Ethiopian Broadcasting corporation ®
8.88K subscribers
17.9K photos
205 videos
14 files
1.62K links
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Download Telegram
ሲዳማ ቡና ወደ ሊጉ ሻምፒዮናነት ይበልጥ የተቃርበበትን ድል አስመዘገበ
********

በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 35ኛ ሳምንት ጨዋታ፤ ሲዳማ ቡና ተጠባቂውን ጨዋታ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር አድርጎ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለዋንጫው ያለውን ዕድል ይበልጥ አስፍቷል።

ለሲዳማ ቡና ያሬድ ባዬ እና ብርሃኑ በቀለ ግቦቹን ሲያስቆጥሩ፣ ለኢትዮጵያ ቡና ዘላለም አባተ ከሽንፈት ያልታደገቻቸውን ከመረብ አሳርፏል።

ይህንን ውጤት ተከትሎ ሲዳማ ቡና ነጥቡን 64 በማድረስ የሊጉን መሪነት ይበልጥ ከማጠናከሩም በላይ ወደ ሻምፒዮንነቱ እጅግ ሲቃረብ፤ ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ በ46 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በሌላ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ መቻልን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።

ለፈረሰኞቹ የማሸነፊያ ግቦቹን ፍጹም ጥላሁን፣ ሀብታሙ ጉልላት እና የአብሥራ ተስፋዬ ከመረብ አሳርፈዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ49 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣ በመሸነፉ የዋንጫ ፉክክር ዕድሉ የጠበበው መቻል በ53 ነጥብ በ2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

#EthiopianFootballEthiopianBroadcastingCorporation #EthiopianPremierLeague
👍1👏1
የ6ኛ ክፍል ከተማ እና ክልል አቀፍ ማጠናቀቂያ ፈተና በነገው ዕለት መሰጠት ይጀምራል
***************

የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ከተማ አቀፍ እና ክልል አቀፍ ፈተና በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በሌሎችም የሀገራችን ክልሎች በይፋ መሰጠት ይጀምራል።

ከነገ ሰኔ 8 እስከ ረቡዕ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በሚሰጠው በዚህ ማጠናቀቂያ ፈተና ላይ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ የሚሸጋገሩበትን ብቃት ለመመዘን በየክልሎቹ የትምህርት ቢሮዎች አዘጋጅነት አስፈላጊው የቅድመ-ዝግጅት ሥራ ተጠናቆ ነገ መርሐ ግብሩ በይፋ እንደሚጀመር…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02vfQ3Ff6YNutwgQmts4y9dXae1sGoNnXRxRbNPo2t6ft2emb94Y9TN9KnMN3QpaFhl
👏2
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘገበ።

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የተለያዩ ባህላዊ እና ሌሎች ይዘቶቸ ያሏቸው የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድማጭ ተመልካች አበርክቷል፡፡

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበር።

ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ/ም
😢1
ቱኒዚያ አሰልጣኝ ሳብሪ ላሙቺን አሰናበተች
*********

የቱኒዚያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ቡድኑ በዓለም ዋንጫው መክፈቻ በስዊድን 5 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት መሸነፉን ተከትሎ፣ የ54 ዓመቱን ዋና አሰልጣኝ ሳብሪ ላሙቺን ማሰናበቱን ‘ዘ ሰን’ ዘግቧል።

ውሳኔው የተላለፈው የፌዴሬሽኑ አመራሮች ከሽንፈቱ በኋላ ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ ሲሆን፣ ደጋፊዎች ድርጊቱን በዓለም ዋንጫ መድረክ ላይ የተወሰደ እጅግ አስከፊ ውሳኔ ሲሉ እየተቹት ይገኛል።

አሰልጣኝ ሳብሪ ላሙቺ የካርቴጅ ንስሮቹን በዋና አሰልጣኝነት የመሩት ለአምስት ጨዋታዎች ብቻ ሲሆን፣ በዓለም ዋንጫው መድረክ ግን በአንድ ጨዋታ ብቻ መርተው መሰናበታቸው በውድድሩ ታሪክ ክስተት ሆኗል።

ቱኒዚያ ከዓለም ዋንጫው በፊት በቤልጂየም እና በስዊድን በሰፊ ግቦች መሸነፏ ይታወሳል። ይህ ደግሞ በደጋፊዎችና በቦርዱ አባላት ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።

ላሙቺ ቡድኑን ከተረከቡ በኋላ በሄይቲ ላይ ካስመዘገቡት ብቸኛ ድል ውጭ ከካናዳ፣ ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም እና ስዊድን ጋር ባደረጓቸው ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።

የካርቴጅ ንስሮቹ የፊታችን ቅዳሜ ከጃፓን ጋር ወሳኝ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ በመሆኑ፣ የቀድሞ ኮከቡን ዋህቢ ኻዝሪን ወይም የቀድሞውን አሰልጣኝ ሞንድሄር ኬባየርን በጊዜያዊነት ለመሾም ማሰባቸውን ዘ ሰን እና ስፖርት ሞል ዘግበዋል።

በአዲስ የሺዋስ

#FIFAWorldCup #tunisia #Ebc #Sport
👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በይፋ አስጀመሩ
****************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ በዚህ ዓመት 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ግብ አስቀምጠን፣ ከፍ ወደ አደረግነው 65 ቢሊዮን ችግኞች ግብ የመድረስ ትልማችንን ለማሳካት በጽናት እየገሰገስን እንገኛለን ብለዋል።
‎
‎ንቅናቄውን ተቀላቅለው ለመጭው ትውልድ አረንጓዴ ዐሻራዎን ያኑሩ ሲሉም ለመላው ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርበዋል።

#Ethiopia #EBC #PMAbiyAhmed
👏1