Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.86K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
"አሰብ ለእኛ እናታችንና ብርሃናችን ነበረች፤ ያ ታሪካዊ ቀን ሲመለስ ለማየት እንመኛለን" - የቀድሞ የአሰብ ነዋሪዎች
******************

በአሰብ ከተማ ነግደው ያተረፉ፣ ወልደው የከበሩና ከተማዋን ያቀኑ ኢትዮጵያውያን፤ ዛሬ በኮምቦልቻ ከተማ "የአሰብ ተፈናቃዮች" በሚል መጠሪያ በራሳቸው መንደር ማህበር መስርተው ይኖራሉ።

ኢቢሲ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በእነዚህ ነዋሪዎች ዘንድ ተገኝቶ ባደረገው ቆይታ፣ ነዋሪዎቹ ሀብትና ንብረታቸውን በአሰብ ጥለው ቢመጡም አሁንም ድረስ ስለ ከተማዋ ጥልቅ ትዝታና ቁጭት እንዳላቸው ታዝቧል።

የኮምቦልቻ ከተማ የመንግስት ኮሚኒኬሽን መመሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ዘሪቱ ሁሴን እንደገለጹት፤ እነዚህ ወገኖች ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ በቋሚነት እየኖሩ ይገኛሉ።

ቀደም ሲል በአሰብ በንግድ ስራ ይተዳደሩ የነበሩት አቶ አሊ ኢድሪስ፣ አሰብ የሁሉም አካባቢ ህዝብ የሚገናኝባት "የፍቅር ከተማ" እንደነበረች ያስታውሳሉ።

አቶ አሊ አክለውም ቀይ ባህር ለኢትዮጵያ እንደ ልብና አእምሮ ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑን ገልጸው፣ ኢትዮጵያ ዳግም የባህር በር ባለቤት ብትሆን የብልጽግና ማማ ላይ ለመድረስ እንደሚያስችላት በልበ ሙሉነት ይናገራሉ።

በወቅቱ በባህር ትራንስፖርት ዘርፍ ያገለግሉ የነበሩት አቶ ሲሳይ አሰፋ፣ የባህር በሩ ለኢትዮጵያ እንደ እናትና እንደ ብርሃን እንደነበር በቁጭት ያወሳሉ።

ኢትዮጵያ የባህር በር በመነጠቋ ምክንያት እንደ ሌሎች የሰለጠኑ ሀገራት እንዳታድግ እንቅፋት እንደሆነባትም ይገልጻሉ።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02qgB7LctQrJwwTJMoaRSz5akwEvMkA3GeD8qPP4PtVm5H1ytnKugiSjYSauFDejrol
👏1
አዲስ አበባ፤ የአፍሪካ የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከልነቷን እያጸናች ያለች የዲፕሎማሲ መዲና
**************

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ መዲና ብቻ ሳትሆን፣ የታሪክና የዘመናዊነት መገናኛ በመሆን የአፍሪካ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ የልብ ትርታነቷን እያረጋገጠች ትገኛለች።

በአሁኑ ወቅት ከተማዋ በከፍተኛ የልማት አብዮት ውስጥ እያለፈች ሲሆን፣ በአህጉሪቱ ተወዳዳሪ የሌላት የኮንፈረንስ ቱሪዝም መዳረሻ ለመሆን ዳግም ተውባ ቀርባለች።

ይህን አዲስ ገጽታ የታዘቡ እንደ ሙሳ ፋኪ እና ሲሪል ራማፎሳ ያሉ ታዋቂ መሪዎች በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በአድናቆት መመልከታቸው የለውጡ ማሳያ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደሚሉት፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት …https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0yft6m8kYJQnhwmvqKktnfzyzV7Tg3r3s9fUpcJhLFL1uKXFr7RnPtXyxBowYG7yrl
👏1
ከ42 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተመዝግበዋል፤ እርስዎስ?
*************
በሀገር ጉዳይ ላይ ባለቤትነትዎን የሚያረጋግጡበት የመራጮች ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም መራዘሙን ያውቃሉ? እስካሁን ባለው የምዝገባ ሂደት ከ42 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ተመዝግበዋል፤ እርስዎስ ተመዝግበዋል?
ባሉበት ሆነው በ*ምርጫዬ” የሞባይል መተግበሪያ ወይም ስድስት ወር እና ከዚያ በላይ በኖሩበት አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ በአካል በመገኘት በቀላሉ መመዝገብ ይችላሉ።
የዛሬው ካርድዎ የነገዋን ታላቂቷን ኢትዮጵያ መገንቢያ ዋነኛ መሣሪያ ነው!
ምርጫ መብት ብቻ ሳይሆን፣ "በሀገሬ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ወሳኙ እኔ ነኝ!" ብለው በኩራት ለዓለም የሚያበስሩበት የታሪክ መድረክ ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራር በመዘርጋት ምዝገባውን ቀላልና አስተማማኝ አድርጎታል። ይህንን ዕድል በመጠቀም ሳይዘገዩ የመራጭነት ካርድዎን ማመቸዎት አማራጭ ይውሰዱ!
Ethiopian Broadcasting Corporation #ምርጫ #ኢትዮጵያ #ይመዝገቡ
👏1
በነጻ የንግድ ቀጣና ውስጥ ተሰማርተው ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርቡ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቅዷል፡- የገንዘብ ሚኒስቴር
***************

የሀገራችንን የኢንዱስትሪ ልማት ለማቀላጠፍና በዘርፉ የሚታዩ የካፒታል እጥረት፣ የግብዓት አቅርቦትና የባለሙያ እጥረት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል አዲስ መመሪያ ይፋ መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር ገለጸ።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ በኢንዱስትሪ ልማት ውስጥ የሚታዩ ማነቆዎችን ደረጃ በደረጃ ለማቃለልና የሀገር ውስጥ ምርታማነትን ለማሳደግ ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን፣ በተለይም አስመጪዎች ምርቶችን ለገበያ ከማቅረባቸው በፊት የሚከፍሉት ቀረጥና ታክስ ውስን የሆነውን ካፒታላቸውን በመያዝ በስራቸው ላይ ጫና እንዳይፈጥር ታሳቢ ተደርጓል።

ይህንኑ ችግር ለመቅረፍ አስመጪዎች ግብዓቶችንና ምርቶችን ቀረጥና ታክስ ሳይከፍሉ ወደ ሀገር አስገብተው፣ ለምርቶቻቸው ገበያ ባገኙ ጊዜ ክፍያውን የሚፈጽሙበት የነጻ ንግድ ቀጣና አሰራር…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02tmPV5xmUTrXRjAdtXuXNdTzt92mApnE8xSUWJkVcEoHp25GqMT4pNKzyUGPdRBWhl
👏1
ፓኪስታን ከኢራን ጋር በመተባበር ወደ መካከለኛው እስያ ሀገራት የሚወስድ አዲስ የንግድ ኮሪደር በይፋ አስጀመረች
****************

ፓኪስታን ከኢራን ጋር በመተባበር ወደ መካከለኛው እስያ ሀገራት የሚወስድ አዲስ የንግድ መስመር በይፋ ማስጀመሯን አስታውቃለች።

ይህ አዲስ የንግድ ኮሪደር ፓኪስታን በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን ግጭት ለማርገብና በኢራን እና በምዕራባውያን መካከል የተፈጠረውን ውጥረት በሰላም ለመፍታት ከምታደርገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ጋር ተያይዞ የመጣ መሆኑን የዘርፉ ተንታኞች ገልጸዋል።

የመጀመሪያው የታሸገ የቀዘቀዘ ሥጋ ጭነት ባለፈው ዓርብ ወደ ኡዝቤኪስታን መዲና ታሽከንት መጓጓዙን ተከትሎ፣ የፓኪስታን-ኢራን የትራንዚት ኮሪደር በይፋ…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02v4dmGqRHx2vjiXWTDK5p2t7zMpVudcjZ9GVGih3i3pkGF69aZyjx8wcJJBC6Z1DQl
👏1