St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
ኢትዮጵያዊያን … በአርበኝነት : በሀገር ፍቅር እና በዓላማ አንድነት የተባበሩበት !
እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ
እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል
   በዓል በሰላም አደረሰዎ


ዓድዋ በሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ግጥም ሲታወስ
------------------------------------------------

ዋ!... ያቺ አድዋ
ዋ!...
ዓድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ…
ባንቺ ህልውና
በትዝታሽ ብጽዕና
በመሥዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና…
ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰዉብሽ ለት፤
ዓድዋ
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
ዐፅምሽ በትንሣኤ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው-እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው-በለው-በለው-በለው!
ዋ!... ዓድዋ…
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ በለው፣ በለው- በለው!
ዋ! … ዓድዋ …
ዓድዋ የትላንትናዋ
ይኸው ባንቺ ህልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመሥዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሡ እደገና፡፡
… ዋ! … ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የዐለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ…

ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን

መልካም በዓል
Study Reveals High Psychological Distress among Chronic Patients during COVID-19
A recent study conducted at St. Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC) and Black Lion Hospital has uncovered high levels of depression, anxiety and perceived stress among patients with chronic illnesses during the COVID-19 pandemic.
The cross-sectional study, carried out from April to June 2021, involved 426 adult patients attending outpatient clinics. The research assessed the psychological impact of the pandemic on individuals living with hypertension, heart disease, diabetes and other chronic conditions.
According to the findings, 45.5 percent of participants reported severe perceived stress, while 39.7 percent experienced symptoms of depression and 26.5 percent showed signs of anxiety. Nearly half of the respondents were living with multiple chronic diseases.
The study identified younger age, female gender, multiple comorbidities, unmarried status, lower educational attainment and poor social support as significant factors associated with increased psychological distress.
Researchers indicated that although patients with chronic illnesses were already vulnerable to severe COVID-19 outcomes, the pandemic further intensified their mental health burden due to healthcare disruptions, social isolation and fear of infection.
The findings highlight the urgent need to integrate mental health screening and psychosocial support into chronic care services. The researchers also recommended further longitudinal studies to better understand the long-term mental health consequences of the pandemic on high-risk populations.
The study provides important evidence to inform policymakers and healthcare providers in strengthening integrated and patient-centered care services in Ethiopia.
Enrich:
Full article: https://doi.org/10.1371/journal.pgph.0005838
Open dataset: https://doi.org/10.6084/m9.figshare.31143931
Publisher link: https://journals.plos.org/globalpublichealth/article?id=10.1371/journal.pgph.0005838
SPHMMC Launches Pain Medicine Initiative to Improve Quality of Care

St. Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC) has launched a Pain Medicine Initiative in collaboration with Ethiopian diaspora Professor Salahadin Abdi, Chair of the Department of Pain Medicine at University of Texas MD Anderson Cancer Center.
The initiative aims to ease the suffering of patients living with cancer and other chronic illnesses by strengthening specialized pain management services. During discussions with SPHMMC Provost Dr. Muluken, Professor Abdi emphasized the need to establish a structured Pain Medicine Fellowship Program, expand clinical services, and promote multidisciplinary approaches to pain care.
Officials noted that integrating modern pain management practices will significantly improve patient comfort, dignity, and overall treatment outcomes.
The meeting was attended by SPHMMC Vice Provost Dr. Ewenet G.Hanan and Dr. Metasebia, Head of the Family Medicine Department.
The new initiative is expected to play a vital role in advancing patient-centered care at SPHMMC and strengthening pain medicine services nationwide.
የዓለም ቲቢ ቀንን ምክንያት በማድረግ የሕጻናት የስዕል ውድድር ተዘጋጅቷል፡፡ ከ3ኛ- 6ኛ ያሉ ተማሪዎች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
በውድድሩ ላሸነፉ ተማሪዎች ልዩ ልዩ ሽልማት ይሰጣቸዋል፡፡
የውድድር መስፈርት-
የሥዕል የወረቀት መጠን፡- ከA4 በላይ
ቀለም፡- በእርሳስ፣በቀለም ወይም በከለር መጠቀም ይችላሉ፡፡
ማሣሠቢያ፡- የሥዕል ሥራዎቻቸው ጀርባ፤ሙሉ ስማቸውን፣ ትምህርት ቤታቸውን፣ስልክ ቁጥራቸውን መጻፍ አለበት፡፡ በተጨማሪም የትምህርት ቤታቸው ማህተም ያርፍበታል፡፡
ተማሪዎች፡ የስእል ስራቸውን ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየምሕክምና ኮሌጅ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ፡ አሰተዳደር ሕንጻ አንደኛ ፎቅ ክፍል ቁጥር C-30 ማቅረብ ይችላሉ፡፡
"ማርች" የትልቁ አንጀት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር

የአንጀት ካንሰር  በትንሹ አንጀት : በትልቁ አንጀት እንዲሁም በፊንጢጣ ላይ የሚከሰት የካንሰር ህመምን ያጠቃልላል።

በሀገራችን ያለበት ሁኔታ ምን ይመስላል?

በወንዶች ላይ እንደአዲስ ከሚታወቁ (newly diagnosed) የካንሰር አይነቶች መሀከል በአንደኛነት እንዲሁ በሴቶች ላይ ደሞ( ከጡትና ከ ማህጸን በር ካንሰር በመቀጠል) በሶስተኛ ደረጃነት ይገኛል።

በአጠቃላይም በሀገራችን በ2020  አውሮፓውያን አቆጣጠር 6050 የሚሆኑ አዳዲስ የትልቁ አንጀት ካንሰር ታማሚዎች ተገኝተዋል። ይህም አሀዝ በሚቀጥሉት አመታት እንደሚጨምር ይጠበቃል።

ለትልቁ አንጀት ካንሰር አጋላጭ ነገሮች ምንድናቸው?

1.እድሜ 
የአንጀት ካንሰር እድሜኣቸው ከ50 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች ላይ የመከሰት እድሉ ከፍ ይላላል,ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የአንጀት ካንሰር በወጣቶችና በጎልማሶች ላይ ቁጥሩ እየጨመረ ነው።

በሀገራችን በሚገኝ አንድ ሆስፒታል በተሰራ  ጥናትም 40% የሚሆኑት የትልቁ አንጀት ካንሰር ታማሚዎች እድሜኣቸው ከ40 አመት በታች ነው ይህም ከሌሎች የአለም ሀገራት በጣም የተለየና የትልቁ አንጀት ካንሰር በሀገራችንና ከሰሀራ በታች ባሉ ሀገራት በብዛት በጎልማሶች ላይ የመከሰት እድሉ ከፍ ያለ ነው።( በአለም አቀፍ ደረጃም የአንጀትና ፊንጢጣ ካንሰር በወጣቶች ላይ በካንሰር ከሚከሰት የሞት ምክንያት ቀዳሚ ነው)

2.የቤተሰብ ታሪክ
የትልቁ አንጀት ካንሰር ወይም የሌላ የሰውነት ክፍል ካንሰር በቤተሰብ ውስጥ  የተከሰተ ከሆነ ሌሎች የቤተሰብ ኣባላት ወደ ፊት የመያዝ እድላቸው ይጨምራል።

3.የቅድመ ካንሰርነት ደረጃ የደረሱ አንጀት ላይ የሚከሰቱ እባጮች (colonic polyps)

4.ለካንሰር አጋላጭ የሆኑ የዘረመል ለውጦች

5.ረጅም ጊዜ የቆዩ የአንጀት ቁስለት ህመሞች (inflamatory bowel disease)

6.የእንስሳት ተዋጽኦ የሆኑ ምግቦችን ማዘውተር

7.ሲጋራ ማጤስና አልኮል አብዝቶ መጠቀም

8.ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት
9.አካላዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ


ምልክቶቹስ?

የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ የሆድ መነፋት፣ምግብ ቶሎ መጥገብ አይነምድር እና ፈስን በተለመደው ሁኔታ ለማውጣት መቸገር፤ በፊንጢጣ በኩል ደም መፍሰስ፣ መጸዳጃ ቤት ከሄዱ በኋላ ያለመጨረስና  የማስማጥ ስሜት ፣ ምክንያቱ ያልታወቀ በተደጋጋሚ የደም ማነስ ህመም መከሰት፣ ደረጃው ከፍ እያለ ሲሄድም የአንጀት ሙሉ በሙሉ መዘጋትን ሊያመጣ ይችላል ህመሙ በፊንጢጣ አካባቢ ከሆነም ሰገራ ና ፈስ የመቆጣጠር አለመቻል::

ምን ይደረግ?

1.እንድሜው/ዋ ከሀምሳ አመት በላይ የሆነ ሰው ወይም  አጋላጭ ነገሮች ያሉት/ያላት አልያም ከላይ የተገለጹት ምልክቶች ካሉ አለመዘናጋትና በአፋጣኝ ወደሀኪም ቀርቦ መመርመር።

በሚያስቆጭ ሁኔታ አብዛኛዎቹ ታካሚዎቻችን የአንጀት ካንሰር ህመም ምልክቶች ከታዩ በኋላ ወደ ህክምና ዘግይተው እና ማዳን የማይቻልበት ሁኔታ ላይ ወደ ሀኪም ይመጣሉ። ከተለመዱት የመዘግየት ምክንያቶችም  አሜባ ወይም  የፊንጢጣ ኪንታሮት ተብለው በተደጋጋሚ መታከም አልያም እንደአማራጭ  የተለያዩ መፍትሄዎችን መፈለግ ነው።

2. መቀየር የሚችሉ አጋላጭ ባህሪያት ካሉ ማስተካከል።

3. ህመሙ ከታወቀ በኋላም ከሀኪም ጋር ተመካክሮ  በቀጣይ ህክምናዎችን በአግባቡ መከታተል።

ያስታውሱ

የአንጀት ካንሰር በየትኛውም የእድሜ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል!
የአንጀት ካንሰርን በቅድመ ምርመራ መከላከል ይቻላል!



ቸር እንሰንብት!

Dr. Binyam Yohannes: General surgeon, colorectal surgeon
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ
Excellence in Surgery Starts Here.
SPHMMC General Surgery Graduates – 2026