St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት እና የኢፌዲሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በጋራ ጋር ያዘጋጁት የመንግሥት አግልግሎት አሰጣጥ ጥራት ልዩ ውድድር ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በከፍተኛ ደረጃ የማዕረግ ተሸላሚ ሆኗል።
አገልግሎቱን በማዘመን እና አገልግሎትን በጥራት በመሥጠት ነው ኮሌጁ ለዚህ ሽልማት የበቃው።
የሽልማት ድርጅቱ ለውድድር የቀረቡትን በቁጥር አሥር ከሚደርሱ ድርጅቶች መካከል ነው ለሽልማት የተመረጠው።
የሽልማት ድርጅቱ ለበርካታ ቀናት በኮሌጁ አገልግሎት አሠጣጥ የቅርብ ክትትል አድርጓል ።

በሽልማት ሥነሥርዓቱ የተገኙት የኮሌጁ የሥራ ኃላፊዎች የላቀ አገልግሎት ለመሥጠት ቃል ገብተዋል ።
እንደምን አደራችሁ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ወዳጆችና ቤተሰቦች!
======================

ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ለእናንተ የሚበጁ አስተማማኝ የጤና መረጃ ወደ እናንተ ማድረስ እንጀምራለን ።

የዛሬውን ዕለት የፌስቡክ ገጻችንን በመጎብኘት ለእናንተ ያዘጋጀነውን የጤና መረጃ እንድትቋደሱ ግብዣችን ነው።

አሳሳቢ የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል የሚያግዝ ክልከላ መንግሥት መጣሉን ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።

የጤና ሚኒስቴር እና የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በሰዎች እንቅስቃሴና ማህበራዊ ተግባራት ላይ
ክልከላ የሚጥልና በወንጀል የሚያስጠይቅ መመሪያ ይፋ አድርገዋል::

በአዲሱ መመሪያ መሰረት በየትኛውም ቦታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ሳያደርግ መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን የንግድና ሌሎች የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማስክ ያላደረገ ሰውን እንዳያስተናግዱ የክልከላው መመሪያ ያዛል::(ሙሉ መመሪያውን በትናንቱ ልጥፋችን ያገኙታል።)

መመሪያውን ተግባራዊ በማያደርጉ አካላት ላይም እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲሁም ሌሎች ቅጣቶችን ያስከትላል ።

ውድ ወዳጆችና ቤተሰቦች ክልከላው ከዛሬ ስለሚጀምር ጠንቅ በሉ ለማለት እንወዳለን።

አካላዊ ርቀታችንን መጠበቅ፣ እጃችንን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አንርሳ።በ

ራሳችንና ወገኖቻችን ከኮቪድ እንከላከል ።
ጤና ሁኑልን! ደስ የሚል ቀን ይሁንላችሁ !
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር ከሁለት መቶ ሺህ አለፈ
⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳
የኮቪድ-19 ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱ ከታወቀ አንድ አመት አለፈው። ለ2.3 ሚሊዮን በላይ ግለሰቦች የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓጊ። ከ200,000 በላይ ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 154,323 ከኮቪድ-19 ቫይረስ አገግመዋል።

በትላንትናው ዕለት ደግሞ 7,250 ግለሰቦች የኮቪድ-19 ምርመራ ተደርጎ 1,769 ግለሰቦች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ናሙና ከሰጡ 100 ግለሰቦች 24 ወይም (24%) ግለሰቦች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል እንደማለት ነው።
805 ግለሰቦች ደግሞ በፅኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ እየታከሙ ይገኛሉ። ለ 2,801 ግለሰቦች ሕይወት በኮቪድ ሳቢያ ሕይወታቸው ተቀጥፏል።

አካላዊ ርቀታችንን መጠበቅ፣ እጃችንን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አንርሳ።

ራሳችንና ወገኖቻችን ከኮቪድ እንከላከል ።
ኢሕጤኢ
የአዕምሮ ህመም መንስኤዎች

መግቢያ 

የአእምሮ ህመም ምክንያቶች የተለያዩ ናቸው፤ ሆኖም ግን አብዛኛዎች የስነ-ህይወታዊ፣ የስነ-ልቦናዊ እና የማህበራዊ ችግሮች ስብጥር የሆነ መነሻ አላቸው፡፡ የአእምሮ ጤና ባለሞያዎች የአእምሮ ህመምን በተመለከተ ከላይ የተገለፁትን መንስኤዎች መስተጋብር አያያይዞ የሚያስረዳ “ስነህይወት-ስነልቦና እና ማህበራዊ (bio-psychosocial)” የተባለ ሞዴል አዘጋጅተዋል፡፡

ስነህይወታዊ፣ ስነልቦናዊ፣ ማህበረሰባዊ ጉዳዮች/ችግሮች አብዛኛዉን ጊዜ የመደራረብ ባህሪያት አላቸው፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የስነህይወት፣ የስነልቦና እንዲሁም የማህበራዊ የአእምሮ ህመም መንስዔዎች በምሳሌነት ቀርበዋል ፡-

1. ስነ-ህይወታዊ መንስኤዎች (biological causes): የተፈጥሮ/በዘር የሚወረስ- ይህም ማለት የአዕምሮ ህመም ካለበት ቤተሰብ ወደ ልጅ የመተላለፍ ወይም ደግሞ ልጆቹ ይበልጥ ተጋላጭ መሆን (ለምሳሌ እንደነ ስኪዞፍሬኒያ፣ ሽቅለት እና ድባቴ በቤተሰብ የመከሰት እድላቸዉ የሰፋ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ)፣ በአዕምሮ ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገር (ኬሚካሎች) መዛባት፤ በጭንቅላት ላይ የደረሰ አደጋ፣ ሱስ አምጪ ንጥረ ነገሮችን መጠቀም (አልኮል መጠጣት ወይም ጫት መቃም ሌሎችንም ሱሶች መጠቀም፣ የምግብ እጥረት፣ ኢንፌክሽን አምጪ በሽታዎች ወዘተ…

2. ስነ-ልቦናዊ መንስኤዎች (psychological causes): እነዚህ መንስኤዎች ደግሞ ከአስተዳደግ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ሁኔታዎች ናቸዉ። ለምሳሌ፡- በልጅነት ጊዜ በቂ እንክብካቤ አለማግኘት፣ አብዝቶ መጨነቅ፣ የቤተሰብ መበታተን፣ በተረበሸ ቤተሰብ ዉስጥ ማደግ፣ የቅርብ ሰዎችን በሞት በማጣት ምክንያት የሚመጣ ውጥረት፣ ሀዘን /ብስጭት፣ መረበሽ ፍርሃት ፣ከልጅነት ጀምሮ የተለያዩ አካላዊ፣ ጾታዊ ወይም ስነ ልቦናዊ ጥቃቶች ዉስጥ ማለፍ፣ ወዘተ…

3. ማህበራዊ መንስኤዎች (social causes): ችግር፣ ስራ ማጣት፣ ስደት፣ ድህነት፣ ስራ አጥነት ፣ የእኔ የሚሉትና ችግራቸውን የሚያካፍሉት ሰው አለመኖር፣ መገለል፣ ብቸኝነት… ወዘተ

የአዕምሮ ህመም ባብዛኛዉ የሚከሰተዉ ግን ተጋላጭነታቸዉ ከፍ ያሉ ሰዎች ላይ ሌሎች የሚቀሰቅሱ ምክንያቶች ወይም ስነ ልቦናዊ ዉጥረቶች (Psychological Stressors) ሲፈጠሩ ነዉ።

እንደ አለም ጤና ጥበቃ ጥናት መሰረት ከ 5 ሰዉ አንዱ የአዕምሮ ህመም በህይወቱ ሊገጥመዉ እንደሚችል ያሳያል። በአለማችን በ 2030 እንደ አዉሮፓዉያወን አቆጣጠር በተራ ቁጥር አንድ ላይ የሚቀመጥ የጤና እክል ወይም ዲስኤቢሊቲ ምክንያት እንደሚሆን ያሳያል።

በሀገራችን የተሰሩ ጥናቶችም ቢያንስ እስከ 28% ድረስ የሚደርሱ የህብረተሰባችን ክፍሎች ለተለያዩ የአዕምሮ ህመሞች ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ ያሳያል። አሁን ላይ በሀገራችን ላይ እየበዛ የመምጣቱ ምክንያቶች መካከል ሱሰኝነት ይካተትበታል። ለምሳሌ፡- በሀገራችን ጫት እስከ 64 በመቶ ድረስ የሚቃምበት አካባቢዎች ይገኛሉ። ወደ ሶስት በመቶ የሚያክሉ የህብረተሰባችን ክፍሎች ደግሞ በአስቸጋሪ የአልኮል አጠቃቀም ልማድ ዉስጥ ይገኛሉ። ማሪዋና እስከ 1.5 በመቶ ያክል ተጠቃሚ በሀገራችን ይገኛሉ፣ የማሪዋና ተጠቃሚዎች ግን እጅግ እየጨመረ ነዉ። ሱስ በራሱ ለ አዕምሮ ህመም ሊያጋልጥ ቢችልም በተዘዋዋሪ መንገድ ደግሞ የተለያዩ የጤና፣ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ስነልቦናዊ ጫና የተነሳ ለአዕምሮ ህመም ሊዳርግ ይችላል።

ከነዚህም በተጨማሪ ጉዳዩን የሚያባብሰዉ በቂ የሆነ የአዕመሮ ጤና ግንዛቤ ያለመኖር፣ የተሳሳተ አመለካከት በህብረተሰቡ መንሰራፋት፣ ተገቢ ትኩረት ያለመሰጠት እና በቂ የሆነ የአዕምሮ ህክምና አገልጋዮችም ሆነ አገልግሎቱ በሀገራችን ያለመኖሩ ብሎም ህብረተሰባችን እርዳታ በጊዜ ያለመፈለጉ ይካተቱበታል።

ዶር አሥራት ሐብተጊዮርጊስ
የሥነ አዕምሮ ስፔሻሊስት
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ

ያጋሩ
ለእናቶች ደም እንለግስ!
ቀኑን እንዳይይረሱት! መጋቢት 30 -ሚያዚያ 2/2021
የኢትዮያጵያ መድኃኒት ና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር ኬይረዲን ረዲ አገራቸውንና ህዝባቸውን በማገልገል ላይ እያሉ በኮቪድ 19 ምክንያት ህይወታቸው በማለፉ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለመላው ቤተሰቦቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን::
ማስታወቂያ

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2013 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በህክምና /Medicine/ ለመማር የሚፈልጉ አመልካቾች ቢሮ በመምጣት ፡ በስልክ እና በኢሜይል አየጠየቁን ይገኛሉ፡፡
በቅርቡ የቅበላውን መስፈርትና ምዝገባውን አስመልክቶ መረጃውን በዚህ ፌስ ቡክ እና በቴሌግራም ገጻችን የምንለቅ ይሆናል ፡፡ በትእግስት ጠብቁን፡፡

Telegram: t.me/spmmc


Notice for applicants to join Doctor of Medicine at St Paul’s Hospital Millennium Medical College

Admission requirements

1.    The applicant should only be who took Ethiopian higher education entrance examination (EHEEE) in 2013 E.C.

2.    Ethiopian higher education entrance examination (EHEEE) result should be:

                                   i.         For Afar, Borna zone (Oromia) Benshagnul Gumze, Gabmbella, Somali, South Omo zone (SNNP), Wagehmira Zone (Amhara) and West Omo Zone (SNNP): 525 and above

                                 ii.         For Addis Ababa and other regions: For Male 575 and above and for Female 550 and above

3.    The transcript average mark from 9th -12th should be 80% and above.

4.    High school transcript from 9th -12th grade should be uploaded.

5.    EHEEE result print out that show clear admission number should be uploaded.

6.    Additional copy of all necessary educational documents should be uploaded.

7.    Application fee of 50 birr should be paid and uploaded.

8.    The application will be complete if all necessary information filled and uploaded

9.    Application date starts on  Saturday April 3, 2021

10. Only online application will be accepted – Please use the following link to register http://197.156.83.153/admission/

Remark

No.

Description

Score (%)

Remark

1

Written examination will cover Aptitude, Situational judgment testing

55%

 

2

Multiple mini interview

20%

only for short listed applicant’s

3

Academic records

25%

Transcript 5 % and EHEEE result 20%)

 

The maximum intake capacity of the college is 80 students

From the total Intake 20% will be accepted from the following emerging regions and zone: Afar, Benshgangule -Gumze, Borena ( Oromia), Gambella, Somalia, South Omo (SNNP), West Omo(SNNP), Wagimeria ( Amhara )

Written examination will be held on Sunday April 11, 2021GC

Written Examination and Interview will be given only in Addis Ababa, and place of examination center will be communicated on the college official website, Facebook and Telegram account.

Bank Account number of the college: Commercial Bank of Ethiopia, St. Paul's Hospital Millennium Medical A/C Number 1000208431068

·        For additional information - you can contact Registrar office via:

email: tamedi30@gmail.com 

phone: +251118965125

·        Application deadline is Thursday, April 8, 2021 at 6PM (12 o’clock local time)

 

 

 

                               

 
ማስታወቂያ
ለአዲስ ተመዝጋቢዎች በሙሉ

ምዝገባን አስመልክቶ የሚነሱ ማንኛውንም ጥያቄዎች በሚከተለው አድራሻ የሪጅስትራር ጽ/ቤትን ማግኘት ይቻላል።
email: registrar@sphmmc.edu.et
በኦን ላይን ምዝገባ ለሚያጋጥም የቴክኒክ ችግር በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች የባለሙያ ምክር ያግኙ።

+251118965125/+251911421162

ማሳሰቢያ : ማንኛውም ተመዝጋቢ በኦንላይን ብቻ ነው መመዝገብ የሚችለው ።

መልዕክቱን Share ያድርጉ።
በቴሌግራም t.me/spmmc
የዛሬ መጋቢት 26 የኮቪድ ሪፖርት
t.me/spmmc
👉 27 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል‼️
👉 1,878 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ‼️
👉 857 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ ናቸው‼️

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6,962 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 1,878 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 215,189 ደርሷል።

ርቀታችንን መጠበቅ፣ እጃችንን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አንርሳ!
ቀኑን ያስታውሱ!
እንደምን አደራችሁ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ወዳጆች!
=========================
በወሊድ ጊዜ እና ተያዥ የጤና ችግር ሳቢያ ደም ለሚያስፈልጋቸው እናቶች የተዘጋጀው የደም ልገሳ ፕሮግራም ዛሬ ሦስት ሰዓት ይጀምራል። ፦
ቦታው በአምስተኛው በር አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ ቶታል ወይም ሴና ካፌ አጠገብ ነው።

አሁንም የደም እጥረት አለ። በተለይ ኦ(O) የደም ዓይነት ያላችሁ መጥታቻሁ ደማችሁን ለወገናችሁ እንድትለግሱ እንጠይቃለን ።

ወጣት በጎ ፈቃደኞች :
ታዋቂ ሰዎች
የቲክሻህ ቤተሰቦች ተገኝተው ደም እንደሚለግሱ ከወዲሁ አሳውቀውናል ። እናመሰግናለን ።

ኑ ለእናቶች ደም እንለግስ!

አደራ ! ርቀታችንን መጠበቅ፣ እጃችንን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አንርሳ!
ቀናችሁ ያማረ ይሁን፤ ብሩክ ቀን ይሁንላችሁ! ጤና ሁኑልን!
መልካም ቀን!
ደም ልገሳው ተጀምሯል!፡ ደም ለእናቶች ለግሱ! ኦ የደም ዓይነት ያላችሁ እባካችሁ መጥታችሁ እንድትለግሱ አናሳስባለን፡፡
የዶር ሊያ ታደሠ መልዕክት

በዚህ "የዓለም የጤና ሰራተኞች ሳምንት" ፣ ለጤና ሰራተኞቻችን ሁሉ ያለኝን ክብር እና ምስጋና፣ ማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡ በመላ አገሪቱ ያሉ የጤና ባለሙያዎቻችን እና ሰራተኞቻችን፣ እኛ ጤና እንድንሆን፣ እኛ በጎ እንድንሆን፣ ከልባቸው ይጥራሉ፣ ሌት ተቀን ይደክማሉ፡፡ በማህበረሰቡ ውስጥ፣ በጤና ተቋማት ፣ በመጠለያ ጣብያዎች፣ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች እና በሌሎችም አደገኛ ቦታዎች፣ ለደህንነታቸው ሳይሳሱ፣ ዘወትር ስለሚለፉ፣ ከልቤ አመሰግናቸዋለሁ፡፡

በተለይም በዚህ አደገኛ የወረርሽኝ ወቅት፣ ለህብረተሰቡ የምትሰጡት አገልግሎት እና የምታሳዩት ቁርጠኝነት፣ የተለየ ክብር ይገባዋል፡፡ ጥረታችሁ የበለጠ እንዲሳካ ወደፊትም፣ በምንችለው ሁሉ እንደምንደግፋችሁ እና ከጎናችሁ እንደምንቆም፣ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ!
የጤና ባለሙያዎችንና ሰራተኞቻችን ለመደገፍ ሁላችንም ቀላል የኮቪድ19 መከላከያ መንገዶችን ሳንሰለች እንተግብር!

On this World Health Workers Week, we express our gratitude to our health workers. Our Health workers across the entire nation are diligently working and striving to make sure we stay healthy and safe, dedicating themselves to providing care in health facilities, communities, IDP sites, conflict areas, and more.

Your hard work, service, and devotion to your community, especially during this unprecedented pandemic, is well recognized. We also take this opportunity to escalate our determination to make sure that you are supported for your efforts. You are greatly appreciated!
In support of our health workers, let us all follow simple CoVID 19 protocols.
D/r Lia Tadesse
Minister of Health
#WHWWeek
አስቸኳይ - [ Emergency Call ]

🚨 የኦ (O) የደም ዓይነት ያላችሁ 🚨

#Ethiopia | ኢትዮጲያ በባንክ ያላት የኦ (O) የደም ዓይነት ለሚቀጥሉት 7 ቀናት ብቻ የሚበቃ ነው።

የኦ (O) የደም ዓይነት የደም ዓይነት ባለቤት የሆናችሁ እባካችሁ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ 5ኛ በር አካባቢ በመምጣት ደም በመለገስ የወገኖቻችሁን ህይወት ታደጉ !