የህፃናት ጭንቅላት መናጋት(shaken baby syndrome) ምንድነው?
t.me/spmmc
የህፃናት ጭንቅላት መናጋት በህፃናት ላይ የሚደርስ የጥቃት አይነት ሲሆን የሚከሰተውም የጨቅላ ህፃን ልጅ ጭንቅላት በሀይል ሲወዘወዝ ወይም ሲነቀነቅ ነው ::
ይሄ አደጋ ብዙ ጊዜ የሚከሰተው አሳዳጊዎች የህፃኑ ለቅሶ ለማስቆም በሚል ካለማወቅ ወይም በጣም ከመጨነቅ የተነሳ ልጁን በሀይል ሲወዘውዙት ነው ::
በዚህ ወቅት የልጁ አንጎል በራስ ቅሉ ውስጥ ከኃላ ወደ ፊት ከፊት ወደ ኋላ እየሄደ ከራስ ቅሉ (አጥንቱ) ይጋጫ ል ።በዚህም ጊዜ በተለያዩ አይምሮ ወይም አንጎል ክፍል ዉስጥ ደም መድማት ያስከትላል።
የህፃናት ጭንቅላት መናጋት (shaken baby syndrome) የደም ስሮችን እና የአንጎል ህዋሶችን በማውደም አይምሮ ዉስጥ በቂ የደም ዝውውር እንዳይኖር እና የነርቭ ህዋሶች ኦክሲጅን እንዳያገኙ ይከለክላል❗️
ከዚህ አልፎ ተርፎም የሕፃናቱን አንጎል በመጉዳት ሞትን ሊያስከትል ይችላል‼️
✔️ ህፃናት በተለያየ ምክኒያት ያለቅሳሉ፤ ወላጆች አልያም ተንከባካቢ ሞግዚቶች የሚያለቅሰዉን ህፃን ተረጋግተው ማባበል ይጠበቅባቸዋል።
✔️ በማልቀስ ላይ ያለው ልጅዎ ዝም አልል ሲል ተረጋግተው የሚችሉትን ሁሉ ያድርጉ።
በፍፁም ጨቅላ ህፃን ልጅዎን በሀይል አይወዝዉዙት። በህፃናት የአንጎል ላይ የማይስተካከል ጉዳት ለማድረስ የጥቂት ሰኮንዶች መናጋት ብቻ ይበቃል❗️
ልጁዎትን በመንከባከብ ረገድ ሌላ ተቀጣሪ የሆነ ሰው ፣ የቤት ሠራተኛ ፣ እህትና ወንድም ወይም አያት ካገዟችሁ ስለ ህፃናት የአንጎል መናጋት አደጋን እንደሚያውቁ እርግጠኛ ይሁኑ ‼️
🔷 ጨቅላ ልጁዎት በጣም አልቃሻ እና አስቸጋሪ ከሆነ፣ ለሌሎች ከመስጠትዎ በፊት ቆም ብለው ያስቡ።
ታዲያ የህፃናት አንጎል መናጋት(shaken baby syndrome) ምልክቶች ምንድናቸው?
🔘 በጣም የከፋ ከ ወትሮ ለየት ያለ ለቅሶ ወይም መነጫነጭ
🔘 የአተነፋፈስ ችግር ለምሳሌ ማቃሰት
🔘 ራስን መሳት እና ማንቀጥቀጥ
🔘 ኃይለኛ ትውኪያ
🔘 የገረጣ ወይም ደም ያዘለ ቆዳ
🔘 አልፎ አልፎ ህፃኑ የመናጋት አደጋ ደርሶበት እንኩዋን ጤነኛ መስሎ ሊታይ ይችላል❗️
ከላይ ያሉ ምልክቶች ግን ሁልጊዜ ከአይምሮ መናጋት ጋር ብቻ ይያያዛሉ ማለት አይደለም ‼️ ሌሎች ህመሞችም ከላይ ያሉትን ምልክቶች ሊያመጡ ይችላሉ ::
ሆኖም ጥርጣሬ ካለዎት ግን ሐኪምዎን ያማክሩ ::
ዶር ፋሲል መንበረ
የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና ክትባት ዙሪያ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
የመግለጫቸው ዋና ዋና ዓብይ ሀሳቦች የሚከተሉት ናቸው
በባለፈው ሳምንት ብቻ 5547 ሰዎች በኮቪድ-19 የተያዙ ሲሆን ከጥቂት ወራት በፊት ሁለት እና ሶስት በመቶ የነበረው የስርጭት ምጣኔ በአሁኑ ሰዓት በአማካይ አስራ ሁለት (12 %) በመቶ ደርሷል፡፡
በየቀኑ ወደ ጽኑ ህሙማን ማዕከላትም የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ ጨምሯል። እስከ ትላንት ድረስ 510 ሰዎች በጽኑ ታመዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት ብቻ 66 ሰዎች በወረርሽኙ አርፈዋል። በአሁኑ ሰዓትም በቀን በአማካይ 9 (ዘጠኝ) ሰዎች እየሞቱ ነው።
አሁን ላይ ያለው ቁጥራዊ መረጃዎችና ሁኔታዎች የሚያሳዩት የሶስተኛው ዙር ማዕበል (3rd wave) በሀገራችን እንደጀመረ ያመላክታል።
ሕብረተሰቡ የሚጠበቅበትን መሰረታዊ የመከላከያ መንገዶችን አጠናክሮ የማይተገብር ከሆነ ነገሮች እየከፉ ሊመጡ እንደሚችሉ ሳይንሳዊ ትንበያዎች ያሳያሉ።
በመሆኑም መሰረታዊ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች በተጨማሪ ክትባቱን መከተብ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ክትባቶችን ለማህበረሰቡ ተሰጥቷል ።
ርቀትን በ 2 ሜትር መጠበቅ፣ ማስክን ሁልጊዜና በአግባቡ ከማድረግ ባለፈ የእጅ ንፅህናን በተገቢው መንገድ መጠበቅ የሚኖርበት ሲሆን አላስፈላጊ መሰባሰቦችን መቀነስ (በተለይ በዝግ ቦታዎች ላይ የሚደረጉትን)፤ እንዲሁም ምልክቶች ሲታዩም በአፋጣኝ ራስን በማግለል የባለሙያ ምክር መጠየቅ ይገባል ።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ ቁጥር 30/2013 ማሻሻያ በማድረግ አዲስ መመሪያ (መመሪያ ቁጥር 803/2013) ወጥቷል።
መመሪያ 803/2013 ሊንኩን ተጭነው ማግኘት ይችላሉ፡-
https://drive.google.com/file/d/1c63ANoG1UaFhssD6RZzitwroUNDNe1Ek/view?fbclid=IwAR1PfjwUw4CKLPJdf3EAN7gaAXK27zTeSBGIZhttWbvr0tpHYXvLuFgNrJ0

Google Docs
Covid-19 Directive 803 _210822_140019.pdf
የኮቪዴ-19 ወረርሽኝ የመከላከልና ለመቆጣጣር ተሻሽሎ የወጣውን መመሪያ ቁጥር 803/2013 ያውቁታል?
መመሪያው ’የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጣር ስላሚወሰድ ክልከላዎችን እና ስለሚጣሉ ግዴታዎች ስለመወሰን ተሻሽሎ የወጣ መመሪያ ነው፡፡ ሙሉ መረጃውን ማስፈንጠሪያውን በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡
t.me/spmmc
https://drive.google.com/file/d/1c63ANoG1UaFhssD6RZzitwroUNDNe1Ek/view?fb
መመሪያው ’የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጣር ስላሚወሰድ ክልከላዎችን እና ስለሚጣሉ ግዴታዎች ስለመወሰን ተሻሽሎ የወጣ መመሪያ ነው፡፡ ሙሉ መረጃውን ማስፈንጠሪያውን በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡
t.me/spmmc
https://drive.google.com/file/d/1c63ANoG1UaFhssD6RZzitwroUNDNe1Ek/view?fb
Google Docs
Covid-19 Directive 803 _210822_140019.pdf
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM

የኮቪድ-19 ምልክት ያላቸው እና ምርመራ ማድረግ የሚፈልጉ በ30 ደቂቃ ውስጥ ውጤት የሚያደርስ ፈጣን የኮቪድ-19 መርመሪያ መሳሪያ (Antigen RDT) አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡
t.me/spmmc
t.me/spmmc
ለ2013 ዓ.ም የህክምና ዶክትሬት ትምህርት ወይም (NIMEI) እጩ ተማሪዎች በሙሉ
__________
በ2013 ዓ.ም የህክምና ዶክትሬት ትምህርት ወይም New Innovative Medical Education Initiative (NIMEI) ለመከታተል በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒም ሜዲካል ኮሌጅ የተሰጠውን የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ በኮሌጁ የተመረጣችሁ ሰልጣኞች ትምህርታችሁን የምትከታተሉባቸውን ኮሌጆች ምድብ አባሪ በተደረገው ሊንክ( https://www.moh.gov.et/ejcc/am/NIMEI_Final_Deployment) መሰረት ኮሌጆቹ በሚያወጡት የምዝገባ ጊዜ ሰሌዳ ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃል፡፡

ወላጆች ሊያውቋቸው ስለልጆች ሊያውቁት የሚገባ 10 አበይት ጉዳዮች
---------------------------------------------------
ወላጆች ማድረግ ያለባቸው
1. ለልጆች ስለሚችሉት ነገር እንጂ ስለማይችሉት ነገር አይንገሩዋቸው። ዘወትር አሉታዊ ንግግርን የሚሰሙ ልጆች ይህንን አሉታዊውን ንግግር ይላመዱታል፡፡
በጣም አንገብጋቢ ሁኔታ ላይ ከባድ አሉታዊ ቃላትን ከመናገር ከተቆጠቡ ልጆች የሚጠቀሙበትን ቃላት ይሰማሉም፤ያከብራሉም፡፡
2. ልጆችዎ እንዲይዙ የሚፈልጉትን ባህሪ ለማየት ለልጅዎችዎ አስተማሪ ቃላትን ይናገሩ፡፡
ልጆች መሆን የሚፈልጉት ጎልማሶች እንዲሆኑላቸው የሚመኙትን ነው፡፡
ልጆቻችን ተወዳጅና ብቁ እንዲሆኑ ከጠበቅን ልጆችም
እንደዚያ ለመሆን ጥረት ያደርጋሉ፡፡
3. ልጆች የመወደድና ብቁ እንደሆኑ ስሜት ካደረባቸው በራስ መተማመናቸው ይጨመራል።
በቤተሰብ ደረጃ ማራኪ ምግብ ማዘጋጀት ልጆቹ የባለቤትነት ስሜት እንዲያዳብሩ እና ለቤተሰብ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ስሜት ያዳብራሉ።
4. በቤተሰብ ደረጃ አብሮ በአንድ መዓድ ( ጠረጴዛ )መመገብ በቤተሰብ ደረጃ ማህበራዊ ግንኙነት እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል ፡፡
ይህም ጊዜ ስለ ቤተሰቡ ሁኔታና ስለልጆች የቀለም ትምህርት ብቃትና የትምህርት ቤት ሁኔታ ለመወያየት ጊዜ ይሰጣል፡፡
ጥናቶች አንደሚጠቁሙት ዘወትር ከቤተሰብ ጋር ማዕድ የሚቀርቡ ልጆች የቋንቋ ችሎታቸውም ሆነ የትምህርት ብቃታቸው ከሌሎች አዘውትረው ማዕድ ከማይቀርቡት ልጆች የተሻለ ነው፡፡
5. ለልጆች ምርጫዎችን ማቅረብ ያለብዎት የልጆችን የምርጫ ውሳኔ ለመቀበል ፈቃደኛ ሲሆኑ ብቻ ነው።
6. ልጅች ለመስራት የሚሞክሩትን ያጢኑና ከዚያም ለመስራት የሞከረውን ወይም የሞከረችውን ነገር ሁሉ ያድንቁ ።
አስፈላጊ ከሆነ ያግዙዋቸው ወይም ከሱ /ከርሷ ጋር አብረው ይሆኑ፡፡
7.ልጆች በአካል ንቁ እንዲሆኑ ቤተሰቦች የልጆችን የ ማህበራዊ ገፅ ዕይታ ጊዜያቸውን መቀነስን አለባቸው ።
በዚህ ፋንታ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም በማውጣት አብሮ መስራት ::
8. የልጆችን ቴሌቪዥን፣ ኮምፒተርና ቪዲዮ የሚመለከቱበትን ጊዜን መወሰን ይገባል።
9. ለልጆችዎ ሊገባቸው ወይም ሊረዱት የሚችሉትን የተወሰኑ ጥብቅ ህጎችን ሊኖር ይይኑራቸው
በሕጉ ትግበራ ወቅት እናትም እና አባት አንድ አይነት አቁአም ይኑራቸው።
ልጆች ሲባልጉ ከመቅጣት ይቅር ምክርን ማስቀደም
ልጆች በምክር ካልተመለሱ በተቀመጠው ሕግ መሰረት መቅጣት ተገቢ ነው ።
10. ወላጆች ልጆች እንዲይዙት የምትፈልጉትን ባህሪ ልጆች ማወቃቸውን በደንብ መገንዘባቸውን እና መስማማታቸውን እርግጠኛ ይሁኑ ።
ዶር ፋሲል መንበረ
የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪምና ረዳት ፕሮፈሰር

የጨቅላ ህፃናት ላብ መብዛት ምክንያቱ ምንድነው?
ላብ በተለያዩ ምክንያቶች ጨቅላ ህፃናት ላይ በተደጋጋሚ ሊታይ የሚችል ነው። ብዙ ጊዜ ደሞ ተፈጥሯዊ ሲሆን ምንም አይነት ችግር የሚያመጣ አይደለም።ነገር ግን
አንዳንዴ በሌሎች ምክንያቶችም ሊከሰት ይችላል ።
የህፃናት ላብ መብዛት ሌሎች ምክንያቶች ምንድናቸው ?
✔️ ረጅም ሰአት ማልቀስ
✔️ ጥልቅ የሆነ እንቅልፍ
✔️ የልብስ መብዛት እና በከፍተኛ ሙቀት መጨነቅ
✔️ በኢንፌክሽኖች የሚመጣ ትኩሳት
✔️ ኃይለኛ ማንኮራፋት እና የጉሮሮ መጥበብ
✔️ የተለያዩ የ አጥንት ህመሞች ለምሳሌ ፀሐይ እጥረት ምክንያት የሚመጣው ሪኬትስ እና ሌሎች ህመሞች
✔️ በተፈጥሮ ከፍተኛ የሆነ የላብ አመንጪ ህዋሳት(sweat gland) መብዛት
✔️ የልብ ህመም
የተለያዩ በተፈጥሮ የሚከሰቱ የልብ አፈጣጠር ችግሮች (Congenital Heart Diseases) ልጆች ላይ ላብ እንዲበዛ ሊያረጉ ይችላሉ ።
በተለይ የሚከተሉት ምልክቶች ከላብ መብዛት ተጨማሪ ልጆዎ ላይ የሚታዩ ከሆነ ሐኪምዎን ያማክሩ ።
# ጡት እየጠቡ ደክሟቸው ጡት የሚያቋርጡ ከሆነ
# ከንፈራቸው የሚጠቁር ከሆነ
#ተደጋጋሚ የሳምባ ምች የሚያጠቃቸው ከሆነ
# ቶሎ ቶሎ መተንፈስ እና ማቃሰት ካለ
# ስለዚህ ወላጆች መረዳት ያለባቸው ላብ ተፈጥሯዊ እና በእድሜ የሚጠፋ እንደሆነ እና ሆኖም ሌሎች አጠራጣሪ የሆኑ ማንኛዉም ምልክቶች ሲያዩ ግን ሐኪም ማማከር አለባቸው።
ዶክተር ፋሲል መንበረ
(በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የህፃናት ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር)

SPHMMC, department of psychiatry, child and adolescent unit provides a caregivers skill training (applying WHO's guidelines) for caregivers of children with neurodevelopmental disorders.
This is the 7th group to graduate after 10 weeks of training.

በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ስዎች ቁጥር በዕጥፍ ጨምሯል፤ የጽኑ ህሙማን ቁጥርም በየቀኑ እያሻቀበ ነው!
የዛሬ ሪፖርት
# 17 ሰው ሕይወቱ አልፏል ።
# 1,217 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ።
# 620 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ ናቸው።
በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7,278 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 1,217 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 309,351 ደርሷል።
እባክዎን ራስዎን እና ቤተሰብዎንና ከኮቪድ -19 ይጠብቁ!
ማስክ ያድርጉ፣ ከመሰባሰቦች ይቆጠቡ፣ አካላዊ ርቀትዎንና የእጅ ንፅህና ምንግዜም ይጠብቁ ዘንድ እናሳስባለን ።