የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ በሰጡት መግለጫ ምን ምን ጉዳዮችን አነሱ?
**********************
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ፣ ከድምፅ መስጫ ቀን በኋላ ያለውን አጠቃላይ የምርጫ ሂደት ሁኔታና ቀጣይ ሥራዎችን አስመልክተው በሰጡት ማጠቃለያ መግለጫ በርካታ ዋና ዋና ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡ ሰብሳቢዋ በመግለጫቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦
የድምፅ አሰጣጥ እና የቆጠራ ሂደት ወቅታዊ ሁኔታ፦ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን የተከናወነው የድምፅ መስጠት ሂደት በአብዛኛው በጥሩ ሁኔታ መከናወኑን የገለጹት ሰብሳቢዋ፣ የተወሰኑ ክልሎች በሰዓቱ አጠናቀው ወዲያውኑ ወደ ቆጠራ መግባታቸውንና አንዳንዶቹ ደግሞ ቆጠራውን አሳድረው ማከናወናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በተለየ ሁኔታ በአዲስ አበባ በነበረው ረጅም ሰልፍ ምክንያት ቦርዱ እስከ ሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ድረስ የጊዜ ማራዘሚያ ማድረጉንና በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ እንዲሁም በሲዳማ፣ በጋምቤላ፣ በአማራ እና በሶማሌ ክልሎች የሚገኙ የተወሰኑ ምርጫ ጣቢያዎች አሁንም በድምፅ ቆጠራ ሥራ ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡
የመዘግየት ችግሮች እና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች፦ በአዲስ አበባ የተስተዋለውን የሰልፍ መርዘምና የመዘግየት ችግር ለመፍታት ቦርዱ በርካታ ከፍተኛ ባለሙያዎችንና ኤክስፐርቶችን ወደ ጣቢያዎች መድቦ እንደነበር ሰብሳቢዋ አስታውቀዋል፡፡
ለመዘግየቱ እንደ ምክንያት ያነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች በመራጮች መዝገብ ላይ ስም የመፈለግ ሂደት መርዘም እና በአንዳንድ ጣቢያዎች የዕጩዎች ቁጥር እስከ 123 መድረሱ መራጮች በምስጢር ድምፅ መስጫ ክፍል ውስጥ የሚወስዱትን ደቂቃ ማርዘሙን ነው፡፡
ይህንን ችግር ለመቅረፍም ቦርዱ ተጨማሪ የድምፅ መስጫ ሳጥኖችንና ቡዞችን ወደ ጣቢያዎች ልኮ መፍትሔ ለመስጠት መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ቅሬታዎችን ማስተናገድና የተወሰዱ የቅጣት እርምጃዎች፦ ቦርዱ በሕግ ክፍል፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች የሥራ ክፍል፣ በ6412 የጥሪ ማዕከልና ከታዛቢዎች በሚደርሱት ጥቆማዎች መሠረት የርምትና የማጣራት እርምጃዎችን ሲወስድ መቆየቱን ሜላትወርቅ ኃይሉ ገልጸዋል፡፡
በአዲስ አበባ አንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች መግባት የሌለባቸው ሰዎች ስለመታየታቸው የቀረቡ ጥቆማዎችን ቦርዱ በሞኒተሪንግ ቡድን አጣርቶ እውነት ሆነው በተገኙት ላይ እርምጃ መውሰዱንና ሕግና ደንብ ጥሰው የተገኙ የምርጫ ጣቢያ ሠራተኞችን ማሰናበቱን አረጋግጠዋል፡፡
የውጤት አሰጣጥ እና የማረጋገጥ ቀጣይ ሥራዎች፦ በአሁኑ ወቅት የምርጫ ውጤታቸው በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ተደምሮ ያለቀላቸው ውጤቶች በየጣቢያዎቹ ተለጥፈው ለሕዝብ ይፋ መደረጋቸውን የጠቀሱት ሰብሳቢዋ፣ ቀጥሎም ውጤቶቹ ወደ ምርጫ ክልል ሄደው የማዳመር ሥራ እንደሚሠራ አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም ውጤቶቹ ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት የማረጋገጫ ማዕከል ከመጡ በኋላ፣ ከተመዘገበው የመራጭ ቁጥር አንጻር ዋጋ ያላቸው እና የሌላቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ተለይተው የማረጋገጥ ሥራው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ቦርዱ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

👏1
የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አደነቁ
**************
የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት፣ ካናዳ፣ ኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ በጋራ ባወጡት መግለጫ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቀዋል።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለእጩዎች እና ለሲቪል ማኅበራት ለምርጫው ስኬት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንዲሁም ለአፍሪካ ኅብረት እና ለኢጋድ የምርጫ ታዛቢነት ሚና እውቅና ሰጥተዋል።
#EBC #Ethiopia #democracy #peace #DemocraticRights

👍1
"ኡሁሩ ኬንያታ እና ባልደረቦቻቸው ለዲሞክራሲ ግንባታ ሂደታችን ላበረከቱት አገልግሎትና አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልእክት የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የስራ ባልደረቦችን በማግኘቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል። የተከበሩ ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና 73 አባላት የያዘውን የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ፤ ለዲሞክራሲ ግንባታ ሂደታችን ላበረከቱት አገልግሎትና አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል።
ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ከአኅጉራችን ነባራዊ ሁኔታና ተሞክሮ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ለማድረግ አፍሪካዊ ተቋማት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። የምርጫ ሂደታችንን ለመደገፍ በመላው ሀገሪቱ ታዛቢዎችን በማሰማራት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩ ላደረገው ያልተቆጠበ ጥረት እውቅና እና አድናቆት እየሰጠን፣ የምልከታውን የተሟላ ውጤት እንጠብቃለን ሲሉም ነው ጠቅላይ መኒስትሩ የገለፁት።
Ethiopian Broadcasting Corporation #ምርጫ

ሊቨርፑል አንዶኒ ኢራኦላን በአሠልጣኝነት አስፈረመ
*****************
አንዶኒ ኢራኦላ እስከ ሰኔ 2028 ድረስ የሊቨርፑል አሠልጣኝ ለመሆን የሁለት ዓመት ውል ፈርመዋል።
ስፔናዊው የቀድሞው የበርንማውዝ አሠልጣኝ ባለፈው ቅዳሜ ከክለቡ ጋር የተለያዩትን አርነ ስሎትን የሚተኩ ይሆናል።
#EBC #englishpremierleague #Liverpool #football

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ከቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተወያዩ
************************
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ከአፍሪካ ህብረት የታዛቢዎች ቡድን መሪ እና ከኬንያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር መክረዋል።
ውይይቱ ትኩረቱን ያደረገው የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ምልከታ አካል በሆነው የድህረ ምርጫ የምክክር መድረክ ላይ ነው።
ህብረቱ ወደፊት በሚደረጉ የምርጫ ሂደቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኝነቱን አስታውቋል።
በምክክሩ ላይ የቦርዱ ሌሎች አመራሮች እና የህብረቱ ታዛቢ ቡድን አባላት ተገኝተዋል።
Ethiopian Broadcasting Corporation

ከምርጫ በኋላ ምን ይከናወናል?
****************
1. የድምፅ ቆጠራ እና ማረጋገጥ
ከምርጫ ጣቢያዎች ጀምሮ የተሰጡ ድምፆችን በጥንቃቄ መቁጠር እና ማረጋገጥ።
2. ውጤትን ይፋ ማድረግ
ከምርጫ ጣቢያ ጀምሮ በየደረጃው ውጤት መግለጽ፣ በመጨረሻም በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የተረጋገጠውን አጠቃላይ ውጤት ለሕዝብ ይፋ ማድረግ።
3. የታዛቢዎች መግለጫ
የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች የሒደቱን አጠቃላይ ሁኔታ አስመልክቶ ሪፖርት (መግለጫ) ማቅረብ።
4. ቅሬታዎችን በሕግ መፍታት
ተፎካካሪ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች የሚያነሷቸውን አቤቶታዎች በሕገ-መንግሥታዊ መንገድ እና በሕግ አግባብ መፍትሔ መስጠት።
5. የአፈጻጸም ግምገማ
የምርጫ አስፈጻሚ አካላት በምርጫው የነበራቸውን አጠቃላይ ሒደት፣ ጥንካሬና ክፍተት መገምገም።
6. መንግሥት መመሥረት
የሕዝብን ውሳኔ (ድምፅ) መሠረት በማድረግ ሥልጣን ማስተላለፍ እና ወደ ተግባራዊ የመንግሥት ምሥረታ መቀየር።

ሰሞኑን በአርሲ እና ጎንደር የተፈጸሙ የሽብር ጥቃቶችን መንግሥት በጽኑ ያወግዛል፡- የሰላም ሚኒስቴር
*************
በአርሲ ዞን እና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በንጹኃን ዜጎችና በእምነት ተቋማት ላይ የተፈጸሙትን አሳዛኝ የሽብር ጥቃቶች መንግሥት በጽኑ እንደሚያወግዝ የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሀመድ እድሪስ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ ሀገራዊ ለውጡንና የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ ተስፋ የቆረጡ ጽንፈኛ ኃይሎችና የውጭ ጠላቶች፥ የኢትዮጵያን ሰላምና የሕዝብ አብሮነት ለማፍረስ አደገኛ የትንኮሳ ካርዶችን እየመዘዙ መሆኑን አስታውቀዋል።
በአርሲ ዞን የሽብርተኛው የሸኔ ቡድን መጀመሪያ ከጸጥታ አካላት ጋር ግጭት መፍጠሩን ሚኒስትሩ ገልጸው፣ በአካባቢው ሕዝብ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ በጀግንነት የተዋጉ 5 የሚሊሻ እና 3 የፖሊስ አባላት መስዋዕት መሆናቸውን ተናግረዋል።
በቡድኑ እኩይ ጥቃት ንጹሃን ዜጎች መገደላቸው እና አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0314Q7kY1Hj6MKR1y6PKofq5qbzM38Nvo3VhfeEevh4z1erSpDyJBHiw4PQSkxUizEl

ሀገርን ለመበተን የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ህልም ማምከን ተችሏል፡- ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
***************
መከላከያ ሠራዊቱ በታላቅ ተጋድሎና መስዋዕትነት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያስጠበቀ፣ የዳር ድንበሯን ያስከበረና ለሕዝቧ ሰላምና ልማት መረጋገጥ ግዳጅና ተልዕኮዎቹን በብቃት የተወጣ የሕዝብ ኩራት መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ፡፡
የሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የ27ኛ ዙር የፅናት ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ የጀግኖች እና የአርበኞች ሀገር ናት ብለዋል፡፡
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከውጭ ኃይሎች የገንዘብ ድጋፍና ተልዕኮ በመቀበል ሀገርን ለመበተን ሴራ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ህልም ማምከን መቻሉንም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ገልጸዋል።
ዕጩ መኮንኖቹ ሕዝብና መንግሥት የጣሉባቸውን አደራ በመቀበል…(20+) ሀገርን ለመበተን የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ህልም... - Ethiopian Broadcasting Corporation | Facebook