ሕጻናትና የስኳር በሽታ
በአለም ላይ አምስት መቶ ሺ የሚሆኑ ህፃናት የስኳር በሽታ አለባቸው ከነዚህም ህፃናት መካከለኛ አብዛኞቹ ያለባቸው የመጀመሪያው አይነት የስኳር በሽታ(Type 1 Diabetes Mellitus) ነው ::
የስኳር በሽታ በማንኛዉም እድሜ ዉስጥ ያለ ልጅ ላይ ሊታይ ይቻላል ::
የስኳር በሽታ ዋናው ምክንያቱ ቆሽት የሚባለው አካላችን ኢንሱሊን የሚባለውን ንጥረ ቅመም(Insulin hormone) በሚያስፈልገው ልክ ሳያመነጭ ሲቀር ወይም የተመረተው እንሱሊን በበቂ መጠን ስራዉን ሳይሰራ ሲቀር ነው::(defect on insulin production or action)
የራሳችን የበሺታ መከላከያ ንጥረ ነገሮችን የ ራሳችንን የቆሽት ህዋሶችን (Beta cells of Pancrease) ሲያጠቁ እና ቆሽት ስራዉን ሲቀን ብሎም ሊያቆም ይቻላል::
ይህ ከላይ የጠቀስነው ችግር ደሞ ህፃናት ላይ በተለያዩ አጋላጭ ነገሮች(Risk factors) ሊከሰት ይቺላል
- በዘር ወይም በቤተሰብ
- የልጅነት የሚከሰቱ የተለያዩ የቫይረስ በሽታዎች
- የላም ወተት መጠቀም
- በልጅነት የሚያጋጥም የምግብ እጥረት
- ህፃኑ ሳይወለድ ማህፀን ዉስጥ ጀምሮ በቂ ምግብ ካላገኘ አዋቂ ከሆነ በኋላ ለሁለተኛው አይነት ስኳር በሽታ ተጋላጭ ሊሆን ይቻላል።
የስኳር በሽታ የህመም ምልክቶች ምንድናቸው?
ከፍተኛ የዉሃ ጥማት እና ቶሎ ቶሎ መጠጣት
- ብዙ ሽንት መሽናት
- ክብደት መቀነስ
- ከፍተኛ ድካም
- ቁስል ቶሎ አለመዳን
- ዐይን ብዥ ማለት
- አተነፋፈስ መፍጠን
- ራስን መሳት
ሕክምናው ምንድነው?
- ኢንሱሊን ሳያቋርጡ መወሰድ
(በተለይ የመጀመሪያው አይነት የስኳር በሽታ - Type 1 Diabetes Mellitus ከሆነ )
- ጣፋጭ የሆኑ ምግቦችን ማስወገድ
- የቅርብ የሀኪም ክትትል ማድረግ
- የአይን እና የኩላሊት ምርመራ ማድረግ
የስኳር በሽታ ካልታከመ ምን ሊያመጣ ይቻላል?
✔️ የዓይን ብርሃን መቀነስ እስከ መታወር ድረስ
✔️ የደም ዝውውር መቀነስ
✔️ ስትሮክ
✔️ በተደጋጋሚ ኢንፌክሽን መያዝ
✔️ መጠን በላይ ክብደት መጨመር ወይም መቀነስ
✔️ ራስን የመሳት እና ከፍተኛ የስኳር በሽታ ህመም(Diabetic Ketoacidosis)
✔️ የኩላሊት መድከም እና ስራ ማቆም
ዶር ፋሲል መንበረ
የሕጻናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ

የጡት ካንሰር በሽታ ምንድን ነው?
የጡት ካንሰር በአብዛኛው በሴቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ወንዶችንም የሚያጠቃ የካንሰር ዓይነት ነው፡፡የጡት ካንሰርም በቅድሚያ በጡት ላይ በመከሰት በሽታው በአጭር ጊዜ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በመዛመት የከፋ ችግር ያስከትላል፡፡
ጡት በተፈጥሮ በውስጡ ወተት ለማመንጨት የሚያስችሉ በርካታ ከረጢት መሰል ነገሮች እንዲሁም እነዚህን ከጡት ጫፍ ጋር የሚያገናኙ ቱቦዎች አሉት፡፡
እነዚህ ቱቦዎች በእርግዝና ወቅት ወተት ለማመንጨት ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ የጡት ካንሰር ጅማሬው በእነዚህ ቱቦዎች ውስጥ ነው፡፡ የጡት ካንሰር ተፈጠረ የሚባለው አንድ ጤነኛ ያልሆነ ህዋስ በሰውነታችን ውስጥ ተፈጥሮ ከገደብ በላይ መራባት ሲጀምር ነው፡፡ የተራባው ህዋስም በጊዜ ሂደት ጤነኛ የነበሩ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ህብረ ህዋሳትን በማጥቃት በሽተኛ ያደርጋቸዋል፡፡
ለጡት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች
የጡት ካንሰር በብዛት ሴቶችን የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡ የሚከሰትበት ምክንያት በውል አይታወቅም፡፡ የሚከተሉት ሴቶች ግን የበለጠ ለበሽታው ተጋላጭ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
• ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ፡፡ የእድሜ መጨመር ለጡት ካንሰር አጋላጭ ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡ ፣
• ከዘር/ከቤተሰብ በጡት ካንሰር የተያዘ ካለ ለበሽታው የመጋለጥ እድል ከፍተኛ
• ካንሰር ያልሆኑ ሌሎች የጡት በሽታዎች አጋጥሞ ከነበረ፣
• የአልኮል መጠጥ የሚያበዙ ሴቶች ለጡት ካንሰር ተጋላጭ ናቸው፡፡ አልኮል መጠጥ አዘውትራ የምትወስድ ሴት አልኮል ከማይጠቀሙት ይልቅ በጡት ካንሰር የመያዝ እድሏ ከፍተኛ ነው፡፡
• የወር አበባቸውን ቀድመው/በልጅነት ያዩ ሴቶች ለጡት ካንሰር ተጋላጭ ናቸው፡፡
• ከ30 ዓመት በኋላ ልጅ የሚወልዱ ወይም ከነጭራሹ የማይወልዱ፣
የወር አበባ ማየት ከማቆም(ከማረጥ) በኋላ የሚመጣ የሰውነት ክብደት መጨመር ለጡት ካንሰር ያጋልጣል፡፡
• ከሚገባው ዕድሜ በጣም ዘግይተው ያረጡ፣
• ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ የሚያዘወትሩና ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው፣
• በስራ ገበታቸው ላይ በከፍተኛ ጨረር ውስጥ ያለምንም መከላከያ የሚሰሩ
• ሰራተኞች በበሽታው የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡፡፡
•
የጡት ካንሰር ምልክቶች
የጡት ካንሰር ሲጀምር ህመምም ሆነ ምልክቶች የሉትም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የጡት ላይ እብጠቶች ካንሰር ባይሆኑም ዋነኛው የጡት ካንሰር ምልክት ግን በጡት ላይ የሚከሰት ጠጣር እብጠት ነው፡፡ የሚከተሉት ደግሞ ተጨማሪ ምልክቶቹ ናቸው፡፡
• ከጡት ጫፍ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ መውጣት፣
• የጡት ጫፍ አካባቢዎች መቅላትና ወደ ውስጥ መሰርጎድ፣
• በጡት አካባቢና በብብት ውስጥ እብጠት መከሰትና ሙቀት ያለው መሆን፣
• የጡት ቆዳ መሸብሸ/ወደ ውስጥ መግባት ወይም እንደብርቱካን ልጣጭ ዓይን ማውጣት፣
• ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ሲታዩ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምናና ምርመራ ማድረግ ነው፡፡
የጡት ካንሰር መከላከያ ዘዴዎች
የጡት ካንሰር ተሰራጭቶ ወደ ሌላ የሰውነት አካል ከመድረሱና ከመባዛቱ በፊት ከተደረሰበት ሙሉ በሙሉ ሊድን የሚችል በሽታ ነው፡፡ በመሆኑም የጡትን ችግር በየወቅቱ ወይም በየጊዜው ለማወቅ ሴቶች በተወሰነ ጊዜ በጡታቸው ላይ የሚከሰተውን እብጠት በጥንቃቄ መመርመር ተገቢ ነው፡፡ የኸውም፣-
1. የማሞግራም ምርመራ ማድረግ
ይህ ምርመራ ጡትን ራጅ በማንሳት የሚደረግ የምርመራ ዘዴ ሲሆን አስተማማኝ የጡት ካንሰር ምርመራ ዘዴ ነወ፡፡ በመሆኑም ብዙ ሐኪሞች ማንኛዋም ሴት ከ40 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ በየዓመቱ እንዲሁም ከ20 እስከ 40 ዓመት ያሉ ደግሞ በየሦስት ዓመቱ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው ይመክራሉ፡፡
2. ሐኪም በመዳሰስ የሚያደርገው ምርመራ
ሐኪም ጋር በየስድስት ወሩ በመቅረብ፣ የሚሰማን ስሜት በመግለጽና ጡትን በማሰዳሰስ ምርመራ ማድረግም ተገቢ ነው፡፡
3. የራስን ጡት በራስ የመመርመር ዘዴ
የራስ በራስ የጡት ምርመራ በየወሩ ማድረግ ህይወትን ከሞት ለመታደግ ያስችላል፡፡ጡት በወር አበባ ምክንያት በቅርጽ፣ በመጠንና በስሜት ስለሚቀያየር ሁልጊዜ በየወሩ በተለመደ ቀን መመርመር አለበት፡፡ ይህን ማድረግ ጡት ላይ የሚከሰት ማንኛውንም ለውጥ ለማወቅ ይረዳል፡፡

Please register for our biweekly Educational Series Via https://echo.zoom.us/meeting/register/tJ0vd-6sqDgqE93zDlc9TkTbASlHWxW4Ss-z
Topic: Keeping out of trouble; defining, avoiding, and managing adverse events in endoscopy.
Date: November 9/2021
Time: 4:00 PM

It's World Pneumonia Day
Pneumonia accounts for 14% of all deaths of children under 5 years old, killing over 740 000 per year. It's the single largest infectious cause of death in children worldwide 🌎🌍🌏.
Pneumonia can be prevented with simple interventions:
💉 Immunization
🥦 Adequate nutrition
🔥 Reducing exposure to indoor air pollution
🏡 Improving housing conditions
🚬 Avoiding smoking near children

ሕጻናት ድንገተኛ የነስር ሕመም ሲያጋጥማቸው ማድረግ የሚገባዎ 7 ነገሮች
• ነስርን ብዙ ጊዜ ቤት ዉስጥ በቀላል ዘዴዎች ማቆም ይቻላል፡፡ ወላጆች ግን መረጋጋት ይጠበቅባቸዋል፡፡የልጅዎን ጭንቀላቱን ትንሽ ወደ ፊት ዘንበል አርጎ አፍንጫው አጥንት በታች ያለውን ለስላሳ የ አፍንጫ ክፍል ቢያንስ ለ10 ደቂቃ ጫን አርጎ መያዝ :: ቶሎ ከለቀቁ መልሶ ሊደማ ይችላል፡፡
• በዚህ መንገድ ቀላል ነስር ከሆነ ይቆማል፡፡ ካልተሳካ ግን ለተጨማሪ 10 ደቂቃ አሁንም ደግሞ አፍንጫውን ጫን አርጎ መያዝ ይገባል፡፡
• በነዚህ ሁለት ሙከራዎች ወይም በ 20 ደቂቃ ዉስጥ ካልቆመ በአፋጣኝ ወደ ሆስፒታል ልጅዎን ሐኪም ዘንድ
• በዚህ ወቅት ልጆዎ በአፉ እንዲተነፍስ ይንገሩት፡፡
• ይጠንቀቁ!በፍፁም ልጆዎን ወደ ላይ ቀና ማድረግ ወይም ማንጋጠጥ የለበትም:: ምክንያቱም ቀና ስላለ ደሙ ወደ ውጭ አይፍሰስ እንጂ ወደ ዉስጥ በምግብ ቱቦ በኩል በብዛት እንዲፈስ እና ወደ ጨጓራው እንዲገባ ያረጋል ይሄ ደሞ ከፍተኛ የደም ማነስ እና ትውከት ሊያስከስት ይችላል::
• ሶፍት ወይም ሌላ ነገር ወደ አፍንጫ አይክተቱ! ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች መድማቱን ሊጨምሩት ይችላሉ፡፡
• የልጅዎን ሁኔታ በቅርበት ይከታተሉ፡፡ነስሩ ከቆመ በዋላ ለተወሰነ ሰዓት ልጆ አፍንጫውን እንዳይነካካ እና በኃይል እንዳይናፍጥ ከባድ ነገር እንዳያነሳ ያርጉት
የልጆች ነስርን መከላከል ይቻላል ?
አዎ መከላከል ይቻላል፡፡ ሆኖም ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ ግን የሚቻለው በሐኪም ሲታከም ነው::
መከላከያ መንገዶቹ ምንድናቸው?
ልጆች አፍንጫቸውን ለአደጋ ከሚያጋልጡ ነገሮች ማራቅ
አፍንጫቸውን እንዳይነካኩ ማስተማር
የልጆች ጥፍርን ማሳጠር
የአየር ንብረቱ ደረቅ ከሆነ አፍንጫቸው ዉስጡን ቫዝሊን በመጠኑ መቀባት ወይም እንፋሎት መታጠን
ጉንፋን እና አለርጂን በአግባቡ መታከም
መድሃኒቶችን ያለ ሐኪም ትእዛዝ አለመውሰድ
ቋሚ የህፃናት ሕክምና ክትትል ማድረግ
በነስር ሕመም የታመመ ልጅዎን መቼ ነው ሆስፒታል መውሰድ የሚገባዎ?
ከላይ እንደ እንደተጠቀሰዉ የማይቆም ከሆነ
ባንዴ ብዙ ደም መፍሰስ ካለ(ከ1 ስኒ በላይ)
ልጆዎ ራስ ማዞር እና መሳት ካጋጠመው
ተደጋጋሚ ነስር እና የጥርስ መድማት ካለ
ቆዳው በቀላል ምት(አደጋ) የሚበልዝ ከሆነ
ከ 2 ዓመት በታች ነስር ከተከሰተ
ልጆዎ ከዚህ በፊት የደም ማነስ ካለበት
ተከታታይ ደም የቀላቀለ ትውከት ካለ
ዶር ፋሲል መንበረ
የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር

ማስታወቂያ
የሕጻናት የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና ለሚፈልጉ በሙሉ!
ሕክምናው የሚመለከታችው፡- እድሜያቸው ከ14 ዓመት በታች ለሆኑ ብቻ፤
ከዚህ ቀደም በየትኛውም የጤና ተቋም የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና እንደሚያስፈልጋቸው የተነገራቸው እና
በየትኛውም የጤና ተቋም ወረፋ በመጠበቅ ላይ የሚገኙ ሕክምናውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለምዝገባ፡- 976 ይደውሉ፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
የዓይን ሕክምና ትምህርት ክፍል
t.me/SPMMC

የኮሌጃችን የ2010 ዓም ምሩቅ የሆነችው ዶር ሩት ድሪባ ' Women in Global Health ' የተባለ ዓለም አቀፍ ድርጅት በሙያዋ ስለስጠችው የላቀ አበርክቶ የ20211 የዓመቱ ጀግና የጤና ባለሙያ በማለት አውቅና ሰጥቷታል፡፡
ከዶር ሩት ጋር የኬንያ፣ የሊባኖስ፣ የሕንድ፣ የፓናማ፣ የፓኪስታን እና የሴራሊዮን ሴት የጤና ባለሙያዎች በጤናው ዘርፍ ስላደረጉት አሰተዋጽኦ ጀግና ተብለው ተወድሰዋል፡፡
ዶር ሩት እንኳን ደስ ያለሽ እንኮራብሻለን! እስቲ እንኳን ደስ ያለሽ እንበላት፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በህወሃት የወደመውን የጭፍራ ጤና ጣቢያ መልሶ በማደራጀት በቀጣይ ሳምንት ወደ ስራ ያስገባል።ጤና ጣቢያውን ወደ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለማሳደግ እየተሠራ ነው።
ኮሌጁ ከዚህ ቀደም በአሸባሪው ህወሃት ቡድን ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን የደሴ ሆስፒታልን መልሶ በማደራጀት አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
አሁን ደግሞ ሁለተኛው የሆነውን አሸባሪ ቡድኑ ያወደመውን የጭፍራ ጤና ጣቢያ መልሶ የማቋቋም ስራ በኮሌጁ ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተከናወነ ይገኛል። ጤና ጣቢያው በቀጣይ ሳምንት ስራ ለማስጀመር እየተሰራ ይገኛል።
ኮሌጁ ጤና ጣቢያውን ወደ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለማሳደግ እና አዳዲስ የሕክምና አገልግሎቶችን ለማስጀመርም እቅድ ተይዟል።
ኮሌጁ በጭፍራ አካባቢ የተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍም አድርጓል።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ ሙያና ተቋማዊ እድገት ማእከል (CPID) በትናንትናው እለት የ ‘Digital Learning Solution (DLS)’ አገልግሎቱን የጤና ሚንስቴር ኃላፊዎችና የኮሌጁ የአካዳሚክና ምርምር ም/ፕሮቮስት በተገኙበት በይፋ አስጅምሯል፡፡ አገልግሎቱ የጤና ባለሞያዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በኢንተርኔት አማካኝነት ስልጠናዎችን እንዲከታተሉ ያስችላል፡፡ አገልግሎቱን በ http://cpid.sphmmc.edu.et ወይም በ IP address 197.156.83.151 ማግኘት ይቻላል፡፡
Prevent #stroke:
🚭Quit smoking
🍺Limit alcohol consumption
⛔Control high blood pressure & high cholesterol
✅Manage diabetes
🏋🏾Watch your waist and weight
🍏Eat healthily
🏃🏻♀️Exercise 30 minutes a day

ማስተወቂያ
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የ Dental & Maxillofacial Surgery ትምህርት ክፍል በ2014 ዓ.ም አዲስ ሬዚደንት ሐኪም ተማሪዎችን በመቀበል በ Oral & Maxillofacial Surgery በድህረ-ምረቃ ፕሮግራም በዚህ ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ማመልከት ትችለላችሁ፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
ከታወቀ የመንግስት ተቋም በ doctor of dental medicine (DDM or DDS ) ዲግሪ ያለዉ/ ያላት
ሁለት አመትና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ያለው/ያላት
ስፖንሰር ሺፕ ማቅረብ የሚችል/ምትችል
በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ የሚገኝ/የምትገኝ
እድሜ ከ 40 ዓመት በታች
NB:
Registration 02/05/2014 - 20/05/2014
Exam 24/05/2014
Registration and orientation for selected candidate 27/05/2014
Class beginning 01/06/2014