ኢትዮጵያ ለትውልድ ግንባታ እና ለህፃናት ሁለንተናዊ እድገት ልዩ ትኩረት ሰጥታለች፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
******************
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘውን ዓለም-አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ አስጀምረዋል።
መንግስት ድሃ-ተኮርና የሰውን ልጅ ልማት ቅድሚያ የሚሰጥ ፖሊሲ በመከተል ላይ እንደሚገኝ የጠቆሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀዳማይ ልጅነት እድሜ ክልል ለበለፀገ ማህበረሰብና ለጠንካራ አገር መሰረት መሆኑን በጥልቀት በመረዳት ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋና ወጊነት የተጀመሩት በህፃናት ሁለንተናዊ እድገት ላይ ያተኮሩ ስትራቴጅካዊ እርምጃዎች ውጤታማ መሆናቸውን በመጥቀስ በከተማዋ የተገኘውን ልምድ በመቀመር ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች ለማስፋት የሚያስችል ስርዓት መዘርጋቱንም አረጋግጠዋል።
ለዚህም ተግባር ይረዳ ዘንድ የቴክኒክና ሳይንሳዊ ዕውቀትን ለፖሊሲ ግብዓት የሚያቀርብ "የአፍሪካ ቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል" በአዲስ አበባ መቋቋሙ የመንግስትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን https://web.facebook.com/share/p/1GHh5gQuco/
#ebcdotstream #አዲስአበባ #ቀዳማይልጅነት #ሕፃናት #ኢትዮጵያ

👏2
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቤጂንግ ገብተዋል
*******************
የዓለማችን ሁለቱ ሀያላን አገራት አሜሪካ እና ቻይና በመሪዎች ደረጃ ለሚያደርጉት ውይይት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር ቤጂንግ ገብተዋል።
ይህ ጉብኝት በሁለቱ ኃያላን ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ብቻ ሳይሆን የዓለምን ጂኦፖለቲካዊ ሚዛን የሚወስን ነው የተባለ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ በቻይና ቆይታቸው በመካከለኛው ምስራቅ በተለይም በኢራን እና በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ ከፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
#USA #China

🤔1
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “የመደመር መንግሥት“ መጽሐፍ የዓረብኛ ትርጉም ነገ ይመረቃል
******************
በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ አቡዳቢ በነገው ዕለት የሚመረቀው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የመደመር መንግሥት“ መጽሐፍ፤ በዋነኛነት በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙ ሁሉም ዓረብኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገራት፣ ሕዝቦች እና መንግሥታት በመደመር እሳቤ የምትመራዋን ኢትዮጵያን በጥልቀት ለማስተዋወቅ ዓላማ ያነገበ መሆኑን በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ገልጸዋል።
መጽሐፉ በዓረቡ ዓለም የኢትዮጵያን ፍላጎቶች እና ብሔራዊ ጥቅሞች የበለጠ ለማስጠበቅ እና ኢትዮጵያም የመካከለኛው ምሥራቅ አድማሷን ለማስፋት የምትጠቀምበትን የጂኦ-ስትራቴጂክ እና የጂኦ-ፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ሚዛኑ የተጠበቀ ሆኖ እንዲቀጥል ካላት ፍላጎት አንጻር የተተረጎመ ነው።
የመደመርን ፍልስፍና ይበልጥ ለቀጣናው ሀገራት ቅርብ በሆነ ቋንቋ ይዞ መምጣት የኢትዮጵያን ትክክለኛ ዕይታ ያሳያል የሚሉት አምባሳደር ጀማል፣ ይህም ሀገራቱ የአዲሲቷን ኢትዮጵያ ተራማጅ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የሁሉን አቀፍ የለውጥ ማዕቀፎች እንዲረዱ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር አብራርተዋል።
በነገው ዕለት በሚመረቀው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የመደመር መንግሥት“ ዓረብኛ ትርጉም መጽሐፍ ላይ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና ንጉሣዊ ቤተሰቦች፣ ዲፕሎማቶች፣ አምባሳደሮች፣ የመካከለኛው ምሥራቅ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት፣ ዳያስፖራዎች እና የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አባላት ይታደማሉ።
በሰለሞን ኃይለኢየሱስ (ከአቡዳቢ)
#EBC #Ethiopia #medemer

👏1
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
*****************
ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት፤ የጋራ ታሪክ፣ የአሁን እና ተሻጋሪ ትብብር፣ በሰላም አብሮ ለመኖር!
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስምንት አስርት ዓመታት ጉዞን ምክንያት በማድረግ፣ "በሰላም አብሮ ለመኖር" በሚል መሪ ቃል ልዩ የመታሰቢያ ቴምብር ስብስብ አውጥታለች።
እነዚህ አራት ቴምብሮች እ.ኤ.አ. በ1945 በሳን ፍራንሲስኮ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን ከመፈረም ጀምሮ፣ በኮንጎ የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን እስከማሰማራት እና በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውን የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እስከ ማስተናገድ ያለውን የጋራ ታሪካችንን የሚተርኩ ናቸው።
በዓለም የፖስታ ህብረት በኩል ለ192 ሀገራት የተሰራጩት እነዚህ ቴምብሮች፣ ለአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን ለትውልድ ሁሉ የሚተርፍ የታሪክ ዐሻራ ማሳያ ናቸው።
በዚሁ አጋጣሚ፣ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ክቡር አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና ለቡድናቸው፣ በዘመናዊው ታሪክ ውስጥ እጅግ ፈታኝ በሆነ ወቅት ላይ ሰላምን፣ ልማትን እና ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር እያሳዩት ላለው ጽኑ አመራር ጥልቅ አድናቆታችንን እንገልጻለን።
የተባበሩት መንግሥታት የጸናው ሀገራት ከመከፋፈል ይልቅ ውይይትን ስለመረጡ ነው።
ኢትዮጵያም ይህንኑ የሁልጊዜ ምርጫዋን ታጸናለች!

“በኢትዮጵያ እና በፈረንሳይ መካከል ያለው ትሥሥር ይበልጥ እየጠነከረ ብቻ የሚዘልቅ ነው” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#EBC #Ethiopia #France #diplomacy
#EBC #Ethiopia #France #diplomacy
👏1
አዲስ አበባ "በብርሃን ፍጥነት" እየተለወጠች ያለች ከተማ ነች፦ አንቶኒዮ ጉተሬዝ
*************************
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፣ ድርጅቱ የተመሰረተበትን 80ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ልዩ የቴምብር ስብስብ ከፍተዋል።
ዋና ጸሐፊው በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ አዲሱ የመታሰቢያ ቴምብር የተመድን 80ኛ ዓመት ከማክበር ባለፈ በኢትዮጵያና በተመድ መካከል ያለውን ታሪካዊና የጠበቀ አጋርነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በአውሮፓውያኑ 1945 የተመድ ቻርተርን ከፈረሙ የመጀመሪያዎቹ 51 አገራት አንዷ መሆኗን ያነሱት ዋና ጸሐፊው፣ አብዛኛው የአፍሪካ አህጉር በቅኝ ግዛት ስር በነበረበት ወቅት ነጻነቷን ጠብቃ የቆየች ጥንታዊ የስልጣኔ ማሳያ መሆኗን አውስተዋል።
ኢትዮጵያ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ነጻነታቸውን እንዲያገኙና የድርጅቱ አባል...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0PoRo9kJYFWZM6p7v9L2Be5RLBeBzuDxtstr2WWtqUygKggUEUM6pQp4i6DSXWFVBl