St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
#በጣም_አሳሳቢ
ያዕቆብ ሰማን
(በጤና ሚኒሰቴር የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር)
ኮቪድ የማህበረሰባችን ከፍተኛ የህልውና አደጋ መሆኑን ሁላችንም መረዳት ይኖርብናል፡፡

ከመቶ ሚሊየን በላይ የአለማችን ህዝብ አጥቅቶ ከሁለት ሚሊየን በላይ ሰዎች ገድሎ የአለም ስጋት እንደሆነ ቀጥሎዋል፡፡
በሀገራችንም እስካሁን ከሁለት ሚሊየን በላይ ሰዎች መርምረን 154,257 ሰዎች በበሽታው ተጠቅተው 2,305 ሰዎች ህይወታቸው አጥተውበት አሁንም በየቀኑ በጣም አሰፈላጊ የሆኑ ሰዎች እያጣን ቤተሰብ እየተበተነ ይገኛል፡፡

ፊት ለፊት ሆነን የዚህን በሽታ ስርጭት እንዳይስፋፋ እና ሰዎች የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ የምንሰራ ሰዎች እያጋጠመን ያለው ችግር እና በየቀኑ የምናሳልፈው በጣም አሳዛኝ ገጠመኞች ይህ በሽታ ምን ያክል ማህበረሰባችን እየጎዳ እንደሆነ በቃላት መግለጽ ይከብዳል፡፡

አሁንም በጣም ቀላል የሆኑትን መከላከያ መንገዶች በመተግበር ብዙ ህይወቶች ማትረፍ እንችላለን፡፡
- የአፍ እና የአፈንጫ መሸፈኛ ጭምብል ሁልጊዜ በሁሉ ቦታ ማድረግ
- የእጅ ንጽህና በአግባቡ መጠበቅ
- አላስፈላጊ መሰባሰቦች ማስወገድ
- ግዴታ ካለሆነ በስተቀር እቤት መቆየት
መስፈርቱን አሟልተው የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ የሚሰጡ የግል ተቋማት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው።
ልብ ይበሉ!
https://t.me/spmmc
https://www.facebook.com/sphmmc
Prof. Senait Fisseha, director of International Programs at The Susan Thompson Buffett Foundation, Visited SPHMMC, whose constructions is well underway incorporating a hospital to treat cancer, cardiac and Gastroenterology (GI) Center for Digestive Diseases and reproductive health training Institute. She also appreciated the Colleges efforts to be a health institution for all Ethiopians via building its capacity.
Professor Senait also expressed her organization’s readiness to work with the college.
Prof. Senait Fisseha is a globally recognized leader in reproductive health and Clinical Professor of Obstetrics and Gynecology, University of Michigan Medical School
Notice
To All accepted MPH applicants
This is to inform you that first-semester registration will be between March 8 and March 10,21. And orientation will be on March 14,21 the morning.
For further information please contact the registrar.
አድዋ ሊወረን ከመጣ ጠላት ድል የነሳንበት የሁላችንም ታሪክ ነው!
ዛሬስ ጠላታችን ማን ነው፤ኮቪድ-19 ትውልድን ሊነጥቀን የመጣ ጠላት ነው!!
Some 200 patients have been provided with ear and hearing screening in Lideta Health center in connection with the celebration of the International Day for Hearing .

The Service was provided by ENT department staff of the SPHMMC and EHC(Ear and Hearing care) project . Those who have been verified to have hearing problem are referred to the college and get additional treatment.

We are really immensely thankful for the ENT staff members and EHC project..
በትናትናው ዕለት የሕሙማን መስተንግዶ (ራነር) ሠራተኛ የነበረችውን እህታችንን ገነት ተስፋዬን በሞት አጥተናል።

ገነት በኮቪድ ምክንያት በጽኑ ሕክምና ክትትል እየተደረገላት ነበር። የቀብር ሥነሥርዓት ዛሬ ከቀኑ 6:00 በሸጎሌ ኪዳነ ምሕረት ይፈጸማል።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅም ለቤተሰቦቿ መጽናናትን ይመኛል።
2.2 million #COVID19 vaccine doses from #COVAX have just arrived in Addis Ababa, Ethiopia.

A step towards increasing equal access to vaccines! #VaccinEquity
እንደምን አደራችሁ የገጻችን ተከታታዮችና የኮሌጃችን ወዳጆች! ያማረ ቀን ይሁንላችሁ!

በማኀበራዊ ገጾቻችን የጤና መረጃዎችን ወደ እናንተ በየእለቱ እናደርሳለን። ዛሬ የዓለም የኩላሊት ጤና ቀን ነው። የዓለም የግለኮማ ሣምንት ደግሞ ካለፈው እሁድ ጀምሮ በመላው ዓለም በግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

ዛሬ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ ብቅ ብትሉ የግላኮማና የኩላሊት ምርመራ በነጻ እናደርግላችኋለን ። እንዲሁም የደም ግፊት እና የስኳር መጠን እንለካለን።

መልካም ቀን።

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/SPMMC

በምስል የሚገኙ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የኢንስታግራም ገፃችንን ይከተሉ
https://www.instagram.com/st_pauls_hospital_mmc /
#የዛሬ_እውነታዎች (መጋቢት 2/March 11)

የኮቪድ ነገር እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው:: ዛሬ በተደረገው ምርመራ እንደ ሀገር በሽታው የመገኘት ምጣኔ 19% ሲሆን
በሽታው የመግኘት ዕድል በጣም ከፍተኛ የሆነበቸው አራት ከተሞች
1. ሐዋሳ - 42%
2. ድሬዳዋ - 27%
3. አሶሳ - 23.5%
4. አዲስ አበባ - 20%
ሁሉንም (17) ሞቶች ከአዲስ አበባ ናቸው::

እነዚህ ቁጥሮች በዓለም ጤና ድርጅት መመዘኛ ወደ complete shoutdown የሚወስዱ እና እጅግ ከፍተኛ የጥንቃቄ እርምጃ የሚያስፈልጋቸው ናቸው::

አሁንም
1. የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ መጠቀም
2. የእጅ ንፅህና መጠበቅ
3. አላስፈላጊ መሰባሰብ መተው
4. ርቀትን ጠብቆ መንቀሳቀስ

ምንጭ
ያዕቆብ ሰማን
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር
ጤና ሚኒስቴር
ኮቪድ-19 አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ነው ።
************************
በኢትዮጵያ ቫይረሱ የመሰራጨት አቅሙን ጨምሯል። አስጊ በሆነ ደረጃ በ12.80% በኮቪድ-19 የመያዝ ምጣኔ ደርሷል።

የትላንት ሁኔታ

በትላንትናው እለት መጋቢት 01/2013 በኢትዮጵያ 7,819 ግለሰቦች የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ አድርገዋል። ከእነዚህም ውስጥ 1,543 ግለሰቦች የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ይህ ማለት ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች 20 ያህሉ ወይም 20% የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበው በነሐሴ/2012 በማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ (COMBAT) ወቅት ብቻ ነው፡፡

የጽኑ ህሙማን ታማሚዎች

ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ግለሰቦች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት ጨምሯል። እስከ ትላንትናው እለት ድረስ ብቻ 438 ግለሰቦች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ኮቪድ-19 ወደ ኢትዮጵያ ከገባ እለት ጀምሮ ይሄ ቁጥር ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የ2‚446 ግለሰቦች ህይወታቸውን አጥተዋል። በትላንትናው እለት ብቻ 15 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በከተሞች ያለው ስርጭት

አዲስ አበባን ጨምሮ በትላንትናው ዕለት ብቻ ከፍተኛ ቁጥር ተመዘግቧል። በአዲስ አበባ 6,392 ግለሰቦች ናሙና የሰጡ ሲሆን 1,269 ግለሰቦች ወይም 20% ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ፤በሲዳማ 91 ግለሰቦች ናሙና የሰጡ ሲሆን 35 ግለሰቦች ወይም 38% ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፤ በድሬደዋ 48 ግለሰቦች ናሙና የሰጡ ሲሆን 16 ግለሰቦች ወይም 33% በቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ፤ በኦሮሚያ ክልል 511 ግለሰቦች ናሙና የሰጡ ሲሆን 149 ግለሰቦች ወይም 29% ያህሉ የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል ፤ በቤንሻንጉል ጉምዝ 43
ዛሬ በኮቪድ-19 ቫይረስ ከፍተኛውን
የሞት ቁጥር ተመዘገበ ።

t.me/spmmc
በዛሬው እለት 27 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ቫይረስ ህይወታቸውን አጥተዋል። እንደዚህ አይነት ከፍተኛ የሞት ቁጥር የተመዘገበው ከአስከሬን ላይ ናሙና ተወስዶ በተመረመረበት ወቅት ነበር።

እስከ ዛሬ ድረስ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ 2,510 ግለሰቦች ህይወታቸውን አጥተዋል። እስከ ዛሬው እለት 454 ግለሰቦች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ ።ይህም ቁጥር ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል።

መዘናጋቱ ይቅር። የኮቪድ መከላከያ መንገዶችን ካለመሠልቸት እንተግብር።

መረጃ: ኢ.ሕ.ጤ.ኢ
You can lower your risk of kidney disease by:
✅ Being physically active
✅ Eating a healthy diet
✅ Having your blood pressure under control
✅ Controlling your diabetes
1. የአዕምሮ ጤና ምንድነዉ?
********************
ስለ አዕምሮ ጤና ከማዉራታችን በፊት ጤና ምንድነዉ የሚለዉን ማየቱ መልካም ነዉ። ጤና (Health) ለሚለዉ ቃል ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል መልስ እስካሁን አልተገኘም። ነገር ግን እንደ አለም ጤና ድርጅት አተረጓጎም ፡- ጤናን “የበሽታ አለመኖር ሳይሆን የተሟላ አካላዊ፣ አዕምሯዊና ማህበራዊ ደህንነት ነዉ” በማለት የሶስቱ ፈርጆች ጤናማነት ሲሟላ የሚመጣ ሁኔታ አድርጎ ይወስደዋል።

ወደ አዕምሯዊ ጤና ስንመጣ የአንድን ሰዉ አስተሳሰብ፣ ስሜትና ድርጊት ይገልጻል። አዕምሯዊ ጤና ስሜታዊና አዕምሯዊ ደህንነት ሲሆን እያንዳንዱ ግለሰብ የማገናዘብ አቅሙንና ስሜታዊ ችሎታዉን ተጠቅሞ በማህበረተሰቡ ዉስጥ ግዴታዉን በመወጣት የዕለት ተለት የኑሮ ፍላጎቱን መሟላት መቻል ነዉ።

አዕምሯዊ ጤና ሰዎች አቅማቸዉ እና መክሊታቸዉን የመጠቀም እና ከችሎታቸዉ ከፍታ የመድረስ ብቃት ነዉ። በስራ ዉጤታማ መሆንና ለማህበረተሰቡ አስፈላጊዉን አስተዋጽኦ ማበርከት መቻል አዕምሯዊ ጤናቸዉ የተስተካከለ ሰዎች መገለጫ ጠባይ ነዉ።
አዕምሯዊ ጤና ባጠቃላይ ከአሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ስሜቶቻችን ጋር የጠበቀ ቁርኝነት አለዉ። የአዕምሯዊ ጤና ባለቤት ልንሆን የምንችለዉ ከራሳችንም ሆነ ከሌሎች ጋር ስንታረቅና ፍሬያማ ግኑኝነት መፍጠር ስንችል ነዉ። ከራስ ጋር ለመታረቅ አስቀድሞ ራስን በማወቅ ከአሉታዊ ስሜቶች (መናደድ፣ ማዘን፣ መፍራት፣ ጥላቻ፣ ተንኮል፣ ምቀኝነት፣ ቅናት፣ ቂም እና ተጠራጣሪነት) በመራቅ ወደ ሳቢ ስሜቶች (ፍቅር፣ ደስታ፣ አድናቆት፣ ሩህሩህነት፣ ጉጉነት፣ ፈጠራና የማወቅ ፍላጎት) መሳብ መቻል ከሌሎች ጋር ለምንመሰርተዉ የሰመረ ግኑኝነት ጠንካራ መሰረት ይጥላል።

አዕምሯዊ ጤና የሰመረ መሆኑ መገለጫዎች መካከል፡-
👉በራስ መተማመን
👉በመጥፎ ልማዶች ያለመዉደቅ እናም ራስን በማየት መታረም
👉ያለመሰላቸት
👉በየጊዜዉ አዲስን ነገር ለመማር ዝግጁ መሆን
👉ስለ ህይወት ትርጉም ያለዉ እንደሆነና፣ የተስተካከለ እና ቀና አመለካከት መኖር
👉አሉታዊ ስሜቶችን እና ዉጥረትን መቆጣጠር መቻል
👉መረጃዎችን አቀናብሮ መጠቀም መቻል
👉ለራስ እንደሚያስቡ ለሌሎችም ግድ ማለት መቻል
👉ችግርን መፍታት መሞከር ካልሆነም ለሌሎች ማካፈል እና አስፈላጊ ሲሆን ትብብር መጠየቅ መቻል
👉ራስን በበጎ አኳኋን መመዘን፣ ማሻሻል እና ማሳደግ መቻል
👉ራስን መምራት መቻል
👉በራስ መወሰን መቻል
እነዚህን ባህርያት መላበስ ከህይወታችን አሰራር ጋር የጠበቀ ዝምድና አላቸዉ። በመሆኑም በህመም ላለመጠቃት ብርታትም ጭምር ናቸዉ።
ባጠቃላይ፤ ዉጤታማነትና ስኬት የአዕምሮ ጤንነት ዋና ማሳያዎች ናቸዉ። ዘና ማለት፣ እችላለሁ ባይነት፣ የተወዳዳሪነት ስሜት፣ ጭንቀትን መቆጣጠር መቻልና ከመጥፎ ሁኔታ በቶሎ ማገገም መቻል አዕምሮ ጤንነት ትሩፋቶች ናቸዉ።
በሚቀጥለዉ ጽሁፍ የአዕምሮ ህመም ምንነት እስክንገናኝ መልካም ጊዜ።


ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር ያድርጉ።


ዶ.ር አስራት ሀ/ጊዮርጊስ
የአዕምሮ ህክምና ስፔሺያሊስት