Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
6.24K subscribers
2.51K photos
190 videos
6 files
279 links
Official Great Ethiopian Run Telegram Channel.

Call 0116635757 for more details.
Download Telegram
🚨 የ2016 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጲያ ዓለምአቀፍ 10 ኪ.ሜ. በ6 ሳምንታት ውስጥ ይካሄዳል፡፡

ልምምድ የሚጀመርበት ጊዜ አሁን ነው! 🏃🏾‍♂️🏃🏾‍♀️

ጠዋትም ሆነ ማታመሮጥ ወይም በጂም ውስጥ መስራትም ቢሆን ዋናው ነገር የማይቋረጥ ልምምድ ማድረጋችሁ ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ ስነምግባር ያስፈልጋል፡፡ በመጨረሻም ለልምምድ አዲስ ከሆኑ ቀስ ብለው ይጀምሩ፡፡

የስድስተኛ ሳምንት የአትሌት ሀይሌ የተከበረ ምክር ለማግኘት👇
https://youtu.be/qNQ8Ao8lB_k?si=u63DQSqPhrmVaseQ

ህዳር 9 እንገናኝ!

#የኛ_መገለጫ
👍13❤1
🪧 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቁጥራቸው ላቅ ያለ የውጪ ተሳታፊችን እና የክብር እንግዶችን ለመቀበል እየተዘጋጀ ነው፡፡

✈️ በ2016 ከ10 በላይ ከሆኑ ሃገራት የሚመጡ ተሳታፊዎች ምዝገባቸውን አጠናቀዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ህንድ፤ ብራዚል፤ ኬንያ፤ ኡጋንዳ፤ ደቡብ አፍሪካ፤ ስዊዘርላንድ፤ አውስትሪያ፤ ስዊድን፤ ኖርዌይ፤ ጀርመኒ፤ አየርላንድ፤ እንግሊዝ እና አሜሪካ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

🏅ከዛም ባለፈ የደቡብ አፍሪካዋ ኤላና ሜየር የዘንድሮ ዝግጅት የክብር እንግዳ ናት።

እ.ኤ.አ. በ1992 ባርሴሎና ላይ በተካሄደው ኦሎምፒክ ላይ ከኢትዮጵያዊቷ ደራርቱ ቱሉ ጋር ባደረገችው ትንቅቅ በተለይ የምትታወሰው ሜየር በውድድሩ ላይ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳልያ ማግኘቷ ይታወሳል፡፡

ኤለና ሜየር በተጨማሪም በ1994 የአለም ግማሽ ማራቶን ሻምፔውና የሆነች ሲሆን የአለም ሪከርዶችንም በ1991፤ 1997፤ 1998 እና 1999 ላይ ያስመዘገበችው ኤለና 1 ሰአት ከ6 ደቂዳ 44 ሰከንድ (1፡06፡44) በ1999 ያስመዘገበችው ፈጣኑ ሰአትዋ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ👇
https://ethiopianrun.org/great-ethiopian-run-prepares-to-welcome-hundreds-of-international-runners-and-guests-to-annual-running-festival/2504/

#GreatEthiopianRun #LandOfRunners #የኛ_መገለጫ
👍8❤4
ባለፈው ሳምንት ልምምዳችሁን በቀስታ እንደጀመራችሁ እናስታዉሳልን፡፡

የዚህኛው ሳምንት ምክር ደግሞ ቀስ በቀስ እንድታዳብሩት ነው፡፡ በዚህኛው ሳምንት ለ30 ደቂቃ ያህል መሮጥ ወይም መራመድ ከቻሉ ለሚቀጥለው ሳምንት 40 ደቂቃ አድርጉት ከዛ ደግሞ ወደ 50 ደቂቃ አሳድጉት፡፡

በሌላ አባባል ደረጃ በደረጃ… ሁል ጊዜ እንደምንለው ለከባድ ልምምድ አንጣደፉ፡፡ ሰውነትን በልምምድ ማዳበር ጊዜ ይፈልጋል፡፡

ለሁሉም ነገር ድግግሞሽ እና ስነ-ምግባር ወሳኝ ናቸው!

የስድስተኛ ሳምንት የአትሌት ሀይሌ የተከበረ ምክር ለማግኘት👇
https://youtu.be/alGoMIL-1xQ

ህዳር 9 እንገናኝ!

#የኛ_መገለጫ
👍12
🔴ቀዩ ማዕበል ለምን ቀረ?🤔

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተ ወቅት ውድድራችንን ለተሳታፊዎች በተቻለ ጥንቃቄ ለማድረግ ይረዳን ዘንድ የባንዲራችንን 3 ቀለማት አረንጋዴ ቢጫ እና ቀይ በመጠቀም በ3 ማእበል መነሻዎችን አድርገን ነበር፡፡

አሁን ግን ከኮቪድ በፊት ወደነበረን አሰራር ተመልሰን የውድድር መነሻችንን 2 ማዕበል ብቻ አድርገናል፡፡

በመሆኑም የባንዲራችንን ቀለም በየአመቱ ከሶስቱ አንዱን የአመቱ ዋና ቀለም በማድረግ የምንጠቀም ይሆናል፡፡

ህዳር 9 እንገናኝ!

#የኛ_መገለጫ #GreatEthiopianRun
👍8👎8🔥4
🇪🇹 ደማቅ ቀለማት አስደሳች ጊዜ!

የ2010 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ትዉስታዎች

የዘንድሮ ታላቁ ሩጫ ላይ የማይረሳ ጊዜ ለማሳለፍ ዝግጁ ናችሁ?!

ህዳር 9 እንገናኝ!

#TBT #GreatEthiopianRun #Ethiopia
👍10
ዱብዱብ ለታላቁ ሩጫ!🏃🏾‍♀️🏃🏾‍♂️

ለዘንድሮ የ2016 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለምአቀፍ 10ኪ.ሜ. ልምምድ ጀምራችኋል⁉️

ለ4 ሳምንት የሚካሄደ የሶፊ ማልት 4 ሳምንት የአካል ብቃት ሥልጠና ይሳተፉ❕

📍 ሥልጠናው የሚካሄደው በቦሌ አለም ሲነማ ሲሆን የፊታችን እሁድ ጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ነው።

🚨 ለግል ተመዝጋቢዎች ዉስን ቦታ ሰላለ መሳተፍ ለምትፈልጉ በ +251 116 635757 ላይ በመደወል ቦታዎን ያሲዙ!

እሁድ እንገኛኝ!

ለበለጠ መረጃ 👇
☎️ +251116635757

#የኛ_መገለጫ #GreatEthiopianRun
👍4❤1
🗣ነገ እንገናኝ!

የሶፊ ማልት 4 ሳምንት የአካል ብቃት ሥልጠና ነገ ይጀመራል!

📍 ሥልጠናው የሚካሄደው በቦሌ አለም ሲነማ ሲሆን የፊታችን እሁድ ጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ነው።

🔴 ከላይፊትነስ አሰሪዎች ጋር ዱብዱብ እያልን ለ2016 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለምአቀፍ 10ኪ.ሜ. አበረን እነዘጋጅ!

#የኛ_መገለጫ #GreatEthiopianRun
👍9❤2
🇪🇹 4 ሳምንታት ብቻ!

ለ2016 ሶፊ ማልት  ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ 10ኪ.ሜ. 4 ሳምንታት ብቻ ቀርተውታል!

ዝግጁ የሆናችሁ እስኪ እንያችሁ! 👍 ዱብዱብ እያልን ካሁኑ እንዘጋጅ!

ታላቁ ሩጫ የኛ መገለጫ! 🇪🇹

ህዳር 9 እንገናኝ!

#የኛ_መገለጫ
👍11
2016 ሶፊ ማልት  ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ 10ኪ.ሜ. በ1 ወር ውስጥ ይካሄዳል! ዝግጁ ናችሁ?

በከፍተኛ ፍጥነት ይሩጡ እና በትንሹ ለማገገም ያርፋሉ፣ ከዛ ይህንኑ መደጋገም ነው

ለምሳሌ፡- ለ1ደቂቃ በፍጥነት ከሮጡ ለ1ደቂቃ በእርምጃ ወይም በሶምሶማ ማረፍ፡፡ ይህን ከ6 እስከ 8 ጊዜ ይደጋግሙ፡፡ ይህ የልምምድ አይነት አካል ብቃትን ለመጨመር ጥሩ መንገድ ነው፡፡

በርቱ! ህዳር 9 እንገናኝ!

የአራተኛ ሳምንት የአትሌት ሀይሌ የተከበረ ምክር ለማግኘት👇
https://youtu.be/tnyI9lYjGd8

ታላቁ ሩጫ የኛ መገለጫ! 🇪🇹

#የኛ_መገለጫ
👍4❤1