St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
SPHMMC Community was recognized by the Federal Ministry of Health for their resilient and responsible response to COVID 19.

The college runs two COVID 19 centers within the city. The lives of many have survived as a number of health professionals have sacrificed life for the sake of beloved citizens at the expense of their own wellbeing and stay in life living up to their professional ethics.
We really thank the government for its move to well acknowledge the immense sacrifice paid by college professionals.
We really thank you, St. Paul, and Ethiopian health professionals.
What is portrayed in the picture below is College provost Dr. Wondimagegn while receiving the trophy from the hands of Addis Ababa City Deputy mayor.
#Hepatitis B is mostly transmitted from mother to child during childbirth or early childhood.

All newborns should be vaccinated against Hepatitis B at birth.

MOTHERS CAN’T WAIT!
It’s World Breastfeeding Week 2021, we are happy to be participating! This year, the theme for breastfeeding week is " Protect Breastfeeding: A shared Responsibility."

የዓለም የጡት ማጥባት ሳምንት በኢትዮጵያ ጡት የማጥባት ልምድን በተሻለ ለማስጠበቅና የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ፤ በመንግስት፣ በጤናው ስርዓት፣ በስራ ቦታዎች እንዲሁም በማህበረሰብ ደረጃ ለጡት ማጥባት አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር ሃላፊነታቸውን በመወጣት ሊረባረቡ ይገባል።
#worldbreastfeedingweek2021
#World_Breastfeeding_Week
#Breastfeeding
#WBW2021
የሕይወት መሰረት መጣል ::
ጡት ማጥባት ህጻኑ በተወለደ በአንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ መጀመር አለበት፡፡ ይህም
• ህጻኑ ጥሩ የአልሚ ምግብና በሽታ የመከላከል አቅም ያለውን የመጀመሪያ ወተት (እንገር) እንዲያገኝ ይረዳል፡፡
• ህጻኑ በመጀመሪያው አንድ ሰዓት ውስጥ ያለውን የተሻለ ተፈጥሯዊ ጡት የመጥባት ብቃትና ፍላጎት ለመጠቀም፤ እንዲሁም የእናት ጡት የተሻለ ወተት የማመንጨት አቅም እንዲኖረው ያደርጋል፡፡
• በዚህ የህይወት መነሻ በሆነችው አንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ ከእናት ጡት ውጭ ሌላ ፈሳሽ ወይም ወተት መስጠት ህጻናት እነዚህን ጥቅሞች በቀሪ ዘመናቸው እንዲያጡ ያደርጋል፡፡
• ስለሆነም ህጻኑ እንደተወለደ (እንግዴ ልጅ ከመውጣቱ በፊትም ቢሆን) ወዲያውኑ ወደ ደረትዎ አስጠግተው ይያዙ፡፡ከዛም በመጀመሪያ የጡትዎን ጫፍ የሕጻኑን ከንፈሮች ያስነኩ፤ በመቀጠልም የሕጻኑ አፍ በሚከፈትበት ጊዜ ህጻኑን በደንብ አስጠግተው ጡትዎን ያጉርሱት፡፡
መልካም መሰረት ለመገንባት በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት የጡት ወተት ብቻ መስጠት
• በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ህጻኑ ለእድገቱ የሚያስፈልገዉን ምግብና ዉሀ ከጡትዎ ወተት ብቻ ማግኘት ይችላል፤ ስለዚህ 6 ወር እስኪሞላው ህጻኑ የእናት ጡት ወተት ብቻ መጥባት አለበት፡፡
• ይህ ማለት በጤና ባለሞያ ካልታዘዘ በቀር ከጡት ወተት ሌላ ምንም አይነት ነገር ማለትም የተለያዩ የእንስሳትና የፋብሪካ ወተቶችን፣ ምግቦችን፣ ፈሳሾችን እና ዉሀን የመሳሰሉትን መስጠት ፈጽሞ አይመከርም፡፡
• በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት (180) ቀናት ከጡት ወተት ውጭ ተጨማሪ ነገር መስጠት የጡትዎን ወተት የማመንጨት ብቃት እንዲቀንስ ከማድረጉም በተጨማሪ ህጻኑን ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣል፡፡
የእናት ጡትን በአግባቡ ማጥባት ሲባል
ህጻኑ ቀንና ሌሊት የቻሉትን ያህል ጊዜ ማጥባት ጡቶችዎ በቂ ወተት እንዲያመነጩ ከመርዳቱ በተጨማሪ ጡቶችዎ በጣም አግተው ህመም እንዳያስከትልብዎ ይከላከላል፡፡ህጻኑ ተጨማሪ መጥባት መፈለጉም በደንብ እያደገ ለመሆኑ ጥሩ ማሳያ ምልክት ነው፡፡ ጡቶችዎ በጣም እንዳያግቱ የማጥቢያ ሰዓትዎ ማሳለፍ የለብዎትም፤ ህጻኑ ሳይጠባ እንኩዋን ቢቀር የተወሰነው ወተት አልበው ጡቶችዎ ላላ እንዲሉ ማድረግ አለብዎት። ያለቡትን የጡትዎን ወተት በንጽህና ከድነው በማስቀመጥ ህጻኑን መመገብ ይችላሉ፤ ያለቡትን የጡትዎን ወተት ግን ከ 8 ሰዓት በላይ ማስቀመጥ የለብዎትም፡፡

ህጻኑ በጥሩ ሁኔታ እየጠባ መሆኑን ለማወቅ የሚከተሉትን ነጥቦች ማስተዋል ጠቃሚ ነው፡፡
⇒ የህጻኑ ሆድ ከእርስዎ ሆድ ጋር ትይዩ መሆኑን ⇒ የህጻኑ ራስና ሰዉነት ክንድዎ ላይ በአንድ መስመር በትክክል ማረፉን
⇒ የህጻኑ አካል ሙሉ በሙሉ ድጋፍ ማግኘቱን ⇒ የህጻኑ አፍንጫ በጡትዎ ጫፍ ትይዩ መሆኑን
⇒ ህጻኑ ክንድዎ ላይ ያረፈበት ሁኔታ ጥሩ ካልሆነ ወይም አንዳች ህመም ከተሰማዋት ህጻኑ በቀስታ ጡትዎ ላይ አላቀው እንደገና ማስጀመር ያስፈልጋል፡፡ ህጻኑን ለማጥባት በደንብ አስተካክለው መያዝዎን ለማረጋገጥ
⇒ አፉ በደንብ ተከፍቶ ጠቆር ያለዉን የጡትዎን ክፍል አብዛኛዉን መጉረሱን ⇒ የታችኛዉ ከንፈሩ ወደዉጭ ገልበጥ ማለቱን ⇒ አገጩ ጡትዎን መንካቱን
⇒ ጉንጮቹ ሞላ ማለታቸዉንና
⇒ በመሀል ትንሽ እያረፈ በደንብ መሳቡን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

ህጻኑ በቂ ወተት እየጠባ (እያገኘ) መሆኑን ለማወቅ
⇒በቀን ቢያንስ 6 ጊዜ ያህል ሽንት መሽናቱን፤
⇒ ክብደቱ እየጨመረ መሄዱን፤ እና
⇒ የህጻኑ ሽንት ፈዘዝ ያለ ቀለም ያለውና ከበድ ያለ ሽታ የሌለው መሆኑን መከታተል ያስፈልጋል፡፡

የአባቶችና ቤተሰቦች እገዛ ጡት ማጥባትን እውን ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
⇒ ህፃናትን በመንከባከብና ማሳደግ ሴቶች ሰፊውን አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ሲሆን ይህም ለሥራ ጫና የሚያመጣና ለሥራ ተሳትፎ ያላቸውን ጊዜ የሚቀንስ ነው፡፡
⇒ የልጃቸውን ጤናና እድገት ለመጠበቅ ሁለቱም ቤተሰቦች ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡
⇒ አባቶች (ቤተሰቦች) እገዛ እንዲያደርጉ ማድረግ የጡት ማጥባትን በሰዓቱ በማስጀመር፣ በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ጡት ብቻ ለማጥባት እና ጡት ማጥባትን የማስቀጠል ምጣኔን በሁለት እጥፍ ከፍ እንዲል ያደርጋል።
የሕይወት መሰረት መጣል

ህጻኑ በቂ
ወተት እየጠባ (እያገኘ) መሆኑን ለማወቅ
⇒በቀን ቢያንስ 6 ጊዜ ያህል ሽንት መሽናቱን፤
⇒ ክብደቱ እየጨመረ መሄዱን፤ እና
⇒ የህጻኑ ሽንት ፈዘዝ ያለ ቀለም ያለውና ከበድ ያለ ሽታ የሌለው መሆኑን መከታተል ያስፈልጋል፡፡

የአባቶችና ቤተሰቦች እገዛ ጡት ማጥባትን እውን ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
⇒ ህፃናትን በመንከባከብና ማሳደግ ሴቶች ሰፊውን አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ሲሆን ይህም ለሥራ ጫና የሚያመጣና ለሥራ ተሳትፎ ያላቸውን ጊዜ የሚቀንስ ነው፡፡
⇒ የልጃቸውን ጤናና እድገት ለመጠበቅ ሁለቱም ቤተሰቦች ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡
⇒ አባቶች (ቤተሰቦች) እገዛ እንዲያደርጉ ማድረግ የጡት ማጥባትን በሰዓቱ በማስጀመር፣ በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ጡት ብቻ ለማጥባት እና ጡት ማጥባትን የማስቀጠል ምጣኔን በሁለት እጥፍ ከፍ እንዲል ያደርጋል።
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ #በኢትዮጵያ_ሆስፒታሎች_ጥምረት_ለጥራት ፕሮግራም ከአገር አቀፍ_ሆስፒታሎች #የ3_ሚሊዮን ብር ተሸላሚ ሆኗል!

ኮሌጁ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ እና ለዚህ ለትልቅ ስኬት ያበቃችሁ መላው ሠራተኞች ምሥጋና ይገባችኋል።ይህ የልፋታችሁ ውጤት ነው።
አብራችሁን የምትሠሩት ባለድርሻ አካላትንም እናመሰግናለን ።
እንኳን ደስ ያላችሁ።
በትላንትናው ዕለት በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር ከ84 ቀናት በኋላ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።
********************
በኢትዮጵያ ያለው የኮቪድ-19 ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህም በበሽታው የሚያዙ ፣ በጽኑ የሚታመሙና ህይወታቸውን የሚያጡ ወገኖቻችን ቁጥር ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ በከፍተኛ መጠን ጨምሯል።

በትላንትናው ዕለት ለ7‚598 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 687 ግለሰቦች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህ ማለት ናሙና ከሰጡ 100 ግለሰቦች 9ኙ (9%) የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። 270 ግለሰቦች ደግሞ በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡

በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በዚህ ፍጥነት እጨመረ የሚሄድ ከሆነ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ይጨምራል። ይህ ደግሞ በኮቪድ-19 ህክምና ማዕከላት ላይ ከፍተኛ የሆነ የአልጋ ፣ ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ እና ኦክስጂን እጥረት ሊያስከትል ይችላል፡፡

በኮቪድ-19 ቫይረስ የሚያዙ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ እና ህይወታቸውን የሚያጡ ግለሰቦች ቁጥር እያሻቀበ ይገኛል።ስለሆነም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ግለሰቦች፤ ቤተሰቦች፤ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፤ የሐይማኖት ተቋማት ፣ ሲቪክ ማህበራት ፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፤ የጤና ባለሙያዎች ፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ማስክ በማድረግ ፣ የእጃቸውን ንጽህና በተደጋጋሚ በመጠበቅ ፣ በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ በተጨማሪም የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የከፋ ችግር እንዳያስከትል በጋራ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስቧል ።
የህፃናት ጉንፋንን ቤት ዉስጥ እንዴት ማከም ይቻላል ?

ጥቂት ሰለ ሕጻናት ጉንፋን

በተለምዶ ጉንፋን የምንለው በሺታ የላይኛውን የትንፋሽ አካላትን(አፍንጫ እና ጉሮሮ አካባቢን ) የሚያጠቃ የተለመደ በሽታ አይነት ሲሆን ከአዋቂዎች ይልቅ ልጆች ላይ በተደጋጋሚ ይታያል::

ልጆች እንደየእድሜ ያቸው ቢለያይም በዓመት ዉስጥ በ አማካይ ከ 6-8 ጊዜ ጉንፋን ሊይዛቸው ይችላል:: በተለይ ደሞ ቤት ዉስጥ ተለቅ ተለቅ ያሉ ትምህርት ቤት ዉለው የሚመጡ ልጆች ካሉ በቀላሉ ወደ ታናናሾቻቸው ሊያስተላልፉ ይችላሉ::

የህፃናት ጉንፋን መንስኤው ምንድነው?

ዋና መንስኤውም የተለያዩ አይነት ያላቸው ቫይረሶች ናቸው ::
ለምሳሌ÷ አዴኖ ቫይረስ ፣ኮሮና ቫይረስ ፣ራይኖ ቫይረስ፣ ኢንፍሉዌንዛ ቫይረስእና የመሳሰሉት ጉንፋንን ያመጣሉ።

አንዳንዴም እ ከጉንፋንም አልፈው የተለያዩ ህመሞች ሊያመጡ ይችላሉ ።ለምሳሌ

#የሳንብ ምች(Pneumonia)

#የልጆች ከፍተኛ የአየር ቧንቧ መቆጣት እና መጥበብ (Brochiolitis)
#የአንጀት ኢንፌክሽን እና የመሳሰሉትን ሊያመጡ ይችላሉ ::

ጉንፋን እንዴት ይተላለፋል?

ጉንፋን ከያዘው ሰዉ በሳል ወይም በማስነጠስ ወቅት ከአፍ እና ከአፍንጫ በሚወጣው የዉሀ ቅንጣት (air droplet) ወይም በቀጥታ ንክኪ ይተላለፋል ።

በተለይ ደሞ አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ህፃናት ጠንካራ የበሽታ የመከላከል እና የመቋቋም ችሎታ ስለሌላቸው በቀላሉ በጉንፋን እና በሌሎች ኢንፌክሽኖች የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው ፡፡

ይሄ ብቻ ሳይሆን እንቦቃቅላ ህፃናት (Infants) እና ጨቅላ ህፃናት (neonates)በአፍንጫቸው ስለሚተነፍሱ አፍንጫቸው በፈሳሽ ወይም በንፍጥ ሲዘጋ ለመተንፈስ በጣም ይቸገራሉ ።

የህፃናት ጉንፋንን ቤት ዉስጥ እንዴት ማከም ይቻላል ?

-- ለብ ያለ ዉሃ ዉስጥ ትንሽ ጨው አርጎ አፍንጫቸው ቀዳዳ ዉስጥ 2 ጠብታ ማድረግ በመቀጠል
-- የአፍንጫ ቀዳዳዎችን በመምጠጫ(bulb suction) ማጽዳት
-- ትኩሳትን የሚቀንስ መድሃኒት የመጠቀም ፣
--ትኩስ ትኩስ ነገሮችን ማጠጣት
-- ንፍጥ እና ትኩሳት በጣም አስፈላጊ ፈሳሾችን እና ንጥረ ነገሮችን ይዘው ስለሚወጡ ተጨማሪ ፈሳሽ ነገሮችን ማግኘት ይኖርባቸዋል ::
--ተጨማሪ ምግቦችን በደንብ መመገብ
--የሕፃኑን ክፍል በደንብ ማፅዳት ማናፈስ
-- ቤቱን በውሀ እንፋሎት ማጠን

የ ጉንፋን ምልክቶች ሙሉ በሙሉ መጥፋት እስከ 2 ሳምንታት ይላል ።
👉 ሆኖም ማንኛውም የከፋ የሕመም ምልክቶች(አደገኛ ምልክቶች)ካሳዩ ሐኪምዎን ማማከር ይኖርቦታል ::

አደገኛ ምልክቶች የሚባሉት የትኞቹ ናቸው?
🔘 ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
🔘 ማቃሰት
🔘 ተደጋጋሚ ማስታወክ
🔘 በትኩሳት ማስታገሻ የማይቀንስ ከፍተኛ ትኩሳት
🔘 የትክ ትክ አይነት ሳል
🔘 ራስን መሳት ወይም ማንቀጥቀጥ
🔘 የከንፈር ወይም የጣት መጥቆር

👉ከላይ ያሉት ምልክቶች ልጆዎ ላይ ቀጣዩ በ አፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም ይሂዱ ።

መረጃው ብዙዎች እንዲያነቡ ሼር ያድርጉ ።

ዶ/ር ፋሲል መንበረ
ረዳት ፕሮፌሰር እና የ ህፃናት ስፔሻሊስት ሐኪም
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ሕክምና ኮሌጅ
የእናት ጡት ወተትን መጨመር የሚቻልባቸው 12 ዘዴዎች

🔘 አሁን አሁን ብዙ እናቶች ከ ወለዱ በዋላ ወድያው ጡቴ ወተት የለውም በማለት የቆርቆር ወተት (formula milk) ያማስጀመራሉ::

👉 በ መጀመርያ እንዴት እንደምታጠቢ የጤና ባለሙያን ምክር ተግባራዊ አድርጊ።ለምሳሌ ስለህፃኑ ትክክለኛ አቀማመጥ(positioning) እና
ጡት አያያዝ እና አጠባብ (Attachment)

👉 ጡትሽ ቶሎ ቶሎ ማለብ ወይም ማጥባት 🤱

👉 በቂ እና የተመጣ ጠ ነ ምግብ መውሰድ ።

👉 ትኩስ ፈሳሽ ምግቦችን መውሰድ ።

👉 በኦፕራሲዎን ወይም በስቲች ምክንያት ህመም ካለሽ ሀኪምሽን አማክረሽ ማስታገሻ መድሃኒት መውሰድ ።

👉 ከልጅሽ ጋር ገላ ለ ገላ (ቆዳ ለ ቆዳ )ንክኪ ማድረግ ይሄንን ለማድረግ ልጅሽ ደረትሽ ላይ ዳይፐር ብቻ አርገሽ አስተኝው ።

👉 ለብ ባለ ዉሃ የተነከሩ 2 ፎጣዎች ከጡትሽ ከላይ እና ከታች ይዘሽ ቀስ ብለሽ ከላይ ወደ ታች ማሳጅ ማድረግ።

👉 ሙቅ ሻወር መውሰድ በተለይ ከ ማጥባትሽ በፊት።

👉 በቂ ፈሳሽ መውሰድ በተለይ ከአትክልት እና ፍራፍሬ ፓፓያ, ብርቱካን, ሃባብ ማንጎ መውሰድ ።

👉 በተቻልሽው መጠን በቂ እንቂልፍ እና እረፍት ማድረግ(ልጅሽ ሲተኛ አብረሽ መተኛት እና እረፍት ማድረግ)

👉 አለመጨነቅ ዘና ማለት

👉 አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ሁሌም ከ ልጅሽ ጋር ሁኚ

👉 እነዚህን ሁሉ አርገሽ ምንም ለውጥ ከሌለ ወይም ልጅሽ ትኩሳት እና በጣም መነጫነጭ ካመጣ እንደራበው ጡትሽን ቀድመሽ ትሰጭ እና ቀጥሎ በንፅህና የተዘጋጀ የጣሳ ወተት መስጠት ትቺያለሽ ይሄ ግን የመጨረሻ አማራጭ ብታደርጊው መልካም ነው::

ዶ/ር ፋሲል መንበረ (በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የህፃናት ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር)
በአዲስ አበባ በአንድ ቀን ብቻ 839 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ቫይረስ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል።
********
በኢትዮጵያ ያለው የኮቪድ-19 ስርጭት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። በበሽታው የሚያዙ ፣ በጽኑ የሚታመሙና ህይወታቸውን የሚያጡ ወገኖቻችን ቁጥር ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ በከፍተኛ መጠን ጨምሯል።

በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር ከ100 ቀናት በኋላ ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል። በትላንትናው ዕለት ለ7,518 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 882 ግለሰቦች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህ ማለት ናሙና ከሰጡ 100 ግለሰቦች 12ቱ (12%) የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል ይህ ደግሞ ከ90 ቀናት በኋላ በኮቪድ-19 የመያዝ ምጣኔ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

በአንድ ቀን ብቻ 22 ግለሰቦች ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የገቡ ሲሆን በአጠቃላይ 324 ግለሰቦች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ 10 ግለሰቦች በትላንትናው ዕለት በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል።

አዲስ አበባ በትላንትናው ዕለት ከፍተኛውን በኮቪድ-19 የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር ያስመዘገበች ሲሆን ለ6,211 ግለሰቦች ምርመራ ተደርጎላቸው 839 ግለሰቦች ላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ናሙና ከሰጡ 100 ግለሰቦች 14ቱ (14%) የኮቪድ-19 ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በዚህ ፍጥነት እጨመረ ከሄደ የአልጋ ፣ ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ እና ኦክስጂን እጥረት ሊያጋጥመን ስለሚችል። ሕብረተሰቡም ይሄንን በመገንዘብ አሁንም የኮቪድ-19 የመከላከያ መንገዶችን ማለትም :-

* ማስክ በማድረግ
* የእጃቸውን ንጽህና በተደጋጋሚ በመጠበቅ
* በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ
* የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የወረርሽኙን ስርጭት እና መዛመት መቆጣጠር ይኖርበታል።

ምንጭ: ኢ.ሕ.ጤ.ኢ
የኮቪድ-19 ወቅታዊ ሁኔታና የክትባት ሂደቱን በተመለከተ የጤና ሚንስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ መግለጫ ሰጥተዋል። ከተናገሩት ዋና ዋና ጉዳዮች እነሆ፡-

ክትባት

የኮቪድ-19 ክትባትን በሚመለከት እስካሁን ባለው ሂደት 2 ሚሊዮን 254 ሺህ 270 ዜጎች የመጀመሪያ ዙር እንዲሁም ከ300 ሺህ በላይ ዜጎች ሁለተኛውን ዙር ክትባት አግኝተዋል፡፡በአዲስ አበባ ከነገ ነሃሴ 7 ጀምሮ በክልሎች ደግሞ ከነሃሴ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ክትባቱ መሰጠት ይጀመራል፡፡

በአዲስ አበባ ካለው ከፍተኛ የወረርሽኙ ስርጭት አንፃር ክትባት ላልወሰዱ እድሜያቸው ከ35 አመት በላይ ለሆኑና በሌሎቸ ክልሎች ደግሞ እድሜያቸው ከ55 አመት በላይ ለሆኑ ክትባቱ ይሰጣል፡፡

ተጓዳኝ የጤና ችግር ያለባቸው እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ ለሆኑ በመላው አገሪቱ የሚገኙ ዜጎች እና
የስራ ባህሪያቸው ከበርካታ ሰዎች ጋር ለሚያገናኛቸው ሰራተኞችም እንዲሁ ክትባቱን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ ታቅዷል፡፡

የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ስደተኞችና የጎዳና ተዳዳሪዎችም የጤና ቢሮዎች በሚያመቻቹት መርሃ ግብር መሰረት ክትባቱን ያገኛሉ፡፡

ወረርሽኙ ጨምሯል፡፡
ባለፉት ሶስት ሳምንታት የወረርሽኙ ስርጭት ጨምሯል፡፡በሶስት ሳምንታት ውስጥ ናሙና ከሰጡ ሰዎች መካከል ኮቪድ-19 የተገኘባቸው በሳምንታዊ ምጣኔ ከነበረበት 2 ነጥብ 8 ወደ 7 ነጥብ 4 በመቶ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት 324 ግለሰቦች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ ፡፡ በሽታው የሚገኝባቸው አማካይ ቁጥር በሳምንት ከ831 የአራት እጥፍ ጭማሪ በማሳየት ወደ 3 ሺህ 302 ከፍ ብሏል፡፡

ማስክ አጠቃቀም

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ) የሚጠቀሙ ሰዎች ምጣኔ ቀንሷል፡፡ እየቀነሰ መጥቷል፡፡
አሁን ላይ በአዲስ አበባ 59 በመቶ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ከተሞች ደግሞ ወደ 20 በመቶ አሽቆልቁሏል፡፡

በሶስተኛው ዙር የወረርሽኙን ስርጭት በሌሎች አገራት ያደረሰው ከፍተኛ ጉዳት በኢትዮጵያ እንዲከሰት ሊያደርግ ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል::
በኢትዮጵያ ያለው የኮቪድ-19 ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ይህም በበሽታው የሚያዙ፤በፅኑ የሚታመሙና ህይወታቸውን የሚያጡ ወገኖች ቁጥር በተለየ ሁኔታ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ይገኛል።

በኢትዮጵያ አንድ በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዘ ግለሰብ ከተመዘገበበት ዕለት መጋቢት 4/2012 ጀምሮ 286‚286 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፣264,872 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፤342 ሰዎች አሁን ላይ በፅኑ ህሙማን ክፍል ይገኛሉ። እንዲሁም 4‚450 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በትላንትናው እለት 6,789 ግለሰቦች ናሙና የሰጡ ሲሆን 873 ያህል ግለሰቦች የኮቪድ-19 ቫይረስ እንዳለባቸው በላብራቶሪ የምርመራ ውጤት ተረጋግጧል፡፡ ይህ ማለት ናሙና ከሰጡ 100 ግለሰቦቸ 13ቱ ወይም (13%) በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

በዚሁ ዕለት አዲስ አበባ በኮቪድ-19 ህይወታቸውን ያጡ እና በኮቪድ-19 የተያዙ ግለሰቦች ከፍተኛ ቁጥር ካስመዘገቡ ክልሎች ቀዳሚውን ድርሻ ይይዛል:-

* በአዲስ አበባ 5‚705 ግለሰቦች ናሙና ሰጥተው 838 ግለሰቦች ወይም 15 ከ 100 (15%) ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል እንዲሁም በትላንትናው ዕለት ህይወታቸውን ካጡ 10 ግለሰቦች 9 ግለሰቦች ከአዲስ አበባ ናቸው።

በዚህ ፍጥነት በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ፣ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ግለሰቦች እጨመረ ከሄደ የአልጋ ፣ ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ እና ኦክስጂን እጥረት ሊያጋጥመን ስለሚችል። ሁሉም የማሕበረሰብ ክፍል ማስክ በማድረግ፣ የእጅን ንጽህና በተደጋጋሚ በመጠበቅ ፣ በማንኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ እና የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የወረርሽኙን ስርጭት እና መዛመት መቆጣጠር ይኖርበታል።
ኢ.ሕ.ጤ.ኢ
የዛሬ ኮሮና ሪፖርት
2 ሰው ሕይወቱ አልፏል ።
898 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ።
353 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ ናቸው።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7,420 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 898 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 287,184 ደርሷል።

በሌላ በኩል 63 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 264,935 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መጥቷል። እባክዎን ራስዎን እና ቤተሰብዎን ይጠብቁ ።

የሶሻል ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙን!
ቴሌግራም
https://t.me/spmmc
ትዊተር
https://twitter.com/SPHMMC_Official
ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/sphmmc
ኢኒስትግራም፡- st_pauls_hospital_mmc