Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
6.21K subscribers
2.5K photos
190 videos
6 files
279 links
Official Great Ethiopian Run Telegram Channel.

Call 0116635757 for more details.
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ኃይሌ የቅዳሜ ቀጠሯችሁን በእንጦጦ ፓርክ እንድታደርጉ ይጋብዛችኋል! 🤩

✨እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ ✨

#EntotoParkCBERun #GreatEthiopianRun
👍6❤3🔥2
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እና ኢትዮ ቴሌኮም በአትሌቶች መገኛዋ ቦቆጂ ለአምስተኛ ተከታታይ ዓመት ውድድር ሊያደርጉ ነው
 
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በዓለም ታዋቂ የረጅም ርቀት ሯጮች መፍለቂያ በሆነችው በቦቆጂ ከተማ ከአምስት ዓመታት በፊት የጀመሩትን ስኬታማ አጋርነት በዚህ ሳምንት በሚደረገው ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በቦቆጂ ላይ ለማድረግ ምዝገባን አጠናቅቀዋል።

ይህ ግማሽ አስርት ዓመታትን ያስቆጠረ ትብብር ማህበረሰብን ለማብቃት፣ የዲጂታል ተጠቃሚነትን ለማስፋፋት እና በስፖርት አማካኝነት ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ሁለቱ ተቋማት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ ነው።

ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሔደው የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በቦቆጂ ታዋቂ አትሌቶችን፣ ታዳጊ እና ወጣት ሯጮችን፣ የማህበረሰብ መሪዎችን፣ የአካባቢው ነዋሪዎችን እና የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞችን በአንድ የጋራ ዓላማ ስር የሚያሰባስብ ይሆናል። ባለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮ ቴሌኮም አጋርነት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ክልላዊ ተደራሽነቱን እንዲያሰፋ ትልቅ እገዛ አድርጓል።

የዚህ አጋርነት ትልቁ ስኬት ቴክኖሎጂን ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ ጋር የሚያዋህደውና በሀገሪቱ ማዕዘናት ሁሉ ለሚገኙ ተጠቃሚዎች ተደራሽ የሆነው የኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊ የሩጫ እና የጤና መተግበሪያ አገልግሎት ላይ መዋሉ ነው።

ዘንድሮም በቦቆጂ የሚካሔደው ውድድር የኢትዮ ቴሌኮም እና የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን የጋራ ራዕይ ማለትም ኢትዮጵያን በሩጫ እና በቴክኖሎጂ የማገናኘትን ዓላማ የሚያሳይ ነው። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፣ ኢትዮ ቴሌኮም ለተከታታይ ዓመታት የውድድሩ የስያሜ አጋር በመሆን ላሳየው ዘላቂ ታማኝነት ያለውን ጥልቅ ምስጋና ያቀርባል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ “ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ያለን አጋርነት እጅግ የላቀ ዋጋ ያለው እና የምንኮራበት ነው። የእነሱ ታማኝ ድጋፍ ጥራታቸውን የጠበቁ ውድድሮችን እንድናዘጋጅ እና ውብ በሆነችውና ኢትዮጵያ እየተዘዋወርን አምስት ክልሎች ውስጥ ውድድሮችን እንድናከናውን በእጅጉ ረድቶናል” በማለት ሁለቱ ተቋማት እያበረከቱ ስላሉት አስተዋጽኦ ገልጸዋል።

ይህ ታማኝ አጋርነት ኢትዮ ቴሌኮም ከቦቆጂ ውድድርም ባሻገር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሚያካሒደው የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ውድድሮች ስር ካሉት ስድስት መዳረሻ ከተሞች ውስጥ አምስቱ (ደብረብረሃን፣ ሐዋሳ፣ ጅማ፣ ቦቆጂ፣ እና ሐረር) ላይ የስያሜ አጋር በመሆን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ እና የማህበረሰብ ልማት እውነተኛ ባለውለታ መሆኑን ያረጋገጠበት ነው።
❤14
 የአትሌቶች መፍለቂያዋ ቦቆጂ ነገ ጠዋት ታላቁ ሩጫን ታስተናግዳለች

በርካታ የዓለምና የኦሊምፒክ ሻምፕዮን አትሌቶችን በማፍራት የምትታወቀው የቦቆጂ ከተማ ፣ 5ተኛውን ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁሩጫ በቦቆጂ ውድድር በደመቀ ሁኔታ ለማስተናገድ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።

ዘንድሮ በዋናነት የ12ኪ.ሜ. ርቀት የሚሸፍነው የሩጫ ውድድር ከ100 በላይ ፕሮፌሽናል ተወዳዳሪ አትሌቶችን፣ ከአዲስ አበባ የሚጓዙ ከ70 በላይ ተሳታፊዎችን እና 2500 የከተማዋ ነዋሪዎችን ያሳትፋል። ውድድሩ የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ 2018 ዓ.ም. የመጀመሪያ መዳረሻ በነበረችው ደብረ ብርሃን ከተማ አሸናፊ የሆኑ አትሌቶችንም ያሳትፋል።

እንደ ደራርቱ ቱሉ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ጥሩነሽ ዲባባ እና ላሜቻ ግርማያሉ የዓለም የአትሌቲክስ ከዋክብቶች በተወዳደሩበት የቦቆጂ ስታድየም ውስጥ መነሻ እና መድረሻውን የሚያደርገው ይህ ውድድር በበርካታ ተመልካቾች ድጋፍ የሚታጀብም ነው። በቦቆጂ ስታድየም በተለያየ የዕድሜ ክልል የሚገኙ 2,500 አዋቂዎች እና 500 ህጻናት ይሳተፋሉ።

በተጨማሪም ተተኪዎችን ለማፍራት ያለመውና ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ታዳጊዎችን የሚያሳትፉ የ11ዓመት በታች እና የ15ዓመት በታች ውድድሮች ይካሔዳሉ። በዕለቱ አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶች እንደየደረጃቸው የሚበረከት በጠቅላላ ከ150 ሺህ ብር በላይ የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል።

በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የቱሪዝም ዘርፍ ተወካዮች ቦቆጂ ከተማ ይገኛሉ።

ከእነዚህም መካከል የቱሪዝም ሚኒስቴር ኃላፊዎች፣ የአርሲ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሒም ከድር እና የበቆጂ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ብርሃኔ ነገሰ ይገኙበታል። በተጨማሪም ከ70 በላይ ተሳታፊዎች ከአዲስ አበባ ከተማ ተጉዘው በሩጫው ላይ የሚሳተፉ ሲሆን፣ በርካታ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች እና ታዋቂ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ቦቆጂ ከተማ ይገኛሉ።

ውድድሩ በየአመቱ ስኬታማ ይሆን ዘንድ ኢትዮ ቴሌኮም ላለፉትአምስት ተከታታይ ዓመታት በስያሜ አጋርነት ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር እየሰራ ይገኛል። በተጨማሪም ቴሌብር፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ዳሽን ባንክ፣ ፔፕሲ፣ ፋብ ሳሙና፣ ቶፕ ውኃእና አፍራን ሆስፒታል የውድድሩ አጋሮች ናቸው።
አትሌት ማሞ ሐጫሉ እና ማህሌት ካሳሁን የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በቦቆጂ ሩጫን አሸነፉ

ለአምስተኛ ጊዜ በተደረገውና 12ኪ.ሜ. በሸፈነው የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ የቦቆጂ ሩጫ የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን አትሌት የሆነው ማሞ ሐጫሉ ውድድሩን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ አማን ቃዲ እና አልዬ ቃሲም ተከታትለው የ2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።

በሴቶች አሸናፊ የሆነችው የአሰላ አትሌቲክስ ክለብ አትሌቷ ማህሌት ካሳሁን ስትሆን፤ ኪያ ፍስሃ ከአሰላ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ሁለተኛ፣ ድርቤ ኢርኮ ሶስተኛ በመሆን አሸናፊዎች ሆነዋል።

የዘንድሮው ውድድር የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ መኪዩ ሙሐመድ ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር)፣ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሮዛ ቢያ እና የቦቆጂ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ብርሃኔ ነገሰ‘ን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ኃላፊዎች እንዲሁም የቦቆጂ ከተማ ነዋሪዎች የተገኙበት ነበር።

የ'ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ’ ተከታታይ ውድድር አራተኛ መዳረሻ የሆነችውና አትሌቶችን በመፍጠር በምትታወቀው ቦቆጂ፤ ዛሬ መነሻና መድረሻውን በቦቆጂ ስታድየም በማድረግ የ15ዓመት በታች የታዳጊዎች ሻምፕዮና ሲካሔድ አባይ ከተማ በሴቶች እንዲሁም ካሊድ ሱልጣን በወንዶች አሸናፊ በመሆን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በአርሲ አባቶች እና በኢትዮዽያ ብሔራዊ ህዝብ መዝሙር የተጀመረው የዛሬው ውድድር ከአትሌቶች ጠንካራ ፉክክር 2500 የቦቆጂ እና አካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም ከ70 በላይ ሯጮች ከአዲስ አበባ ተጉዘው ተሳትፈውበታል። በተጨማሪም የ11 ዓመት በታች እና የህጻናት ውድድሮችም የዝግጅቱ ተጨማሪ ውበት ነበሩ።

የ'ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ’ የስድስት ተከታታይ ከተሞች ውድድር በቀጣይ መዳረሻው አርባምንጭ ከተማ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ፤ እንዲሁም ሐምሌ 12 በታሪካዊቷ ሐረር ከተማ ላይ ማጠቃለያውን ያደርጋል።
❤7
🤩ሰኔ 21 በአረንጓዴዋ አርባ ምንጭ 10ኪ.ሜ. ሮጠን፣ ሰኔ 27 እንጦጦ ፓርክ ላይ 5ኪ.ሜ. ዱብ ዱብ እንልና፣ ሐምሌ 12 ሐረር ላይ የልወቅሽ ኢትዮጵያ ጉዟችንን እናጠናቅቃለን።🤩

💫ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ💫

✨ይጎብኙ፣ ይሩጡ፣ ሀገርዎን ይወቁ ✨

#GreatEthiopianRun #DiscoverEthiopiaClassics #Arbaminch #EntotoParkCBERun #Harar
❤10