Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.86K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
በካሜራችን እይታ ውስጥ የገቡ
***************

ከአዲስ አበባ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 03 በሚገኝ ምርጫ ጣቢያ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል አመመኝ፣ ደከመኝ፣ አልተመቸኝም የሚል ሰበብ ሳያበዛ ሁሉም መጥቶ ዴሞክራሲያዊ መብቱን እየተጠቀመ ነው።

ኢትዮጵያ ስትመርጥ ከቤቱ የቀረ የለም!!

Ethiopian Broadcasting Corporation #ምርጫ #ኢትዮጵያ #ዴሞክራሲ
👏1
አርቲስቶች ድምፃቸውን ሰጥተዋል
*****************
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሙዚቃ አቀናባሪው ካሙዙ ካሳ፣ ጋዜጠኛ እና የማስታወቂያ ባለሞያዋ በሻቱ ቶለማሪያም እና አርቲስት ሰለሞን ታሼ በአዲስ አበባ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
Ethiopian Broadcasting Corporation #ምርጫ #ዴሞክራሲ #ኢትዮጵያ
👏1
የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ድምፃቸውን ሰጡ
********************
እየተካሄደ በሚገኘው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ከተማ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 መሐንዲስ ኮንዶሚንዬም ምርጫ ጣቢያ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!!
Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢቢሲ #ምርጫ #ዴሞክራሲ
👏1
በአዲስ አበባ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጠት ሂደቱ ምሽቱንም እንደቀጠለ ነው፦

#ኢትዮጵያ #ምርጫ #ምርጫ2018 #ብሔራዊምርጫቦርድ #Ethiopia #Elections #Elections2026 #NEBE #EBC
👏1
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
****************

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-

• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።
👍4👏2
🎰 Welcome Bonus 1200% — Maczo Crypto Casino
🎮 Crypto exchange · Sports · Live casino — all in one place
💳 USDT instant deposit & withdrawal
→ https://tglink.io/41ec2690ebc969
👍1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለው የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ መርቀው ሥራ አስጀመሩ
**********************

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት፣ ዛሬ ጠዋት ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለውን የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት መርቀው በይፋ ሥራ ማስጀመራቸውን ገልጸዋል።
‎
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ‎ይህ ትልቅ ተነሣሽነት፤ የተራቆቱ አካባቢዎችን በዘመናዊ የአፈር ጥበቃ እና በወንዝ ማጣራት ወደ አረንጓዴ ስፍራዎች በመቀየር፣ የፍራፍሬ ፓርኮችን ከእግር ጉዞ እና ከብስክሌት መንገዶች ጋር በማቀናጀት መዲናችንን አድሷል ብለዋል።
‎
‎በአጠቃላይ 22.25 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማትን የሚሸፍነው ይህ ፕሮጀክት፣ የማይቆራረጥ የልማት ሥራችን ሕያው ምስክር ከመሆኑም በላይ የሀገራዊ ዕድገታችን፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የከተማ እድሳት በተግባር የታየበት ነው ሲሉም አክለዋል።

#EBC #Ethiopia #PMAbiyAhmed #development
👏1😁1