ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቻይና ያደረጉት ጉብኝት ‘የጋራ መግባባትንና መተማመንን የሚያጎለብት’ ነው፦ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ
***********************
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ቤጂንግ ያደረጉት የ3 ቀን ጉብኝት “በሁለቱ ሀገራት መካከል መግባባትንና መተማመንን ያጠናክራል” ሲሉ ገልጸውታል።
ሺ ጂንፒንግ የትራምፕን ጉብኝት "ሁሉም አካላት አሸናፊ የሚሆኑበት፣ ታሪካዊ፣ አስፈላጊ እና ወቅቱን የጠበቀ” ነው ሲሉ ገልፀውታል።
ሁለቱ መሪዎች የተረጋጋ የኢኮኖሚ እና የንግድ ግንኙነትን ለመጠበቅ፣ በተለያዩ መስኮች ተግባራዊ ትብብርን ለማስፋፋት እና የጋራ ስጋቶችን በአግባቡ ለመፍታት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ፕሬዝዳንት ሺ እንደገለጹት፣ ጉብኝቱ በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ ሰላማዊ አብሮ መኖር እና የሁለቱንም ሀገራት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚጠብቀው ጉዳይ ነው።
ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በተጨማሪም ቻይናና አሜሪካ በዓለም አቀፍና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ መስማማታቸውን ጠቁመዋል።
ይህ ጉብኝት በ9 ዓመታት ውስጥ ወደ ቻይና የተጓዘ የመጀመሪያው በሥልጣን ላይ ያለ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ያደርጋቸዋል።
Ethiopian Broadcasting Corporation #China #USA #Beijing #ChinaUSRelations #WorldNews #Geopolitics
See less

👏1
“የሀገራዊ ምክክር የእስካሁን ሂደቱ በማኅበረሰባችን በየደረጃው የመደማመጥን ከፍ ያለ ጠቀሜታ አሳይቷል” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
********************
“የሀገራዊ ምክክር የእስካሁን ሂደቱ በማኅበረሰባችን በየደረጃው የመደማመጥን ከፍ ያለ ጠቀሜታ ማሳየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት ዓመታት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የምክክር ሂደቱ ወደፊት እንዲራመድ በትዕግሥት እና ከፍ ባለ የሞያ ሥነ-ምግባር በማከናወን አሁን ያለበት ምዕራፍ ያደረሱትን ሁሉንም ኮሚሽነሮች አመስግነዋል።
የምክክር ባህል እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፣ ጠንካራ የሲቪክ ማኅበረሰብ ባህል ግንባታ ደግሞ ያላሰለሰ የመነጋገር ልምምድ እና የሰከነ የወል መደማመጥን እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።
“የእስካሁን ሂደቱም በማኅበረሰባችን በየደረጃው የመደማመጥን ከፍ ያለ ጠቀሜታ አሳይቷል፤ ሂደቱ በሀገራችን ሁሉም ማዕዘናት የሚገኙ ከ90 በመቶ በላይ ኢትዮጵያዊያንን አመለካከቶች እና የውይይት ውጤቶች ያንፀባረቀ ነውም” ብለዋል።
ለሀገር ወሳኝ ፋይዳ የያዘው የምክክሩ ምዕራፍ ተጨባጭ ውጤት ወደሚያስገኘው ቀጣይ ምዕራፍ በሚሸጋገርበት በዚህ ወቅት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለሀገራችን ሰላም፣ አንድነት እና ዘላቂ መረጋጋትን የሚያረጋግጥ የጋራ ፅኑ አቋም እና ገንቢ በሆነ መንገድ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።
#EBC #Ethiopia #PMAbiyAhmed #Nationaldialogue
Ethiopian Broadcasting Corporation

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደብረ ማርቆስ ታሪካዊ የተሳካ በረራ አደረገ
***************
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ያደረገውን የመጀመሪያ የሙከራ በረራ ዛሬ በተሳካ ሁኔታ አከናውኗል።
የደብረ ማርቆስ ከተማና የአካባቢው ማህበረሰብ ለብዙ ዓመታት በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው ይህ የተሳካ የበረራ አገልግሎት፣ ዛሬ የመጀመሪያውን አውሮፕላን በስኬት አስተናግዷል።
ይህ ታሪካዊ ክስተት ለአካባቢው የኢኮኖሚ፣ የንግድና የቱሪዝም እንቅስቃሴ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ታላቅ ስኬት መሆኑ ተገልጿል።
የአውሮፕላን ማረፊያው ሥራ መጀመር የከተማዋን የትራንስፖርት ተደራሽነት ከማሻሻሉም…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0jhrKMbfJ6hJznHhJeEuLka5twTncQ8ecWYNDT6y7ov4DGTPGBif3ZPDYHzMbFrVl

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክን መረቁ
*************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተጠናቀቀውን ምዕራፍ አንድ ግንባታ ዛሬ በይፋ መርቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የዚህ ፕሮጀክት መመረቅ አስተማማኝ እና ጠንካራ ኢኮኖሚን ለመገንባት በተጀመረው የብልጽግና ጉዞ ውስጥ ተደማሪ እመርታ መሆኑን አስታውቀዋል።
በመዲናዋ በአጠቃላይ በ93.9 ሄክታር መሬት ላይ ከሚያርፈው የፓርኩ አጠቃላይ ስፋት ውስጥ፣ የመጀመሪያው ምዕራፍ በ43 ሄክታር መሬት ላይ ተገንብቶ ዛሬ የተመረቀ ሲሆን፣ ይህም ለመካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0F6SZw5gs9YUpKEQ3uXQ5VntvPVuAAkeXwrEfBfWMeJnnPZHnzwCHmfrveQcpJ8Hjl