መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
****************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት" በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው ሀገራዊ ጉባኤና ኤግዚቢሽን ላይ በመገኘት፣ ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉዓላዊነት ጉዞ ያስመዘገበችውን ትልቅ ድል እና በዘርፉ የታየውን እመርታ ተመልክተው አድንቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላፉት መልዕክት፤መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የተዋሰ አሊያም በውጭ አካላት ላይ ጥገኛ የሆነ መረጃ ሀገራዊ መሻትን ማሳካት ስለማያስችል የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት እንደ...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0FjnwA6j6ArHprnbNjZSh9s1Y4WUiND8KxBZYTXSC2wsuCuE2GMpNxqLcqjFmG4Qal

👏2
#ስፖርት : አርሴናል ከ22 ዓመታት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ ዋንጫ ማሸነፉን አረጋገጠ።
አርሴናል ብርቱ ተፎካካሪው ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት ከበርንማውዝ 1 ለ 1 በመውጣቱ በሊጉ አንድ ጨዋታ እየቀረ የዋንጫ ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ላይ ከፍተኛ ተወዳጅነትና እጅግ በርካታ ተመልካች ባለው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዘንድሮው የውድድር አመት አሸናፊና የዋንጫ ባለቤት አርሴናል ሆኗል።
አርሴናል ዋንጫውን ያገኘው ከ22 ዓመታት በኋላ ነው።
በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ መሪነት ላለፉት ዓመታት የተገነባው ስብስብ በዘንድሮው ውድድር ዘመን በሜዳውም ሆነ ከሜዳው ውጭ ባደረጋቸው ወሳኝ ጨዋታዎች ያስመዘገበው ውጤት ለዚህ ታሪካዊ ስኬት አብቅቶታል።
ቡድኑ ከዚህ ስኬት በተጨማሪ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚም ነው።
ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ/ም

🕊2👏1
1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል የፊታችን ረቡዕ ይከበራል
*****************
የ1447ኛው ዓ.ሒ (የ2018 ዓ.ል) የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል የፊታችን ረቡዕ እንደሚከበር የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አስታወቀ።
ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤቱ በዓሉን አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
ፍርድ ቤቱ በመግለጫው፣ ዋናው የሐጅ ቀን (ውቅፍ ዓረፋ) ማክሰኞ ዙል ሒጃ 9 ቀን መሆኑን ጠቅሶ፣ ዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) ረቡዕ ዙል ሒጃ 10 (ግንቦት 19) ቀን ተከብሮ እንደሚውል አስታውቋል።
በዓሉ የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞቱን የገለጸው የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት፣ ምዕመናን በዓሉን ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመርዳት እንዲያከብሩት ጠይቋል።
#world #Ethiopia #Islam #Muslims #Eid #EidAlAdha #EBC

👍1
አል ናስር የሳውዲ ፕሮ ሊግ ሻምፒዮን ሆነ
****************
አል ናስር አል ዳማክን 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፉን ተከትሎ የሳውዲ ፕሮ ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።
ለአል ናስር ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ፤ ሳዲዮ ማኔ እና ኮማን የተቀሩትን ግቦች አስቆጥረዋል።
ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከአል ናስር ጋር የመጀመሪያውን የሊግ ዋንጫ ማሸነፍ ችሏል።
አል ናስር የሊጉን ዋንጫ ከ 7 ዓመታት በኋላ ሲያነሳ በአጠቃላይ ለ4ኛ ጊዜ አሸንፏል።
በዘረንቶስ ሰለሞን

👍2
በሚመርጡበት ወቅት ድምፅዎን ዋጋ አልባ የሚያደርጓቸውን 5ቱን ምክንያቶች እናስታውስዎ
****************
1. የመራጩ ማንነት በስም የተገለጸበት ከሆነ፣
2. ምልክት የተደረገባቸው ዕጩዎች ቁጥር ለምክር ቤቱ ሊመረጡ ከሚችሉ ተመራጮች ቁጥር በላይ ከሆነ፣
3. ምንም ምልክት ያልተደረገበት ከሆነ፣
4. መራጩ ማንን እንደመረጠ መለየት የሚያስቸግር ከሆነ፣
5. ሕጋዊ የድምፅ መስጫ ወረቀት ያልሆነ ወይም በምርጫ ጣቢያው ያልተሠራጨ የድምፅ መስጫ ወረቀት ከሆነ ዋጋ አልባ ይሆናል፡፡
ከተገለጹት 5 ምክንያቶች በአንዱ ድምፅ የተሰጠባቸው ወረቀቶች ዋጋ አልባ ሊሆኑ ይችላሉ!
Ethiopian Broadcasting Corporation #ምርጫ #በምርጫብቻ #ኢትዮጵያ #ምርጫ #democracy

የዴሞክራሲያዊ ጉዞአችን ቀጠሮ ሰአቱ ደርሷል
አሁን ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ሆኗል - ኢትዮጵያ በይፋ ነገዋን መምረጥ ጀምራለች!!
ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሀገራችን ታሪካዊ ቀን ነው።
ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በሚሳተፉበት ምርጫ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ለነገ ሀገራቸው ተስፋ መጠቀም ጀምረዋል።
ለቀጣይ 5 ዓመታት ታላቂቷን ኢትዮጵያ የሚመራውን ፓርቲ ዛሬ በድምፃቸው ይመርጣሉ።
ይህ አስደናቂ ህዝባዊ ክንውን ሀገራችን በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላይ እያሳየች ያለውን ተስፋ ሰጪ እርምጃ እና የህዝቧን የፖለቲካ ንቃተ ህሊና በጉልህ የሚያንፀባርቅ ነው።
በአፍሪካ የዴሞክራሲ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛው የመራጮች ቁጥር በተመዘገበበት የዘንድሮው ምርጫ ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በድምፃቸው ያረጋግጣሉ።
ይህ የህዝብ ተሳትፎ ጠንካራ ተቋማት እና የዳበረ የፖለቲካ ባህል እየተገነባ ለመምጣቱ ህያው ምስክር ነው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ድምፅ በአንድነት ሲሰባሰብ የማይበገር ሀገራዊ አቅም እና ጠንካራ መንግስታዊ መሰረት ይፈጥራል።
ዛሬ ኢትዮጵያውያን ሉአላዊነታቸውን በድምፃቸው ያረጋግጣሉ።
Ethiopian Broadcasting Corporation #ምርጫ #በምርጫብቻ #ኢትዮጵያ #ምርጫ #በምርጫብቻ #ኢትዮጵያ #democrac #ምርጫ #በምርጫብቻ #ኢትዮጵያ #ምርጫ #በምርጫብቻ #ኢትዮጵያ #democrac

አፍሪካ ኅብረት ታዛቢ ቡድን መሪ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የምርጫ ዝግጅትን ተዘዋውረው እየጎበኙ ነው
👏2
የመጀመሪያዎቹ መራጮች
************
አዲስ አበባ ድምፅ እየሰጠች ነው!!
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!!
Ethiopian Broadcasting Corporation #ምርጫ
************
አዲስ አበባ ድምፅ እየሰጠች ነው!!
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!!
Ethiopian Broadcasting Corporation #ምርጫ
👏2