Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.86K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
“የሐረርጌ ሕዝብ በመደመር የልማት እሳቤ እየተመራ በአዲስ የለውጥ ጎዳና ግስጋሴ ላይ ነው” - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
**********************

የሐረርጌ ሕዝብ በመደመር የልማት እሳቤ እየተመራ በአዲስ የለውጥ ጎዳና ግስጋሴ ላይ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ።

ሕዝቡ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃን በንቃት ከመተግበር ባሻገር፤ ከሰላም እና ከለውጥ ጋር ለመተባበር ልቡ የቀና መሆኑንም አብራርተዋል።

አካባቢው ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች የዕርዳታ ጠባቂ የነበሩበት ቢሆንም፤ አሁን ላይ መንግሥት ለግብርና በሰጠው ልዩ ትኩረት በስንዴ፣ በቆሎ እና በተለያዩ ፍራፍሬዎች የልማት ሥራዎች ተጠናክረው በመሠራታቸው የተረጂዎችን ቁጥር ወደ መቶ ሺሕ ዝቅ ማድረግ መቻሉን አድንቀዋል።

የሐረርጌ አርሶ አደሮች በላባቸው ሀገርን በመቀየር እና ራስን በመቻል ለሌሎች አርአያ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በሐረርጌ የተሠሩ የልማት ሥራዎች ከሐረርጌ አልፈው፣ የውኃ አቅርቦት ድጋፍ እስከ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ በመግባት የሐረርጌ አባቶች እና ወጣቶች አሻራ በመላው ኢትዮጵያ ማስተጋባቱን ጠቅሰዋል።

ሕዝቡ የጀመረውን የልማት ጉዞ አጠናክሮ እንዲቀጥል እና የተተከሉትን ችግኞች እንዲንከባከብ ያሳሰቡት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በቀጣዩ ጠቅላላ ምርጫም ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በመሳተፍ ለሥራ እና ለልማት የሚያነሣሣውን እና ‘ሁሌ እንሥራ’ የሚለውን ብልጽግና ፓርቲ እንዲመርጥ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ በድህነት፣ በግጭት እና በኋላቀርነት የምትታወቅበትን የታሪክ ምዕራፍ ዘግታ፣ አሁን በሥራ እና በለውጧ ዓለም አቀፍ ዕውቅናን እያገኘች መምጣቷንም አስገንዝበዋል።

በቢታንያ ሲሳይ
👏1
ማንችስተር ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 2 አሸነፈ
**************

በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል ።

በኦልድ ትራፎርድ በተደረገው ጨዋታ ሉክ ሾው፣ ማቲያስ ኩኛ እና ምቤሞ ለማንችስተር ዩናይትድ ግቦቹን ሲያስቆጥሩ፣ ለኖቲንግሃም ፎረስት ሞራቶ እና ሞርጋን ጊብስ ዋይት አስቆጥረዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 68 በማድረስ በ ሊጉ 3ተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን አረጋግጧል።

ፖርቹጋላዊው አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በውድድር አመቱ 20 ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል በቴሪ ሄንሪ እና ኬቨን ዴብሮይን ተይዞ የነበረውን በአንድ ዓመት ብዙ ጎል አመቻችቶ የማቀበል ሪከርድ መጋራት ችሏል።

በዘረንቶስ ሰለሞን
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #ማንችስተርዩናይትድ #ፈርናንዴዝ
👍1
አምሥት ዓመታትን በከፍታ የዘለቀው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር
********************

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ላለፉት አምሥት ዓመታት የኢትዮጵያን መልክ የለወጠ ታላቅ ብሔራዊ ተጋድሎ ነው።

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአንድ ልብ በመነሳት፣ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል የተራቆቱ የነበሩ አካባቢዎችን በአረንጓዴ ካባ አልብሰዋል።

ይህ ጉዞ የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም ብቻ ሳይሆን፣ ለትውልድ የሚተርፍ የተስፋ እና የጽናት አሻራ የማሳረፍ ታላቅ ስኬት ነው።

ዛሬ በእያንዳንዱ የሀገራችን ጋራ እና ሸለቆ ላይ የለመለሙት ችግኞች፣ የኢትዮጵያን የነገ ብልጽግና እና የልማት መሪነት ለዓለም በኩራት እያበሰሩ ይገኛሉ።

Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢትዮጵያ #አረንጓዴአሻራ #ድል #አረንጓዴ #GreenLegacy #ClimateAction #Ethiopia
👏1
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ 14 ቀናት ብቻ ቀርተውታል

እርስዎስ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በድምፅዎ መሪዎን ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል?

Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢትዮጵያ #ምርጫ #ዴሞክራሲ #በምርጫብቻ
👏1
ከአቧራ ወደ ዐሻራ፤ ከቅርስ ወደ ቁርስ
*************

በቅርብ ዓመታት ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍን ከተራ የኢኮኖሚ ምንጭነት ባለፈ ለሀገር ግንባታ፣ ለሰላም፣ ለብዝኃነትና ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት መገንቢያ ስትራቴጂካዊ መሣሪያ አድርጋ በመውሰድ ላይ ትገኛለች።

ሀገራችን በታሪክ፣ በባሕልና በተፈጥሮ ያላትን እምቅ ባለጠግነት ለመጠቀም ቱሪዝምን ዋነኛ የኢኮኖሚ ምሰሶ ያደረገች ሲሆን፣ ይህም መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት፣ ገቢን ለማሳደግና ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር መሠረት ሆኗል።

መንግሥት የመንግሥትና የግል ዘርፍ ቅንጅትን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በመምራት፣ ቱሪዝም የጋራ ታሪክን የሚያሳይና ብሔራዊ ማንነትን የሚያጠናክር የጋራ መድረክ እንዲሆን እያደረገ ነው።

ይህን ዘርፍ ለማሳደግ ለ16 ዓመታት ሳይሻሻል የቆየው የቱሪዝም ፖሊሲ በአዲስ መልክ ተሻሽሎ በሚኒስቴር ደረጃ እንዲደራጅ መደረጉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን አሳድጎታል።

በተጨማሪም የስብሰባ፣ የጉዞ፣ የኮንፍረንስና የኤግዚቢሽን (MICE) ስትራቴጂዎች ተቀርጸው…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02pnRquhRdd9JwfFdS5G9GwG7vRZ2CseeUgGxQ7yXBigNTbMsTUSuMUNFgNkVi9TGpl
👏1🕊1
የምርጫ ቦርድ የክትትል ቡድኖች በምርጫ አካባቢዎች ላይ ያጠኑትን የፀጥታ ሪፖርት አቀረቡ
**************

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ላይ ሥምሪት ሰጥቷቸው የነበሩ የክትትል ቡድኖች ያጠኑትን ዝርዝር ሪፖርት በይፋ ተረክቧል።

ቦርዱ ቀደም ሲል በጥር ወር 2018 ዓ.ም. ከተለያዩ ተቋማት የተሰበሰበውንና በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ የተፈረጀውን የፀጥታ መረጃ መሠረት በማድረግ ውይይቶችን አድርጓል።

ይሁን እንጂ ከመንግሥት አካላትና ከተፎካካሪ ፓርቲዎች በደረሱ መረጃዎች መካከል የነበሩትን ልዩነቶች በጥልቀት ለመመርመር መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. የጋራ የክትትል ቡድን አዋቅሮ ሥምሪት ሰጥቷል።

ከፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማኅበረሰብና ከቦርዱ የተውጣጡትና በዘጠኝ ንዑሳን ቡድኖች…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02fEJA88G5EoS7RneGapxcrV9pUXtxB6F1wNMHpVAHVrXWZAwtefrLcatiisAFeBRul
👏1