St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
የወር አበባሽ ተዛብቶብሽ ይሆን?

የወር አበባ ዑደት ተዛባ የምንለው አንዲት ሴት ወትሮ ከምታየው የተለየ ጠባይ ሲገጥማት ነው፡፡

1) የወር አበባ መዛባት ዓይነቶች
· የፍሰት መጠን መብዛት
· የፍሰት መጠን ማነስ
· መቅረት
· የቀኑ መዛባት
· ቶሎ ቶሎ መምጣት

2) የወር አበባ መዛባት መገለጫዎች
የፍሰት መጠን መብዛት- ከዚህ በፊት ይፈስሽ ከነበረው መጠን በላይ ሲበዛ፣ ከ7 ቀናት ባላይ ሲፈስሽ፣ ብዙ የንጽሕና መጠበቂያ ለመጠቀም ስትገደጂ፣ ሲፈስሽ የሚረጋ ከሆነ፣ የድካ ስሜት ካለሽ፣ የማዞር ስሜት ካለሽ እና ራስን እስከ መሳት ስትደርሺ ፍሰቱ ተዛብቷል ማለት ነው፡፡

መንስኤዎች፡- ማህፀን እጢዎች፣ የሆርሞን መዛባት፣ ጭንቀት፣ መድሀኒቶች፣ የደም መርጋት ችግር ሊሆን ይችላል።

የፍሰት መጠን ማነስ፡- ከ35 ቀናት በላይ እየቆየ የሚመጣ ከሆነ፣ ከሁለት ቀናት ባነሰ ጊዜ ብቻ በመጠኑ የሚፈስሽ ከሆነ ይሄ የማነስ ምልክት ነው።
መንስኤዎች፡- የእንቁላል አመራረት ሂደት መዛባት(PCOD)

መቅረት፡- ለ3 ተከታታይ ዑደት ወይም ለ6 ወራት የወር አበባ መቅረት፤ መንስኤዎቸሁም
· እርግዝና፣ የማኅጸን ጠባሳ፣ የማኅጸን ኢንፌክሽን፣ የሆርሞን መዛባት
· ጭንቀት፣ ከባድ የሆነ የስፖርት እንቅስቃሴ ወይም ማረጥ ሊሆኑ ይችላሉ።

ቀኑን ማዛባት፡- ወቅቱን ጠብቆ የማይፈስ የወር አበባ ዑደት
መንስኤዎች፡- የማኅጸን ዕጢዎች፣ የማህጸን ጫፍ ካንሰር

ቶሎ ቶሎ መጣ የምንለው፡- ከ21 ቀናት በታች ተደጋሞ የሚመጣ ከሆነ ነው።
መንስኤዎች፡- ማህፀን እጢዎች፣ የሆርሞን መዛባት፣ ጭንቀት፣ መድሀኒቶች፣ የማረጥ እድሜ ላይ መድረስ ሊሆኑ ይችላሉ።

መፍትሔዎች እንደ መንስኤዎች ዓይነት ይለያያል።
(በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)
ቸር እንሰንብት
የኮሮና ቫይረስ እና ሕፃናት

በኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት 69 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከጥቂት ሳምነታት በፊት የተገኘው መረጃ አንዳሚያሳየው 644 የሚሆኑት ከ 0 እስከ 4 አመት ያሉ ሕፃናት ሲሆኑ 788 ያህሉ ደግሞ ከ 5 እስከ 14 አመት ያሉ ሕፃናት ልጆች ናቸው፡፡ህፃናት ልጆችም በኮሮና ቫይረስ ተይዘው እንደ አዋቂውች ምንም የህመም ስሜቶች ወይም ቀላል የህመም ስሜቶች ሊያጋጥማቸው ሲችል ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የመግባታቸው እድል ግን ዝቅ ያለ ነው፡፡
ቫይረስ ከጨቅላ ህፃናት ጀምሮ የሚይዝ በሽታ ሲሆን ህፃናቱ ምንም አይነት የህመም ምልክት ላያሳዩ ወይም ቀለል ያለ የህመም ምልክቶች ሊኖራቸው ቢችልም ወደ ሌላው የማህበረሰብ ክፍል ግን ቫይረሱን ያስተላልፋሉ፡፡ ህፃናት ልጆች በሽታን የመከላከል አቅማቸውን ለማጎልበት ቤተሰቦች አቅማቸው በሚችለው መጠን ለልጆቻቸው የተመጣጠነ ምግብ ቢመግቡ ተመራጭ ነው፡፡
የተለየ የህመም ስሜት እንደ ሳል ትኩሳት፣የአየር/ማጠር፣ቶሎቶሎ የመተንፈስ እና ሌሎች የበሽታ ምልክቶች ካየንባቸው ወደ ጤና ተቋማት መውሰድ እና አስፈላጊውን የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
ልብ ይበሉ! የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በምናደርገው ጥንቃቄ ለልጆቻችን የሚያስፈልጉ የህክምና ክትትሎችን መዘንጋት ተጨማሪ የጤና እክል እንደሚያስከትሉ አንዘንጋ፡፡ስለሆነም ህፃናት በቂ የቀጥታ የፀሀይ ብርሀን እንዲያገኙ ማድረግ ፣ የእናት ጡት ወተት እስከ 2 አመት ድረስ (ከ6 ወር በኃላ ከተጨማሪ ምግብ ጋር) መመገብ እንዲሁም የክትባት ጊዜያቸውን በጠበቀ መልኩ እና በተለያየ ጊዜ ለተላላፊ በሽታዎች ማስከተብ የሚኖርብንን ክትባት እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
በዚህ ወቅት ግዴታ ሆኖ ህፃናት ልጆቻችንን ይዘን ከቤት ከወጣን ከሁለት አመት በላይ ለሆኑ ህፃናት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያወልቁ፣የእጃቸውን ንፅህና እየጠበቅን ርቀታቸውን በመጠበቅ ለኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት ባለመሆን ራሳችንን እና ልጆቻችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ፡
ክ EPHI የተገኘ፡፡( ለገጻችን እንዲመች አጠር እነዲል ተደርጓል፡፡
⩩###(##((######################⩩###############
ለግንዛቤዎ !

ኮሮና ቫይረስ የህክምና ማስረጃ እንዴት ይሰጣል? ለማንስ ይሰጣል?

የኮቪድ 19 የህክምና ክትትልን ያጠናቀቁ ከኮሮና ቫይረሱ ነጻ መሆንን የሚያሳይ የህክምና ማስረጃ/ደብዳቤ በሁለት መንገድ ይሰጣል፡፡
1. ራሳቸውን ለይተው በቤት ውስጥ የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ለነበሩ ታካሚዎች ክትትል ሲያደርግላቸው የነበረው የጤና ባለሙያ በአካልም ሆነ በስልክም ክትትል ሲያደርግላቸው ካረጋገጠ ደብዳቤ ( ማስረጃ) ይሰጣል ፡፡
2. በጤና ተቋማት በኩል ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ሆነው የህክምና ክትትል ሲያድርግላቸው በነበረው ጤና ተቋም በኩል ክትትላቸውን አጠናቀው ከቫይረሱ ነጻ ስለመሆናቸው ሲረጋገጥ የህክምና ማስረጃ ይሰጣል፡፡
EPHI
የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአዋጅ የተሰጣቸውን ስልጣን በመጠቀም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር የሚያግዝ መመሪያ አውጥተዋል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር የወጣ መመሪያ ቁጥር 30/2013 ዝርዝር መመሪያውን ይህን ሊንክ ተጭነው ማግኘት ይችላሉ፡፡
http://www.moh.gov.et/ejcc/am/COVID19_Ditective_30
እነዚህን የተከለከሉ ተግባራት ያውቃሉ?
-------------
# በላብራቶሪ የተረጋገጠ የኮቪድ 19 ቫይረስ ያለበት ሠው ወደ ሀገር ውሰጥ መግባት ከማህበረሰብ ጋር መቀላቀል ፣ እንዲሁም ወደ ሌሎች በሽታውን በሚያስተላለፍ የተከለከለ መንገድ መገናኘት
# ማንኛውም ግለሰብ መጨባበጥ ሆነ አካላዊ ንክኪ ማድረግ
# የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ከመኖሪያ ቤት ውጭ በማንኛውም ቦታ ሳያደርጉ መንቀሳቀስ
# በመንግስታዊም ሆነ በግል ተቋማት ውስጥ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ አገልግሎት መስጠት ፣ ከሁለት የአዋቂ እርምጃ በታች መጠጋጋት፣በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዲቀመጡ ማድረግ
# የንግድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ላላደረገ አገልግሎት መስጠት
# የግልም ሆነ የመንግስት ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርሲቲ የፊትለፊት ትምህርት መስጠት መጀመር እንደሚቻል ሳይወሰን እንዲሁም የጥንቃቄ እርምጃዎችን ሳያከብር ትምህርት መስጠት
# የህጻናት ማቆያ ማዕከል አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል ሳይወሰን እንዲሁም አገልግሎት የሚሰጥበት ሁኔታ በተመለከተ በመመሪያ የሚወጡ ሊወሰዱ የሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎችን ሳያከብር አገልግሎት መስጠት

የተከለለ ነው!!
እነዚህን አውቀን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ስርጭትን እንግታ!
EPHI
ሾተላይ ምንድን ነው?

ሾተላይ በመባል የሚታወቀው ክስተት ብዙ ጊዜ አንዲት እናት ከመጀመሪያ እርግዝናዋ በኃላ በተደጋጋሚ የሚከሰት የጽንሱ መጥፋት ነው።
ይህ ለምን ይሆናል?

የሰዎች ደም በአራት መደብ ይከፈላል(A, B, AB, O) እነዚህ ደግሞ እያንዳንዳቸው በሁለት አበይት መደብ ይከፈላሉ፡ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) እና አር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-)።

ለምሳሌ፦ የአንድ ሰው የደም ዓይነት A+ ወይም A- ሊሆን ይችላል።

የሰው ማንነቱ ከእናቱና ከአባቱ በሚወስደው የዘር-መል ይወሰናል። የደም ዓይነትም በዚሁ መልክ እንወስዳለን። ከአር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) አባት እና ከአር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-) እናት የሚፈጠር ጽንስ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የመሆን እድሉ የሰፋ ነው።

ሾተላይ የሚከሰተው አንዲት ሴት የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ሆኖ ከዚህ በፊት አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) የሆነ ደም ወደ ሰውነቷ ሲገባ ደሟ ውስጥ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የሆኑ የደም ህዋሶችን የሚያጠፋ ንጥረ-ነገር በደሟ ውስጥ ይመረታል። ይህ ንጥረ-ነገር አንዴ ከተመረተ በደሟ ውስጥ እስከ ህይወቷ ፍጻሜ ድረስ ይኖራል።

በመሆኑም በማህጸንዋ ውስጥ የያዘችው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ የተመረተው ንጥረ-ነገር ጽንሱን እንደ ባእድ አካል ስለሚቆጥረው ያጠቃዋል። በዚህም ምክንያት በተደጋጋሚ የምትይዘው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ አስፈላጊውን ህክምና ካልተደረገላት ይሞትባታል።

የደም ዓይነቱ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ከሆነ ግን በጤና ይወለዳል። ይህ እንዲሆን ግን የአባትየው የደም ዓይንት አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) መሆን አለበት?

ሕክምናው

1. የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) የሆነች እናት ሕክምናዋ በሆስፒታል ውስጥ መሆን አለበት።
2. በደሟ ውስት ያለውን የንጥረ-ነገር መጠን መለካትና የጽነሷን የጉዳት መጠን በማየት ብዙ ሳይጎዳ እንዲወለድ ማድረግ።
3. በሀገራችን በቅርቡ የተጀመረው ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እያለ ደም በመለገስ እንዲያድግና እንዲወለድ ማስቻል።

እንዴት እንከላከለው?

1. ማንኛዋም ሴት ከማርገዟ ወይም ማንኛውንም ደም ከመውሰዷ በፊት የደም ዓይነቷን ማወቅ አለባት።
2. የወንድ አጋሯን የደም ዓይነት ማወቅ አለባት።
3. እርግዝና አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ አጋሯ ከተፈጠረ መጀመሪያ በሚደረግላት ምርመራ (indirect coomb’s test) ንጥረ-ነገሩ አለመመረቱን ያረጋግጣል። እዳይመረት የሚከላከል መድኃኒት (Anti-D) 7ተኛ ወሯ ላይ ይሰጣታል። ከወለደች በኃላ የልጇ የደም ዓይነት አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ በድጋሚ መድኃኒቱ ይሰጣታል።n
4. እርግዝናው ከማህጸን ውጭ ወይም በውርጃ ቢያበቃም መከላከያውን መድኃኒት መውሰድ አለባት።

ጽሑፉን ከወደዱት(Like) በማድረግ ለሌሎችም (share)ያድርጉት፡፡
(በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)
ዓለም አቀፋዊ ስታስቲክሶች- በአእምሮ ጤና ዙሪያ

 ዓለማችን በኢኮኖሚው ዘርፍ በአባች ድባቴ (Major Depression) እና ከፍተኛ የአዕምሮ ውጥረት ምክንያት በየዓመቱ ከ 92-300 ትሪሊየን ብር ታጣለች፡፡

 ሌሎች የአዕምሮ ጤና መታወኮች ሲደመሩ ደግሞ ዓለማችን በየዓመቱ ከ 2.5 እስከ 8.5 ትሪሊየን ዶላር ታጣለች፡፡
 አባች ድባቴ (Major Depression) 264 ሚሊየን ግለሰቦችን ያጠቃል፡፡ ግማሽ የሚሆኑትን የአዕምሮ ጤና እክሎች የሚጀምሩት ከ14 ዓመት ጀምሮ ነው፡፡
 ራስን ማጥፋት (Sucide) ከ 15-29 ዕድሜ ያላቸው ግለሰቦች 2ኛው ቀዳሚ የሞት ምክንያት ነው፡፡
 ይህም አምራች ኃይል የምንለው የማሕበረሰብ ክፍልን በዋነኝነት እንደሚያጠቃው ያመላክታል፡፡
 በዓለማችን ግጭቶች እና የተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶች በሚበዙባቸው አካባቢዎች ከ 5 ሰዎቹ አንዱ እርዳታ የሚሻ የአዕምሮ ጤና እክል በሕይወት ዘመኑ እንደሚያጋጥመው መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
 ከፍተኛ የአዕምሮ መታወክ ያላቸው ግለሰቦች ከጠቅላላው ማህበረሰብ 10 እና 20 ዓመት ቀድሞ ሕይወታቸው ያልፋል፡፡
 ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ የሚገኙት የአዕምሮ ህመም ያላቸው ግለሰቦች ከ76-85% የሚሆኑት ህክምና አያገኙም፡፡
 ጥናቶች ግን የአዕምሮ ህክምና ብዙ ወጪ ሳያስፈልገው ተደራሽ መሆን እንደሚችል ያሳያሉ፡፡
 በዓለም አቀፍ ደረጃ አንድ የአዕምሮ ጤና ባለሙያ ከ10,000 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦችን ይደርሳል፡፡

ምንጭ፡- UN Policy brief
በዶ/ር ሙሉቀን ተስፋዬ
(የአዕምሮ ሐኪም)
ከማህጸን ውጪ እርግዝና (Ectopic pregnancy)

በመደበኛው (ጤናማው) የእርዝና ሥርዓት የተፈጠረው ጽንስ በማህጸን ውስጥ ያድጋል፡፡ አልፎ አልፎ ግን ከመደበኛው (ጤናማው) አርግዝና ውጪ ጽንሱ ከማህጸን ውጪ የሚያድግበት እድል ሊኖር ይችላል፡፡ ይህም በጥናት እንደተረጋገጠው በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚመዘገቡ 6በመቶ ለሚሆኑ እናቶች ሞት ምክንያት ይሆናል፡፡
ከአምስ በላይ ከማህጸን ውጪ የእርግዝና ዓይነቶች ቢኖሩም 95 ከመቶ የሚሆኑት የሚፈጠሩት በማህጸን ቱቦ ውስጥ ነው፡፡

ምክንያቶች እና አጋላጮች

1) የመራቢያ አካት ኢንፌክሽን
2) በማህጸን ቱቦ ላይ የሚደረግ ቀዶ ጥገና ወይንም መቋጠር
3) ከዚህ በፊት ተከስቶ የነበረ የማህጸን ውጪ እርግዝና
4) ውርጃ
5) መካንነት
6) ትምባሆ ማጤስ
7) ከአንድ በላይ የወሲብ ጓደኛ መኖር
8) ፖስት ፒል መጠቀም

ምልክቶቹ

1) ህመም (በአብዛኛው ከእምብርት በታች የሚሰማ የሆድ ህመም)
2) ከማህጸን የሚወጣ መጠነኛ የደም መፍሰስ
3) ማዞር ወይንም ራስን መሳት

ህክምናው

1) በቀዶ ጥገና ጉዳት የደረሰበትን የማህጸን ቱቦ ማስወገድ ወይንም እርግዝናውን ማቋረጥ
2) በመድኃኒት ማከም

መከላከያው

1) የመራቢያ አካላት ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር መከላከል
የወሲብ ጓደኛን ቁጥር በአንድ በመወሰን
ይህ የማቻል ሲሆን ኮንዶምን በመጠቀም
ኢንፌክሽኑ ከተፈጠረም ወዲያውኑ በመታከም
2) ከትምባሆ ሱሰንነት መራቅ
3) መደበኛ የሆነ የወሊድ መቆጣጠሪያ መጠቀም

(በዶ/ር ቤተል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)
..........................................................
እባክዎን ለጣና የሶሻል ሚደያ ሽልማት እንድናገኝ- ድምጽዎን ይስጡን። 7147 ላይ T8 ብለው ቴክስት ያድርጉልን። እናመሠግናለን ።
Announcement

The department of internal medicine, SPHMMC, kindly invites all qualified and competent applicants to apply for fellow-ship program in physical medicine and rehabilitation.

Admission requirements

1. The candidate must have doctor of medicine from a recognized medical school
2. Completed residency program in internal medicine, neurology, family medicine, orthopedics or emergency medicine from a recognized medical school.
3. Served at least for two years
4. Must complete screening process for admission to be undertaken by the department of internal medicine including entrance examination.
5. Registered and licensed to practice medicine in Ethiopia by the relevant authorities
6. Should have adequate physical and mental health to deliver both his/her academic and clinical service responsibilities.
Applicant should write a brief intent letter describing their interest in the fellowship, expectations and impact on their career after joining the program.

Applicants should submit the following documents.

Application letter
Recent CV with intent letter
Copy of credentials including degrees, student copy
Two letters of recommendation in a sealed envelope
Letter of sponsorship from sponsoring institution (not applicable for private/self-sponsoring applicants)

Interested applicants can apply in person to the department of internal medicine or use this email: dawit.bacha@sphmmc.edu.et until October 25/2020.

Interview of candidates will be on November 10/2020 and admission will be on December 01/2020

For further information you can use the following telephone numbers,
Dr. Dawit: 0911714774
Dr. Tesfaye: 0911405676
Announcement

The department of internal medicine, SPHMMC, kindly invites all qualified and competent applicants to apply for fellow-ship program in adult cardiology

Admission requirements
1. The candidate must have doctor of medicine from a recognized medical school
2. Completed residency program in internal medicine from a recognized medical school.
3. Served at least for two years
4. Must complete screening process for admission to be undertaken by the department of internal medicine including entrance examination.
5. Registered and licensed to practice internal medicine in Ethiopia by the relevant authorities.
6. Should have adequate physical and mental health to deliver both his/her academic and clinical service responsibilities.


Applicant should write a brief intent letter describing their interest in the fellowship, expectations and impact on their career after joining the program.
Applicants should submit the following documents.
 Application letter
 Recent CV with intent letter
 Copy of credentials including degrees, student copy
 Two letters of recommendation in a sealed envelope
 Letter of sponsorship from sponsoring institution (not applicable for private/self-sponsoring applicants)

Interested applicants can apply in person to the department of internal medicine or use this email: dawit.bacha@sphmmc.edu.et until October 25/2020.
Interview of candidates will be on November 10/2020 and admission will be December 01/2020


For further information you can use the following telephone numbers
Dr. Dawit: 0911714774
Dr. Seifu: 0911684654
Wish you all Global Hand Washing Day 2020!

Stay safe by ensuring proper hand washing and Hygine.
Why did I become Anesthesiologist?
Dr.Blen Ayele
Black Lion Specialized Hospital.

People ask you what you want to become and why since like I can ever remember. As a child, I can say I have wondered through all the fields. But it was later in my life that I understood the ultimate luxury is to be passionate about your job. Years passed by and choices were made. In fact, there were some fields I liked but I was not passionate enough to stay in the fields.
In joining anesthesiology, however, I was so impressed by the science first. It is such a fascinating and applied physiology and pharmacology at its best. It was something you want to know and apply more every day. Then I soon learned that the operation theatre was a very interesting place where important things happen to patients on a daily basis and a safe and standard perioperative care is crucial. There is a great pleasure that comes with becoming the trusted guardian who provides a safe and standard perioperative care for patients.
Further, giving critical care for a potentially very sick patient where things change moment to moment also makes it an exciting specialty. It taught me to become a team performer and vigilant in treating potentially fatal but preventable conditions.
It is also true that no one wants to see patients in pain but to be the ultimate equipped person to relief their pain is really satisfactory. It overrides all the pleasure that comes with it.
In addition the fact that anesthesiology, critical care and pain medicine gives me the opportunity to work with a wide range of patients, including, pediatrics, elderly, obstetrics, emergency, trauma and others makes it a phenomenal and a never boring experience to me.
So, to wrap up, why did I become anesthesiologist? Because the specialty has a lot to offer and because I believe I can make a difference in the field I am passionate about.
የሐኪሙ ምክር -ዶር አፈወርቅ ሐጎስ ! t.me/spmmc

ባሳለፍነው ሳምንት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የኮሮና አስተኝቶ ማከሚያ ክፍል ተረኛ ሲኒየር በመሆን ለአንድ ሳምንት ሰርቼ ነበር። በሆስፒታላችን የኮሮና ህክምና ከተጀመረበት ላለፉት ሰባት ወራት ገደማ በኮንሰልታንትነት፣ በኮቪድ19 ምክንያት የሚከሰቱ የደም ችግሮች ምርመራ ማድረግ እንዲሁም ህክምናው ለይ ማማከር ፣ የኮቪድ19 ህክምና አጋዥ መመሪያ ዝግጅት ላይ ስሳተፍ የነበረ ቢሆንም በተኝቶ ህክምና ክፍል ውስጥ ተመድቤ ከክፍሉ ባለሞያዎች ጋር በመሆን ወገኖቼን መርዳት በመቻሌና የሞያ ግዴታዬን በመወጣቴ ደስታ ተሰምቶኛል።
በኮቪድ19 በሽታ ለከፋ ጉዳት እና ሞት የሚዳረጉት በዋናነት ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው ታማሚዎች እንደሆኑ ሁላችንም የምናወቅ ቢሆንም በነኝህ ወገኖች ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት መገንዘብ የሚችሉት በቅርበት የደረሰባቸው ታማሚና ቤተሰብ እንዲሁም የጤና ባለሞያዎች ይመስሉኛል። እነኚህ ተጋላጭ ወገኖች በኮቪድ19 በሽታ ለከፋ ህመምና ሞት ከመጋለጣቸው በተጨማሪ የተለያዩ የደምና ሌሎች የካንሰር ታማሚዎች የምርመራ ሂደታቸውና ሕክምናቸው ተቋርጦ በሽታቸው ስር ሲሰድ በወቅቱ ህክምና ማግኘት ሳይችሉና ሲመቱ፣ የኩላሊት ታማሚዎችና ጥሪታቸውን ሸጠው ህይወታቸውን በዳያሊስ ለማቆየት የሚታገሉ ወገኖች በተለይ ደግሞ በከፍተኛ ወጪ የመልካም ወገኖችና ቤተሰብ ውድ የሂወት ስጦታ ተደርጎላቸው የኩላሊት ንቅለ ተካላ ተሰርቶላቸው በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ የነበሩ ወገኖች በኮቪድ19 ተጠቅተው ከባድ የጤና ውስብስብ ውስጥ ሲገቡና ለሞት ሲዳረጉ ማየት የዕለት ተዕለት ክስተት እየሆነ ነው። እነኚህንና ሌሎች በኮቪድ19 ምክንያት እየደረሱ ያሉ ጉዳቶችን ከቀጥተኛ ተጠቂዎች እና የጤና ባለሞያዎች አንደበት ለሕብረተሰቡ በየወቅቱ ማቅረብ በተለይ በአሁኑ ወቅት ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዛመተ ባለበትና ሕብረተሰባችን የመከላከያ ጥንቃቄዎች ላይ ከፍተኛ ቸልተኝነት እያሳየ ባለበት ሁኔታ ከላይ የጠቀስኳቸውን መንገዶች መጠቀም አስተማሪ ሊሆን ይችላል እላለው ። እስቲ እናንተም ጨምሩበት።
ዛሬ የጤና ሚኒስቴርና ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። የመግለጫው አንኳር ሃሳብ እንዲህ አቅርበነዋል።

ካለፈው ሐምሌ እና ነሐሴ ወራት በላይ አሁን ላይ ወደ ፅኑ ሕሙማን የሚገቡ ታማሚዎች ብዛት እየጨመረ መጥቷል።

በኢትዮጵያ ያለውን የቫይረሱን ስርጭት ለማወቅ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደ የአንድ ወር አገር አቀፍ የምርመራ ዘመቻ ከ73 በመቶ በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መለየታቸው ተገልጿል።

1.4 በመቶ የሚሆኑት በሆስፒታል የሚገኙ ታማሚዎች በፅኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል።

በኢትዮጵያ ሁሉም ወረዳዎች ቢያንስ አንድ በኮቪድ የተያዘ ሰው ሪፖርት ተደርጓል።

በአሁኑ ወቅት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተይዘው የሚገኙ ሰዎች ውስጥ 63 በመቶው ምልክት የማያሳዩ ናቸው።

እስካሁን በኢትዮጵያ በቫይረሱ ከሚያዙት 57 በመቶ የሚሆኑት እድሜያቸው ከ15-34 ሲሆን ከሟቾች ውስጥ ደግሞ 51.9 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ ናቸው።

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተይዘው ለህልፈት የሚበቁ ሰዎች ምጣኔ 1.52 በመቶ ነው።

አሁን ላይ የምርመራ መጠን የቀነሰ ቢሆንም ቫይረሱ የሚገኝባቸው እና ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑም ተመልክቷል።

ባለፉት ሁለት ሳምንት ውስጥ እንደአገር ያለው የቫይረሱ ስርጭት 10 ነጥብ 4 በመቶ ደርሷል።

አዲስ አበባ ከተማ፣ ኦሮሚያ ፣ ትግራይ ፣ አማራ ፣ ደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች በቅደም ተከተል ከፍተኛ የቫይረሱ ተጠቂዎች የተገኙባቸው ናቸው።

ርቀትን ሳይጠብቁና ማስክ ሳያደርጉ አገልግሎት መቀበልም ሆነ መስጠት ለቫይረሱ ተጋላጭነትን ስለሚጨምር ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያድርግ ተብሏል።

በቫይረሱ የሞት ምጣኔ በኢትዮጵያ 1.52 በመቶ ፣ በአፍሪካ 2.4 በመቶ ፣ በዓለም ደግሞ 2.8 በመቶ መሆኑንም በመግለጫው ወቅት ተገልጿል።

በአጠቃላይ በኢትኦጵያ 89 ሺህ 860 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ፤ የ1,365 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 43,149 ከበሽታው አገግመዋል።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር የወጣውን መመሪያ ቁጥር 30/2013 መጣስ እስከ ሁለት አመት በሚደርስ እስራት ያስቀጣል
*******************
የኮቪድ -19 ወረርሽ በአለም ላይ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ በሰው ልጆች ላይ ዘርፈ ብዙ የሚባሉ ጉዳቶች ደርሰዋል፡፡ በሽታው ከሰው ወደ ሰው ተላላፊ በመሆኑ የአለም የጤና ድርጅት በሽታው የሚተላለፍባቸውን መንገዶች እና የወረርሽኙን መስፋፋት ለመቀነስ የሚያስችሉ የጥንቃቄ እርምጃዋችን በየጊዜው ሲያሳውቅ ቆይታል፡፡ ሀገራትም እንደየሀገራቸው ነባራዊ ሁኔታ የጥንቃቄ እርምጃዎችን የህግ ማዕቀፍ በመስጠት ሲተገብሩ ቆይተዋል እየተገበሩም ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያም የወረርሽኙን መስፋፋት ለመቀነስ ያስችል ዘንድ የአስቸካይ ጊዜ አዋጅ እና መመሪያዎችን በማውጣ ስትተገብር ቆይታለች፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተነሳ በኃላም በአሁኑ ወቅት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር የወጣ መመሪያ ቁጥር 30/2013 በተለያዩ አካላት ላይ ማለትም በግለሰቦች፣ በመንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና በድርጅቶች ላይ ክልከላዎችን እና ግዴታዎችን ጥሏል፡፡ በመመሪያው የተጣሉ ክልከላዎችን እና ግዴታዎችን ባለፉት ፕሮግራሞቻችን እንደተመለከትን የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዝግጅት ክልከላዎች መተላለፍ እና ግዴታዎችን አለመወጣት የሚያስከትለውን የወንጀል ተጠያቂነት እንመለከታለን፡፡
በመመሪያው የተቀመጡ ክልከላዎች እና ግዴታዎች ተላላፊ በሽታን ለመከላከል እና ለመግታት የተደነገጉ የጥንቃቄ እርምጃዎች አካል ሲሆኑ ክልከላዎቹን መተላለፍ እና ግዴታዎቹን አለመወጣት አግባብ ባለው የወንጀል ህግ እንደሚያስቀጣ በመመሪያው ተደንግጎ ይገኛል፡፡
ከኮቪድ -19 ወረርሽ የመተላለፍ ባህርይ አንፃር በመመሪያው ከተቀመጡ ክልከላዎች ለአብነት ያክል ለሰላምታና ሌላ ለማንኛውም አላማ በእጅ መጨባበጥ፣ ሆነ ብሎ የእርስ በእርስ አካላዊ ንክኪ ማድረግ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አለማድረግ፣ በክፍት ገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች ከሁለት የአዋቂ እርምጃ በታች ርቀት መቆምም ሆነ መቀመጥ፣ አገልግሎት ሰጪ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ሰራተኞች ከሁለት የአዋቂ እርምጃ በታች ተጠጋግተው እና የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ፣ ተገልጋዮች በሚቀመጡበት ጊዜም ይሁን በማንኛዉም አኳኋን አገልግሎት ሲያገኙ ከሁለት የአዋቂ እርምጃ በታች ተጠጋግተው እና የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ወይም በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዲቀመጡ ማድረግ ከክልከላዎቹ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ግዴታዎችን በተመለከተ ደግሞ የመንግስታዊ እና የግል ተቋማት አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ተቋሙ ለሚመጡ ተገልጋዮች ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ ለሰራተኞቻቸው የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን እና ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ፣ ለምሳሌ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በህግ በሚወሰነው የመጫን አቅም ልክ ሰዎችን የመጫን፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ያላደረጉ ሰዎችን አገልግሎት አለመስጠት፣ መስኮቶችን በመክፈት በተሽከርካሪው ውስጥ በቂ የአየር ዝውርውር እንዲኖር የማድረግ እና በዘርፉ በመመሪያ የሚወጡ ሌሎች መወሰድ የሚገባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች በመተግበር አገልግሎት የመስጠት ግዴታዎች ይገኙበታል፡፡
እነዚህ ከላይ ለአብነት ያክል የተጠቀሱትን እና ሌሎች በመመሪያው የተካተቱ ክልከላዎችን እና ግዴታዎችን የተላለፈ ማንኛውም ሰው አግባብነት ባለው የወንጀል ህግ አንቀጽ መሰረት የሚቀጣ መሆኑን መመሪያው አንቀፅ 30 ላይ ያስቀመጠ ሲሆን ለጉዳዩ አግባብነት ያለው የወንጀል ህግ በ1996 ዓ.ም የወጣው የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 522 ነው፡፡ ይህም ጤናን ለመጠበቅና ለመንከባብ በህግ የተደነገጉትን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መጣስ የሚያስከትለውን የእስራት እና የገንዘብ መቀጮ ይመለከታል፡፡
በዚህም መሰረት በወንጀል ህጉ አንቀፅ 522 ንዑስ አንቀፅ 1 ስር እንደተደነገገው ማንም ሰው ማለትም የተፈጥሮ ሰው ወይም በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ተላላፊ በሽታን ለመከላከል፣ ለመግታት ወይም ለማቆም በህግ የተደነገጉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን አስቦ የጣሰ እንደሆነ ከሁለት ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ይቀጣል፡፡ እንዲሁም ወንጀሉ የተፈፀመው በቸልተኝነት እንደሆነ ቅጣቱ ከስድስት ወር የማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም ከሦስት ሺህ ብር የማይበልጥ መቀጮ መሆኑን አንቀፅ 522/2 ይደነግጋል፡፡
ከወንጀል ድንጋጌዎቹ ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮችን መገንዘብ እንችላለን፡፡ አንደኛ ክልከላዎችን መተላለፍ ወይም ግዴታዎችን አለመወጣት የወንጀል ተጠያቂነት ለማስከተል ሆን ተብሎ (intentionally) ወይም በቸልተኝነት (negligently) ሊፈፀም እንደሚችል እና ድርጊቶቹ በተፈጥሮ ሰዎች ወይም በህግ ሰውነት በተሰጣቸው ማለትም በተቋማት እና በድርጅቶች ሊፈፀም የሚችሉ መሆኑን ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ጥሰቱን የፈፀመውን አካል እና የሀሳብ ክፍሉን (ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት) መሆኑን መሰረት በማድረግ የወንጀል ቅጣቱ የእስራት ወይም የገንዘብ መቀጮ ይሆናል ማለት ነው፡፡
በአጠቃላይ ህብረተሰቡ ወረርሽኑን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር መደረግ ያለባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን ያለመታከት በመተግበር ራሱን ብሎም ሌሎችን ከወረርሽኙ እና ከሚያስከትለው ጉዳት እንዲሁም በመመሪያው የተቀመጡ ክልከላዎች እና ግዴታዎችን መጣስ ከሚያስከትለው የወንጀል ተጠያቂነት መጠበቅ ይኖርበታል፡፡
(ምንጭ :ፌዴራል አቃቤ ሕግ )
ማስታወቂያ ለድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች

ኮሌጃችን በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ከዚህ በታች የተገለጹን የትምህርት ፕሮገራሞች በመደበኛ እና የቅዳሜ እና እሁድ ፕሮግራም ለ2013 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት የመመዝገቢያ መስፈርቶች እና ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን የምታሟሉ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡


1. ስልጠና የሚሰጥባቸው የትምህርት መስኮች፣
በ Masters in Medical Microbiology (Regular Programme /በመደበኛ ፕሮግራም)
በ General Master of Public Health (Weekend Programme/ የቅዳሜ እና እሁድ ፕሮግራም)
በ Master of Public Health in Epidemiology (Weekend Programme/የቅዳሜ እና እሁድ ፕሮግራም)
በ Master of Public Health in Public Health Nutrition (Weekend Programme/የቅዳሜ እና እሁድ ፕሮግራም)

2. የመመዝገቢያ መስፈርቶች፣
2.1 Masters in medical Microbiology:
እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም የመጀመሪያ ዲግሪ በ (Laboratory Technology, Medicine Veterinary Medicine and Biology) ያለው ወይም ያላት
2.2 Maters of Public Health (MPH)
እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም የመጀመሪያ ዲግሪ በ (Nutrition, Occupational health, Health officer, Nurse, Midwifery, Medical doctor, Environmental health professionals, Health education, Pharmacist, Anaesthesia and Medical laboratory technology). ያለው ወይም ያላት
ተጨማሪ ለሁለቱም ፕሮገራሞች የሚያስፈልጉ መስፈርሮች
ሀ፡ ከተመረቀ/ች በኃላ ቢያንስ ሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ላት/ እና ከሚሰሩበት መሰሪያ ቤት የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፣
ለ. ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ Official Transcript ማቅረብ የሚችል/የምትችል/፣
ሐ.ኮሌጅ የሚያዘጋጀውን የቃል /Interview/እና የፁሑፍ /written /ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል/፣
መ. በስፖንሰርሺኘ የሚማሩ ተማሪዎች የስፖንሰርሺኘ ደብዳቤ ከሚሰሩበት መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ ፣
ሠ. ሁለት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡-
 አንድ አሁን ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት እንዲሁም፡-
 አንድ ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ ከአስተማሪዎቻቸው የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
3. የመመዝገቢያ ቦታ፡-
በቅ/ጳ/ሆ/ሚ/ሜ/ኮሌጅ ሬጅስትራር (online registration at http://197.156.83.153/admissionpost/)
ማሳሰቢያ፡- ምዝገባው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ ከተነገረበት/ከወጣበት/ ቀን ጀምሮ 10/አሥር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲሆን በተጨማሪም የመመዝገቢያ የማይመለስ 200 ( ሁለት መቶ ብር) መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
• የ መግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ወደ ፊት በኮሌጁ ደረ-ገጽ ይገለፃል፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 0118 96 51 25
ወይም በኮሌጁ ድህረ ገጽ www.sphmmc.gov.et ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር በወጣ መመሪያ የተጣሉ ግዴታዎች
____________
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር የሚያግዝ መመሪያ ቁጥር 30/2013 ወጥቷል። ከመስከረም 25/2013 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ ውሏል፡፡

በዚህ መመሪያ በግለሰቦች እና በተቋማት ላይ የተለያዩ ግዴታዎች ተጥለዋል፡፡ እነዚህ ግዴታዎች ሁሉም በቅንነት ሊተገብራቸዉ የሚገቡ እና ወረርሺኙን ለመከላከል የሚረዱ ናቸዉ፡፡

በግለሰቦች ላይ የተጣሉ ግዴታዎች
------------------------
በመመሪያዉ አንቀፅ 5 ላይ ማንኛውም ኮቪድ 19 በሽታአለብኝ ብሎ እራሱን የሚጠረጥር ሰው ለሚመለከተው አካል ሪፖርት በማድረግ የመመርመርና ቫይረሱ ወደ ሌሎች እንዳይተላፍ አስፈላጊውን ጥንቃቄ የማድረግ ግዴታ ተጥሎበታል፡፡ በተጨማሪም በሽታው አለበት ተብሎ የሚጠረጠር ሰው ሰለመኖሩ የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ለጤና ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በአቅራቢያው ለሚገኙ የጤና ተቋም ወይም ባለሞያ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡

አገልግሎት ሰጪ በሆኑ የመንግስትና የግል ተቋም ላይ የተጣሉ ግዴታዎች
------------------------------------
ማንኛውም አገልግሎት የሚሰጥ የመንግስታዊ እና የግል ተቋም አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ተቋሙ ለሚመጡ ተገልጋዮች ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳሶችን የማቅረብ፣ ተገልጋዮች ሁለት የአዋቂ እርምጃ ተራርቀው የሚቆሙበትን ቦታ ምልክት የማድረግ እና ተገልጋዮች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን እና ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ በተጨማሪም ለሰራተኞች ስለበሽታው አስፈላጊውን መረጃ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማድረስ፣ በመግቢያና መውጫ በሮችና ሌሎች አስፈላጊ ቦታዎች በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ ነገሮችን የማዘጋጀት፣ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን እና ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው፡፡

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የተጣሉ ግዴታዎች
-------------------------------
ሀገር አቀፍም ሆነ የከተማ ውስጥ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሰው በህግ ከሚወሰነው የመጫን አቅም ልክ ሰዎችን የመጫን፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ያላደረጉ ሰዎችን አገልግሎት አለመስጠት፣ መስኮቶችን በመክፈት በተሽከርካሪው ውስጥ በቂ የአየር ዝውርውር እንዲኖር የማድረግ እና በዘርፉ በመመሪያ የሚወጡ ሌሎች መወሰድ የሚገባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች በመተግበር አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡

የኮንስትራክሽን አሰሪዎች ላይ የተጣሉ ግዴታዎች
----------------------------
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አሰሪዎች በግንባታ ሳይቶች ላይ አስፈላጊውን ንጽህና ለመጠበቅ የሚረዱ እንደ ውሃ፣ ሳሙና፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ፣ ሳኒታይዘር ወይንም አልኮል፣ የሙቀት መለኪያ መሳሪያ እንዲሁም የጸረ ተህዋሲያን ግብዓት የማቅረብ ወይንም የሟሟላት፣ ሰራተኞች በተቻለ መጠን ርቀታቸው ጠብቀው እንዲሰሩ የማድረግ፣ እንዲሁም በኮንስትራክሽን ዘርፍ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተጋላጭነትን ለመከላከል፣ ዝግጁነት ለማረጋገጥና ምላሽ አሰጣጥ ሁኔታን በተመለከተ በዘርፉ በመመሪያ የሚወሰኑ የጥንቃቄ እርምጃዎች የማክበር እና የማስከበር ግዴታዎች አለባቸው፡፡

የሆቴልና ቱሪዝም አሰሪዎች ላይ የተጣሉ ግዴታዎች
--------------------------
ማንኛውም በሆቴል፣ በአስጎብኚነት እና በሌሎችም የቱሪዝም መስክ የተሰማሩ ተቋማት በሰራተኞቻቸው እና ተገልጋዮቻቸው መካከል ሁለት የአዋቂ እርምጃ ወይም የሁለት ሜትር ርቀት እንዲኖር የማድረግ፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን የመቆጣጠር፣ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ ነገሮችን የማዘጋጀት፣ ለሰራተኞቻቸው የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ እንዲሁም የቱሪዝም አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ዘርፉ በመመሪያ የሚያስቀምጣቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።

የኢንዱስትሪ እና ምርት መስክ የተሰማሩ መንግስታዊ እና የግል ተቋማት ላይ የተጣሉ ግዴታዎች
-----------------------------
ለሰራተኞቻቸው ስለበሽታው አስፈላጊውን መረጃ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማድረስ፣ በመግቢያና መውጫ በሮችና ሌሎች አስፈላጊ ቦታዎች በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ ነገሮችን ማዘጋጀት፣ የስራ ቦታዎችን በቂ የአየር ዝውውር ሊኖርበት በሚችል መልኩ የማደራጀት፣የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ ሰራተኞች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን እና ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችንመተግበራቸውን የማረጋገጥ፣ እንዲሁም ሌሎች ዘርፉ በመመሪያ የሚያስቀምጣቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡

በሁሉም ዘርፍ ያሉ ተቋማት ላይ የተጣሉ ግዴታዎች
----------------------
ማናቸውም መንግስታዊም የሆነ የግል ተቋም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተጋላጭነትን ለመከላከል፣ ዝግጁነት ለማረጋገጥ እና ምላሽ አሰጣጥ ሁኔታን በተመለከተ በዘርፉ በመመሪያ የሚወሰኑ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር በወጣ መመሪያ የተጣሉ ግዴታዎች
____________
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር የሚያግዝ መመሪያ ቁጥር 30/2013 ወጥቷል። ከመስከረም 25/2013 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ ውሏል፡፡

በዚህ መመሪያ በግለሰቦች እና በተቋማት ላይ የተለያዩ ግዴታዎች ተጥለዋል፡፡ እነዚህ ግዴታዎች ሁሉም በቅንነት ሊተገብራቸዉ የሚገቡ እና ወረርሺኙን ለመከላከል የሚረዱ ናቸዉ፡፡

በግለሰቦች ላይ የተጣሉ ግዴታዎች
------------------------
በመመሪያዉ አንቀፅ 5 ላይ ማንኛውም ኮቪድ 19 በሽታአለብኝ ብሎ እራሱን የሚጠረጥር ሰው ለሚመለከተው አካል ሪፖርት በማድረግ የመመርመርና ቫይረሱ ወደ ሌሎች እንዳይተላፍ አስፈላጊውን ጥንቃቄ የማድረግ ግዴታ ተጥሎበታል፡፡ በተጨማሪም በሽታው አለበት ተብሎ የሚጠረጠር ሰው ሰለመኖሩ የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ለጤና ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በአቅራቢያው ለሚገኙ የጤና ተቋም ወይም ባለሞያ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡

አገልግሎት ሰጪ በሆኑ የመንግስትና የግል ተቋም ላይ የተጣሉ ግዴታዎች
------------------------------------
ማንኛውም አገልግሎት የሚሰጥ የመንግስታዊ እና የግል ተቋም አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ተቋሙ ለሚመጡ ተገልጋዮች ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳሶችን የማቅረብ፣ ተገልጋዮች ሁለት የአዋቂ እርምጃ ተራርቀው የሚቆሙበትን ቦታ ምልክት የማድረግ እና ተገልጋዮች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን እና ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ በተጨማሪም ለሰራተኞች ስለበሽታው አስፈላጊውን መረጃ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማድረስ፣ በመግቢያና መውጫ በሮችና ሌሎች አስፈላጊ ቦታዎች በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ ነገሮችን የማዘጋጀት፣ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን እና ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው፡፡

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ