Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.86K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
ከአቧራ ወደ ዐሻራ፤ ከቅርስ ወደ ቁርስ
*************

በቅርብ ዓመታት ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍን ከተራ የኢኮኖሚ ምንጭነት ባለፈ ለሀገር ግንባታ፣ ለሰላም፣ ለብዝኃነትና ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት መገንቢያ ስትራቴጂካዊ መሣሪያ አድርጋ በመውሰድ ላይ ትገኛለች።

ሀገራችን በታሪክ፣ በባሕልና በተፈጥሮ ያላትን እምቅ ባለጠግነት ለመጠቀም ቱሪዝምን ዋነኛ የኢኮኖሚ ምሰሶ ያደረገች ሲሆን፣ ይህም መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት፣ ገቢን ለማሳደግና ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር መሠረት ሆኗል።

መንግሥት የመንግሥትና የግል ዘርፍ ቅንጅትን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በመምራት፣ ቱሪዝም የጋራ ታሪክን የሚያሳይና ብሔራዊ ማንነትን የሚያጠናክር የጋራ መድረክ እንዲሆን እያደረገ ነው።

ይህን ዘርፍ ለማሳደግ ለ16 ዓመታት ሳይሻሻል የቆየው የቱሪዝም ፖሊሲ በአዲስ መልክ ተሻሽሎ በሚኒስቴር ደረጃ እንዲደራጅ መደረጉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን አሳድጎታል።

በተጨማሪም የስብሰባ፣ የጉዞ፣ የኮንፍረንስና የኤግዚቢሽን (MICE) ስትራቴጂዎች ተቀርጸው…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02pnRquhRdd9JwfFdS5G9GwG7vRZ2CseeUgGxQ7yXBigNTbMsTUSuMUNFgNkVi9TGpl
👏1🕊1
የምርጫ ቦርድ የክትትል ቡድኖች በምርጫ አካባቢዎች ላይ ያጠኑትን የፀጥታ ሪፖርት አቀረቡ
**************

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ላይ ሥምሪት ሰጥቷቸው የነበሩ የክትትል ቡድኖች ያጠኑትን ዝርዝር ሪፖርት በይፋ ተረክቧል።

ቦርዱ ቀደም ሲል በጥር ወር 2018 ዓ.ም. ከተለያዩ ተቋማት የተሰበሰበውንና በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ የተፈረጀውን የፀጥታ መረጃ መሠረት በማድረግ ውይይቶችን አድርጓል።

ይሁን እንጂ ከመንግሥት አካላትና ከተፎካካሪ ፓርቲዎች በደረሱ መረጃዎች መካከል የነበሩትን ልዩነቶች በጥልቀት ለመመርመር መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. የጋራ የክትትል ቡድን አዋቅሮ ሥምሪት ሰጥቷል።

ከፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማኅበረሰብና ከቦርዱ የተውጣጡትና በዘጠኝ ንዑሳን ቡድኖች…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02fEJA88G5EoS7RneGapxcrV9pUXtxB6F1wNMHpVAHVrXWZAwtefrLcatiisAFeBRul
👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ‘በመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት’ ብሔራዊ ጉባኤ ላይ የቀረቡ የዳሽቦርዶችና የኤግዚቢሽን ዝግጅቶችን ጎበኙ
***********************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች "በመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ብሔራዊ ጉባኤ ላይ የተካሄዱ የኤግዚቢሽንና የዲጂታል ዳሽቦርዶችን ሥራዎች ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የቀረቡት የብሔራዊ ዕቅድ እና ስታቲስቲክስ ዳሽቦርዶች (የመረጃ መከታተያ ሰሌዳዎች)…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid04HMijqHA8dCbkiddzt2M3qucze2LrvciKEiM5Jy8kam3MFJYuNeLFDzi1Pm9Rmr3l
👏1