መልካም የእናቶች ቀን!
To all Mothers on this very special day, WE LOVE YOU! Happy Mother's Day from SPHMMC! #mothersday

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ ነባር ህንፃ በ45 ሚሊዮን ብር እድሳት ሊደረግለት ነው።
በዛሬው እለት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ ነባር ህንፃ በ45 ሚሊዮን ብር እድሳት ዛሬ ተጀመረ።
እድሳቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በኮሌጁ ተገኝተው በይፋ አስጀምረዋል።
የኮሌጁ ነባር ህንፃ እድሳት በዋንኝነት የድንገተኛ አገልግሎቱን ለማስፋፋትና የቀዶ ህክምናና የውስጥ ደዌ ህክምናን ለማጠናከር ነው ።
ዶር ሊያ በተጨማሪም የካንሰርና የልብ ህክምና ማዕከል፣ የአንገት በላይና የአይን ህክምና እንዲሁም የተለያዩ ንቅለ ተከላ ህክምና የሚሰጡ ግንባታዎች አፈፃፀምማቸውን ተመልክተዋል።
እነዚህ ግንባታዎች በቀጣይ አንድ አመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቁ በዕለቱ ባለሙያዎች ተገልጿል።

የ3ኛው ዙር #በኢትዮጵያ_ሆስፒታሎች_ጥምረት_ለጥራት ፕሮግራም ሀገር አቀፍ የሆስፒታሎች የምዘና ወድድር ውጤትን ዛሬ ይፋ ሆኗሆኗል።
በዚህ ውድድር በአዲስ አበባ ካሉ 12 ሆስፒታሎች መካከል የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የሁለተኛ ደረጃን አግኝቷል፡፡ በዚህ ውጤትም ኮሌጁ ሁለት ሚሊየን ብር እና አንድ ፒክ አፕ መኪና ተሸልሟል፡፡
የኮሌጃችን ተገልጋዮች፡ መላው ሰራተኛ እና በየደረጃው ያለችሁ የስራ ሓለፊዎች፡ በሙሉ ይህ ስኬት የተገኘው በእናንተ ብርታት ነው ! ድካማችሁ ለውጤት በቅቷል! ምስጋና ይገባችኃል ! እንኳን ደስ ያላችሁ!

በጣም ለምንወዳችሁ ነርሶቻችን!
እንኳን ለዓለም የነርሶች ቀን አደረሳችሁ! በእናንተ የስራ ትጋትና ድካም ኮሌጃችን ብዙ ስኬቶችን ተጎናጽፎአል፡፡ በዚህ በዘመነ ኮቪድም ለራሳችሁ ህይወት ምንም ሳትሳሱ ወገናችሁን ለማዳን ያደረጋችሁትን ስራ ምንጊዜም አይዘነጋም፡፡ ክብር ይገባችኋል! እናመሰግናለን -የሚለው ቃል ብቻ ለወገናችሁ የሰጣችሁትን አገልግሎት ለመግለጽ ቢያንስም እናመሰግናችኋለን !
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ሕክምና ኮሌጅ ማሕበረሰብ
#NursesWeek2021 #ThankYouNurses #Internationalnursesweek

የእናት ጡት ወተት ጥቅሞች
📌 በአሁኑ ወቅት በተለይ በከተሞች አካባቢ አንዳንድ እናቶች ልጆቻቸዉን የሚያጠቡት ከራሳቸው የጡት ወተት ይልቅ የጣሳ ወተትን ስመርጡ ይስተዋላሉ::
📌 በእርግጥ ሁሉም እናቶች የራሳቸው ምክንያት አላቸው::
📌ሆኖም ግን እስካሁን በተጠኑት ጥናቶች መሰረት የእናትን ወተት የሚተካ ሌላ አይነት ወተት ወይም ምግብ እስካሁን አልተገኘም ‼️
📌የእናት ጡት ወተት ጥቅሙ ልጇ ብቻ ሳይሆን ለእናትም ለቤተሰብም ለማህበረሰብም ከፍ ሲልም ለሀገር ነው:: እስኪ በዝርዝር እንየዉ፦
1. ጡት ማጥባት ለእናት ያለው ትቅም ፦
✍️ ከ ወሊድ በዋላ ማህፀን ቶሎ እንዲኮማተር እና ወደ ቦታ እንዲመለስ ያረጋል ይሄም የደም መፍሰስ እንዳይከሰት ይከላከላል
✍️ ከወሊድ በዋላ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል
✍️ የጡት እና የእንቁላል ማኩረቻ ካንሰርን ይከላከላል
✍️ በ እድሜ የሚመጡ በሽታዎችን ለምሳሌ ስኳር ደም ግፊት እና የመሳሰሉትን በሽታዎችን ይከላከላል
✍️ በ እናት እና በልጅ መሃል ያለውን ፍቅር ይጨምራል
✍️ በተፈጥሮ ስለሚገኝ ወጪ ቆጣቢ ነው
✍️ ለአጭር ጊዜ ቢሆንም እርግዝናን ይከላከላል
2. የእናት ጡት ወተት ለህፃናት ያለው ጥቅም:
👉 ትክክለኛ እና በቂ የሆኑ ንጥረ ነገሮች በውስጡ ስለያዘ ህፃናት በተገቢው ሁኔታ እንዲያድጉ ይረዳል
👉 የብሩህ አይምሮ(Higher IQ) ባለቤት ያረጋቸዋል
👉 የተለያዩ የህፃናት ኢንፌክሽኖችን ይከላከላል ለምሳሌ የ ጆሮ፣የሳምባ፣ የአንጀት ፣የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
👉 የልጆች አለርጂን ይከላከላል
👉 ልጆች ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንዳይኖራቸዉ ይከላከላል
👉 የመጀመርያዉ አይነት የስኳር በሽታ(Type 1 Diabetus Mellitus) ይከላከላል
👉 ድንገተኛ የሆነ የጨቅላ ህፃናትን ሞት ይከላከላል
3. የእናት ጡት ወተት ማጥ ባት ለቤተሰብ እና
ለ ማህበረሰብ ያለው ጥቅም
📌 የተለያዩ የህፃናት በሽታ በመከላከል የሀገሪቱን የ ጤና ወጪ ይቀንሳል
📌 ልጆች ባለ ብሩህ አይምሮ ሆነው እንዲያድጉ በመርዳት በትምህርትም ዉጤታማ እንዲሆኑ ከዛም እንደ ሀገር ጥሩ አበርክቶ እንዲኖራቸዉ ቀላል የማይባል አስተዋፆ አለው::
እባክዎን ካነበቡ በኋላ ሼር ያድርጉት !
ዶክተር ፋሲል መንበረ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የህጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም

የልጆች ስቅታ(Hiccup) መንስኤው ምንድነው ?
እንዴትስ ማቆም እንችላለን?
ስቅታ በአዋቂም ሆነ ልጆች ላይ ሊታይ የሚችል ብዙ ጊዜ ጤናማ እና ተፈጥሯዊ ምላሽ(reflex)ነው።
አዋቂ ሰዎችን እንደሚረብሽው ግን ህፃናትን ብዙ ጊዜ አይረብሻቸውም። እንደውም ህፃናት ስቅ እያላችው ጥሩ እንቅልፍ መተኛት ይችላሉ ::
ስቅታ የሚመጣው እንዴት ነው?
ስቅታ የሚከሰተው ዲያፍራም የሚባለው ሳንባችን ከታች ደግፎ የሚገኘው ጡንቻ ድንገት ስኮማተር እና ቮካል ኮርድ የሚባለው የአየር መግቢያ ድንገት ሲዘጋ ነው::
የልጆች ስቅታ መንስኤው ምንድነው?
1.ቶሎ ቶሎ እና ብዙ ምግብ መመገብ: ቶሎ ቶሎ ብዙ ጡት ወይም ጡጦ መጥባት። ይህም ብዙ አየር ወደ ጨጓራ እንዲገባ እና ዲያፍራም የሚባለው ሳንባችን ከታች ደግፎ የሚገኘው ጡንቻ ድንገት እንዲኮማተር ያደርጋል::
2.ህፃናት የሚያስደስታቸውን ወይም ለየት ያለ ነገር ሲያገኙ( excitement)
3. ህፃናት ሙቀት በተለይ ሆድ አካባቢ ያለ ሙቀት በድንገት መቀነስ እና የመሳሰሉት ናቸው።
መፍትሄው ምንድነው?
1. ጡት ወይም ጡጦ ከጠቡ በኋላ በደንብ ማስገሳት። የአሜሪካ የህፃናት ሕክምና ማህበር አንድ ህፃን ከ60 ሚሊ ሊትር በላይ ከጠባ በደንብ ማስገሳት እና ልጁን ከ 20-30 ደቂቃ ቀና አድርጎ(upright position) ማስቀመጥን ይመክራል::
2.ልጆች በጣም ሳይርባቸው መመገብ ወይም ማጥባት መሃል ላይ ስቅታ ከጀመራቸው ማጥባቱ ቆም አድርጎ ማስገሳት እና ትንሽ ቆይቶ ማጥባት
3. የእንጀራ እናት(Pacifier, dummy) መስጠት።
ይህ መፍትሄ እድሜያቸው ከ1 ወር በታች ላሉ ህፃናት እና ባጠቃላይ እንደኛ ላሉ ሃገራት ላይ ከንፅሕና ጋር ተያይዞ ብዙም አይመከርም። ሆኖም ልጅን ለማረጋጋት ተብሎ እንደ አማራጭ ይቀርባል
4. ዋናው መፍትሄ ግን ወላጆች ስቅታ ቀላል እንደ ሆነ ልጁ ላይ ጉዳት እንደማያደርስ ማወቅ እና 5-10 ደቂቃ ዉስጥ እንደሚቆም ማወቅ እና በመረጋጋት ልጃቸውን ማጫወት ማዝናናት አለባቸው:: ከዚህ ዉጭ ያሉት ባህላዊ መንገዶችን ባንጠቀም ይመከራል።
ስቅታ መቼ ነው መታከም ያለበት?
1.የተከሰተው ልጁ 1 ዓመት እድሜ በላይ ከሆነ እና ስቅታው በጣም ተከታታይ ከሆነ
2.ህፃኑ እድሜው ከ 1 ዓመት በታች ሆኖ ከ ስቅ ታው ጋር ተደጋጋሚ ትውከት ቅርሻት ሳል እና መነጫነጭ ካለው ምን አልባት ከ ጨጓራ ጋር ሊያያዝ ይችላል ። በዚህ ጊዜ ሐኪምን ማማከር ተገቢ ነው::
መረጃውን አንብበው ሼር ያድርጉ
ዶክተር ፋሲል መንበረ
የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ

የሕጻናት ጤናማ አመጋገብ
(ከህፃናት ከ6 ወር - 2 ዓመት)
# ህፃናት 6 ወር ከሞላቸው በኋላ የእናት ጡት ወተት ለብቻው የምግብ ፍላጎታቸውን ስለማያሟላ ተጨማሪ ሌሎች ምግቦችን መጀመር ይኖርባቸዋል ::
# በዚህ የእድሜ ክልል ህፃናት እድገታቸው ፈጣን ስለሚሆን በቂ የሆነ ምግብ ካላገኙ ለስውነታቸው የሚሆን በቂ ኃይል (calorie) አያገኝም። በተጨማሪም ሰውነታቸው ለመቀጨጭ እና መቀንጨር ይዳረጋል ::
# በተጨማሪም የበሽታ የመከላከያ ሀይላቸው (Immunity) ዝቅተኛ ስለሚሆን ለተለያዩ ኢንፌክሽኖች ተጋላጭ ይሆናሉ::
# ሕጻናት ከ 6 ወር በፊት ሌሎች ምግቦችን ቢጀምሩ ችግር ይኖረዋል?
አዎን! ከ6 ወር በፊት ሌሎች ምግቦችን መጀመር ለተቅማጥ እና ትውከት: የጡት ወተት መቀነስ እና የመሳሰሉት ችግሮችን ያስከትላል።
# ሕጻናት ተጨማሪ ምግቦችን ዘግይቶ ቢጀምሩ ጉዳቱ ምንድነው?
ህፃኑ በቂ የሆነ ክብደት እንዳይጨምር እና የተለያዩ ንጥረ ነገሮች (minerals) እና ቫይታሚን እጥረት እንዲያጋጥመው ያደርጋል። ይሄም የራሱ ከሆነ ከፍተኛ የጤና ችግርን ያመጣል::
🔷 ከ6 ወር - 2 ዓመት ያሉትን ህፃናት ምን እንመግባቸው?
በየትኛውም የእድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ ህፃናትም ሆነ አዋቂዎች የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ይኖርባቸዋል:: የተመጣጠነ ምግብ ማለት መሰረታዊ የሆኑ የምግብ ክፍሎችን የሚያካትት ነው:: እነሱም የእህል ዘር፣ ጥርጣሬ፥ አትክልት፥ ፍራፍሬ፥ ወተት እና የወተት ምርቶች፥ እንቁላል እና ስጋ ናችው::
ከላይ የተጠቀሱት ን የምግብ አይነቶች በተለያየ መንገድ ማዘጋጀት ይቻላል:: በሀገራችን የተለመደው አሰራር የምጥን ዱቄት ይባላል:: ይሄም በውስጡ የተለያዩ ከእህል ዘሮችን ማካተት ይቻላል ለምሳሌ 3 እጁ ከእህል ዘሮች ማለትም የተፈተገ ስንዴ ÷በቆሎ ÷ማሽላ ÷ጤፍ ÷አጃ እና የመሳሰሉት አድርጎ አንድ እጁን ደሞ ከጥራጥሬ አይነቶች ደሞ ባቄላ ÷ሽንብራ÷ አተር÷ ምስርን ÷ኦቾሎኒ ማካተት ይኖርበታል::
ለልጅዎ ምግብ ስጀምር ምን ያህል ነው መስጠት ያለብዎ?
ከ 6 - 8 ወር : በቀን 2 - 3 የቡና ሲኒ ☕️
ከ 9 ወር - 1 ዓመት : 4-5 የቡና ሲኒ☕️
ከ 1 ዓመት በላይ ግን በ ሲኒ መለካት አስፈላጊ አይደለም ሆኖም ግን 3 ዋና ዋና የምግብ ሰዓቶችን ጠብቆ በመስጠት በተጨማሪ ደሞ በ መሃል በመሃል 2 መክስሶችን መስጠት ይገባል::
# እድሜያቸዉ 6 - 8 ወር ላሉ ህፃናት ከአጥሚት ትንሽ ወፈር ያሉ ምግቦች ይመከራሉ ::
#እድሜያቸው 8-12 ወር ለሆናቸዉ ደሞ በከፊል ጠጣር(semi solid) ወይም ለስለስ ያለ ገንፎ በቀን 4-5 ጊዜ መመግብ ይኖርባቸዋል፡፡
በዚህ የእድሜ ክልል ላሉ ህፃናት ምግብ ስንጀምር የታሸጉ ምግቦችን(Processed food) ትተን በተፈጥሮ ከእህል ዘሮች ከተዘጋጁ እና በተለመዶው ምጥን ከሚባሉ ምግቦች ብንጀምር መልካም ነው:: እነዚህ ምግቦች በቀላሉ የሚፈጩ እና በዉስጣቸው ከፍ ያለ የብረት ማእድን ስለሚይዙ የደም ማነስን ይከላከላሉ ። በተጨማሪም ኃይል ሰጪ (carbohydrate) እና ገንቢ(protein) የሆኑ ምግቦች ናቸው::
ልጆች የእህል ዘሮችን ከለመዱ በዋላ በስለዉ የተፈጩ አትክልቶችን ቀስ በቀስ ማስለመድ ተገቢ ነው::
በመቀጠልም የተፈጨ አቦካዶ ሙዝ ፓፓያ ካስለመዱ በኋላ ቀስ በቀስ ደሞ እንቁላል እና የተፈጨ ስጋ መስጠት ይቻላል ።
በዶክተር ፋሲል መንበረ

ሕጻናት ለምንድነው ረጅም ሰዓት የሚያለቅሱት?
ሕጻናት የሚያለቅሱበት ምክንያት ብዙ ነው። የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው።
♦️ ጡት ሲፈልጉ ወይም ሲርባቸው
♦️ ሲደክማቸው ወይም መተኛት ሲፈልጉ
♦️ ሲበርዳቸው ወይም በጣም ሲሞቃቸው
♦️ ብቸኝነት ሲሰማቸው እና መታቀፍ ሲፈልጉ
♦️ ሆድ ቁርጠት ሲኖራቸው
♦️ ዳይፐራቸው ሲሞላ ወይም ሲያቃጥላቸው
♦️ ሆዳቸው ከመጠን በላይ ሲወጠር (በወተት ወይም በአየር )
♦️ ትኩሳት ሲኖራቸው
♦️ ጣት ላይ የተጠመጠመ ፀጉር ወይም ክር
♦️ እናት በዉስጣቸው ካፌን የያዙ መጠጦች ወይም ምግቦች አዘውትራ የምትጠቀም ከሆነ
♦️ አካላዊ ህመሞች እና ጉዳቶች (ማንኛዉም አካል ላይ ያለ ቁስል: የጆሮ ህመም እና የመሳሰሉት)
# ህፃናት በቀን ዉስጥ የምያለቅሱበት ሰዓት ሲደመር ከ1 - 3 ሰዓት ሊሆን ይቻላል ይሄ በብዙ ህፃናት ላይ የሚከሰት እና ተፈጥሯዊ ሂደት ነው ስለዝህ ብዙ አይጨነቁ ።
# ሆኖም ልጆዎ የሚያለቅስበት ሰዓት በቀን ዉስጥ ከ3 ሰዓት በላይ ከሆነ እና ለቅሶው በሳምንት ዉስጥ ቢያንስ 3 ቀን እና ከዛ በላይ ከሆነ እና ከ 3 ሳምንት በላይ ከቆየ ልጆዎ የሆድ ቁርጠት(Infantile colic) አለው ማለት ነው ::
ስለዚህ በቅርብዎ የሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ የሕጻናት ሐኪምን ያነጋግሩ።