St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
ዛሬ የዓለም የልብ ቀን ነው፡፡(መስከረም 19/2014)
ምንግዜም የደም ግፊትዎን ይለኩ፡፡
#WorldHeartDay
#Cancer is the 2nd leading cause of death globally.
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ የዓለም ዓቀፍ ትንባሆ ቁጥጥር ላስመዘገቡት የላቀ ውጤት የዊከንፊልድ ሽልማት ተሸለሙ።
____________

ሄራን ገርባ ትንባሆ በህብረተሰብ ጤና ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በመዋጋት ረገድ ግንባር ቀደም በመሆን ጠንካራ አመራር ሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪም
ትንባሆን ለመቆጣጣር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣውን ጠንካራ ህግ እንዲፈጸም በስፋት ሰርተዋል፡፡

ወይዘሪት ሄራን ባሳዩት የአመራር ብቃት እና ለሌሎች አራዓያ የሚሆን ስራ በመስራታቸው ሽልማቱን ማግኘታቸው ተገቢ መሆኑን የጁዲ ዊከንፊልድ ሽልማት ኃላፊዎች ገልፀዋል፡፡
የልጆች አስተዳደግ ዘይቤዎች (Parenting styles)
እርስዎስ ልጅዎን እንዴት እያሳደጉ ነው?

ህፃናት የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች ናቸው ዛሬ አበባው ላይ የምናደርገው እንክብካቤ ፍሬው ላይ ውጤቱን እናየዋለን።

እንደ የስነ-ልቦና ባለሞያዎች ወላጆች ልጆቻቸውን የሚያሳድጉባቸው መንገዶች በአራት ይከፈላሉ፡፡

1.አምባገነን (ኮስታራ) ፦

ይህ አይነት የልጅ አስተዳደግ በአለማችን በይበልጥ ደግሞ በሀገራችን ለረጅም ጊዜ የነበረ የማሳደጊያ መንገድ ነው፡፡ ከእናቶች ይልቅ ደግሞ አባቶች ላይ ይስተዋላል፡፡ እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው 'ኮስተር' ብለው ይነግሩና ልጆች 'ወለም ዘለም' ሳይሉ እንዲከተሉ ይጠብቃሉ፡፡

እንደዚህ ሆነው የሚያድጉ ልጆች በአብዛኛው ስኬታማ ለመሆንና 'ትክክል' የሆኑ ነገሮችን ለማድረግ የሚጣጣሩ ሲሆኑ አዲስ ነገር ለመሞከር ወይም ያልተለመደ ስራ ለመስራት ይከብዳቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ ከቤተሰብ ሲርቁ የማያምኑባቸውን ነገሮች ለማድረግ ይገፋፋሉ፡፡

አምባገነናዊ ስልትን የሚጠቀሙ ወላጆች በትንንሽ ጉዳዮች ላይ እራሱ ጥብቅ የሆነ የዲሲፕሊን/ የመመርያ ዘይቤን ይጠቀማሉ ፡፡

በዚህ ስልት ውስጥ ቅጣት በጣም የተለመደ ነው በወላጅና በልጅ መካከል በሚደረግ ንግግር ውስጥም ደግሞ ወላጆች ብቻ ተናጋሪ ሲሆኑ ልጆቻቸውን አያዳምጡም ወይም የልጆችን ሃሳብ በፍጹም አያንሸራሽሩም

የተለያዩ ጥናቶች የዚህ አይነቱ የወላጅነት ስልት ብቻውን ውጤታማ እንዳልሆነ ያስረዳሉ።

በእርግጥ ለነገሮች ገደብና ወሰን መስጠት ልጆችን ለማሳደግ ጤናማና የሚመከር ነው ነገር ግን ከፍቅር ከክብርና ከእንክብካቤ ጋር አብሮ መሆን አለበት።

ልጆች መጥፎ ምግባር በሚያሳዪበት ግዜ በማስፈራራት እና ከባድ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ቅጣቶችን በመጠቀም ጥሩ ባህሪን ለማስፈፀም ለግዜው ቀላሉ መንገድ መስሎ ሊታይ ይችላል ነገር ግን የዚህ አይነቱ ቅጣት ዘላቂ የሆነ የባህሪ ለውጥ አያመጣም!

እንደዚህ አይነት ወላጆች ልጆቻቸው ዝቅተኛ ውጤት ሲያመጡ በመቅጣት በማሸማቀቅ እና በማሳፈር ልጆቻቸው ችግሮችን የመፍታት አቅማቸውን እንዲያሳድጉ የረዷቸው ይመስላቸዋል ግን ይሄ ልጆች ለራሳቸው ዝቅተኛ ክብር እንዲኖራችው ከማድረጉም በላይ የአዕምሮ ዕድገታቸውን ያጨናግፋል በረጅም ግዜ ሂደት ውስጥም ወላጆች ለልጆቻቸው ይህንን ስልት እንደ አርዓያ ያወርሷቸዋል ።በዚህ ምክንያት ልጆቹ ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር ይህን ስልት እንደ ብቸኛ ችግር መፍቻ ዘዴ እኩዮቻቸው ላይ እና ወደፊት ወላጅ ሲሆኑ

2.የሚያሞላቅቁ (ሁሉንም የሚፈቀዱ)፦

ይሄ የልጅ አስተዳደግ በቅርብ የተጀመረ ሲሆን በከተማዎች በጣም እየተስፋፋ የመጣ አይነት ነው፡፡

እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸው ያለ ገደብ እንደፈለጉ አንዲሆኑ ይፈቀዳሉ፡፡ ልጆቻቸው ያለ ከልካይና ያለ ገደብ እንደልባቸው እንዲሆኑ ከመፍቀድ ውጪ ምን ማድረግ እንዳለባቸው አይነግሯቸውም፡፡ ልጆቻቸው እስከፈለጉ ድረስ ከቤተሰቡ አቅም በላይ ቢሆንም እንኳ ለማሟላት ይጣጣራሉ፡፡

ይህን ስልት የሚጠቀሙ ወላጆች ‘’ ልጆች ሁልግዜም ልጅ ናቸው “ የሚል አመለካከት የያዙ ናቸው።አብዛኛውን ግዜ ከልጆቻቸው ጋር ባላቸው ግንኙነትም ከወላጅነት ሚና ይልቅ የጓደኝነቱ ሚና ጎልቶ ይወጣል።

እንደዚህ የሚያድጉ ልጆች ከቤት ውጭ እንደፈለጉ መሆን ስለማይችሉ ጭንቀት ይሰማቸዋል፡፡

የተለያዩ ልምዶችን አይቆጣጠሩም እንዲሁም ልጆቻቸው የግል ደንብና ስርዓት እንዲኖራቸው አያስገድዱም ልጆቻቸውም ግብ እንዲኖራቸው እና ዓላማቸውን እንዲያውቁ ስለማይጠየቁ እራስን መግዛት ላይ ደካማ ናቸው። ይህ አይነቱ ስልት ደግሞ በመጨረሻ ወደ ዝቅተኛ የትምህርት እና የህይወት ውጤት ያመራል

የተወሰኑት ልጆች ደሞ ለምንም ነገር ሀላፊነት የማይሰማቸው ይሆናሉ፡፡

3.ግድ የለሽ( የማይሳተፍ )

እነዚህ ወላጆች ለልጆቻቸው ግድ የሌላቸው ሲሆኑ ቁጣም ሆነ አድናቆት አያሳዩም፡፡ ልጆቻቸው እነሱን እስካላስቸገሩ ድረስ የትም ቢውሉ፤ የፈለጉትን ቢያደርጉ ግድ አይሰጣቸውም፡፡

እንደዚህ የሚያድጉ የተወሰኑት የቤተሰብ ሀላፊነት ስለሚሸከሙ ልጅነታቸውን ይነጠቃሉ፡፡ ሲያድጉ ብቸኝነት የሚሰማውና ሰውን ማመን የሚከብደው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በራስ መተማመናቸው ዝቅተኛ( ወይም ለማካካስ በጣም ከፍተኛ) ሊሆን ይችላል፡፡

4. ዲሞክራሳዊ (ነጻነት በወሰን የሚሰጡ) ፦

እነዚህ ወላጆች የልጆቻቸውን ሀሳብ፣ ስሜትና አስተያየት ያዳምጣሉ፡፡ በጣም ጠቃሚ ነገሮች ላይ የሚወስኑት ወላጆች ናቸው፡፡ በአቅማቸው የሚችሉትን ያደርጋሉ፡፡

ይህ አይነቱ አስተዳደግ ልጆች ሃሳባቸውን እንዲገልጹ መፍቀድ ፣ በአማራጮች ላይ እንዲወያዩ ማበረታታት ፣ ነፃነትን እና ምክንያታዊነትን ማሳደግ ፣ በልጆች ጠባይ ላይ ገደቦችን(ወሰኖችን) ማስቀመጥ ያለበት ፣ ሞቅ ያለ ፍቅርንና እንክብካቤን ማሳየት፤ ፍትሃዊ እና ወጥነት ያለው መመርያ መስጠት ህጎች ሲጣሱ ተገቢውን ቅጣት መስጠት ያካትታል::

የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ዲሞክራሲያዊ የሆኑ ወላጆች ያላቸው ልጆች የበለጠ ብቃትን ፣ ብስለትን ፣ በራስ መተማመንን እና ራስን መግዛትን የመሳሰሉ ባህሪዎችን ያሳዩ እና ከፍተኛ የሞራል ጤናማነትን እና ፣ ሕሊና ነጻነትም አላቸው ::

እነዚህ ወላጆች ለልጆቻቸው ወሰን አስቀምጠው ነጻ እንዲሆኑ የሚፈቅዱ ሲሆኑ የልጆቻቸውን ምርጫ ያከብራሉ፡፡ በዚህ መንገድ የሚያድጉ ልጆቸ ከሌሎች ጋር ተባብረው መስራት የሚችሉና በራሳቸው የሚተማመኑ ስኬታማ ሰዎች ይሆናሉ፡፡

ዶር ፋሲል መንበረ
የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪምና ረዳት ፕሮፌሰር
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ
How can cervical cancer be cured?

👉🏽 regular screening
👉🏽 early diagnosis
👉🏽 prompt treatment
t.me/spmmc
October is #BreastCancerAwarenessMonth.

Awareness & regular screening is the best strategy to discover breast cancer early & improve the outcome. Know when & how often to do a:
✅self exam
✅clinical breast exam
✅mammogram

#PinkOctober
ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ በድጋሚ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ዛሬ ተሾመዋል፡፡ የቅዱስ ጳወሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ማህበረሰብ የተሰማንን ደስታ እንገልጻለን፡፡ መልካም የስራ ዘመን ይሁንልዎ!
Notice . To all who applied for MSc ln Medical Microbiology
Enterence exam date: October 18, 2021.
Time : 2:00 pm (afternoon)
Place: SPHMMC academic building.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር ዐቢይ አህመድ ለፌዴራል ጤና ሚኒስቴር ሶስት ሚኒስትር ዴኤታዎችን ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህም መሠረት
ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ- በጤና ሚኒስቴር የአገልግሎትና ፕሮግራም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

ዶ/ር አየለ ተሾመ- በጤና ሚኒስቴር የሥርዓት ዐቅም ግንባታ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ

ወ/ሮ ሠሐረላ አብዱላሒ- በጤና ሚኒስቴር የሐብትና ግብዓት አሥተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ማሕበረሰብም
ሀገርንና ሕዝብን ለማገልገል በመሾማቻው መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን፡፡
ማስታወቂያ
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2014 ዓ.ም የቅዳሜ እና እሁድ የትምህርት ኘሮግራም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት የመመዝገቢያ መስፈርቶች እና ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

1. ስልጠና የሚሰጥባቸው የትምህርት መስኮች፣
በ General Master of Public Health
በ Master of Public Health in Epidemiology
በ Master of Public Health in Public Health Nutrition
2. የመመዝገቢያ መስፈርቶች፣
ሀ. እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም የመጀመሪያ ዲግሪ በ(Nutrition, Occupational health, Health officer, nurse, midwifery, medical doctor, Environmental, health education, pharmacy, anaesthesia, medical laboratory technology).
የተመረቀ/የተመረቀች፣
ለ. የተሟላ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ የምትችል/የሚችል፣/Student copy & Degree/፣
ሐ፡ ከተመረቀ/ች በኃላ ቢያንስ ሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ላት/፣
መ. ከሚሰሩበት መሰሪያ ቤት የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
ሠ.ኮሌጅ የሚያዘጋጀውን የቃል /Interview/ እና የፁሑፍ/written/ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል/፣
ረ. በስፖንሰር ሺኘ የሚማሩ ተማሪዎች የስፖንሰር ሺኘ ደብዳቤ ከሚሰሩበት መ/ቤት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
ሰ. ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት ለኮሌጁ የተፃፈ አንድ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
ሸ. ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ Official Transcript ማቅረብ የሚችል/የምትችል፡፡

ምዝገባው የሚካሄደው፡- online በኮሌጁ ድህረ ገጽ www.sphmmc.edu.et መሆኑን
እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- 1. ምዝገባው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15/አሥር አምስት /ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲሆን በተጨማሪም የመመዝገቢያ የማይመለስ 350/ሶስት መቶ ሃምሳ/ብር በኮሌጁ አካውንት ቁጥር (1000006577192) መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
2. አስፈላጊውን ዶክመንት ያላሟላ ፈተናው ላይ እንደማይቀመጥ በጥብቅ
እናሳውቃለን፡፡
3. ፈተናው የሚሰጥበት ቀን አና ቦታ በኮሌጁ የ Facebook (sphmmc)ገጽ እና በማስታወቂያ ቦርድ ላይ እንደሚወጣ እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ ፡- የኮሌጁ ሬጅስትራር ስልክ ቁጥር 0118 96 51 25 ወይም 976 ላይ
ይደውሉ፡፡
Please use the following link to register: https://197.156.83.153/mph-reg/
And while using the link please choose the advance option which comes during connecting with the link.
በኢኒስትግራም ያገኙናል ። st_pauls_hospital_mmc