Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.86K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
በመቅደላ ጦርነት የተዘረፉ ቅርሶች ከ158 ዓመታት በኃላ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ
***********************
በመቅደላ ጦርነት ወቅት ተዘርፈው ወደ እንግሊዝ ተወስደው የነበሩት የንጉሠ ነገሥት አፄ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል፣ የልብስ ቁራጮች እና የወርቅ አምባር ከ158 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

ቅርሶቹን ከእንግሊዝ ይዘው የመጡት የንግሥቲቱ ቤተሰብ ሙዚየም ኃላፊ ሮቢን ጃክሰን (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ አባልና ተመራማሪው አሉላ ፓንክረስት (ዶ/ር) ናቸው።

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው እና የኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር አባላት..https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0jUM3K224vkuFeBcLq2JAiw1kgPBfUAswabLUCH7mLU3HPRn9VWe39bYUSocxUt9xl
👏1
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት እና የሀገርን ሰላም በሚያጠናክሩ ውሳኔዎች ተጠናቀቀ
******************
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሰባት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፤ በሀገራዊ ሰላም፣ በቤተ ክርስቲያን አንድነትና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፎ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።

የቤተ ክርስቲያኗን ሉዓላዊ ክብርና አንድነት መጠበቅ ዋነኛ ተግባሩ መሆኑን ያረጋገጠው ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ለዚህም ሲባል የተቋቋመው “የሀገራዊ ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት” ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ወስኗል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሕዝብ አንድነት የሚበጅ እንዲሆን ቤተክርስቲያን ፀሎት...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02FpNnbDKxXrwy7CpxRG9cqPYj8fpz15TNKFEjuhXx5Yt2t6Q5Q1B7JApQjby3m7wvl
👏1
የዓለም ተስፋ በኒው ዴልሂ፦ የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ተጀምሯል
***********************
በህንድ መዲና ኒው ዴልሂ የተጀመረው የብሪክስ (BRICS) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ፣ በዓለም ዙሪያ የሚታዩ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታትና አዲስ የትብብር ምዕራፍ ለመክፈት ትልቅ ተስፋን ሰንቋል።

ይህ ስብሰባ በመጪው መስከረም ወር በህንድ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ስኬታማነት ወሳኝ መሠረት የሚጥል ሲሆን፣ የአባል ሀገራቱን አንድነትና ለዓለም አቀፍ መረጋጋት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

"ለጥንካሬ፣ ለፈጠራ፣ ለትብብር እና ለዘላቂነት መገንባት" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው ይህ ስብሰባ፣ በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት የሚሹ የጤና ጉዳዮችን እና የኢኮኖሚ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ነው።

በስብሰባው ላይ የኢትዮጵያ፣ የሩሲያ፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የብራዚል፣ የኢራን እና የኢንዶኔዥያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተገኙ ሲሆን...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0WNnkUECSH5PuHongtmKJagC2K2ZQtFMgVgmwDBWYaakj2XKu9wjUiorYTtMfWvSDl
👏1
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበጎነት መንደር የተገነባውን 29ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል መርቀው ሥራ አስጀመሩ
*****************
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነባውንና ለከተማዋ 29ኛ የሆነውን "የተስፋ ብርሃን" የምገባ ማዕከል መርቀው ሥራ አስጀመሩ።

ማዕከሉ ማኅበራዊ ፍትህን ለማንገሥ የሚከናወኑ የበጎነት ተግባራት አካል ሲሆን፣ በተለይም በልማት ምክንያት ተነስተው በተገነቡ 492 ቤቶች ውስጥ ለሚኖሩ 2 ሺህ 460 ነዋሪዎች ትልቅ እፎይታ እንደሚሆን ከንቲባዋ ገልጸዋል።

በተለይ አረጋውያን፣ ለማኅበራዊ ችግር የተጋለጡና ድጋፍ የሚሹ ወገኖች በሚኖሩበት በዚህ "የበጎነት መንደር" ውስጥ የተከፈተው ማዕከል፤ ነዋሪዎች ንጹሕና ትኩስ ምግብ በቀን አንድ ጊዜ…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0NS2qrQcPKze7yTj8Qc6hVjXEz61mmd7Kxfpsj7GJiUXNivrXJMSTdJKaTXCjbfjFl
👏1