የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ምዝገባ ነገ ይጀመራል
የብር ኢዮቤልዩ ላይ የደረሰው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ውድድሩን ምዝገባ ነገ ይጀምራል።
የ25ኛ ዓመት ውድድሩ ላይ ለመመዝገብ እና ተሳታፊ ለመሆን የሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ በህያት ሬጀንሲ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።
ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ ምዝገባውን በዲጂታል / በኦንላይን እንደሚያከናውን የገለፀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ፤ ተመዝጋቢዎች ቴሌብር እና ዳሽን ባንክ ሱፐር አፕን በመጠቀም መመዝገብ እንደሚችሉ አሳውቋል።
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ “እንደ አንድ የአለም አትሌቲክስ ሌብል ያለው ውድድር (World Athletics Label Race) የምዝገባ መንገዳችን መዘመኑ አስደሳች ነው። በተጨማሪም እያደገ ለመጣው ውድድራችን እና ለተሳታፊዎቻችን የተሻለ እና ቀላል አማራጭ ማቅረብ የምንችልበት መንገድ ሆኗል” ብለዋል።
ህዳር 14 / 2018 ዓ.ም. ላይ የሚካሔደው ውድድሩ እንዳለፉት አመታት ሁሉ ሁለት የመሮጫ ማዕበሎች ይኖሩታል። በዚህም መሰረት ከነገ ጀምሮ በሚኖረው ምዝገባ ላይ ፤ የመመዝገቢያ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ለዘና ማዕበል 790 ብር እና ለፈጣን ማዕበል 950 ብር ይሆናል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የውድድሩን 25ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለእያንዳንዱ 25’ኛ ተመዝጋቢ ግለሰብ በነጻ የመመዝገብ ዕድል እንደተመቻቸ ፤ ይህም ከ700 በላይ ተሳታፊዎች በነጻ እንዲመዘገቡ ዕድልን ይፈጥራል ተብሏል።
ባለፈው የውድድር አመት ከነበረው የ50ሺህ ተመዝጋቢዎች ቁጥር በአምስት ሺህ ከፍ በማድረግ ፤ ዘንድሮ 55ሺህ ተሳታፊዎች ይመዘገባሉ ፤ በውድድሩ ቀንም ከዚህ ዓመታት የላቀ ቁጥር ያላቸው ተሳታፊዎች እንደሚኖሩት እና 10ኪ.ሜ. ርቀቱን እንደሚጨርሱ ይታመናል።
ልዩ ዝግጅቱ ላይ የሰራተኞቻቸውን ጤና በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የሚጠብቁ እና በተለያዩ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድሮች ላይ በተደጋጋሚ የሚያሳትፉ 11 ተቋማት ለሁለተኛ ጊዜ በተካሔደው የ'ኮርፖሬት ዌልነስ አዋርድ’ ላይ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከሚደረገው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ጎን ለጎን በ25 የአለማችን ከተሞች ላይ ኢትዮጵያን እና ሩጫውን በሚያስተዋውቅ መልኩ የርቀት (ቨርችዋል) ተሳታፊዎችን በማካተት ይካሔዳል።
የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ህዳር 14 ቀን 2018ዓ.ም. የሚከናወን ሲሆን ፤ ከነገ ጀምሮ ምዝገባቸውን የሚያከናውኑ ተመዝጋቢዎች መወዳደሪያ ቲሸርቶቻቸውን የውድድሩ ሳምንት ላይ በሚኖሩት 3 ቀናት የሚረከቡ ይሆናል።
የዘንድሮ ውድድር አጋሮች- ሶፊ ማልት የስያሜ አጋር ፣ ዩኒሴፍ የመልዕክት አጋር ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉዞ አጋር ፣ ኢትዮ ቴሌኮምና ቴሌ ብር የቴክኖሎጂ አጋር ፣ ዳሽን ባንክ የባንክ አጋር ፣ ፋብ የውበት ሳሙና የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫዎች የንዕህና አጋር ፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር ፣ ቶፕ ውሃ ፣ ሃያት ሬጀንሲ ፣ ኢ.ቢ.ሲ. እና አፍራን ሆስፒታል ናቸው።

❤39👍12👏3
ምዝገባ ተጀምሯል🤩✨
ባላችሁበት ሆናችሁ በቴሌብር እና በዳሽን ባንክ ሱፕር አፕ ይመዝገቡ!
ሀገር በ10ኪ.ሜ.!✨
2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ.!
#GreatEthiopianrun #10k #25thEdition #Registration

❤27👍5
🎉 100 ቀናት ብቻ ..... ቀሩ! 📢
በአንድነት ድምቅ ፍክት የምንልበት የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. - 100 ቀናት ብቻ ይቀሩታል ✨
💫 2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ.✨
#GreatEthiopianrun #25thEdition #10k #ANationIn10km
💻/ 📱- Facebook | TikTok | Instagram | YouTube

❤17🔥9👍1
በዓመቱ ከነበሩን 16 ሩጫዎች ውስጥ ተሳትፈው ከነበር ይህ ቪድዮ ለእርስዎ ነው!
እኛ አመቱን እንዲህ አሳልፈናል 🤩 በቀጣይ ከተጨማሪ ውድድሮች ጋር እንመጣለን።
https://youtu.be/d3VVN1vdaJg?si=Ic0G4Kh93wix1B1S
#GreatEthiopianRun #Ethiopia

YouTube
16 Races, One Spirit | Great Ethiopian Run 2024/25 Season Recap
From the streets of Addis to breathtaking regional landscapes, the Great Ethiopian Run brought together thousands of runners across 16 unforgettable races in the 2017 Ethiopian Calendar (2024/25).
One organization. Sixteen races. Thousands of stories. ✨ …

❤6👍6👏1
🚨 ማስታወቂያ! ለክለቦች፣ ለአትሌት ማናጀሮች እና በግል ለሚወዳደሩ አትሌቶች በሙሉ 🏃🏾♀️🏃🏾
የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. የአትሌቶች ምዝገባ ተጅምሯል!
ምዝገባ:- ላምበረት ማራቶን ህንፃ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮአችን በመግኘት አልያም በስልክ በመደወል እንድትመዘገቡ / አትሌቶቻችሁን እንድታስመዘግቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ለበለጠ መረጃ
011-663-5757
011-663-3646
#GreatEthiopianRun #Ethiopia #ANATIONIN10KM #10k

❤12👍2
በነጻ 💫ምዝገባ!!!!
የእንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ ምዝገባ ተጀምሯል!
ለአዲስ አመት አዲስ ስጦታ!
እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ💫💫
#GreatEthiopianrun #Ethiopia #entoto #cbe

👍18❤13
ቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ በእንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን እንገናኝ!✨
📌ጥቅምት 1 / 2018!
አሁኑኑ በሲቢኢ ብር ፕላስ ተመዝግበው ይቀላቀሉን!✨
እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ✨
#GreatEthiopianRun #EntotoCBERun
📌ጥቅምት 1 / 2018!
አሁኑኑ በሲቢኢ ብር ፕላስ ተመዝግበው ይቀላቀሉን!✨
እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ✨
#GreatEthiopianRun #EntotoCBERun
❤7🤩1
🎉 50 ቀናት ብቻ - ቀሩን! 📢
ሀገር በ10ኪ.ሜ.
በአንድነት ድምቅ ፍክት ልንል - 50 ቀናት ብቻ ይቀሩናል ✨
💫 2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ.✨ ህዳር 14
#GreatEthiopianrun #25thEdition #10k #ANationIn10km
ሀገር በ10ኪ.ሜ.
በአንድነት ድምቅ ፍክት ልንል - 50 ቀናት ብቻ ይቀሩናል ✨
💫 2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ.✨ ህዳር 14
#GreatEthiopianrun #25thEdition #10k #ANationIn10km
❤18👏8
የ2018 ዩኒሴፍ የልጆች ሩጫ ምዝገባ እና ‘ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ’ ዘመቻ ተጀመረ
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ2018 ዩኒሴፍ የልጆች ሩጫ ምዝገባን እንዲሁም የ'ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ' ዘመቻ ማስጀመሩን ዛሬ በህያት ሬጀንሲ በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ አድርጓል።
በተለያዩ የዕድሜ ደረጃዎች ለልጆች የሚዘጋጀው ይህ ልዩ የውድድር ቀን ከ11 ፣ ከ8 እና ከ5ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች ሁሉ ክፍት ነው።
ከነገ ጀምሮ በቦሌ አለም ሲኒማ እና በታላቁ ሩጫ ቢሮ ላምበረት ምዝገባ የሚካሔድ ሲሆን ፤ የመመዝገቢያ ዋጋ 400 ብር ብቻ ነው ሲሆን ‘የልደት ምዝገባ ለሁሉም ህጻናት’ በሚል መሪ ቃል ይካሔዳል።
በተጨማሪም በመግለጫው የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. አካል የሆነው የ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ የበጎ አድራጎት ዘመቻ መጀመሩ ይፋ ተደርጓል።
ዘንድሮም በዘመቻው አራት (4) ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ የታቀደ ሲሆን ፤ ቼሻየር ኢትዮጵያ ፣ ተስፋ ማህበራዊ እና ልማት ማህበር እና የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ድጋፍ እንዲደረግላቸው በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የተመረጡ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ናቸው።
በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ያሉ የታላቁ ሩጫ ተሳታፊዎች ደጋፍ ማሰባሰብ የሚችሉባቸው የድረ-ገፅ እና የመሰብሰቢያ ቅጽ አማራጮች ይፋ ተደርገዋል። በተጨማሪም የ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ምዝገባ ላላከናወኑ በተጨማሪ ክፍያ የሚደረግ ጥቂት ምዝገባ ለዚሁ አላማ ይውላል።
በዝግጅቱ ላይ ባለፉት የውድድር ዓመታት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከ40ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ እንዲችል ያገዙ እና ድጋፍ ያሰባሰቡ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

❤19🔥3👍2👏1