St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
The St. Paul’s community would like to congratulate the Internal Medicine Class of 2021. We commend you on your hard work and dedication to the field of medicine and we wish you the best of luck in your future endeavors!
Picture: Sel Seyoum MD
This is the architectural model for the future gate of St. Paul's Hospital Millennium Medical College.
ይህ በቅርቡ የሚገነባው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የዋናው መግቢያ በር ዲዛይን ነው፡፡ምን አስተያየት አላችሁ?
ማስታወቂያ
የሕጻናት የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና ለሚፈልጉ በሙሉ!
ሕክምናው የሚመለከታችው፡- እድሜያቸው ከ14 ዓመት በታች ለሆኑ ብቻ፤
ከዚህ ቀደም በየትኛውም የጤና ተቋም የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና እንደሚያስፈልጋቸው የተነገራቸው እና
በየትኛውም የጤና ተቋም ወረፋ በመጠበቅ ላይ የሚገኙ ሕክምናውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለምዝገባ፡- 976 ይደውሉ፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
የዓይን ሕክምና ትምህርት ክፍል
t.me/SPMMC
የኮሌጃችን የ2010 ዓም ምሩቅ የሆነችው ዶር ሩት ድሪባ ' Women in Global Health ' የተባለ ዓለም አቀፍ ድርጅት በሙያዋ ስለስጠችው የላቀ አበርክቶ የ20211 የዓመቱ ጀግና የጤና ባለሙያ በማለት አውቅና ሰጥቷታል፡፡

ከዶር ሩት ጋር የኬንያ፣ የሊባኖስ፣ የሕንድ፣ የፓናማ፣ የፓኪስታን እና የሴራሊዮን ሴት የጤና ባለሙያዎች በጤናው ዘርፍ ስላደረጉት አሰተዋጽኦ ጀግና ተብለው ተወድሰዋል፡፡

ዶር ሩት እንኳን ደስ ያለሽ እንኮራብሻለን! እስቲ እንኳን ደስ ያለሽ እንበላት፡
የዶር ሊያ መልዕክት
የኮቪድ19 መከላከያ ክትባት በሁሉም ጤና ጣቢያ ይገኛል።
ያልተከተባችሁ ዛሬ ነገ ሳትሉ ክትባቱን ውሰዱ!

እንደእኔ ከተከተባችሁ 6 ወር ያለፋችሁ ተጨማሪ ክትባቱን (Booster Dose) ውሰዱ!
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በህወሃት የወደመውን የጭፍራ ጤና ጣቢያ መልሶ በማደራጀት በቀጣይ ሳምንት ወደ ስራ ያስገባል።ጤና ጣቢያውን ወደ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለማሳደግ እየተሠራ ነው።

ኮሌጁ ከዚህ ቀደም በአሸባሪው ህወሃት ቡድን ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን የደሴ ሆስፒታልን መልሶ በማደራጀት አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
አሁን ደግሞ ሁለተኛው የሆነውን አሸባሪ ቡድኑ ያወደመውን የጭፍራ ጤና ጣቢያ መልሶ የማቋቋም ስራ በኮሌጁ ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተከናወነ ይገኛል። ጤና ጣቢያው በቀጣይ ሳምንት ስራ ለማስጀመር እየተሰራ ይገኛል።
ኮሌጁ ጤና ጣቢያውን ወደ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለማሳደግ እና አዳዲስ የሕክምና አገልግሎቶችን ለማስጀመርም እቅድ ተይዟል።

ኮሌጁ በጭፍራ አካባቢ የተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍም አድርጓል።
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ ሙያና ተቋማዊ እድገት ማእከል (CPID) በትናንትናው እለት የ ‘Digital Learning Solution (DLS)’ አገልግሎቱን የጤና ሚንስቴር ኃላፊዎችና የኮሌጁ የአካዳሚክና ምርምር ም/ፕሮቮስት በተገኙበት በይፋ አስጅምሯል፡፡ አገልግሎቱ የጤና ባለሞያዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በኢንተርኔት አማካኝነት ስልጠናዎችን እንዲከታተሉ ያስችላል፡፡ አገልግሎቱን በ http://cpid.sphmmc.edu.et ወይም በ IP address 197.156.83.151 ማግኘት ይቻላል፡፡
Prevent #stroke:

🚭Quit smoking
🍺Limit alcohol consumption
⛔Control high blood pressure & high cholesterol
✅Manage diabetes
🏋🏾‍Watch your waist and weight
🍏Eat healthily
🏃🏻‍♀️Exercise 30 minutes a day
ማስተወቂያ
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የ Dental & Maxillofacial Surgery ትምህርት ክፍል በ2014 ዓ.ም አዲስ ሬዚደንት ሐኪም ተማሪዎችን በመቀበል በ Oral & Maxillofacial Surgery በድህረ-ምረቃ ፕሮግራም በዚህ ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ማመልከት ትችለላችሁ፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
 ከታወቀ የመንግስት ተቋም በ doctor of dental medicine (DDM or DDS ) ዲግሪ ያለዉ/ ያላት
 ሁለት አመትና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ያለው/ያላት
 ስፖንሰር ሺፕ ማቅረብ የሚችል/ምትችል
 በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ የሚገኝ/የምትገኝ
 እድሜ ከ 40 ዓመት በታች

NB:
Registration 02/05/2014 - 20/05/2014
Exam 24/05/2014
Registration and orientation for selected candidate 27/05/2014
Class beginning 01/06/2014
በጎ ፈቃደኛ ነርሶች ይፈለጋሉ!
ከ3 አስከ 6ወር ነጻ አገልግሎት መስጠት የሚፈልጉ BSc ዲግሪ እና ክሊኒካል ነርሶችን እንፈልጋለን፡፡
ስለዚህ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ የሆናችሁ ከጥር 9 ቀን ጀምሮ በተከታታ ይ ለአስር የስራ ቀናት መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡ ለምዝገባ ዋናውን የትምህርት ማስረጃ እና የማይመለስ ኮፒ ይዞ መምጣት ያስፈልጋል፡፡
የምዝገባ ቦታ፡ የኮሌጁ ሰው ሀብትና ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት(ቁጥር -98)
t.me/spmmc
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጥምቀት በዓል አደረሳችሁ!
#Epiphany
የደም ግፊት መቼ እና በየስንት ጊዜው መለካት አለብዎ?
• የደም ግፊት እንዳለብዎት በሐኪምዎ ከተነገረዎት በኋላ ቢቻል በየጊዜው የደም ግፊትዎን መለካት ያስፈልጋል፡፡
• ምን ግዜም የደም ግፊት ልኬትዎን ይመዝግቡ፡፡
• የደም ግፊትዎን የሚለኩበት ግዜ በተመሳሳይ ሰአት ቢሆን ይመረጣል፡፡ ጠዋት ከእንቅልፍዎ ከተነሱ በኋላ ወይም ማታ ወደመኝታዎ ከመሄድዎ ቀደም ብለው ቢያደርጉት መልካም ነው።
• የሐኪምዎን ምክር ተግባራዊ ያድርጉ፡፡
We are very happy to announce that we are going to launch a new dialysis center at Dessie Hospital. Currently, we have trained three nurses who are to be equipped to administer dialysis treatment to patients. This center will make a big impact on the town of Dessie and the surrounding areas. We are proud to support this effort.

We are also working to launch various other medical services in Dessie hospital. Stay tuned!
Trainee nurses from Dessie Specialized Hospital.
በስኳር ሕመም ምክንያት የዓይን ችግር( Diabetic macular edema) ላጋጠማችሁሕሙማን በመርፌ የሚሰጥ የመድኃኒት ሕክምና (Avastin injection ) ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ስለዚህ በስኳር ህመም ምክንያት የዓይን ችግር ( Diabetic macular edema) አለባችሁ ተብላችሁ መደኃኒቱን በተለያየ ምክንያት ማግኘት ያልቻላችሁሕሙማን 976 በመደወል ከየካቲት 2 -15 ድረስ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡
የቅዱስ ጳወሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
የዓይን ሕክምና ትምህርት ክፍል
#DiabeticRetinopathy #MacularEdema #VisionLoss #WeakVision #Diabet