St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
የኮቪድ ምልክቶች ከታየብዎ ጸሎትዎንና ስግደትዎን በቤትዎ ያድርጉ።
#SPHMMC_COVID_19
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎ ከአፍንጫዎ እስከ አገጭዎ መሸፈኑን ያረጋግጡ።
#COVID_19_SPHMMC
💔 💔ዛሬ ልጄ ከተወለደ ገና 4 ቀኑ ነው:: ለክትትል ሆስፒታል ሄደን ነበር እና ሐኪሙ ልጅሽ ቢጫ ሆኗል አለኝ እና በጣም ተጨንቂያለው ‼️ ለምንድነው ልጄ ቢጫ የሆነው መፍትሄውስ ምንድነው?? 🤔🤔
📌 አይጨነቁ‼️ በአለም ላይ ከሚወለዱ ህፃናት ቢያንስ 60% የሚሆኑት ቢጫ ሊሆኑ ይቺላሉ::
📌 የጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን በሕክምናው Neonatal Jaundice ይባላል እንደ ምክንያቱ አይነት ቀላል ወይም ከባድ ሊሆን ይችላል:: ምክንያቶቹ ደሞ በጣም ብዙ ናቸው:: ለዛሬ የተወሰኑትን ብቻ መርጠን እናያለን::
📌 የመጀመሪያው ምክንያት ተፈጥሯዊ ቢጫነት (Physiologic Jaundice) የሚባለው ሲሆን ብዙ ጊዜ በብዙ ጨቅላ ህፃናት ላይ የሚያጋጥመን በቀላሉ እና በራሱ ጊዜ የሚጠፋው ቢጫነት ነው:: ይህ አይነት ቢጫነት እስከ 10 ቀን ወይም እስከ 2 ሳምንት ባለው ጊዜ በራሱ ይጠፋል:: ጡት በደንብ ማጥባት እና ፀሐይ ማሞቅ በቂ ነው ::
📌 ሁለተኛው ምክንያት ደሞ የእናት እና የልጅ የደም አለመመሳሰል(Blood group incompatibility) ለምሳሌ:
➡️ 1. የእናትየደም አይነት Negative(O negative, A negative, B negative ወይም AB negative) ሆኖ የልጅ ደሞ Positive ሲሆን ከባድ ቢጫ መሆን ሊያመጣ ይቻላል አልፎ ተርፎም ህፃኑ ላይ ከባድ አዕምሮ ጉዳትም ሊያደርስ ይቺላል:: አልፎ አልፎም ገና ልጁ ሳይወለድ በማህፀን እንዳለ ሊሞት ይቻላል:: ይሄም በሀገራችን በተለምዶ ሾተላይ የሚባለው ነው‼️
➡️ 2. የእናት የደም አይነት O ሆኖ የልጁ ደሞ A ወይም B ከሆነም ቢጫ መሆን ይከሰታል
📌 ሶስተኛው ምክንያት ደሞ ልጁ በቂ የሆነ ወተት ካላገኘ ቢጫ ሊሆን ይቺላል::
📌 አራተኛው ምክንያት ደሞ የጨቅላ ህፃናት ኢንፌክሽን (neonatal sepsis) ሲሆን ይህም ብዙ ጊዜ በባክቴሪ የሚመጣ ነው::
👉 የጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን ከላይ ያልተጠቀሱ በ ሕክምናው የሚታወቁ በጣም ብዙ ምክንያቶች ያሉት ሲሆን ምክንያቱን በትክክል ለማወቅ ከፈለጉ ሐኪሞን ያማክሩ:: አስፈላጊ ከሆነ ሐኪሞም የደም ምርመራ ለልጆዎ ልያዝ ይችላል::
📌ለማንኛውም ከልጆ ጤና የሚበልጥ ነገር የለምና የቅርብ ክትትል እንዲሁም ሕክምና ያድርጉ ‼️

ዶ/ር ፋሲል መንበረ
(በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የህፃናት ስፔሻሊስት ሐኪም)
Happy international #midwifeday !Thank-you everyone midwife working in SPHMMC and around the country .
ነገ የዓለም አቀፍ የሚድዋይፍ ቀን ነው። በመላው ሀገራችን ወገናችሁን በማገልገል ላይ የምትገኙ ክብር ይገባችኋል ።
እንኳን ለዓለም አቀፉ የሚድዋይፍ ቀን አደረሳችሁ!
#midwifeday
#internationalmidwifeday2021
#IDM2021
#UNFPA
Today is the international day of the midwife to all the amazing midwives.
Thank you for all you do for all women , families and your colleagues ! #IDM2021

ዛሬ የዓለም የሚድዋይፎች ቀን ነው ። እስቲ እንኳን አደረሳችሁ እንበላቸው።
Lia Tadesse, Minister of Health
UNFPA Ethiopia
የታካሚዎች መልዕክት
የኮሌጃችን የ forensic medicine autopsy ቴክኒሽያን የሆነው ፈቃዱ ታደሰ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በትናትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ላለፉት አምስት ዓመታት በሙያው ኮሌጁን በትጋት አገልግሏል።
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ማሕበረሰብም ለቤተሰቡና ለወዳጆቹ መጽናናትን ይመኛል ።
መልካም የእናቶች ቀን!
To all Mothers on this very special day, WE LOVE YOU! Happy Mother's Day from SPHMMC! #mothersday
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ ነባር ህንፃ በ45 ሚሊዮን ብር እድሳት ሊደረግለት ነው።

በዛሬው እለት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ ነባር ህንፃ በ45 ሚሊዮን ብር እድሳት ዛሬ ተጀመረ።
እድሳቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በኮሌጁ ተገኝተው በይፋ አስጀምረዋል።

የኮሌጁ ነባር ህንፃ እድሳት በዋንኝነት የድንገተኛ አገልግሎቱን ለማስፋፋትና የቀዶ ህክምናና የውስጥ ደዌ ህክምናን ለማጠናከር ነው ።

ዶር ሊያ በተጨማሪም የካንሰርና የልብ ህክምና ማዕከል፣ የአንገት በላይና የአይን ህክምና እንዲሁም የተለያዩ ንቅለ ተከላ ህክምና የሚሰጡ ግንባታዎች አፈፃፀምማቸውን ተመልክተዋል።
እነዚህ ግንባታዎች በቀጣይ አንድ አመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቁ በዕለቱ ባለሙያዎች ተገልጿል።
የ3ኛው ዙር #በኢትዮጵያ_ሆስፒታሎች_ጥምረት_ለጥራት ፕሮግራም ሀገር አቀፍ የሆስፒታሎች የምዘና ወድድር ውጤትን ዛሬ ይፋ ሆኗሆኗል።
በዚህ ውድድር በአዲስ አበባ ካሉ 12 ሆስፒታሎች መካከል የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የሁለተኛ ደረጃን አግኝቷል፡፡ በዚህ ውጤትም ኮሌጁ ሁለት ሚሊየን ብር እና አንድ ፒክ አፕ መኪና ተሸልሟል፡፡
የኮሌጃችን ተገልጋዮች፡ መላው ሰራተኛ እና በየደረጃው ያለችሁ የስራ ሓለፊዎች፡ በሙሉ ይህ ስኬት የተገኘው በእናንተ ብርታት ነው ! ድካማችሁ ለውጤት በቅቷል! ምስጋና ይገባችኃል ! እንኳን ደስ ያላችሁ!
እንኳን ደስ ያላችሁ!
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለ1ሺ442ኛው ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ !
በጣም ለምንወዳችሁ ነርሶቻችን!
እንኳን ለዓለም የነርሶች ቀን አደረሳችሁ! በእናንተ የስራ ትጋትና ድካም ኮሌጃችን ብዙ ስኬቶችን ተጎናጽፎአል፡፡ በዚህ በዘመነ ኮቪድም ለራሳችሁ ህይወት ምንም ሳትሳሱ ወገናችሁን ለማዳን ያደረጋችሁትን ስራ ምንጊዜም አይዘነጋም፡፡ ክብር ይገባችኋል! እናመሰግናለን -የሚለው ቃል ብቻ ለወገናችሁ የሰጣችሁትን አገልግሎት ለመግለጽ ቢያንስም እናመሰግናችኋለን !
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ሕክምና ኮሌጅ ማሕበረሰብ

#NursesWeek2021 #ThankYouNurses #Internationalnursesweek
የዓለም ጤና ድርጅት በህንድ የተከሰተው የኮቪድ-19 ቫይረስ አሳሳቢ ዝርያ እንደሆነ እና ዓለም አቀፍ ስጋት እየሆነ እንደመጣ ቫይረሱ እስካሁን በ44 ሃገራት እንደተሰራጨ ገልጿል።
ስለሆነም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ለኮቪድ-19 አጋላጭ ሁኔታዎችን በማስቀረት የመከላከያ መንገዶቸን በጥንቃቄ እንዲተገብር የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያሳስባል፡: