ማንችስተር ሲቲ የእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ
*************
በዌምብሊ ስታዲየም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ቼልሲን 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት በመርታት የ2025/26 የውድድር ዓመት የኤፍኤ ካፕ ባለቤት ሆኗል።
በስፔናዊ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ፣ በጨዋታው ላይ የታየውን ስልታዊ የበላይነት ወደ ድል በመቀየር በክለቡ ታሪክ ሌላ የክብር ምዕራፍ አስመዝግቧል።
ምንም እንኳ የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋንጫውን ለማሸነፍ እስከመጨረሻው ደቂቃ ድረስ…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0ZsbS5XJKckhcbuHn6tY1aD6i6xmathUkMJVQaqor6eqPxN11j3TwSZcaFq6eAHvDl

👏1
የሀገራዊ ምክክሩ ወደ እያንዳንዱ ወረዳ በመሄድ ሕዝብን የማሳተፍ እጅግ አስቸጋሪውን ምዕራፍ በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እያካሄደችው ያለው ሀገራዊ ምክክር፣ የተመረጠው መመሪያና የተከተለው አካሄድ ለብዙ የአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ልምድና ምሳሌ የሚሆን መሆኑን ገልጸዋል።
ምክክሩ እስካሁን ባደረገው ስኬታማ ጉዞ ትልቁንና እጅግ አስቸጋሪውን ምዕራፍ ማለትም ወደ እያንዳንዱ ወረዳ በመውረድ ሕዝብን የማሳተፍ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ይህ ሂደት የኢትዮጵያን ባህል፣ ማኅበራዊ እሴትና የሕዝብን የዘመናት ጥልቅ ጥበብ ማዕከል ማድረጉ ልዩ እንደሚያደርገውም አብራርተዋል።
ጽንፈኛ የብሔርና የፖለቲካ አስተሳሰቦችን በማራመድ አብሮ መኖርን ሲያስተጓጉሉ የነበሩ "ሊቃውንት"…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02XKWDXUymKV1SfELo2vWHJ4zgJ9GaWHV8XKZN1MYZC33XH7WbZmqzArojeJQrGyCHl

"ዛሬ ማለዳ ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን በጎዴ ተገኝቼ ሥራው የደረሰበትን ደረጃ ለመገምገም የፕሮጀክት ስፍራውን ጎብኝቻለሁ"፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባለፈው ዓመት ነሐሴ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመሆን በአመት 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካ ለማቋቋም ትልቅ የባለድርሻ ስምምነት አድርገን ነበር ሲሉ አስታውሰዋል።
በያዝነው ዓመት ጥቅምት ወር ደግሞ የፕሮጀክቱን ግንባታ በይፋ ጀምረናል። ይኽ ሥራ ከመሠረተ ልማት ግንባታም በላይ ነው።
በኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ የምግብ ሉዓላዊነት፣ የኢንደስትሪ እድገት እና በኢኮኖሚ ራስ የመቻል ጥረት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ኢንቬስትመንት ነው።
የማዳበሪያ ፋብሪካው በሚጠናቀቅበት ወቅት የሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን ያጎለብታል፣ ከውጭ በሚገባ ማዳበሪያ ላይ ያለውን ጥገኝነት ይቀንሳል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አርሶአደሮቻችንን ይደግፋል።
ለኢንቨስትመንት እና የሥራ ዕድል ፈጠራም አዳዲስ እድሎችን ይከፍታል።
ዛሬ ማለዳ ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን በጎዴ ተገኝቼ ሥራው የደረሰበትን ደረጃ ለመገምገም የፕሮጀክት ስፍራውን ጎብኝቻለሁ።
በመላው የፕሮጀክቱ ስፍራ የሚታየው የሥራ ሂደቱ ፍጥነት አበረታች ነው። ይኽን ግዙፍ እና እጅግ ጠቃሚ ሀገራዊ ፕሮጀክት ለመፈፀም ያለውን ቁርጠኝነት እና ትብብር በሚያንፀባርቅ ሁኔታ በተለያዩ የፕሮጀክቱ ክፍሎች ያሉት ግንባታዎች በእቅዳችን መሠረት እየተጓዙ ይገኛሉ።

“የሐረርጌ ሕዝብ በመደመር የልማት እሳቤ እየተመራ በአዲስ የለውጥ ጎዳና ግስጋሴ ላይ ነው” - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
**********************
የሐረርጌ ሕዝብ በመደመር የልማት እሳቤ እየተመራ በአዲስ የለውጥ ጎዳና ግስጋሴ ላይ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ።
ሕዝቡ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃን በንቃት ከመተግበር ባሻገር፤ ከሰላም እና ከለውጥ ጋር ለመተባበር ልቡ የቀና መሆኑንም አብራርተዋል።
አካባቢው ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች የዕርዳታ ጠባቂ የነበሩበት ቢሆንም፤ አሁን ላይ መንግሥት ለግብርና በሰጠው ልዩ ትኩረት በስንዴ፣ በቆሎ እና በተለያዩ ፍራፍሬዎች የልማት ሥራዎች ተጠናክረው በመሠራታቸው የተረጂዎችን ቁጥር ወደ መቶ ሺሕ ዝቅ ማድረግ መቻሉን አድንቀዋል።
የሐረርጌ አርሶ አደሮች በላባቸው ሀገርን በመቀየር እና ራስን በመቻል ለሌሎች አርአያ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
በሐረርጌ የተሠሩ የልማት ሥራዎች ከሐረርጌ አልፈው፣ የውኃ አቅርቦት ድጋፍ እስከ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ በመግባት የሐረርጌ አባቶች እና ወጣቶች አሻራ በመላው ኢትዮጵያ ማስተጋባቱን ጠቅሰዋል።
ሕዝቡ የጀመረውን የልማት ጉዞ አጠናክሮ እንዲቀጥል እና የተተከሉትን ችግኞች እንዲንከባከብ ያሳሰቡት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በቀጣዩ ጠቅላላ ምርጫም ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በመሳተፍ ለሥራ እና ለልማት የሚያነሣሣውን እና ‘ሁሌ እንሥራ’ የሚለውን ብልጽግና ፓርቲ እንዲመርጥ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ በድህነት፣ በግጭት እና በኋላቀርነት የምትታወቅበትን የታሪክ ምዕራፍ ዘግታ፣ አሁን በሥራ እና በለውጧ ዓለም አቀፍ ዕውቅናን እያገኘች መምጣቷንም አስገንዝበዋል።
በቢታንያ ሲሳይ