ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውን የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ በይፋ መረቁ
*******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ '‘ዲጂታል ለልህቀት'’ በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ በመገኘት፣ ከተለያዩ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በአንድ መድረክ ላይ የሚያጣምረውን እና በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውን የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ በይፋ መርቀው ስራ አስጀመሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልእክት፣ ይህ ታላቅ ስኬት ለሀገራችን ከፍተኛ የኩራት ምንጭ ከመሆኑም በላይ በቴክኖሎጂ የሚመራ እና ዓላማ ተኮር ኢንቨስትመንት ምን ሊያስገኝ እንደሚችል ማረጋገጫ መሆኑን ገልጸዋል።
"መሶብ" የተሰኘው ይኸው የአንድ ማዕከል አገልግሎት ወሳኝ የኢኮኖሚ መሠረተ ልማት መሆኑን ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መተግበሪያው የዜጎችን ጊዜ እንደሚቆጥብ፣ የሙስና ቀዳዳዎችን እንደሚደፍን፣ እንዲሁም በመንግሥት በኩል የተቋማትን ታማኝነትና ጥንካሬ እንደሚያጎለብት አስታውቀዋል።
አያይዘውም ይህ ስኬት ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ትልሞች ተራ ምኞት ብቻ ሳይሆኑ፣ በራሳችን እጆችና አቅም የምንገነባቸው እውነታዎች መሆናቸውን በግልጽ የሚያሳይ ምስክር መሆኑን አብራርተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንን ስኬት ይበልጥ በማጠናከር፣ የተገኘውን ልምድና ተሞክሮ ለአፍሪካውያን ወንድሞች እና እህቶች በማካፈል፣ እንዲሁም ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት ወደፊት መጓዝ እንደሚገባ አገራዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

👍1👏1
ከ60 ኮርሶች 47ቱን 'A+' ያስመዘገበችው የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የዓመቱ ኮከብ መሃንዲስ ሩት አባተ
*********************
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) በዛሬው ዕለት ካስመረቃቸው 1 ሺህ 387 ተማሪዎች መካከል የኤሌክትሪካል ፓወር ኤንድ ኮንትሮል ኢንጅነሪንግ ተማሪዋ ሩት አባተ የዓመቱ ኮከብ ተማሪ በመሆን የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።
ሩት በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ ከወሰደቻቸው 60 ኮርሶች መካከል 47ቱን 'A+' እንዲሁም 13ቱን 'A' በማምጣት ሙሉ 4.00 (አራት ነጥብ) ውጤት ያስመዘገበች ሲሆን፣ በእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ (Very Great Distinction) ተመርቃለች።
በአዳማ ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ያጠናቀቀችው ሩት፣ ለዚህ ውጤት የበቃችው ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ ባደረገችው ተከታታይ ጥረትና ከመጀመሪያው ዓመት ጀምሮ ለትምህርቷ ልዩ ትኩረት በመስጠቷ እንደሆነ ገልጻለች።
ለስኬቷ የቤተሰቦቿ ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበር የጠቀሰችው ሩት፣ በተለይም አባቷ የቅርብ አማካሪና አስጠኝ በመሆን፣ እናቷ ደግሞ የዕለት ተዕለት ክትትል በማድረግ ለውጤቷ መሳካት ትልቅ እገዛ ማድረጋቸውን ገልጻለች።
ሴቶች የመማር ዕድል ካገኙ ማህበራዊ ጫናዎችን አልፈው ስኬታማ መሆን እንደሚችሉ ሩት ትናገራለች።
በቀጣይም የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቷን የመቀጠል እቅድ ያላት ሲሆን፣ “በኢነርጂውና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ለሀገሬ ጠቃሚና ችግር ፈቺ ባለሙያ ለመሆን እተጋለሁ” ስትል ምኞቷን ገልጻለች።
በአሸናፊ እንዳለ
Ethiopian Broadcasting Corporation #አዳማ #ዋንጫ #ሜዳሊያ #ኢትዮጵያ #ጀግና

👏4
ሲዳማ ቡና የ2018 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ
*
ዛሬ በ36ኛው ሳምንት የሊጉ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ነጌሌ አርሲን የገጠመው ሲዳማ ቡና 1 ለ 1 አቻ ተለያይቷል።
የሲዳማ ቡናን ግብ ያስቆጠረው ብርሀኑ በቀለ ሲሆን፤ በረከት ወልዴ ነጌሌ አርሲን በፍፁም ቅጣት ምት አቻ አድርጓል።
በዚህም ነጥቡን 65 ያደረሰው ሲዳማ ቡና ሁለት ሳምንታት እየቀሩ ከወዲሁ የ2018 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።
#EthiopianPremierLeague

👍3👏3
አጀንዳዎቹ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ድምፅ እና ፍላጎት የተቀዱ ናቸው፡- ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ
*****************
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕ/ር) ኮሚሽኑ ላለፉት አራት ዓመታት በመላው ኢትዮጵያ እና በውጭ ሀገር ከ200 ሺህ በላይ ዜጎችን በማማከርና በማወያየት ያሰባሰባቸውን ዋና ዋና አጀንዳዎች ዛሬ ይፋ አድርገዋል።
ኮሚሽነሩ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ሀገራዊ መግባባትና የጋራ ዕድልን በጋራ መበየን በሚያስፈልጋት ታሪካዊ መስቀለኛ መንገድ ላይ የምትገኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም ኮሚሽኑ በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሕዝብን ተሳትፎ ያረጋገጠና ከታች ወደ ላይ የሚመጣ ስልትን በመከተል አካታችና ሁሉን አቀፍ በሆነ መንገድ ስምንት ሀገራዊ አጀንዳዎችን ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።
በዚህ መሠረት የተዘጋጁት ስምንቱ አጀንዳዎች ሙሉ በሙሉ...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0Ajrt8YFPVB14LFsrc8bamSTTU8LbcuoJM6hxM6dpe4am3vEk4BwYo3skavLSAwWYl

👏1
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለምክክሩ መሳካት ሁሉም ወገኖች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ
****************
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከቀረቡለት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ጉዳዮች መካከል ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው 8 ዓበይት አጀንዳዎችን መለየቱን አስታውቋል።
እነዚህ አጀንዳዎች በመጪው ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚጀምረው ታላቅ ጉባኤ ላይ 130 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብን የሚወክሉ ተሳታፊዎች በሰፊው የሚመክሩባቸው ዋና ዋና ጭብጦች መሆናቸውን ገልጿል።
ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ የተመረጡት 8 አጀንዳዎች በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የተካሄዱ...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02manwTgihXyRC5CDjhxV7mMkzhkQ2TEAt6RFt5Li5stYjG48nDUAHqQ5yrz52GVjRl