Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.86K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል የፊታችን ረቡዕ ይከበራል
*****************

የ1447ኛው ዓ.ሒ (የ2018 ዓ.ል) የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል የፊታችን ረቡዕ እንደሚከበር የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤቱ በዓሉን አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ በመግለጫው፣ ዋናው የሐጅ ቀን (ውቅፍ ዓረፋ) ማክሰኞ ዙል ሒጃ 9 ቀን መሆኑን ጠቅሶ፣ ዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) ረቡዕ ዙል ሒጃ 10 (ግንቦት 19) ቀን ተከብሮ እንደሚውል አስታውቋል።

በዓሉ የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞቱን የገለጸው የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት፣ ምዕመናን በዓሉን ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመርዳት እንዲያከብሩት ጠይቋል።

#world #Ethiopia #Islam #Muslims #Eid #EidAlAdha #EBC
👍1
አል ናስር የሳውዲ ፕሮ ሊግ ሻምፒዮን ሆነ
****************

አል ናስር አል ዳማክን 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፉን ተከትሎ የሳውዲ ፕሮ ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።

ለአል ናስር ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ፤ ሳዲዮ ማኔ እና ኮማን የተቀሩትን ግቦች አስቆጥረዋል።

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከአል ናስር ጋር የመጀመሪያውን የሊግ ዋንጫ ማሸነፍ ችሏል።

አል ናስር የሊጉን ዋንጫ ከ 7 ዓመታት በኋላ ሲያነሳ በአጠቃላይ ለ4ኛ ጊዜ አሸንፏል።

በዘረንቶስ ሰለሞን
👍2
በሚመርጡበት ወቅት ድምፅዎን ዋጋ አልባ የሚያደርጓቸውን 5ቱን ምክንያቶች እናስታውስዎ
****************

1. የመራጩ ማንነት በስም የተገለጸበት ከሆነ፣

2. ምልክት የተደረገባቸው ዕጩዎች ቁጥር ለምክር ቤቱ ሊመረጡ ከሚችሉ ተመራጮች ቁጥር በላይ ከሆነ፣

3. ምንም ምልክት ያልተደረገበት ከሆነ፣

4. መራጩ ማንን እንደመረጠ መለየት የሚያስቸግር ከሆነ፣

5. ሕጋዊ የድምፅ መስጫ ወረቀት ያልሆነ ወይም በምርጫ ጣቢያው ያልተሠራጨ የድምፅ መስጫ ወረቀት ከሆነ ዋጋ አልባ ይሆናል፡፡

ከተገለጹት 5 ምክንያቶች በአንዱ ድምፅ የተሰጠባቸው ወረቀቶች ዋጋ አልባ ሊሆኑ ይችላሉ!

Ethiopian Broadcasting Corporation #ምርጫ #በምርጫብቻ #ኢትዮጵያ #ምርጫ #democracy
👍1
የዴሞክራሲያዊ ጉዞአችን ቀጠሮ ሰአቱ ደርሷል
አሁን ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ሆኗል - ኢትዮጵያ በይፋ ነገዋን መምረጥ ጀምራለች!!
ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሀገራችን ታሪካዊ ቀን ነው።
ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በሚሳተፉበት ምርጫ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ለነገ ሀገራቸው ተስፋ መጠቀም ጀምረዋል።
ለቀጣይ 5 ዓመታት ታላቂቷን ኢትዮጵያ የሚመራውን ፓርቲ ዛሬ በድምፃቸው ይመርጣሉ።
ይህ አስደናቂ ህዝባዊ ክንውን ሀገራችን በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላይ እያሳየች ያለውን ተስፋ ሰጪ እርምጃ እና የህዝቧን የፖለቲካ ንቃተ ህሊና በጉልህ የሚያንፀባርቅ ነው።
በአፍሪካ የዴሞክራሲ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛው የመራጮች ቁጥር በተመዘገበበት የዘንድሮው ምርጫ ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በድምፃቸው ያረጋግጣሉ።
ይህ የህዝብ ተሳትፎ ጠንካራ ተቋማት እና የዳበረ የፖለቲካ ባህል እየተገነባ ለመምጣቱ ህያው ምስክር ነው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ድምፅ በአንድነት ሲሰባሰብ የማይበገር ሀገራዊ አቅም እና ጠንካራ መንግስታዊ መሰረት ይፈጥራል።
ዛሬ ኢትዮጵያውያን ሉአላዊነታቸውን በድምፃቸው ያረጋግጣሉ።
Ethiopian Broadcasting Corporation #ምርጫ #በምርጫብቻ #ኢትዮጵያ #ምርጫ #በምርጫብቻ #ኢትዮጵያ #democrac #ምርጫ #በምርጫብቻ #ኢትዮጵያ #ምርጫ #በምርጫብቻ #ኢትዮጵያ #democrac
👍2
አፍሪካ ኅብረት ታዛቢ ቡድን መሪ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የምርጫ ዝግጅትን ተዘዋውረው እየጎበኙ ነው
👏2
የመጀመሪያዎቹ መራጮች
************
አዲስ አበባ ድምፅ እየሰጠች ነው!!
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!!
Ethiopian Broadcasting Corporation #ምርጫ
👏2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በበሻሻ ድምፅ ሰጡ
*******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትውልድ ቀያቸው በሻሻ ድምፅ ሰጥተዋል።
#EBC #Ethiopia #ebcdotstream #democracy #PMAbiyAhmed #Ethiopiaisvoting
👏1