" በጎነት ለጤናችን " በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን የክረምት የበጎ ፍቃድ የጤና አገልግሎት ነጻ ምርመራ ዛሬ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶር ደረጄ ዱጉማ በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል፡፡ ለተከታታይ ስድስት ቀናት በሚቆየዉ ነጻ የሕክምና ምርመራ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ መጥቶ የጤና ምርመራ ማድረግ እንደሚችል በመክፈቻው ላይ ተገልጿል፡፡
ለምን አመታዊ የጤና ምርመራ ማድረግ አለብን?
አመታዊ የጤና ምርመራ በተለያየ የዕድሜ ክልል ላይ ላሉ ሰዎች የሚደረግ እና ለአንድ በሽታ የመጋለጥ ዕድላቸውን ቀድሞ ለማወቅ የሚያስችል የምርመራ ዘዴ ነው።
እድሜ እና ፃታን መሠረት አድርገው በየአመቱ እና ከዛም በላይ ሊደረጉ የሚገቡ የምርመራ አይነቶች አሉ። እነዚህን ምርመራዎች መረዳት እና መቼ መጠየቅ እንዳለብዎት ማወቅ ጤናማ ሆነው እንዲቆዩ ያግዝዎታል። እንደ ካንሰር ፤የልብ ህመም፤ስትሮክ ፤የኩላሊት ህመም፤የስኳር ህመም፤የደም ግፊት መጨመር እና አንዳንድ በቅድመ ጥንቃቄ ልንከላከላቸው የምንችላቸውን ህመሞች ለመቆጣጠር ቀደም ብሎ ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።
ታዲያ የጤናዎን ሁኔታ ለማወቅ ለምን ወደ እኛ አይመጡም? በራስ ኃይሉ የስፖርት ማዘውተሪያ እንገኛለን። ምርመራው ደግሞ ነጻ ነው።

ኡሁን ምንም ዓይነት ሕመም ስሜት ላይሰማዎት ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ በሽታዎች ምልክታቸው በውል የምንገነዘበው አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ዓመታዊ የጤና ምርመራ ማድረግ የበሽታው ሰስር ሳይሰድ አስቀድሞ መከላከል ይቻላል፡፡ በተለያየ የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች የሚያደርጉት የጤና ምርመራ ለአንድ በሽታ የመጋለጥ ዕድላቸውን ቀድሞ ለማወቅ ያስችላቸዋል፡፡
ታዲያ እርስዎ ወረፋ ሣይጠብቁ፡ ካርድ ሳያወጡ፡ ምንም ሳይከፍሉ ለምን የጤና ምርመራ አያደርጉም? ፈቃድዎ ከሆነ መድሐኔያለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደተጃ ትምህርት ቤት ዝቅ ብሎ በሚገኘው የራስ ኃይሉ ስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል ተገኝተው የጤና ምርመራ እንዲያድርጉ ጋብዘንዎታል፡፡

ተቋርጦ የነበረው የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ተጀመረ፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የኩላሊት እጥበት መስጫ ማዕከል( Dialysis center ) የእጥበት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ መሳሪያዎች ረዘም ላለ ጊዜ በማገልገላቸው እድሳት ስለሚያስፈልጋቸው ለተወሰነ ጊዜያት ማእከሉ አገልግሎቱን አቋርጦ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ የማዕከሉ የእጥበት መሳሪያዎች እድሳት በመጠናቀቁና አስፈላጊ ግብኣት በመሟላቱ አገልግሉቱን በያዝነው ሳምንት ሙሉ ለሙሉ መጀመሩን ለታካሚዎቻችንን ለመብሰር እንወዳለን፡፡ ታካሚዎቻችን ከዚህ ቀደም የሚያገኙትን አገልግሎት በማእከሉ ማግኘት እንደሚችሉ ለማሳሳብ እንወዳለን፡፡