St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
You can lower your risk of kidney disease by:
✅ Being physically active
✅ Eating a healthy diet
✅ Having your blood pressure under control
✅ Controlling your diabetes
1. የአዕምሮ ጤና ምንድነዉ?
********************
ስለ አዕምሮ ጤና ከማዉራታችን በፊት ጤና ምንድነዉ የሚለዉን ማየቱ መልካም ነዉ። ጤና (Health) ለሚለዉ ቃል ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል መልስ እስካሁን አልተገኘም። ነገር ግን እንደ አለም ጤና ድርጅት አተረጓጎም ፡- ጤናን “የበሽታ አለመኖር ሳይሆን የተሟላ አካላዊ፣ አዕምሯዊና ማህበራዊ ደህንነት ነዉ” በማለት የሶስቱ ፈርጆች ጤናማነት ሲሟላ የሚመጣ ሁኔታ አድርጎ ይወስደዋል።

ወደ አዕምሯዊ ጤና ስንመጣ የአንድን ሰዉ አስተሳሰብ፣ ስሜትና ድርጊት ይገልጻል። አዕምሯዊ ጤና ስሜታዊና አዕምሯዊ ደህንነት ሲሆን እያንዳንዱ ግለሰብ የማገናዘብ አቅሙንና ስሜታዊ ችሎታዉን ተጠቅሞ በማህበረተሰቡ ዉስጥ ግዴታዉን በመወጣት የዕለት ተለት የኑሮ ፍላጎቱን መሟላት መቻል ነዉ።

አዕምሯዊ ጤና ሰዎች አቅማቸዉ እና መክሊታቸዉን የመጠቀም እና ከችሎታቸዉ ከፍታ የመድረስ ብቃት ነዉ። በስራ ዉጤታማ መሆንና ለማህበረተሰቡ አስፈላጊዉን አስተዋጽኦ ማበርከት መቻል አዕምሯዊ ጤናቸዉ የተስተካከለ ሰዎች መገለጫ ጠባይ ነዉ።
አዕምሯዊ ጤና ባጠቃላይ ከአሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ስሜቶቻችን ጋር የጠበቀ ቁርኝነት አለዉ። የአዕምሯዊ ጤና ባለቤት ልንሆን የምንችለዉ ከራሳችንም ሆነ ከሌሎች ጋር ስንታረቅና ፍሬያማ ግኑኝነት መፍጠር ስንችል ነዉ። ከራስ ጋር ለመታረቅ አስቀድሞ ራስን በማወቅ ከአሉታዊ ስሜቶች (መናደድ፣ ማዘን፣ መፍራት፣ ጥላቻ፣ ተንኮል፣ ምቀኝነት፣ ቅናት፣ ቂም እና ተጠራጣሪነት) በመራቅ ወደ ሳቢ ስሜቶች (ፍቅር፣ ደስታ፣ አድናቆት፣ ሩህሩህነት፣ ጉጉነት፣ ፈጠራና የማወቅ ፍላጎት) መሳብ መቻል ከሌሎች ጋር ለምንመሰርተዉ የሰመረ ግኑኝነት ጠንካራ መሰረት ይጥላል።

አዕምሯዊ ጤና የሰመረ መሆኑ መገለጫዎች መካከል፡-
👉በራስ መተማመን
👉በመጥፎ ልማዶች ያለመዉደቅ እናም ራስን በማየት መታረም
👉ያለመሰላቸት
👉በየጊዜዉ አዲስን ነገር ለመማር ዝግጁ መሆን
👉ስለ ህይወት ትርጉም ያለዉ እንደሆነና፣ የተስተካከለ እና ቀና አመለካከት መኖር
👉አሉታዊ ስሜቶችን እና ዉጥረትን መቆጣጠር መቻል
👉መረጃዎችን አቀናብሮ መጠቀም መቻል
👉ለራስ እንደሚያስቡ ለሌሎችም ግድ ማለት መቻል
👉ችግርን መፍታት መሞከር ካልሆነም ለሌሎች ማካፈል እና አስፈላጊ ሲሆን ትብብር መጠየቅ መቻል
👉ራስን በበጎ አኳኋን መመዘን፣ ማሻሻል እና ማሳደግ መቻል
👉ራስን መምራት መቻል
👉በራስ መወሰን መቻል
እነዚህን ባህርያት መላበስ ከህይወታችን አሰራር ጋር የጠበቀ ዝምድና አላቸዉ። በመሆኑም በህመም ላለመጠቃት ብርታትም ጭምር ናቸዉ።
ባጠቃላይ፤ ዉጤታማነትና ስኬት የአዕምሮ ጤንነት ዋና ማሳያዎች ናቸዉ። ዘና ማለት፣ እችላለሁ ባይነት፣ የተወዳዳሪነት ስሜት፣ ጭንቀትን መቆጣጠር መቻልና ከመጥፎ ሁኔታ በቶሎ ማገገም መቻል አዕምሮ ጤንነት ትሩፋቶች ናቸዉ።
በሚቀጥለዉ ጽሁፍ የአዕምሮ ህመም ምንነት እስክንገናኝ መልካም ጊዜ።


ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር ያድርጉ።


ዶ.ር አስራት ሀ/ጊዮርጊስ
የአዕምሮ ህክምና ስፔሺያሊስት
በአዲስ አበባ እፎይታ ጤና ጣቢያ የኮቪድ-19 ክትባት በይፋ ተጀመረ ።

በዚህ መርሐግብር ላይ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ በጤና ጣቢያው በመገኘት የኮቪድ-19 ክትባት ወስደዋል።


የኮቪድ-19 ክትባት በዛሬው ዕለት በከተማዋ በሁሉም ጤና ተቋማት ለሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች እንዲሁም በእድሜ ጭምር ለበሽታው አጋላጭ በሆነ የጤና ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሰጥ ዶር ዮሐንስ ተናግረዋል ።

ክትባቱ ቅድሚያ ለጤና ባለሞያዎች ይሰጣል ፤ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸውንና እድሜያቸው የገፉ ሰዎች ደግሞ ከጤና ባለሞያዎች ቀጥሎ ክትባቱ እንደሚሰጣቸው ኃላፊው ገልጸዋል።

በተመሣሣይ መልኩ በክልል ከተሞችም በዛሬው ቀን የኮቪድ ክትባት ተጀምሯል ።
Dr. Tenaye Desalegn is the first person to be vaccinated from #COVID19 in Ethiopia.
እንደምን አደራችሁ የገጻቸን ተከታታዮች!
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ የፌስ ቡክ ገጻችን የተለያዩ የጤና መረጃዎችን ወደ እናንተ ማድረሱን ቀጥሏል።

የከቪድ ወርረሽኝ አሁንም እጅግ አሳሳቢ የጤና ችግር መሆኑ ቀጥሏል። በትናትናው ዕለት ብቻ ሞት 27 ተመዝግቧል ።
በትናትናው ዕለት የወጣው መረጃ መሠረትም

እንደ ሀገር በሽታው የመገኘት ምጣኔ 19.5% ሲሆን
በሽታው የመግኘት ዕድል በጣም ከፍተኛ የሆነባቸው አራት ከተሞች
1. ባህርዳር - 38%

2. ሐዋሳ - 33%
3. አዲስ አበባ - 20%
4. ድሬዳዋ - 17% ናቸው።
ሞት አጠቃላይ 27 ሲሆን-13 ከአዲስ አበባ ÷2 ከ አማራ÷4 ከደቡብ ሕዝቦች ÷ 2 ከሐረር እና 6 ከኦሮሚያ ተመዝግቧል ።

ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሕሙማን ቁጥርም እየጨመረ ነው። ከትላንትና በስቲያ ብቻ 454 ግለሰቦች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ኮቪድ-19 ወደ ኢትዮጵያ ከገባ እለት ጀምሮ ይሄ ቁጥር ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ወደ ኮቪድ- 19 የህክምና ማዕከል ከሚገቡት 100 ሕሙማን መካከል 61 የሚሆኑት በተለያየ መጠን ኦክስጅን የሚያስፈልጋቸው ናቸው። በትናትናው ዕለት ብቻ 7 ያህል ግለሰቦች ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ መጠቀም ÷የእጅ ንፅህና መጠበቅ:÷ አላስፈላጊ መሠባሰብን ማስወገድ እና ርቀትን መጠበቅን ምንጊዜም አንርሳ።

እሁንም መከላከያ መንገዶችን ያለመሠልቸት እንተገብር።

መልካም እሑድ ! መልካም የዕረፍት ቀን! ጤና ሁኑልን!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የእንቅርት ሕመምና የሕክምናው ሂደት-ከዶር ይስሐቅ ገሠር።
#የዛሬ_መጋቢት5_ሁኔታ
24% national positivity rate.The higest so far!
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአራት ሰው አንድ ሰው በኮቪድ ተይዞዋል ወይም ኮቪድ ሊኖርበት ይችላል እንደማለት ነው::

ከ20% በላይ የበሽታው ስርጭት የሚታይባቸው ክልሎች
1. ሲዳማ-39%
2. ኦሮሚያ-38%
3. ድሬዳዋ-25%
4. ሐረር-25%
5. አዲስ አበባ-24%

እነዚህ ቁጥሮች ምን ማለት እንደሆኑ አለመገንዘብ በእራስ እና በሀገር ላይ ሞት እንደማወጅ ይቆጠራል::

ያዕቆብ ሰማን
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር
ጤና ሚኒስቴር
ኮቪድ -19 ወርሽኝ በእጅጉ አሳሳቢ ሆኗል። መጠንቀቅ ይበጃል።
የሰሞኑ ስታስቲካዊ መረጃ

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ባሳለፍነው 7 ቀናት
(ከየካቲት29 – መጋቢት 05/2013)

* ከ 49‚326 ምርመራዎች 9,329 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፡፡ (ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች በአማካኝ 19 ሰዎች የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል ማለት ነው።)

* ካለፉት ሳምንታት ጋር ሲነጻጸር በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በ32% ጨምሯል።

* 121 ግለሰቦች ህይወታቸውን አጥተዋል።( ካለፉት ሳምንታት ጋር ሲነጻጸር ህይወታቸውን ያጡ በ89% ጨምሯል፡፡)

* በኮቪድ-19 ሳቢያ በትላንትናው እለት ብቻ 467 ሰው በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ወደ ኮቪድ- 19 የህክምና ማዕከላት ከሚገቡት 100 ግለሰቦች 69 ያህሉ በተለያየ መጠን ኦክስጅን የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡

(ከየካቲት29 – መጋቢት 04/2013)
የኮቪድ-19 ምርመራ ካደረጉት መካከል የተመረመሩበትን ምክንያት እና የመያዝ ምጣኔ ፤

*1‚989 (4%) ግለሰቦች ናሙና ሲሰጡ ከእነዚህም ውስጥ 393 ግለሰቦች ወይም 19.7% ወደ ጤና ተቋማት በተለያዩ ምክንያት የሄዱ

* 20‚746 (42.1%)ግለሰቦች ናሙና ሲሰጡ ከእነዚህም ውስጥ 5‚965 ግለሰቦች ወይም 28.7% በማህበረሰብ ቀኝት እና ዳሰሳ (community surveillance)

*4‚667 (9.5%) ግለሰቦች ናሙና ሲሰጡ ከእነዚህም ውስጥ 1‚204 ግለሰቦች ወይም 25.7% ከ ኮቪድ-19 ታማሚ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው

*15‚768 (31.9%) ግለሰቦች ናሙና ሲሰጡ ከእነዚህም ውስጥ 1‚736 ግለሰቦች ወይም 11% ወደ ውጭ ሀገር ለመሄድ የኮቪድ -19 ናሙና ምርመራ ያደረጉ፤ቫይረሱ የተገኝባቸው እና የመያዝ ምጣኔ ነው፡፡

6‚156 (12.5%) ነፃ መሆናቸውን ለማወቅ በድጋሚ የላብራቶሪ ምርመራ ያደረጉ ግለሰቦች ይገኙበታል፡፡

ይህ የሚያሳየው የኮቪድ-19 በማህበረሰብ ደረጃ በከፍተኛ የመዛመት ደረጃ ላይ እንዳለ ነው፡፡

እባካችሁ ምንግዜም የሚከተሉትን እናድርግ:-
1. የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ መጠቀም
2. የእጅ ንፅህና መጠበቅ
3. አላስፈላጊ መሰባሰብ መተው
4. ርቀትን ጠብቆ መንቀሳቀስ



ይህ የሚያሳየው የኮቪድ-19 በማህበረሰብ ደረጃ በከፍተኛ የመዛመት ደረጃ ላይ እንዳለ ነው፡፡

ምንጭ: ኢ.ሕ.ጤ.ኢ
#የዛሬ_መጋቢት6_ሰኞሁኔታ

አጅግ_አሳሳቢ !
20% national positivity rate. በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአምስት ሰው አንድ ሰው በኮቪድ ተይዞዋል ወይም ኮቪድ ሊኖርበት ይችላል እንደማለት ነው::

ከ20% በላይ የበሽታው ስርጭት የታየባቸው ክልሎች
1. ሲዳማ-55%
2. ቤንሻንጉል-73%
3. ድሬዳዋ-31%
4. አዲስ አበባ-22%

በፍጥነት የመከላከያ መንገዶች ትግበራ ወደ አስገዳጅነት እንዲገባ ካላደረግን የከፋ ጊዜ ሊመጣ እንደሚችል ከእነዚህ ቁጥሮች በላይ ምስክር የለም::

ሁላችንም የበሽታውን ስርጭት በመግታት ሕይወት እናድን::

ያዕቆብ ሰማን
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር
ጤና ሚኒስቴር
የጤና ሚኒስትርዋ ዶር ሊያ ታደሰ ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የመግለጫው አበይት ጉዳዩች እጥርጥር እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

 ስርጭቱ ባለፉት ወራት በተለይም ባለፉት ሳምንታት እጅግ ጨምሯል፡፡
 በመቶኛ ከ10 በታች የነበረው በቫይረሱ የሚያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር በአማካይ 17 በመቶ ወይም ከመቶው 17 ሰው አሻቅቧል፡፡
 እስካሳለፍነው ቅዳሜ ብቻ በነበሩ 10 ቀናት ከ12 ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ የ149 ሰዎች ህይወትም አልፏል፡፡ (የሞት ምጣኔው ቀደም ባለው ሳምንት 123 ነበር፡፡)
 የጽኑ ታማሚዎች ቁጥርም በነዚሁ ቀናት ለመጀመሪያ ጊዜ ከ450 በልጧል፡፡
 የጽኑ ህሙማን ክፍሎች ሞልተዋል፡፡ የመተንፈሻ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር) በህሙማን በሙሉ ተይዘዋል፡፡ የኦክስጅን እጥረትም አጋጥሟል፡፡
 የአስትራ ዜኔካ ክትባት መስጠት ይቀጥላል፡፡
 የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከቁጥጥር ውጭ ከመሆኑ በፊት ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት አለበት፡፡
 በትራንስፖርት አካባቢ ጥብቅ ቁጥጥር መደረግ አለበት ፡፡
 የእምነት ተቋማትም ኃላፊነቱን ወስደው ህዝቡን ከወረርሽኙ ሊታደጉ ይገባል፡፡

t.me/spmmc
College offers Media training
St. Paul Hospital Millennium Medical College in collaboration with Light for the World Ethiopia office organized a media training aiming at helping journalists drawn from government and private media houses raise their awareness on Glaucoma and foster their reporting work about the disease taking advantage of the world Glaucoma week. The training is significantly useful in equipping media professionals about the concepts and important inputs to well enrich their reporting on how to prevent Glaucoma and eye care.
#glaucomaweek #Glaucoma #glaucomaweek #GlaucomaAwarenessWeek
አሁንም ትኩረት ይሻል!!!
***********************************
ጽኑ ሕሙማን ክፍል ገብተው የሚታከሙ የኮቪድ 19 ታካሚዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።
***********************************
በዛሬው እለት ብቻ 8 ያህል ግለሰቦች ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

እስከ ትላንትናው ዕለት 531 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ቫይረስ ተይዘው በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ይህ ቁጥር ኮቪድ-19 ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጊዜ ጀምሮ የመጀመሪያው ከፍተኛ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።ከእነዚህም ውስጥ 66 ግለሰቦች በአርቴፊሻል ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡

እስከ ትላንትናው እለት ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የገቡ፤በፅኑ ህክምና ማዕከል ድጋፍ ሲደረግላቸው ከነበሩት ግለሰቦችውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያስመዘገቡት ክልሎችን የሚከተሉት ናቸው ።
*በአዲስ አበባ 409
* በኦሮሚያ ክልል 57
*በሲዳማ ክልል 33 ግለሰቦች ወደ ፅኑ ህሙማን መርጃ ክፍል የገቡ እና በፅኑ ህክምና ማዕከል ድጋፍ ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው፡፡

በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የሚገኙ ታማሚዎች በባለፈው ወር በአማካኝ 260 ነበር። አሁን በእጥፍ ጨምሯል፡፡
በአሁኑ ወቅት የህክምና ማዕከላት ከፍተኛ የሆነ የአልጋ፤አርቴፊሻል ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ እና ኦክስጂን እጥረት አጋጥሟቸዋል ፡፡

የኮቪድ-19 ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በተለይም ሳንባን የሚያጠቃ ሲሆን በበሽታው ክፉኛ ለተያዙ ፅኑ ህሙማን አርቴፊሻል ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ እና ኦክስጂን ህይወታቸውን ለመታደግ ለሚደረገው ጥረት በእጅጉ አስፈላጊ ናቸው።

አሁንም
1. የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ መጠቀም
2. የእጅ ንፅህና መጠበቅ
3. አላስፈላጊ መሰባሰብ መተው
4. ርቀትን ጠብቆ መንቀሳቀስ
Dr Tigist Luleseged’s research article entitled "Laboratory biomarkers of COVID-19 Pandemic severity and outcome: Findings from a developing country" is Published in the international journal - PLOS ONE. Her peer-reviewed article has been based on admitted patients to the millennium COVID -19 Care centre.
Dr Tigist is currently working as a Research development officer at SPHMMC.)
Please click the link below to find the article.
https://journals.plos.org/plosone/article?id=10.1371%2Fjournal.pone.0246087&fbclid=IwAR1LOLczqyJ62xEKkT6xjYtCUkN20AGOSqBrn8X50X_qMIPJ5389Sa1kI4Y
#የዛሬ_መጋቢት8_ሁኔታ_ምን_ይመስላል? ( በአጭሩ )

- 597 ከፍተኛ ክትትል እና ፅኑ ሕክምና የሚፈልጉ ወገኖች - - - 23% ሀገር አቀፍ በበሽታ የመያዝ ምጣኔ--
- 19 ሰዎች ሕይወታቸው ያጡ ዜጎች--

በዛሬው ቀን ከተመረመሩት ዉስጥ ከፍተኛ የበሽታ ስርጭት የታየባቸው ክልሎች
1. ሲዳማ-42%
3. ድሬዳዋ-65%
4. አዲስ አበባ-24%

በጽኑ የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር እጅግ ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች ከፍተኛ የሆነ #የኦክስጅን እጥረት አጋጥሟል::

በፍጥነት የመከላከያ መንገዶች ትግበራ ወደ አስገዳጅነት እንዲገባ ካላደረግን እና ሁላችንም በሚገባ ካልተጠነቀቅን የከፋ ጊዜ ሊመጣ እንደሚችል ከእነዚህ ቁጥሮች በላይ ምስክር የለም::

ሁላችንም የበሽታውን ስርጭት በመግታት የራሳችን እና የምንወዳቸው ቤተሰቦቻችን ሕይወት እናድን::
(ያዕቆብ ሰማን :-በጤና ሚኒስቴር የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር)
ፎቶ: አማኑኤል ስለሺ
# FOR YOUR INFORMATION
#National_Oxygen_Production_Capacity

For those who are asking for the details

Due to the current critical case surge exponential demand for oxygen in Ethiopia particularly in Addis Ababa has been recorded in the last few days.

Last year May/2020 during the early month of COVID pandemic our worst case scenario oxygen demand forcast was around 66,000m3/day (2,750m3/hr.) production.
The baseline during the same month last year was around 21,000m3/day (approximately 875m3/hr).

The current summery of oxygen production capacity in the country is as follows.

1.We have a total of 33 oxygen plants #throughout the country. 20 plants are #functional, 10 plants are #nonfunctional and 3 are new uninstalled machines.

2.The current #potential production capacity is 3,267 m3/Hr. but our #actual production capacity is 1,805m3/Hr. 45% unmet production capacity is due to non-
functional plants, inefficient production and uninstalled machines due to bureaucracy related problems.

3. 89% of oxygen production is from the #private sector, 7% from public and 4% from public-private model.

4.The key challenges to narrow the gap between potential production and action production are frequent #power outage, unable to get foreign #currency for spare part importation, #Bureaucracy problems, Technical capacity limitation to install and to maintain plants.

5. People are #procuring oxygen to keep stock at home and #using oxygen at home with remote follow up which end up with more critical cases from home.

6. From the nonfunctional plants 2 from AA, 2 from Harar, 2 from Amhara, 4 from Oromia, 1 from Sidama, 1 from SNNPR and 2 from Tigray.

Maintenance of nonfunctional machines and improving powe supply are the low hanging fruit to address the problems.
(Yakob Seman ,FMOH)