St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
Washing your hands regularly with soap and water or an alcohol-based hand rub can reduce your risk of COVID19 infection by 3️⃣6️⃣%.
ኢትዮጵያ እና እስራኤል የኮቪድ- 19 ክትባትን በጋራ ሊያመርቱ መሆኑ ተገለጸ
********************

ኢትዮጵያ እና እስራኤል የኮቪድ- 19 ክትባትን በጋራ በኢትዮጵያ ሊያመርቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ፣ ምክትል አምባሳደር ኦር ዳንኤሊ እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በጤናው ዘርፍ አብሮ ለመስራት ላይ በማተኮር ውይይት አድርገዋል።

ኢትዮጵያ እና እስራኤል በኢትዮጵያ የኮቪድ- 19 ክትባት በጋራ ለማምረት በሚቻልበት ሁኔታ፣ የአቅም ግንባታ፣ የጤና ዘርፍ ኢንቨስትመንት እና በሁለቱ አገራት ጤና ሚኒስቴር መካከል ትብብር ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት አድርገዋል።
EBC
ምግብ አልበላም ብለው ለሚያስቸግሩ ህፃናት በምን መልኩ የምግብ ፍላጎታ ቸውን ማስተካከል እንደሚቻል እና እንዴት አድርገን መመገብ እነሆ የምንችልባቸው 20 ዘዴዎች:-

1. አዲስ ምግብ ለማስለመድ ሲያስቡ 20 ጊዜ ይሞክሩ ።

ልጅዎ አዲስ ምግብ ለመጀመር አስቸግሮት ሊሆን ይችላል:: እየቀመሰ ይተፋውም ይሆናል ። ሆኖም በትግስት በየቀኑ ቢያንስ ለ20 ቀን ይሞክሩ::
እንዲህ ዓይነቱ ሙከራ ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በመጨረሻ ላይ ዉጤታማ ሆኖ ታይቷል ::

2. ልጆች አንድን ምግብ እምቢ ሲላሉ ቶሎ ሌላ ተለዋጭ ምግብ ለመስራት እና ለማቅረብ አይቸኩሉ። ደጋግመው ያቅርቡላቸው።ልጅዎ እንደ ምግብ ቤት ምግብ እንዲያዝ እና እንዲቀያይር አይፍቀዱለት።

3. ልጆች ምግብ አልበላም ሲሉ በምትኩ ወተት ወይም ጁስ አይስጡት።

ከዛ ይልቅ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ራሱን ምግብ ያቅርቡለት። አሁንም እምቢ የሚል ከሆነ ምግቡን ያንሱት። ይሄንን በተደጋጋሚ ካደረጉ ልጆ እምቢ ስላለ ብቻ የሚቀየር ነገር እንደሌለ ቀስ በ ቀስ ይረዳል

4. ቋሚ የምግብ ሰዓትን ያስለምዱ ።
ይህን ሲያረጉ የምግብ ሰአትን እና ስርዓትን ለልጅዎ ያስተምሩታል::

5. ጣፋጭ ነገሮችን ከልጅዎ የምግብ አይነት ዉስጥ ይቀንሱ:: ጣፋጭ ነገር ካስፈለጋ ቸው በሚመገቡበት ጊዜ ወይም መጨረሻ ላይ ጣፋጭ ፍራፍሬዎችን ይመግቧቸው፡፡

6. ትኩረትን የሚወስዱ ነገሮችን ያስወግዱ።
ለምሳሌ: መጫወቻዎች ፣ የቤት እንስሳት ፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ወይም ቴሌቪዥን ያሉ ነገሮች የሕፃን ልጅዎን ትኩረት ከምግቡ በላይ ሊወስዱ እና በዚህም የተነሳ በትንሹ በልተው እንዲያበቁ ያረጋቸዋል ።
ስለዚህ ልጅዎ ከምግብ ጋር ጤናማ ግንኙነት እንዲኖረው ሲመግቡት ሙሉ ትኩረቱ ምግብ ላይ እንደሆነ ያረጋግጡ ፡፡

7. አይን የሚይዙ ምግቦችን ማዘጋጀት

ሳያዩት ያላማረ... " አይደል የሚባለው?
ልክ እንደ አዋቂዎች ሁሉ ሕፃናትም በዓይናቸው ይመገባሉ። የሚያዩት ነገር በጣም ይስባቸዋል::

ለህፃናት ምግባቸውን ሲያቀርቡ በቀለማት ያማረ የሚስብ እና አስደሳች ሆኖ እንዲታይ ማድረግ ይኖርብዎታል ፡፡ ፈጠራ የታከለበት የኮከብ የአበባ የ አሻንጉሊት ቅርፅ ያላቸውን ፍራፍሬዎች አትክልቶችን ወይም ፓንኬኮች ይስሩ።


8 .ልጅዎን ምግብ ለምን አትበላም/አትበይም ብለው አያስጨንቋቸው ።

በምግብ ሰአት አንዳንዴ ለብቻቸው እንዲሆኑ እና ነፃነትን እንዲለማመዱ ያድርጉ ።ሕፃናት አንዳንድ ጊዜ በምግብ ሰአት ብቻቸውን ሲተዉ የተሻለ ነው ፡፡

በምግብ ሰአታቸው ላይ የእራት ጠረጴዛቸውን ከጎንዎ ያዘጋጁ እና ትንሽ ማንኪያ እና ሳህን ይስጧቸው። ከዛም በቅርብ ርቀት ሆነው ይከታተሏቸው::

9. ለልጅዎ የምግብ ሽልማት ያዘጋጁ።

ልጆችን በሚወዷቸው እና ጤናማ በሆኑ ምግቦች ሽልማት ያዘጋጁላቸው። ይሸልሟቸው :: ለምሳሌ አፕል እንጆሪ ሙዝ እና የመሳሰሉትን ፍራፍሬ የሚወዱ ከሆነ ምግባቸውን ከጨረሱ እንደሚሰጣቸው መንገር እና ማጓጓት።

ከዚያም ምግባቸውን እንደጨረሱ በሽልማት መልክ መስጠት ፡፡ ሆኖም እነዝህ ሺልማት ያልናቸው ምግቦች ጤናማ እና ለአካላዊ እድገታቸው አስፈለጊ መሆን አለባቸው ።

ጣፋጭ ከረሜላ ኬክ አይስ ክሬም ፒዛ በርገር እና የመሳሰሉት ግን ጤናማ ያላልሆኑ ምግቦችን እንደ ማታለያ በጭራሽ መጠቀም የለብንም ።

10. ለልጆዎ በምግቡ የተለያየ ጨዋታ ያጫውቱት

ልጅዎ እራሱ የሚመግበው አዲስ መጫወቻ ነው ብሎ እንዲያስብ ለማድረግ በቀለማት ያሸበረቁና የተለያዩ ዕቃዎችን ይጠቀሙ !!

በተጨማሪ የፈጠራ ብቃቶን በመጠቀም በተለያዩ ፍራፍሬዎች የተለያዩ ቅርፅ ያላቸዉን አሻንጉት የሚመስሉ ነገሮችን መስራት እና በዛ እያጫወቱ ቀስ ብለው ማብላት::

11. በተቻለ መጠን የምግብ አይነቶችን ይቀያይሩ።

ህፃናት ሁሌም አዲስ ነገር ያስደስታቸዋል
አንድ የአይነት ምግብ አይደጋግሙ ፡፡ ለልጅዎ አዲስ ምግብ ከተለያዩ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች ጋር መስጠቱን ይቀጥሉ። አማራጮችን ካላገኙ በስተቀር ህፃናት መብላት የሚፈልጉትን መወሰን አይቺሉም::

12.ልጅዎን በራበው ሰአት የማይወደውን ምግብ ያቅርቡለት።

13. አብረዋቸው ይመገቡ ።

❤️ ህፃናት ወላጆች የሚያደርጉትን ማንኛዉንም ነገር ደግሞ ማድረግ ይወዳሉ ።ተፈጥሯ ቸውም ነው:: ስለዚህ ልጆዎ እንዲበላ የሚፈልጉትን ነገር እርሶም እየበሉ ያሳዩዋቸው።
👉 ለምሳሌ: ልጆዎ ሙዝ አልበላም ቢል አንድ ሙዝ ያንሱ እና አቤት ሲጣፍጥ እያሉ እየበሉ ግማሹን ለልጆ እንዲቀምሰው መስጠት

14. ማበረታታት እና ማድነቅ

ሕፃናት በባህሪያቸው መንቆለጳጰስ ይወዳሉ። ስለዚህ ጥሩ ነገር ሲያረጉ በደንብ ማበረታታት እና ማድነቅ ያንን ነገር በተደጋጋሚ እንዲያረጉ ይገፋፋቸዋል ፡፡

ልጅዎ አዲስ ምግብ ከሞከረ ሞቅ ያለ ፣ ሰፊ ፈገግታ እና አንዳንድ የማበረታቻ ቃላትን ይስጡት። ይህ ልጅዎ አዳዲስ ምግቦችን ከእርስዎ ደስተኛ ቃላት ጋር እንዲዛመድ ያደርገዋል። ስለሆነም እነሱን ለመመገብ ቀላል ያደርግልዎታል።

15. ልጆቾዎ ምግብ ሲሰራ በአቅማቸው እንዲያግዙ እና እንዲሰሩ ማድረግ ይሄም የምግቡን ሽታ እንዲለምዱ እና ለመብላት እንዲጓጉ ያረጋቸዋል🫕

16. ወደ ገበያ ሲወጡ ልጆችዎ የተለያዩ አትክልቶችን እና ፍራፍሬዎችን እንዲያዩ እንዲመርጡ ማድረግ እና የወደዱትን አይነት ገዝቶ መግባት በመቀጠል አብሮ አዘጋጅቶ አብሮ መብላት ::

17. ፈሳሽ ምግብችን አያብዙ!

በተለይ ከምግብ ሰዓት ጥቂት ሰዓታት በፊት ለህፃን ልጅዎ እንደ ወተት ፣ ጭማቂ ያሉ ማንኛውንም ፈሳሾች መስጠቱ አይመከርም ፡፡ እነዚህ ፈሳሾች ልጆችን ሆድ በቀላሉ በመሙላት የምግብ ፍላጎታ ቸውን ሊቀንሱ ይችላሉ ፡፡

18. ልጆዎን ቀስ ብለው በትዕግስት ይመግቡት!

እንደ ወላጅ ልጅዎን ለመመገብ ሲያስቡ ሁሌም ለልጆዎ ባህሪ አመቺ የሆነውን ፍጥነት ማወቅ ይኖርብዎታል ፡፡

አንዳንድ ሕፃናት በፍጥነት ይመገባሉ ።አንዳንዶች ግን በሁለት ማንኪያዎች መካከል ጥቂት ደቂቃዎችን መጠበቅ ይፈልጋሉ ፡፡
19. በምግብ ሰዓት ሁሉንም የቤተሰብ አባል በማእድ ላይ እንዲቀርብ አድርጎ መልካም መልካም ነገሮችን በማውራት የምግብ ሰአትን አስደሳች እና ተናፋቂ ማድረግ ።

20. ምግብ አልበላም ስላሉ ልጆችን ማስጨነቅ ተገቢ አይደለም ።

ምግብ አልበላም ያለን ልጅ በኃይል መቆጣት ወይም መምታት ልጁ ወደ ፊት ምግብ እና ቅጣትን በ አይምሮ አብሮ ስለሚቀርፃቸው ከባድ የ ሆነ የ አይምሮ ጠባሳ ሊያኖርበት ይችላል።በዚህም ምክንያት ምግብ ሊጠላ ይችላል::

ዶክተር ፋሲል መንበረ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
የህፃናት ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር
በኢትዮጵያ ሐኪሞች ሳምንት የሐኪሞቻችንን ከራስ በላይ ያለፈ ተግባር የምንዘክርበት ነው፡፡ ሐኪሞቻችንን እናመሰግናለን የምንልበት ወቅት ነው፡፡በዚህ ዙሪያ የአርትስ ቲቪ ጋዜጠኛው መላኩ ብርሀኑ ለ “እናመሰግናለን” ቃላት አቅም ያጡብኛል በማለት የጻፈውን አንብቡለት፡፡ መልካም የሐኪሞች ሳምንት!
ለ “እናመሰግናለን” ቃላት አቅም ያጡብኛል!
በምንችለው ነገር የሚመጣን ሁሉ ለመቋቋም ዝግጁነትም ጉልበትም ሊኖረን ይችላል። በማንችለው ነገር የሚመጣብን ግን ሁሌም ቢሆን እኛን የሚያሸንፍበት ቀዳዳ ይሰፋለታል። እውነቱን ለመናገር ኢትዮጵያውያን ላይ የኮቪድ ወረርሽኝ የመጣብን ልንለውጠው በማንችለው ስስ ጎናችን በኩል ነው። ሰፊና ቶሎ ሊጠብብ የማይችል ስስ ስስ ጎናችን አብሮነት እና ማህበራዊ ህይወታችን ነው።
ኢትዮጵያውያን ህይወታችን በማህበር የሚመራ ዜጎች ነን። ብቻችንን ህይወት መምራት ብንሞክረው የሚከብደን ብቻ ሳይሆን ብንጀምረው እንኳን በምንኖርበት ማህብረሰብ ዘንድ የሚያነውረን ነው። እያንዳንዳችን ከውልደት እስከሞት ያለ ጉዟችን የማህበረሰቡ እጅ ያለበት ነው።ወደዚህች አለም ለመምጣት ከእናታችን ማህጸን ጋር ግብግብ ስንገጥም የጎረቤትና የአካባቢ ሰዎች በ “ማርያም ማርያም” ልመና እና በደማቅ እልልታ ይቀበሉናል። በ”ያሳድግህ፣ ያሳድግሽ” ምርቃት “ቱፍ ቱፍ” ተብሎብን በማህበረሰቡ ፊት እናድጋለን። በጎረቤት እና አካባቢ ሰው “ጎሽ ጎሽ” ማበረታታት እና በ “ተው ልጄ” ምክር ባህሪያችንን አጎልብተንና አርቀን ለቁምነገር እንደርሳለን። በዚሁ ባሳደገን ህዝብ ፊት በእልልታ እና በሆታ ፣ በምርቃት እና በአጀብ ተሰርገን ቤተሰብ ለመመስረት እንበቃለን። ዘመን ተራው ደርሶ ይህችን አለም ስንሰናበትም በህዝብ አጀብ፣ ዋይታ እና እዬዬ እንሸኛለን። ከሰልስት እስከአርባ ታስበን፣ ሙት አመታችን ተዘክሮ ነው የህይወታችን ምዕራፍ የሚቋጨው። ኢትዮጵያዊነታችን የዚህ ሁሉ ስብስብ ፣ አንድነት፣ ህይወትን በአብሮነት የመካፈል እና ኑሮን በጋራ የመምራት ውጤት ነው። ብቻችንን ምንም ነን።
ኮቪድ የመጣብን በዚህ ነው። በደስታም በሃዘንም ጊዜ ብቻችንን እንድናሳልፍ፣ የየዕለት ህይወታችን አካል ከሆነው ማህበረሰብ እንድንራራቅ፣ ማህብራዊ ህይወት እንድናቆም ሊያስገድደን ጥርሱን ስሎ የመጣብን በሽታ ነው። ውልደት፣ ክርስትና፣ በዓላት፣ ሰርግ፣ ሞት እኒህ ሁሉ እንደባይተዋር ለብቻ እንዲታለፉ የሚፈልግ ለእኛ ከባድ ፈተና ነው ኮቪድ። እጅግ ከባድ ነው! ከበሽታውም በላይ ለእኛ ጎጂው፣ በጣም ከባዱ እና የማይገፋው አሳር ይኼው ነበር !። በዚህ ላይ ደግሞ ችግራችንን ተካፍለንና ተጋግዘን እንጂ ብቻችንን የማንዘልቅ ፣ የመጣውን መርግ በአቅም መቋቋም የማንችል ድሃ ህዝቦች ነን። ይህም ሌላው በቡሃ ላይ ቆረቆራችን ነው።
ይህንን ዘመን እንዴት እና በምን ሁኔታ እናልፈው ይሆን ? ማንስ ነው ከዚህ በማንችላቸው ጎኖቻችን ሰርጎ ከገባብን መርገምት ለማዳን ከፊት ሆኖ የሚዋጋልን? እንዴትና በማን “አይዞዟችሁ” ባይነትስ ይህንን ፈተና እናልፈው ይሆን? ይህ ነበር የሁላችንም ጭንቀት። እናም ሸክሞቻችንን ለሁለት ከፍለን ፣ ለሁለት አካላት ወርውረን ቁጭ አልን።ለፈጣሪ እና ለህክምና ባለሙያዎቻችን!!
እነሆ ጧት ማታ በጸሎት ፈጣሪን ስንለምን መሬት ላይ ደግሞ አደራ የሰጠናቸው የህክምና ባለሙያዎች ሁላችንንም ለማዳን የገቡትን ቃል ጋሻ አድርገው ተነሱ። እንደራሳቸው ወንድሞች፣ እናቶቻቸው፣ አባቶቻቸው፣ ልጆቻቸው ቆጥረውን ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ጦርነቱን ከፊት ቆመው ተጋፈጡልን። ለብዙ ወራት ተዋጉ። ቤታቸውን ሳያዩ ፣ ልጆቻቸውን ሳይጎበኙ፣ ኑሯቸውን መላ መላ ሳይሉ፣ ደህና ዋሉ ብለው አንዴ እንደወጡ የኛኑ የሞት ስጋት እና ፍርሃት ለመከላከል ውጪ ከረሙ…በቀዝቃዛ ወለል ላይ እየተኙ ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በአይናቸው ሳይዞር ለቆሙለት ዓላማ እስከመጨረሻው ተፋለሙ። እነዚህ የዘመናችን ወቶ አደሮች እኛን ቤታችን አስቀምጠው እነርሱ ውጊያውን ኖሩበት። ብዙዎች በዚህ ክቡር ሙያ ላይ ሆነው ሲታገሉ ራሳቸው አለፉ። ብዙዎች ለማይጠገን ቁስል ተዳረጉ። ብዙዎች የሚወዷቸውን ልጆቻቸውን ሳያዩ ተሰናበቱ። ብዙዎች ህይወታቸው ተናጋ !!
እነሆ ያ አስከፊ፣ አስፈሪ፣ ተስፋ አስቆራጭ፣ብዙዎቻችንን መሸሻ መጠጊያ ያሳጣን ፣ በተለይ በድህነት አቅማችን የማንችለው መሆኑ ያስበረገገን እና በአብሮ መኖራችን ላይ ጥርሱን አግጥጦ የመጣ ኮቪድ በፈጣሪ እርዳታ እና በነዚህ እንቁ ልጆቻችን የህይወት መስዋዕትነት በከባድ ምት ከውጊያ አውዱ አፈገፈገ። የዘመኑ ድንቅ ጀግኖች አሁንም እስከወዲያኛው ስጋታችንን ሊሸኙት የጦር ቀጠናው ላይ ቢሰለፉም ቢያንስ ጥቂት እፎይታ አገኙ። አሁን እንደፈጣሪ ፍቃድ እና እንደነዚህ ባለውለታዎቻች ድካም ሆኖ ያ አስፈሪ ጨለማ ፈገግ ብሏል። እየተጠነቀቅን ማህበራዊ ህይወታችንን ቀጥለናል። ራሳችንን እየጠበቅን እሴቶቻችንን ዳግም አግኝተናቸዋል። የማንችለው ብቸኝነት በብዙ ሞክሮን ተሸንፎ አብሮነታችን ካፈገፈገበት ዳግም ወደቦታው ተመልሷል።
እንኳን ደስ ያለን!! ለዚህ ክብር ላበቁን፣ ሞተው ላኖሩን፣ ቀን ላስቀጠሉን፣ ራሳቸውን ያለስስት ለሰዉልን፣ ከከባድ አደጋ ጋር ተጋፍጠው ይህንን ቀን ላሳዩን ለነዚህ ጀግና የኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች በሙሉ የአክብሮት ምስጋናዬ ይድረሳቸው!! ክብራችን ናቸው!
በቅርብ ውሏቸውን እንደሚከታተል ጋዜጠኛ ፣ በጦርሜዳው ውስጥ ታሪክ የማይረሳው ጀብዱአቸውን ተከታትሎ ሲዘግብ እንደቆየ የሚዲያ ሰው ለነዚህ ምርጥ ኢትዮጵያውያን ምስጋና ለማቅረብ ቃላት አቅም ያጡብኛል ! አንደበት ይሰንፍብኛል!! በአንድ ቃል ብቻ “እናመሰግናለን!” እላቸዋለሁ። ላሉት ቀሪ ውለታቸውን ደግሞ አምላክ በቁም ይክፈላቸው!! በውጊያ ቀጠናው ለእኛ መዳን ሲሉ ለተሰዉ ባለሙያዎች ሁሉ ነፍሳቸውን ይማር! ታሪክ በደማቅ ቀለም ሲዘክራቸው ይኖራል!!
እንደገና የልጆቼ እናት እንድሆን ለረዱኝ ሐኪሞች ምሥጋና ለማቅረብ የሚበቁ ቃላት የሉኝም። ( የሺእመቤት ደመቀ)
----------------------------------------------------------------------
ጊዜው ከሁለት ዓመት በፊት ነው፤ ቦታው በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና ክፍል፤ ተጨንቄያለሁ፣ ነጭ ጋዎን የለበሱ ዘለግ ያለ ቁመና ያላቸው ሀኪም ስሜን ጠሩና ሠላምታ ሰጡኝ፣ ትህትናና ፈገግታቸው ጭንቀቴን ቀለል አደረግልኝ፤ እያወሩኝ ከቆዩ በኋላ "የሺመቤት አሁን ምላስሽን አሳይኝ ስልሽ እንደቅድሙ ታሳይኛለሽ" አሉኝ እሺ አልኩና ትዕዛዛቸውን ለመፈፀም ተዘጋጀሁ።

ወዲያውኑ "የሺመቤት... የሺመቤት" ስሜ ሲጠራ ምላሴን ለዶክተር ላሳይ .... ዓይኔን ገለጥኩ፣ ሕመም ተሰማኝ ቀዶ ሕክምናው ተጠናቋል። ለእኔ ቅፅበት በምትመስለኝ ባላወቅኳት ጊዜ እነ ዶክተር ጤናዬ እንዲመለስ፣ እስትንፋሴ ቀጥሎ እንደገና የልጆቼ እናት እንድሆን ለከፈሉት ዋጋ ምስጋና ለማቅረብ የሚበቁ ቃላት የሉኝም።

ከተሜና ገጠሬውን፣ ሀብታምና ድሀውን፣ ፅዱና አዳፋ ለባሹን፣ ቁስሉን፣ ደሙን፣ ሌላም ሌላውን.... ፊታቸው ቅጭም ሳይል ሳይጠየፉ .... ከማለዳ እስከ ሌሊት ሲታትሩ፤ ወንበር ላይ ተኮራምተው ሲያድሩ ለተመለከትኳቿው፤ እና ደግሞ ይህን የሚመጥን ክፍያ፣ ዋጋ፣ ክብር ላላገኙት፣ ላልተዘመረላቸው የአገሬ ሐኪሞች በሁሉን አይነቱ ወገኔ ስም ከፍ ያለ አክብሮትና ምስጋናዬን ማቅረብ እሻለሁ።

አሁንም ዓለምን እየፈተነ ያለው ኮቪድ-19 በአገራችን ከተከሰተ ጀምሮ ቤቴ፣ ትዳሬ፣ ልጆቼ፣ እናቴ አባቴ ሳይሉ ለወገናቸው ሲሉ ሕይወታቸውን ጭምር እየከፈሉ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ሐኪሞች "እጅግ ከፍ ያለ ምስጋናና ክብር ይገባችኋል "! አይዟችሁ ኢትዮጵያ ውለታችሁን አትረሳም ትከፍላችኋለች።
የሺእመቤት ደመቀ
የዜና ኤዲተር
ፎረንሲክ እና ቶክሲኮሎጂ ትምህርት ክፍል ምን ይሰራል?
1. የአስከሬን ምርመራ አገልግሎት መስጠት፡፡ ዉጤቱ ተተንትኖ በ ሁለት ሳምንት ዉስጥ ለሚመለከተዉ አካል መስጠት፡፡
2. የፆታዊ ትንኮሳ ጉዳቶችን ፖሊስ በጠየቀዉ ጥያቄ መሰረት በመመርመር እና በማብላላት መረጃዉን ለሚመለከተዉ አካል ማሳወቅ፤
3. የእድሜ ምርመራ በማድረግ ዉጤቱን ለህግ አካላት ማድረስ፤
4. የፍትህ አካላት የተቀበሩ አስከሬኖችን የሞታቸዉ መንስዔ ሲጠይቁን የ “ዲኤንኤ” (DNA) ናሙናን ለመሰብሰብ በቦታዉ ሄዶ በመገኘት በመመርመር እና የተገኘዉን ዉጤት ለጠያቂው አካል ማቅረብ፡፡
5. የተፈጥሮ ወይም የሰዉ ሰራሽ የጅምላ ግድያ አደጋዎች በሰዎች ላይ ሲከሰቱ ከቦታዉ ድረስ በመገኘት መመርመር እና የተገኘዉን ዉጤት ለህግ አካላት መስጠት፤
6. በሰዎች ላይ በመኪና አደጋ በሰዉ ወይም በግንባታ ምክንያት የደረሱ ጉዳቶችን የጉዳቱን መጠንና ዓይነት በመለየትና በመመርመር ዉጤቱን ለሚመለከተዉ መስጠት
7. ለመንገድ ጉዞ እንዲመች ወደኛ የመጡ አስከሬኖችን በማድረቅ ወደተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በአየር ወይም በመንገድ ትራንስፖርት እንዲጓዙ የማመቻቸት ስራ መስራት፤
8. በተደረገልን ሕጋዊ ጥሪ መሰረት ወንጀል ወይም ግድያ የተፈፀመበት ቦታ ድረስ በመሄድ ወይም በመገኘት ለሞት መንስዔ ግኝት ይጠቅም ዘንድ የቦታዉን ሁኔታ መመርመር እና መገንዘብ ወይም (crime scene investigation) ማድረግ፤
9. ፍርድ ቤቶች ሙያዊ ማብራሪያ ሲስፈልጋቸው መስጠት
10. በሜዲካል ኢቲክስ እና የህክምና ስህተቶች ጋር የተያያዙ ማንኛዉንም ጉዳዮችንበመለየት ለፍትህ አካላት መረጃ መስጠት፡፡
11. የተመረመሩ የዉጭ ወይም የሃገር ዉስጥ አስከሬኖችንባለቤት እስኪመጣ ድረስ በፍሪጅ
ማቆየት

ምን ታቅዷል?

1. እስከ አሁን በአገሪቱ ደረጃ የለለዉን የፎረንሲክ የስነ-ምረዛ ላብራቶሪ የሚያሰፈልጉ እቃዎችን ባስቸኳይ በማሟላት በቂ የተማረ የሰዉ ኃይል ስላለን አስፈላጊዉን አገልግሎት ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነን፡፡ ዝግጅታችን የአልኮል መመረዝ እና የተለያ የመመረዝ ሁኔታዎችን መለየት ፣ የ “ዲኤንኤ” (DNA) ምርመራ ማድረግ እና መሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡
2. የፎርንሲክ አገልግሎት ላይ ዉስን ቦታዎች ላይ ብቻ አገልግሎቱ ስለሚሰጥ አገልግሎቱን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች እንዲጀመር እና እንዲስፋፋ ማገዝ
3. የ “Fitness certificate” ወይም የተለያዩ የ አካል ብቃት ማረጋገጫ እና ሌሎችን አገልግሎቶች ለመጀመርም በዝግጂት ላይ እንገኛለን፡፡
የረጅም ጊዜ እቅዳችን ደግሞ በዋናነት እና በግንባር ቀደምነት የስራ ክፍላችን ራሱን የቻለ ተቋም ማለትም በሃገራችን ብሎም በምስራቅ አፍሪካ ግንባር ቀደም የፎረንሲክ እና ስነ-ምረዛ ትልቅ ሃገራዊ ኢንሰቲቱት ወይም ተቋም እንዲሆን ማድረግ ነዉ፡
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
የፎረንሲክ እና ሥነ-ምረዛ ትምህርት ክፍል
ለተጨማሪ ማብራረሪያ
ስልክ-0935665292
“A hero is somebody who is selfless, who is generous in spirit, who just tries to give back as much as possible and help people. A hero to me is someone who saves people and who really deeply cares.” This is a quote taken from Deborah A. Mazaar, a renowned Hollywood actress who impersonates “HEROES” in her films. I believe this quote narrates the life of true heroes, physicians who are selflessly serving their patients in this pandemic. It is indeed the real description of “HEROES” who chose to prioritize their patients’ needs over their own wellbeing, family and mental health. It is indeed “Service above Self “ to set aside one’s comfort, physical pain and fatigue to help and deeply care for others. This is a witnessed truth of our colleagues who fought COVID 19 with their full might and dedications. They will indeed be commemorated as “HEROES” who sacrificed themselves to the greater good of saving patients’ lives.

Rahel A.Kebede(MD,PCCM)

Secretary of Ethiopian Thoracic Society

#ServiceAboveSelf
#EthiopianlDoctorsWeek
#SPHMMCDoctorsWeek
የዓለም የጤና ድርጅት አፍሪካ በሦስተኛ ዙር ከባድ የሆነ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት ላይ እንደምትገኝ አስታወቀ፡፡ ለዚህም በዋናነት በአህጉሪቱ አዳዲስ እና ፈጣን የቫይረሱ ዝርያዎች መስፋፋታቸውን በምክንያትነት አንስቷል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት አራት አሳሳቢ የሆኑ የኮቪድ-19 የቫይረስ አይነት ለይቷል፡፡ እነሱም አልፋ ፣ ቤታ ፣ ጋማ እና በጣም ተላላፊና ተለዋዋጭ ባህሪ ያለው ዴልታ ናቸው፡፡
የዴልታ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተገኘው ከአልፋ ቫይረስ አይነት ከ 40 እስከ 60 በመቶ የበለጠ ተላላፊ መሆኑን ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

ዴልታ ቫርያንት ኦፍ ሳርስ ኮቨ-2 የተሰኘው የኮቪድ-19 ቫይረስ ስርጭት ከ100 በሚበልጡ ሀገሮች መገኘቱ የዓለም የጤና ድርጅት አሳውቁዋል፡፡

ክትባቱን እየተሰጠ ቢሆንም የኮቪደ-19 ክልከላዎችን ማንሳት እና መከላከያ መንገዶችን በአግባቡ አለመተግበር ለከፋ የወረርሽኝ ማዕበል ሊያጋልጥ እደሚችል አሳስቧል ፡፡

ምንጭ: EPHI
የህጻናት የደም ማነስ (Anemia) ምንድነው?

የደም ማነስ ማለት ምን ማለት ነው?

የደም ማነስ ማለት በሰውነታችን ዉስጥ ያለው የቀይ የደም ህዋስ መጠን ወይም ቁጥር መቀንስ ማለት ነው::
የደም ማነስ የሚለካውም የሄሞግሎቢን/ሄማቶክሪት በሚባል የደም ምርመራ ልኬት ነው፡፡ አንድ ሰዉ ሄሞግሎቢን/ሄማቶክሪት በላብራቶሪ ተለክቶ በእድሜ እና በፆታው ከሚጠበቀው ቁጥር የቀነሰ ሆኖ ከተገኘ የደም ማነስ አለበት ማለት ይቻላል፡፡

የህጻናት ደም ማነስ መንስኤዎቹ ምንድናቸው?

የህጻናት ደም ማነስ ዋና ዋና መንስኤዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. አጠቃላይ የምግብ እጥረት ወይም የምግብ ጉዳት ካላቸው
2. ህፃናት ሰውነታቸው ዉስጥ ያለው ማእድናት እጥረት ካለ በተለይ ደሞ የብረት(Iron) የፎሊክ አሲድ እና የቫይታሚን ቢ 12 መጠን ዝቅተኛ ከሆነ፡፡በተለይ ደሞ ከ6 ወር ጀምሮ በቂ የሆኑ እና በውስጣቸው በብዛት የብረት ማዕድን ያላቸዉን ተጨማሪ ምግቦችን ካላገኙ::(ለምሳሌ: የእህል ዘሮች ቀይ ስጋ እንቁላል ወተት እና የመሳሰሉት)ጻናት በተለይ ደሞ ፈጣን እድገት ስላላቸው ብዙ የብረት ማእድን ያስፈልጋቸዋል ይሄንን ብረት ማዕድን በበቂ መጠን ካላገኙ ለደም ማነስ ተጋላጭ ይሆናሉ
3. የደም መፍሰስ ችግር (በ አደጋ ወይም በበሽታ)
4. የላም ወተት አብዝቶ መጠቀም በተለይ ከ አንድ ዓመት በታች ያሉ በቀን ከ 500- 600 ሲሲ. በላይ የሚወስዱ ከሆነ አንጀታቸው ላይ በሚከሰት መቆጣት እና መድማት የደም ማነስ ልከሰትባቸው ይችላል::ስለዚህም ከአንድ ዓመት በታች ያሉ ህፃናት የላም ወተት ባይወስዱ ይመከራል፡፡
5. በተፈጥሮ የብረት ማእድን ከሰውነት ጋር ያለው ውህደት አነስተኛ መሆን(Malabsorbtion)
6. የአንጀት ዉስጥ ጥገኛ ትላትል (parasite)
7. ረጅም ጊዜ የሚቆዩ በሽታዎች (Anemia of Chronic illness)
8. የመቅኔ መድከም(Aplastic Anemia and bone marrow failure )ይህም የቀይ ደም ህዋስ ምርት መቀነስ ያመጣል፡፡
9. የደም ካንሰር፡፡
የደም ካንሰር በራሱ መቅኔን(Bone marrow) በማድከም በተመሳሳይ መልኩ የቀይ ደም ህዋስ ምርት በመቀነስ የደም ማነስ ያመጣል ::
10. የቀይ የደም ህዋስ የአፈጣጠር ችግሮች

የህጸናት ደም ማነስ ምልክቶች ምንድናቸው?
 ምግብ ፍላጎት መቀነስ
 የሰውነት መቀንጨር
 ራስ ማዞር
 የድካም ስሜት
 የላብ መብዛት
 የሰውነት መገርጣት
 የባህሪ መቀየር እና መነጫነጭ
 የራስ ምታት
 የልብ ድካም

የህጸናት ደም ማነስ መፍትሔ

 አይረን ያላቸውን ምግቦች በብዛት መመገብ፡፡ ለምሳሌ ቀይ ስጋ፣ጉበት፣ከእህል ዘሮች ባቄላ፣ አተር፡፡ ከአረንጓዴ ተክሎች ጎመን፣ቲማቲምፓፓዬ እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ፡፡
 ሕጻኑ የላም ወተት አየወሰደ ከሆነ መቆምና በቆርቆሮ ወተት መቀየር፡፡

 ለተጨማሪ መረጃ ሐኪምን ማናገር ይበጃል፡፡
ዶ/ር ፋሲል መንበረ (በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የሕፃናት ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር)
SPHMMC is proud to participate in #WorldMaskWeek with@pandamicAction. Wear a mask to protect others. #ThanksforMasking #WorldMaskWeekSPHMMC
እርግዝና እና ሄፓታይተስ ቢ

ነፍሰጡር ከሆንሽ የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ማድረግ አለብሽ፡፡
አዎ! ሁሉም ነፍሰ ጡር እናቶች የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ማድረግ አለባቸው፡፡ ነፍሰ ጡር ከሆንሽ ዶክተርሽ የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ እንዳደረገልሽ አርግጠኛ ሁኚ:: ልጅሽን ከመውለድሽ በፊት፡፡

የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ለነፍሰጡር እናቶች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ውጤትሽ ፖዘቲቭ ሆኖ ነፍሰጡር ከሆንሽ፤ ቫይረሱ በእርግዝና እና በወሊድ ግዜ አዲስ ወደሚወለደው ህፃን ይተላለፋል፡፡ ሄፓታይተስ ቢ እንዳለብሽ ዶክተሩ ካወቀ በማዋለጃ ክፍል ውስጥ ወደ ልጅሽ እንዳይተላለፍ ተገቢ የሆነ ህክምና ያደርግልሻል፡፡ ተገቢውን ሂደት መከተል ካልተቻለ ልጅሽ ስር በሰደደው ሄፓታይተስ ቢ የመያዝ እድሉ እስከ 95% ይደርሳል፡፡

በሄፓታይተስ ቢ መያዝ ካወቅሽ የሐኪምሽን ምክር መቀበል አለብሽ፡፡
አንቺ በሄፓታይተስ ቢ ስለመያዝሽ ዶክተርሽ ሊውቅ ይገባል፡፡ እንዲያ ከሆነ ክትትል የሚያደርግልሽ ሐኪም ልጅሽ ከተወለደ በኋላ በበሽታው እንዳይያዝ ማድረግ ይችላል፡፡ ሐኪሙ አንቺም ተገቢውን የህክምና ክትትል እንድታገኚ ይረዳሻል፡፡
በሄፓታይተስ ቢ ላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ሊከታተልሽም ይችላል፡፡
ልጅሽ በሽታው እንዳይተላለፍበትም የሐኪም ክትትል ያስፈልገዋል፡፡
ሄፓታይተስ ቢ እንዳለብሽ ከታወቀ ደግሞ አዲስ የተወለደው ልጅሽ በማዋለጃ ክፍል ውስጥ እንዳለ ወዲያውኑ ሁለት ክትባት ይሰጠዋል፡፡
• የመጀመሪያው ክትባት የሄፓታይተስ ቢ ክትባት
• አንዱ ክትባት ሄፓታይተስ ቢ ኢሚዩኖ ግሎቡሊን (HBIG)
በመጀመሪያዎቹ 12 ሰዓታት ውስጥ እነዚህ ሁለቱ መድሀኒቶች በትክክል ቢሰጡት አዲስ የተወለደው ህፃና እድሜ ዘመኑን አብሮት ሊኖር ከሚችለው የሄፓታይተስ ቢ ከ90% በላይ ተጠብቆ የመኖር እድል ይኖረዋል፡፡
ቀሪዎቹን ከ2-3 የሚደርሱ የሄፓታይተስ ቢ ክትባቶች በመርሀግብሩ መሰረት ልጅሽ ስለመውሰዱ እርግጠኛ መሆን አለብሽ፡፡ ጨቅላ ልጅሽን ሙሉ በሙሉ ከሄፓታይተስ ቢ ለመጠበቅ ሁሉንም ክትባቶች ማስከተብ ያስፈልጋል፡፡ ሄፓታይተስ ቢ ካለባት እናት የተወለደ ልጅ ሰሮሎጂክ ምርመራ ከ9-12 ወራት ውስጥ በማድረግ ህፃኑ ከሄፓታይተስ ቢ መጠበቁንና አለመያዙን ማረጋገጥ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ህጻናት ሲወለዱ ሄፓታይተስ ቢ ን ለመከላከል የሚያግዘውን ክትባት መከተባቸው የሚመከርና በቀጣይ ሊመጣ የሚችልን ማንኛውም አይነት የህመም ችግርን የመቀነስ እድልን ይፈጥራል፡፡ ለሄፓታይተስ ቢ ተብሎ የሚታዘዘው ቲኖፎቪር ጡት ለሚያጠቡ እናቶች አስተማማኝ ስለመሆኑ መረጃዎች አሉ፡፡
እርግዝና እና ሄፓታይተስ ቢ

ነፍሰጡር ከሆንሽ የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ማድረግ አለብሽ፡፡
አዎ! ሁሉም ነፍሰ ጡር እናቶች የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ማድረግ አለባቸው፡፡ ነፍሰ ጡር ከሆንሽ ዶክተርሽ የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ እንዳደረገልሽ አርግጠኛ ሁኚ:: ልጅሽን ከመውለድሽ በፊት፡፡

የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ለነፍሰጡር እናቶች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ውጤትሽ ፖዘቲቭ ሆኖ ነፍሰጡር ከሆንሽ፤ ቫይረሱ በእርግዝና እና በወሊድ ግዜ አዲስ ወደሚወለደው ህፃን ይተላለፋል፡፡ ሄፓታይተስ ቢ እንዳለብሽ ዶክተሩ ካወቀ በማዋለጃ ክፍል ውስጥ ወደ ልጅሽ እንዳይተላለፍ ተገቢ የሆነ ህክምና ያደርግልሻል፡፡ ተገቢውን የሕክምና ክትትል ሂደት መከተል ካልተቻለ ልጅሽ ስር በሰደደው ሄፓታይተስ ቢ የመያዝ እድሉ እስከ 95% ይደርሳል፡፡

በሄፓታይተስ ቢ መያዝሽን ካወቅሽ የሐኪምሽን ምክር መቀበል አለብሽ፡፡

አንቺ በሄፓታይተስ ቢ ስለመያዝሽ ዶክተርሽ ሊውቅ ይገባል፡፡ እንዲያ ከሆነ ክትትል የሚያደርግልሽ ሐኪም ልጅሽ ከተወለደ በኋላ በበሽታው እንዳይያዝ ለማድረግ ይችላል፡፡አንቺም ደግሞ ተገቢውን የህክምና ክትትል እንድታገኚ ይረዳሻል፡፡
በሄፓታይተስ ቢ ላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ይከታተልሻል፡፡

ልጅሽ በሽታው እንዳይተላለፍበትም የሐኪምክ ትትል ያስፈልገዋል፡፡

ሄፓታይተስ ቢ እንዳለብሽ ከታወቀ ደግሞ አዲስ የተወለደው ልጅሽ በማዋለጃ ክፍል ውስጥ እንዳለ ወዲያውኑ ሁለት ክትባት ይሰጠዋል፡፡
• የመጀመሪያው ክትባት የሄፓታይተስ ቢ ክትባት
• አንዱ ክትባት ሄፓታይተስ ቢ ኢሚዩኖ ግሎቡሊን (HBIG)
በመጀመሪያዎቹ 12 ሰዓታት ውስጥ እነዚህ ሁለቱ መድሀኒቶች በትክክል ቢሰጡት አዲስ የተወለደው ህፃን እድሜ ዘመኑን አብሮት ሊኖር ከሚችለው የሄፓታይተስ ቢ ከ90% በላይ ተጠብቆ የመኖር እድል ይኖረዋል፡፡
ቀሪዎቹን ከ2-3 የሚደርሱ የሄፓታይተስ ቢ ክትባቶች በመርሀግብሩ መሰረት ልጅሽ ስለመውሰዱ እርግጠኛ መሆን አለብሽ፡፡ ጨቅላ ልጅሽን ሙሉ በሙሉ ከሄፓታይተስ ቢ ለመጠበቅ ሁሉንም ክትባቶች ማስከተብ ያስፈልጋል፡፡ ሄፓታይተስ ቢ ካለባት እናት የተወለደ ሕጻኑ ሰሮሎጂክ ምርመራ ከ9-12 ወራት ውስጥ በማድረግ ህፃኑ ከሄፓታይተስ ቢ መጠበቁንና አለመያዙን ማረጋገጥ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ህጻናት ሲወለዱ ሄፓታይተስ ቢ ን ለመከላከል የሚያግዘውን ክትባት መከተባቸው የሚመከርና በቀጣይ ሊመጣ የሚችልን ማንኛውም አይነት የህመም ችግርን የመቀነስ እድልን ይፈጥራል፡፡ ለሄፓታይተስ ቢ ተብሎ የሚታዘዘው ቲኖፎቪር ጡት ለሚያጠቡ እናቶች አስተማማኝ ስለመሆኑ መረጃዎች አሉ፡፡