Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.86K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የርህራሄ ዓሻራዎች
*****************

በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ታሪክ ውስጥ "ቀዳማዊት እመቤት" የሚለው ስያሜ ከግርማዊነትና ከክብር ባለፈ፣ አዲስ ትርጉም እየያዘ መጥቷል። ይህ ስያሜ ዛሬ ላይ የዝምታ አገልግሎት፣ የትህትና ጉዞ እና የሰብዓዊነት መገለጫ ሆኖ በብዙዎች ልብ ውስጥ ሰርጿል።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያሳዩት የማይነጥፍ ቁርጠኝነት አንድን ትልቅ እውነት በተግባር አረጋግጧል፤ "እናትነት በቤት ውስጥ አይወሰንም፤ የሀገር እናትነት ማለት የሌሎችን ህመም መጋራት፣ የጎደለውን መሙላት ነው" የሚለውን እውነት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) "መደመር" በሚለው ፍልስፍናቸው ኢትዮጵያውያን ተደጋግፈውና ተሳስረው እንዲያድጉ እንደሚወተውቱት ሁሉ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውም ይህንን ራዕይ ወደ ማዕድ ማጋራት ተግባር ቀይረውታል። በመላው ኢትዮጵያ የተገነቡት 14 ግዙፍ የዳቦና የዱቄት ፋብሪካዎች የዚህ የ"መደመር" ፍሬ ህያው ምስክሮች ናቸው።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02wG6LAy54EYfZ8oCz3paD8Hf3oZtf8LkX3tYBaXPQ8AggjSYQ8TjwWE8CjsCRPXkLl
👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከላይቤሪያ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጋር ተወያዩ
***********************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከላይቤሪያ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጋር ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ በውይይታቸው በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን የቆየ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለማስፋት ወሳኝ ምዕራፍ መከፈቱን አስታውቀዋል።

ከሁለትዮሽ ስብሰባው በመቀጠልም፣ በሁለቱ ሀገራት በኩል ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለማሳካት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡ የመግባቢያ ስምምነቶች እንዲፈረሙ መደረጉን ጠቁመዋል።

እነዚህ ስምምነቶች ኢትዮጵያ በፈጣን የለውጥ ጉዞ ያካበተችውን ልምድ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማካፈል፤ እንዲሁም ከአጋሮቻቸው የተለያዩ ዕይታዎችን በመቅሰም ለአኅጉሩ ዕድገት ዘላቂና አፍሪካዊ መፍትሄዎችን በጋራ ለማፍለቅ እንደ ወሳኝ መሠረት እንደሚያገለግሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
👏1
ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
************************

ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ከሁለትዮሽ ስብሰባቸው ቀጥሎ ሁለት የመግባቢያ ስምምነቶች ልውውጥ ላይ ተገኝተዋል።

እነዚህ ስምምነቶች በትምህርት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ በማተኮር ለወደፊት ትብብራችን እንደ ስትራቴጂካዊ መሠረት እና ተግባራዊ ፍኖተ-ካርታ እንደሚያገለግሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት መረጃ አመልክቷል።

የትብብር ማዕቀፉ፤ ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያን በመደመር መርህ በማጣመር ለአኅጉራዊ ትስስር ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ከመሆኑም ባለፈ፣ የአፍሪካ ሀገራት በእውነተኛ ትብብር ምን ሊያሳኩ እንደሚችሉ እንደ ታላቅ ተምሳሌት የሚጠቀስ መሆኑም ተገልጿል።
👏1
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ ከኢራን ጋር ድርድር ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ
******************

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ሁለተኛው ዙር ድርድር በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ በፓኪስታን ሊካሄድ እንደሚችል መናገራቸውን ኒው ዮርክ ፖስት ዘግቧል።

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ለጋዜጣው በስልክ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ “በእውነቱ እዚያው ኢስላማባድ ብትቆዩ ይሻላል፤ ምክንያቱም በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ አንድ ነገር ሊከሰት ይችላል፤ እኛም ወደዚያ የመሄድ ዝንባሌ አለን” ብለዋል።

ይህ አስተያየት የተሰጠው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተካሄደው የመጀመሪያው ዙር ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ቀደም ሲል ሁለተኛው ዙር ቀጥተኛ ድርድር በአውሮፓ ውስጥ የሆነ ቦታ ሊካሄድ እንደሚችል ጠቁመው ነበር። ሆኖም ኒው ዮርክ ፖስት እንደዘገበው፣ ፕሬዚዳንቱ ቆየት ብለው በድጋሚ በደወሉበት ወቅት ድርድሩ ወደ ኢስላማባድ የመመለስ ዕድሉ "ከፍተኛ" መሆኑን ገልጸዋል።

በዚሁ ንግግራቸውም የፓኪስታኑን የጦር አዛዥ አሲም ሙኒርን "ጥሩ ሥራ እየሠሩ ነው" ሲሉ አድንቀዋል።

#EBC #world #middleeast #iran #usa #peacetalks
👏1
“አምራች ኢንዱስትሪ ለኢትዮጵያ ብልጽግና አይተኬ ሚና አለው” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*********************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አምራች ኢንዱስትሪ ለኢትዮጵያ ብልጽግና አይተኬ ሚና እንዳለው እና የኢኮኖሚው ልብ መሆኑን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ በመደመር መንግሥት የሥራ አቅጣጫ ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ትልቅ ቦታ የሰጡበትን ዝርዝር ምክንያቶች አብራርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምራች ኢንዱስትሪን ከሰው ልጅ ልብ ጋር በማመሳሰል፣ “አንድ ሰው ልቡ ካልሠራ ሁሉ አካላቱ ጤነኛ ቢሆኑም ውጤታማ እንደማይሆን ሁሉ፣ ኢኮኖሚን ኢኮኖሚ የሚያደርገው የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ነው” ብለዋል።

ዘርፉ የዕድገት ሞተር ተብሎ የሚጠራውም በሌሎች ዘርፎች ውስጥ ከፍተኛ የምርታማነት ለውጥ ማምጣት ስለሚችል መሆኑን ጠቁመዋል።

ለአብነትም በግብርናው ዘርፍ የኢንዱስትሪ ውጤቶች የሆኑትን ትራክተር እና ማዳበሪያን መጠቀም ምርትን በጊዜ፣ በብዛት እና በጥራት እንደሚያሳድግ ገልጸው፣ ይህም ከባህላዊ አሠራር ወደ ዘመናዊ እና ከፍተኛ ገቢ ወደሚያስገኝ ሽግግር ለመሻገር ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

ለዘርፉ ቅድሚያ የተሰጠባቸውን አራት መሠረታዊ ምክንያቶች ሲዘረዝሩም፦https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02Cbify83LASM4rBsZcK5DTbTk3nWatQnqXEp67CziUGqgRhbiSkNPt4QpYzfC7Sdpl
👏1
“ከሁለት፣ ሦስት ዓመት በፊት ለአያሌ መንግሥታት የባሕር ላይ እንቅስቃሴ አደጋ ሊገጥመው ይችላል፤ በዚህ ውስጥ ሚና አልባ ሆነን ከቆየን 130 ሚሊዮን ሕዝብ አደጋ ውስጥ ይወድቃል የሚል አቋም እናነሣ ነበር። በወቅቱ ምንም ነገር ስላልነበረ እምብዛም ተቀባይነት አልነበረውም። አሁን ግን ብዙዎች እያመኑበት ያለ ጉዳይ ነው። ከባህር መራቅ የባህርን ወይም የየብስን ትራንስፖርት ወይም የአየርን ትራንስፖርት ‘ግዴለም፤ በቀላሉ አገኘዋለሁ’ ብሎ ማሰብ የማይቻልበት ሁኔታ እየተፈጠረ ነው።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

#EBC #Ethiopia #SeaAccess
👏1
ኢትዮጵያ ዓለም እያመራበት ያለውን የ"ኢንዱስትሪ 4.0" እውነታ በንቃት እየተገበረች ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**********************

ዓለም አቀፉ የኢንዱስትሪ ገጽታ ከጭስ እና ብረት ወጥቶ በዳታ፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና አረንጓዴ ኢነርጂ እየተመራ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለ-መጠይቅ፣ ዓለም እያመራችበት ያለውን የ"ኢንዱስትሪ 4.0" እውነታ ኢትዮጵያ በንቃት እየተገበረችው መሆኑን አስታውቀዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረቶች የተነሣ የአቅርቦት ሰንሰለቶች እየተቆራረጡ እና "ፕራግማቲዝም" ወሳኝ መፍትሔ በሆነበት በአሁኑ ወቅት፣ ኢትዮጵያ የነፃ ንግድ ቀጣናዎችን ከደረቅ ወደቦች ጋር በማስተሣሠር የሎጂስቲክስ መሠረቷን እያጠናከረች ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያ በዜሮ ፍሳሽ ማጣሪያ እና በንፁህ የታዳሽ ኃይል ማምረት መቻሏ በርካታ ዓለም አቀፍ የሶላር እና የአልሙኒየም አምራቾችን እየሳበ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ሀገራችን ያለፈውን ሥርዓት ስህተቶች (አክሳሪ ኢንቨስትመንቶች እና የሀብት ብክነት) በማረም፣ አጭር ጊዜ ውስጥ ሀብት በሚመልሱ ፕሮጀክቶች (እንደ ማዳበሪያ ፋብሪካዎች) እና በከተሜነት ላይ ትኩረት አድርጋ ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን እያረጋገጠች ትገኛለች ነው ያሉት።

#EBC #Ethiopia #PMAbiyAhmed #Industry4 #GreenEnergy #RenewableEnergy #Logistics #FreeTradeZone
👍1👏1