሊሆን ይችላል፡፡አስም ወቅትን፣
የአየር ሁኔታን ፣ ቦታን እንዲሁም እድሜን የሚመርጥ
በሽታ ነው፡፡
የአስም በሽታ የአንድ ሰውን የእንቅስቃሴንና ስራ
የመስራት አቅሙን የሚያደክም እንዲሁም ለብዙ
ሰዎች ሆስፒታል ጉብኝት ምክንያት የሆነ በሽታ ነው፡፡
በልጅነት የሚኖር አስም በጎልመሶች ላይ ካለው
በበለጠ በብዛት የሚታይ ሲሆን እድሜ እየጨመረ
በሄደ ቁጥር በሽታው የመጥፋት አዝማሚያ አለው፡፡
አሰምን የሚያመጡ ነገሮች ምንድን ናቸው?
ረዘም ላለ ጊዜ የቆየ ሳል፤ አየር ማጠርና ፤ በቤተሠብ ታሪክ እና ከበባዊ ሆኔታ እንዲሆም በግልፅ አይታወቅም ፡፡ ቀድሙ ካለ
በሚተነፍሱበት ጊዜ የሚሰማ ሲር ሲር የሚል ድምፅ
(wheezing) ዋነኞቹ የአስም መገለጫ ምልክቶች
ናቸው፡፡ ሳሉ ከብዙ እንቅስቃሴ እና ከሳቅ ጋር ተያይዞ
የሚባባስ ሲሆን የታፈነ አይነት ድምፅ ይኖረዋል፡፡
እነዚህ ምልክቶች ባልተጠበቁበት ሰአት የሚነሱ
ሲሆን ብዙ ጊዜ ማታ ማታ እና ጠዋት ይብሳሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ አክታ፣ ቶሎ ቶሎ መተንፈስና ፊት
እና ጀርባ ላይ የማሳከክ ስሜት ይኖራል፡፡ በአይየር
ቱቦዎች መጥበብ የተነሳ የመተንፈሱ ስራ ተጨማሪ
ጡንቻዎችን ሊፈልግ ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት
የጎድን ጡንቻዎች አተነፋፈስን ተከትሎ ገባ ወጣ
ማለት እና የአንገት ጡንቻዎች መገታተርን
ልታስተውል ትችላለህ፡፡ ድካም እና የአቅም ማነስም
ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች ናቸው፡፡ የነዚህ
ምልክቶች መኖር የአስም በሽተኛነትን አያረጋግጥም፡፡
ግን ወደሆስፒታል ለመሄድ ጥሩ ምክንያት ናቸው፡፡
አስም ያለባቸው የቅርብ ዘመዶች – እናትና አባት
ወይም እህት እና ወንድም – ያለው ሰው ከሌላው
ሰው በተለየ በአስም ለመያዝ ትልቅ እድል አለው፡፡
በሽታው በቤተሰብ የሚሄድ ባይሆንም አስም ያለበት
ቤተሰብ ያለው ሰው ሰፋ ያለ ተጋላጭነት ይኖረዋል፡፡
አስምን የሚያባብሱ (የሚያስነሱ) ነገሮች ምንድን ናቸው?
አስምን የሚያስነሱ አሊያም የሚያባብሱ ብዙ ነገሮች
አሉ፡፡ ጉንፋን እና የሳይነስ መቁሰል (sinusitis)
አስምን ያባብሳሉ፡፡ከበድ ያለ እንቅስቃሤ በምታደርግበት ጊዜ
አየር ቶሎ ቶሎ ትተነፍሳለህ፡፡ ይሄ ደግሞ የአየር
ቱቦዎችህ እንዲጠቡ የሚያደርጉ ኬሚካሎች
ከተለያዩ ህዋሳት እንዲመረቱ ያደርጋል፡፡ ድሮም
ጠባብ በነበረው የአይየር ቱቦ ላይ ተጨማሪ
መጥበብ በአተነፋፈስህ ላይ ከበፊቱ በበለጠ
አስቸጋሪ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ቅዝቃዜም የራሱ የሆነ
ድርሻ አለው፡፡ ከባድ ስፖርት ከመስራት ጋር
ተመሳሳይ የሆነ ለውጥ ያስከትላል፡፡
ሲጋራ ማጨስ በጣም መጥፎ ችግሮችን
የሚያስከትል ተግባር ነው፡፡ የሳንባ ጠንቅ የሆነው
ይህ ልማድ ይህንን በሽታ ለማባባስ ትልቅ አስተዋፅኦ
ያደርጋል፡፡ አንዳድ ህመምተኞች ላይ ሽቶ፣ ሳቅ፣
የአየር ለውጥ ፣ ሙቀት እና ጭንቀት ህመሙን
ያባብስባቸዋል፡፡ውፍረትም(ጤናማ ያልሆነ) ከአስም ጋር በተያያዘ
እራሱን የቻለ መጥፎ ጎን አለው፡፡ አንደ አነድ መደሀኒቶችም
አስምን ሊቀሰቅሱ ይችላሉ፡፡ የክረምት
ወራትም ቅዝቃዜ ስለሚኖር አስምህን ሊያስነሳብህ
ይችላል፡፡በተጨማሪም ብዙ ጀርሞች በእነዚህ
ወቅቶች ስለሚራቡ ብዙ የላይኛው መተንፈሻ አካላት
በሽታዎች ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ጉንፋንና ጉንፋን መሰል
በሽታዎች አስምን ያባብሳሉ፡፡ በተጨማሪም ዋነኛው
አለርጂክ አምጪው ፈንገስ በክረምት በየቦታው
ስለሚገኝ አስምህን ያባብሳሎ፡፡
የአስም ህመምተኛ ሰው እራሱን እንዴት ሊንከባከብ
ይችላል?
በሽታው እንዳለብህ ከታወቀ በኋላ የሚሰጡህን
መድሃኒቶች በባለመውያ ትእዛዝ መሰረት በአግባቡ
መጠቀም ፡ በተጨማሪ ቪታሚን ሲ እና ቪታሚን ኤን
የያዙ ምግቦችን ለምሳሌ ፍራፍሬ እና አትክልትን –
ቲማቲም፣ ፣ ጥቅል ጎመን (ቪታሚን ሲ በሙቀት
ቶሎ ስለሚጠፋ በደንብ ባይበስሉ ይመከራል)
በተጨማሪ ሎሚ እና ብርቱካን – እንዲሁም የአሳ
ዘይትን መመገብ፡፡ ከዚህ ባለፈ በቂ እረፍት ማግኘትና
አስሙን ከሚያባብሱ ነገሮች በ አመጋገብ እንደ ጋስ የሚፈጥር ፣ ተጨመሪ ነገር ከፋብሪካዎች በሚወጡ ምግብ ላይ (preservative and adative color ) መቅነስ ተገቢ ነው፡፡
#Share #share ጓደኟችው እንዴቀላቀ @silegnafashion
@silegnafashion
መልካም የጤና እና የዕርፍት ግዜ፡፡