የትውልድ ስንቅ፡ የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የ5 ዓመታት ድንቅ የትምህርት አሻራ
**************
በትውልድ ግንባታ ሂደት ውስጥ ትምህርት የጨለማ መግፈፊያና የሀገር ዕድገት ማሳለጫ ዋነኛው መሣሪያ መሆኑን በተግባር ለመተርጎም የቆረጠው የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በመላ ኢትዮጵያ የፈነጠቀው የብርሃን ጮራ ለብዙ ሺህ ተማሪዎች አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ከፍቶላቸዋል።
ጽሕፈት ቤቱ ትኩረቱን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በማድረጉ፣ በተለይ በገጠራማ አካባቢዎች ተማሪዎች ከአንደኛ ደረጃ በኋላ በትምህርት ቤት ርቀት ምክንያት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡበትንና ለተለያዩ ጥቃቶች የሚጋለጡበትን እንግልት ቀርፏል።
ዛሬ ተማሪዎች በትውልድ መንደራቸው ዘመናዊ ትምህርት የማግኘት ዕድል በማግኘታቸው በርቀት ምክንያት የሚያጋጥመው እንግልት አብቅቶ የዕውቀት ማዕከላት...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0WngsbB7zHZPTpsJuzAp3WTqeQbHx4wrrgsauXrn59CtJTdhbo3xTqMvywnzKZuskl

👏1
የመራጮች ምዝገባ ዜጎች ከሀገረ መንግሥቱ ጋር የሚገቡት "የዜግነት ውል" ነው
********************
የመራጭነት ካርድ መያዝ ማለት በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ተመልካች ከመሆን ወጥቶ ውሳኔ ሰጪ መሆን ነው። የነገዋ ኢትዮጵያ ሥዕል የሚሣለው ዛሬ እርስዎ በሚወስዱት ካርድ አማካኝነት ነው።
ዛሬ የምምናወጣው ካርድ ነገ ለምንጠይቅበት መብት፣ ለምንሻው ተጠያቂነት እና ለምንመኘው ሉዓላዊነት ብቸኛው ሕጋዊ እና ሰላማዊ መሣሪያችን ነው።
የመመዝገብ ጥልቅ ትርጉም፦
• የሀገረ መንግሥት ፅናት፦ አንድ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚቆመው በሕዝብ ፈቃድ ላይ ነው። መመዝገብ ማለት "ሀገሬ በእኔ ድምፅ ትመራለች" የሚል ፅኑ እምነትን በተግባር ማሳየት ነው።
• የፖለቲካ ተሳትፎ ጥራት፦ ዴሞክራሲ በምኞት አይገነባም፤ በሂደት እንጂ። ካርድ ማውጣት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ወሳኝ ተዋናይ የመሆን ፍላጎትን እና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ያለንን ዝግጁነት የሚለካ ብሔራዊ ሚዛን ነው።
Ethiopian Broadcasting Corporation #EBC #Ethiopia #elections #voterscard

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩምን ጎበኙ
***************
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩምን በመጎብኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም ሀገራቸውን በቅንነት በየመስኩ ያገለገሉ፣ ታሪክ ዐዋቂ እና ምክር ለጋሽ አንጋፋ አባት መሆናቸውን ገልጸዋል።
ልዑል ራስ መንገሻ ዛሬም ድረስ ንቁና አስታዋሽ መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ተመስገን፣ እንዲህ ያሉ አባቶችን መዘከር ለቀጣዩ ትውልድ ያለውን ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተውበታል።
"የትናንቶችን ባስታወስን ቁጥር የነገዎችን እናፈራለን" ሲሉ የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የቀደሙ አባቶችን የሥራ ድርሻ እና የሀገር ፍቅር ማስታወስ ለነገይቱ ኢትዮጵያ ግንባታ ብርቱ አቅም እንደሚሆን አመልክተዋል።

አሜሪካ እና ኢራን በኢስላማባድ የሚያደርጉት የሰላም ድርድር መካሄድ ጀምሯል
*******************
የአሜሪካ እና የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት በፓኪስታን አስተናጋጅነት በኢስላማባድ የሚያደርጉትን የሰላም ድርድር ማካሄድ ጀምረዋል።
የአሜሪካው ልዑክ በምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ የሚመራ ሲሆን፣ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ከድርድሩ አስቀድሞ ከፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ ጋር ተገናኝተው መክረዋል።
በኢራን በኩል ደግሞ የሐገሪቱ የፓርላማ አፈ-ጉባኤ መሐመድ ባገር ጋሊባፍ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራቅቺ በኢስላማባድ የሚገኙ ሲሆን፣ እሳቸውም በተመሳሳይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
ይህ ድርድር እ.አ.አ. ከ1979 የኢራን አብዮት በኋላ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረገ ከፍተኛው የዲፕሎማሲ ግንኙነት ሲሆን፣ ከ2015ቱ የኒውክሌር ስምምነት በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ ይፋዊ የፊት ለፊት ንግግር ነው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ እንዲንር እና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና የፈጠረው ይህ ግጭት በኢስላማባድ በሚደረገው ድርድር ስምምነት ላይ ይደርስ እንደሆነ መላው ዓለም በትኩረት እየተከታተለው ይገኛል።
ድርድሩ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየውን ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ለማርገብና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑንም አልጀዚራ በዘገባው አመልክቷል፡፡
#EBC #IslamabadTalks #USIranNegotiations #BreakingNews #MiddleEastPeace