የአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ዝግጅቱን አጠናቅቆ እንግዶቹን እየተጠባበቀ ነው
****
ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ የአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም የሚካሄደው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔ ዝግጅት በምስል -
Ethiopian Broadcasting Corporation #Ethiopian #Africa #Ethiopia #addisababa #APPS

❤19👍6
የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ ኢኮኖሚያዊ መፃኢ እድል ነዳፊዎች"፦ 2ተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ
የዲፕሎማሲ ማዕከልና የአፍሪካ ሕብረት መዲና በሆነችው አዲስ አበባ አህጉራዊ አጀንዳዎችን በታላቅ ድምቀት የሚመራው ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ከደቂቃዎች በኋላ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሊጀምር ነው::
ለእድገት ማስተዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ ኢኮኖሚያዊ መፃኢ እድል ነዳፊዎች በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ የሀገር መሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በአዲስ አበባ ተገኝተዋል

❤8👍4
የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና አዲሷ አዲስ አበባ፤ ከኮሪደር ልማት እስከ አፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔ
የአዲስ አበባ ከተማ የወንዝ ዳርቻዎችና የኮሪደር ልማት ሥራዎች መዲናዋን ከማስዋብና ገጽታዋን ከመቀየር ባለፈ፣ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ፣ የትራንስፖርት እና የማኅበራዊ ዕድገት ቁመና በከፍተኛ ደረጃ ያሳደጉ ታሪካዊና መዋቅራዊ ፕሮጀክቶች ናቸው::
እነዚህ የተቀናጁ የልማት ሥራዎች የከተማዋ ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ በማሳለጥና የከተማዋ መዋቅር ከዘመኑ ጋር እንዲራመድ በማድረግ ረገድ የማይተካ መሠረት ጥለዋል

❤5
የኢትዮጵያን ሚዲያ ዘርፍ አቅምና ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግረው የልህቀት ማዕከል የምርቃት ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ያስገነባው የኢትዮጵያ ሚዲያ የልህቀት ማዕከል የምርቃት ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው::
በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን አመራር አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል

❤6🙏4
ዲፕሎማቶችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች በትግራይ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎች የተሀድሶ ማዕከልን ጎበኙ
በኢትዮጵያ የሚገኙ የልዩ ልዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካዮች በትግራይ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎች ተሀድሶና መልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል በመገኘት የሥራ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል::
በአሁኑ ወቅት 5 ሺህ 500 የቀድሞ ታጣቂዎችን ተቀብሎ የተሀድሶ ስልጠና እየሰጠ የሚገኘው የመቐለው ማዕከል፣ ቀደም ሲልም በተመሳሳይ መልኩ ተገልጋዮችን ሲያስተናግድ መቆየቱ ተጠቅሷል

❤4👍4👏1
ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
ኢትዮጵያ ሀገራዊ ዕድገቷን ለማፋጠንና የኢኮኖሚ መዋቅሯን ለማጠናከር በወጣቶች የሥራ ፈጠራ፣ የክህሎት ማደራጃና የመሪነት ተሳትፎ ላይ ትኩረት አድርጋ እየሠራች ይገኛል::
የዚህ ታላቅ ሀገራዊና አህጉራዊ ራዕይ አካል የሆነው ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ የጀመረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የሴቶችና የወጣቶች የፖለቲካ አመራር ሚና ላይ ያተኮረ ምክክር እየተካሄደ ይገኛል

❤8👏8🙏1
"ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆን አለበት"፡- የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሙፈሪሀት ካሚል
በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 98 የተደነገገው የጋራ ገቢዎች አስተዳደርና ክፍፍል ሕገ መንግሥታዊ መብት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጡን የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክትትልና በግምገማ ሥራዎቹ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንዳለበት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሙፈሪሀት ካሚል አስታወቁ::
አፈ ጉባኤዋ ይህን ያመለከቱት እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትንና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ አቅጣጫዎችን በተመለከተ ከምክር ቤቱ አስተባባሪ ኮሚቴና የማኔጅመንት አባላት ጋር የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ባካሄዱበት ወቅት ነው

❤21👍2
ኮፕ 32 በታላቁ ሩጫ
የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር እና "ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ"፣ ሀገራችን የምታዘጋጀውን የዓለም አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) አስቀድሞ ኢትዮጵያን የስፖርት መዳረሻ አድርጎ ለማስተዋወቅና የስፖርትን ሁለንተናዊ አቅም ለመጠቀም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ::
በስምምነቱ ወቅት የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ስፖርት የዜጎችን ጤና፣ ሰላምና መቀራረብ የሚያጠናክር በመሆኑ እንደ ታላቁ ሩጫ ያሉ ሀገራዊ ሀብቶችን በመጠቀም የመንግሥትን የዘርፍ ግቦች ማሳካት አስፈላጊ ነው

❤23👍2👏2
2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ዛሬም ቀጥሎ ይካሄዳል
ትናንት የተጀመረው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች አህጉራዊ ጉባኤ "ለዕድገት መምራት" በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬም ቀጥሎ ይካሄዳል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ አዘጋጅነት እና በአፍሪካ ገቨርናንስ ሴንተር አስተባባሪነት እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ታላቅ መድረክ፣ የገዢና ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችን፣ የሀገር መሪዎችን፣ ሚኒስትሮችን፣ ምሁራንና የሲቪል ማኅበራት ተወካዮችን ጨምሮ ከ1 ሺህ በላይ እንግዶች ከመላ አህጉሪቱ ተሳትፈዋል::
በአብዛኛው የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምርጫ ውድድር አልፈው በብሔራዊ የልማት ጥቅሞች ላይ በትብብር የመሥራት ልምዳቸው አነስተኛ መሆኑና በዘውግ ፖለቲካ መጠመዳቸው ለልማት ማሽቆልቆል ምክንያት ሲሆን ቆይቷል

👍5❤4
ከአፍሪካ የፖለቲካ ማዕከልነት ወደ አረንጓዴ መዲና፦ የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የCOP32 ታሪካዊ ዝግጅት
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ አረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን በመቋቋም ረገድ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ሀገራት አንዷ ናት::
ሀገራችን 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) ለማስተናገድ የምታደርገው ጥልቅ ዝግጅት የዚህ ታላቅ ሀገራዊ ቁርጠኝነት ትልቁ ማሳያ ሆኖ ይወሰዳል

❤14👏5😢2🕊2👍1