#የዛሬ_መጋቢት10_ሁኔታ_ምን_ይመሥላል ? (በአጭሩ)
#እጅግ_በጣም_አሳሳቢ
- 624 ከፍተኛ ክትትል እና ፅኑ ሕክምና የሚፈልጉ ወገኖች - -
- 24% ሀገራቀፍ በበሽታ የመያዝ ምጣኔ
- 16 ሕይወታቸው ያጡ ዜጎች--
በዛሬው ቀን ከተመረመሩት ዉስጥ 6 ክልሎች ከፍተኛ(ከ20% በላይ) የበሽታ ስርጭት ታይቶባቸዋል::
1. ሲዳማ-48%
3. ድሬዳዋ-22%
3. አዲስ አበባ-25%
4. ኦሮሚያ- 25%
5. ደቡብ- 21%
6. አማራ- 24%
በፀና የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር እጅግ ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች ከፍተኛ የሆነ #የኦክስጅን እጥረት አጋጥሟል።
በፍጥነት የመከላከያ መንገዶች ትግበራ ወደ አስገዳጅነት እንዲገባ ካላደረግን እና ሁላችንም በሚገባ ካልተጠነቀቅን የከፋ ጊዜ ሊመጣ እንደሚችል ከእነዚህ ቁጥሮች በላይ ምስክር የለም::
ሁላችንም የበሽታውን ስርጭት በመግታት የራሳችን እና የምንወዳቸው ቤተሰቦቻችን ሕይወት እናድን::
ምንጭ: ያዕቆብ ሰማን -በጤና ሚኒስቴር የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር)
ፎቶ -አማኑኤል ስለሺ

Happy World Oral Health Day!
#WorldOralHealthDay aims to empower people with the knowledge, tools and confidence to secure good oral health. Take charge of your oral health today!!
Thank you to all SPHMMC‘s amazing dentists, dental surgeons, Maxillofacial Surgeons, nurses and dental teams!

ዛሬ የዓለም የአፍ ጤና ቀን ነው፡፡
የአፍ ጤና መንከባከብ ጠቅላላ ጤናን መጠበቅ ነው፡፡
የአፍን ጤና የሚጎዱ ነገሮችን ሁሉ በማስወገድ ጥሩ የአፍ ንፅህናን አጠባበቅ ልማድ ማዳበር የስፈልጋል፡፡
የአፍዎን ጤና ሲጠብቁ ሌሎች የሰውነትዎን ክፍል ጤና ይጠበቃል፡፡
የአፍ ጤንነትን ባለመጠበቅ ብቻ ለጎሮሮና ለአንጀት ካንሰር እንዲሁም ለጥርስ ህመም እና መበላሸት ብሎም ለሌሎች ችግሮች ያጋልጣል፡፡
t.me/spmmc

የዓለም ቲቢ ቀን በየዓመቱ መጋቢት 15 ቀን “ March 24” ይከበራል፡፡ በዓሉ ዘንድሮ በዓለም ለ39ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ24ኛ ጊዜ ለ15 ጊዜ ከሚካሄደው ብሔራዊ የቲቢ ምርመር ጉባኤ ጋር ተቀናጅቶ ይከበራል፡፡ የዓለም ቲቢ ቀን በየዓመቱ የሚከበርበት ዋና ምክንያት በሽታው ዛሬም በሰው ዘር ላይ ከፍተኛ ሕመምና ሞት እያስከተለ መሆኑን ለማስገንዘብና የቲቢ በሽታን ለመቆጣጠር የሚከናወኑትን ሁሉን አቀፍ ተግባራት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በተጠናከረ መልክ እንዲቀጥል ለማስቻል ነው፡፡
ዕለቱ መጋቢት 15 ቀን እንዲሆን የተመረጠውም የዛሬ 139 ዓመት “March 24, 1882” ታዋቂው ጀርመናዊ ተመራማሪ ዶ/ር ሮበርት ኮች፣ “ማይኮባክቴሪያም ቲዩበርክሎስስ” ተብሎ የሚታወቀውን የቲቢ በሽታ መንስኤ ማግኘቱን ለዓለም ያበሰረበትን ቀን ለማስታወስ ሲባል ነው፡፡ ይህንኑ ቀን ታሳቢ በማድረግ በበሽታው ቁጥጥር ላይ ትኩረት የሚሰጡ መልዕክቶች እንደመሪ ቃል ተወስደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች የሚከናወኑ ሲሆን ዘንድሮም የዓለም ቲቢ ቀን ከዓመታዊ የቲቢ ምርምር ጉባኤ ጋር በመቀናጀት “የቲቢ በሽታን ለመግታት ጊዜው አሁን ነው!” በሚል ተመሳሳይ መሪ ቃል ይካሄዳሉ::

Where Are Our Alumni Now?
Dr Hellina is a visionary young physician working to impact the healthcare system in Ethiopia. She graduated from SPHMMC by October 2017 and she has been working as a lecturer and project coordinator at Innovative Strategies and Operations - International Communications and Partnerships office. She is currently a Chevening scholar at the prestigious London School of Hygiene and Tropical Medicine. Working at ISO/ICP, Hellina has embarked on an innovative path that led her to work on a variety of national projects that affect the lives of many marginalized communities. Through ISO, she started the first bio accelerator program in the continent which entails the promotion of Ethiopian startups startup prototype level to market entry by providing seed investment, technical and business development support as well as angel investments and later rounds of financing. In continuing with creating innovative solutions to Ethiopia's healthcare demands, Hellina also led the breast milk bank project in collaboration with Oslo University Hospital. As malnutrition is one of the top causes of death for children under five years of age, this project aims to reduce mortality by creating a supply of breast milk to distribute to mothers who are unable to produce their own. In addition to leading such type of mega projects, Hellina also founded the St. Paul's Alumni Association with her colleagues and created a platform for collaboration, innovation and mentoring. They are planning much bigger programs within the near future. Through this variety of medical and non-medical experiences she garnered from St. Paul's, Hellina has developed and continues to develop her leadership, communication, innovative thinking, design thinking, strategic management and project management skills.

በቲቢ ምን ተሰራ ? ምንስ ይቀረናል?
በኢትዮጵያ የቲቢ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ሥራ ከተጀመረ ስድስት አሥርት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በዋናነትም የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የምትጠቀምባቸው የዓለም ጤና ድርጅት ለአባል አገራት የሚያቀርባቸውን ሥልቶችን ነው፡፡ እስከ አሁን ከተጠቀመችባቸው የሚጠቀሱት እ. አ. አ. ከ1993 - 2006 ዓ/ም - (DOTS Strategy)፣ እ. አ. አ. ከ2006 - 20014 ዓ/ም - (STOP TB Strategy) እንዲሁም እ. አ. አ. ከ2015 - 2020 ዓ/ም በሥራ ላይ የዋለው (END TB Strategy) ተብለው የሚታወቁ ናቸው፡፡ በእነዚህ ሥልቶች በመታገዝና የዘላቂ ልማት ዕቅድ አካል በሆነው በአገሪቱ የጤናው ዘርፍ ዕቅዶች በመመራት አገራዊ የቲቢ በሽታ መከላከልና ቁጥጥር ሥልታዊ ዕቅዶችን አዘጋጅታ በተሳካ ሁኔታ ተግብራለች፡፡ በአሁኑ ወቅት በሥልታዊ ዕቅዶች በመታገዝ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ማዳረስ በመቻሉ ብዙ ሰዎች የቲቢ በሽታ ምርመራና ሕክምና አገልግሎቶችን አግኝተዋል የበርካታ ዜጎችንም ሕይወት መታደግ ተችሏል፡፡ ለእዚህም በአብነት ሊጠቀሱ የሚችሉት በየዓመቱ አዲስ በቲቢ በሽታ የሚያዙ ሕሙማን ምጣኔ እ. አ. አ. በ2013 ዓ/ም መጨረሻ ከነበረው 247 ከ100,000 እ. አ. አ. በ2020 ዓ/ም ወደ 140 ከ100,000 መውረድ እና በቲቢ የሚከሰተውን የሞት ምጣኔ እ. አ. አ. በ2013 ዓ/ም መጨረሻ ከነበረው 35 ከ100,000 እ. አ. አ. በ2020 ዓ/ም ወደ 22 ዝቅ ማለት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ይሁንና ውጤቶቹ የሚያበረታቱ ናቸው ቢባልም በበሽታው ዙሪያ ቀጥሎ የተጠቀሱና ልዩ ትኩረት የሚሹ ችግሮች አሉ፡፡
• የቲቢ በሽታ ይገኝባቸዋል ተብለው ከሚታሰቡ ሰዎች 30 ከመቶ የማያነሱ ወደ ሕክምና አለመምጣታቸው፣
• የቲቢ መድኃኒቶችን የተላመዱ ተህዋሲያን መፈጠርና መዛመት፤
• የኤች. አይ. ቪ. ወረርሽኝ ተጽዕኖ፤
• በቲቢ በሽታ መከለከልና ቁጥጥር ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ አጋር ድርጅቶች አናሳ መሆን እንዲሁም
• የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በቲቢ በሽታ መከላከልና ቁጥጥር ላይ እያስከተለ ያለው አሉታዊ ተጽዕኖ ወዘተ ናቸው፡፡
ስለሆነም የተጠቀሱትንና ሌሎች የተለዩ ችግሮችን መቅረፍ ያስችላል የተባለለትንና እ. አ. አ. ከ2021 ዓ/ም ጀምሮ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ የቲቢ እና ሥጋደዌ በሽዎች ሥልታዊ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ተግብቷል፡፡ ሥልታዊ ዕቅዱም የአገሪቱ ጤናው ዘርፍ ትራንሰፎርሜሽን ዕቅድ የታገዘ ሲሆን ግቦቹም፡
• በየዓመቱ አዲስ በቲቢ በሽታ የሚያዙ ሕሙማን ምጣኔ እ. አ. አ. በ2020 ዓ/ም ከነበረው 140 ከ100,000 እ. አ. አ. በ2026 ዓ/ም ወደ 91 ከ100,000 ማውረድ፣
• በቲቢ የሚከሰተውን የሞት ምጣኔ እ. አ. አ. በ2020 ዓ/ም ከነበረው 22 ከ100,000 እ. አ. አ. በ2026 ዓ/ም ወደ 07 ከ100,000 ማውረድ እና
• ቤተሰቦች ቲቢ ሕሙማንን ለማሳከም ከተጠቃሚው ኪስ የሚወጣን ወጪ ከ25 ከመቶ በታች ማውረድ ተብለው የተለዩ ናቸው፡፡
የጤና ሚኒስቴር ግቦች ማሳካት የተለመደውን የልሎችንና ከተማ አስተዳሮችን ቅንጅታዊ ሥራ፣ ያልተቋረጠ የአጋሮች ድጋፍ እንዲሁም የሕብረተሰቡን ተሳትፎ ማዕከል ያደረጉ ቀጥሎ የተጠቀሱትን ሥልታዊ ዓላማዎች እንደነደፈ በሥልታዊ ዕቅድ ሠነዱ ላይ ተመልክቷል፡፡
• የቲቢ ታማሚዎች ወደ ሕክምና እንዳይመጡ በሚያግዱ እንቅፋት ላይ ማተኮር፣
• የቲቢ በሽታ እንዳይዛመት መከላከልና በበሽታው የተያዙትን ማከም፣
• ሕዝብን ያማከሉ፣ ፍትሃዊ የሆኑና ደረጃቸው የተጠበቀ አገልግሎቶችን መስጠት፣
• ሕዝብን ታሳቢ ያደረጉ ፖሊሲዎች እንዲተገበሩ ማበረታታትና ድጋፈዊ ሥርዓቶችን ማጠናከር፣
• ወቅታዊና ጥራቱ የተጠበቀ መረጃ አሰባሰብና አጠቃቀም ሥርዓትን ማጎልበት፡፡