St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
እንኳን ደስ ያላችሁ የ 2014 ዓም ተመራቂዎች !
This year, St. Paul’s Hospital Millennium Medical College will mark the 75th anniversary of its foundation! We are honored to have served the community since the days of the late Emperor Haileselassie until now, where we provide quality healthcare to hundreds of Ethiopians each and every day. We cordially invite all Ethiopians to celebrate this grand milestone over the next five months through a series of events. We will be recognizing the key stakeholders who have supported SPHMMC throughout the years, as well as welcome the new generation of medical professionals and community members who will follow in their footsteps.

In marking the college’s 75th anniversary, we’ve adopted the motto “A proud past – an amazing future”. Join us in this celebration!
New Residents welcome event
Monday, March 7 2022
8፡30 12፡30
Venue: EPHI Auditorium
ለአዲስ የሕክምና ትምህርት አመልካቾች የምዝገባና ተያያዥ መሥፈርትን በፌስቡክ እና በቴሌግራም ገጾቻችን ይፋ እናደርጋለን ። ጠብቁን።
እንደምን አደራችሁ የኮሌጃችን ቤተሰቦች!
ዛሬ የካቲት 29 ቀን ነው-ማርች 8 ። የኮሌጁን 75ኛ ዓመት ክብረ በዓል እና ማርች 8 ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት ቀዶ ሕክምና የሚሰጠው በሴት የሚመራ የሕክምና ቡድን አባላት ብቻ ነው። እኛም የቡድን አባላቱን እናስተዋውቃችኋለን። መረጃችንን ባጭር ባጭሩ ወደ እናንተ ማድረሳችን ይቀጥላል ።ደስ የሚል ቀን ይሁንላችሁ። ውብ ማክሰኞ!
የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በሴት የሕክምና ባለሙያዎች ብቻ የተመራ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በዛሬው ቀን ሰጥቷል።
ኮሌጁ በሴት ሐኪሞች ብቻ በሚመራው ሰባት የቀዶ ሕክምና ቡድኖች ለ23 ያህል ሕሙማን ቀዶ ሕክምና ሰጥቷል። በሕክምና ቡድኖቹ ከቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስቶች እስከ ጽዳት ሠራተኞች ተካፋይ ሆነዋል።
እስቲ ባለሙያዎቻችንን አመሥግኑልን።
Upcoming event professorship speech by professor Engida Abebe
Date: March 10/ Thur/
Time: 2: pm
Venue: MCH Building, 8TH floor
የኩላሊት ሕመም ይሰማዎታል? ጥርጣሬ አልዎት?
እንግዲያውስ፡
ይምጡ እና ነጸ የኩላሊት ምርመራ ያድርጉ!
ቀን፡ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም
ሰዓት ፡ 3፡30-9፡30
የኩላሊት ህመም ምልክቶች
የኩላሊት ምልክቶች ሕመም አብዛኛውን ጊዜ ምልክት የለሽ ናቸው፡፡ እነዚህ የህመም ምልከቶች ከታዩም ደግሞ ከህሙማን ሕሙማን ይለያያሉ፡፡ በተለይ የሕመሙ መጀመሪያ አካባቢ መለየት አስቸጋሪ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አበይት ምልክቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
• የፊት እብጠት
ብዙ ጊዜ የፊት ፣ የሆድ እና የእግር እብጠት የኩላሊት ህመም መለያ ናቸው፡፡ በኩላሊት ህመም ምክንያት የሚከሰት እብጠት በመጀመሪያ ከዐይን ሽፋን በታች ሊከሰት ይችላል፡፡ (ይህ የፔሪኦሮቢታል እብጠት ይባላል) በተለይ በማለዳ ጎልቶ ይታያል፡፡ ነገር ግን ሁሉም እብጠት የ የኩላሊት ሕመምን ያመለክታል ማለት አይደለም፡፡ በተወሰኑ የኩላሊት ህመሞች ውስጥ መደበኛ የኩላሊት ሥራ ቢኖርም እብጠት ይከሰታል (ለምሳሌ ኔፍሮቲክ ሲንድሮም)። ከባድ ህመም ቢከሰትም በአንዳንድ ታካሚዎች ላይ እብጠት ላይታይ ይችላል፡፡
• የምግብ ፍላጎት ማጣት
ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ በአፍ ውስጥ ያልተለመደ ጣዕምና የምግብ መመገብ ደካማነት የኩላሊት ችግር ምልክቶች ናቸው::
• ከፍተኛ የደም ግፊት
አብዛኛውን ጊዜ የኩላሊት ችግር ያለባቸው ታካሚዎች የደም ግፊት ይኖራቸዋል። የደም ግፊት ችግር በወጣትነት ዕድሜ (ከ 30 ዓመት በታች) ከተገኘ ወይም በምርመራው ወቅት የደም ግፊት በጣም ከፍተኛ ከሆነ ምክንያቱ የኩላሊት በሽታ ሊሆን እንደሚችል መጠርጠር ያስፈልጋል።
• የደም ማነስ እና ድክመት
የደም ማነስ ችግር ያለበት ሰው ቶሎ መድከም ፣ ማተኮር አለመቻል እና የቆዳ መገርጣት ዋንኛ ምልክቶች ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ሥር የሰደደ የኩላሊት መድከም የመጀመሪያ ደረጃ ላይ አነዚህ ብቸኛ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። የደም ማነስ ያለበት ሰው በመደበኛ ህክምና በሚሰጡ መድኃቶች ካልዳነ፣ የኩላሊት ህመም እንዳለበት መጠርጠር ያስፈልጋል። ከዚህም ተጨማሪ ምልክቶች -መለስተኛ ደረጃ የጀርባ ህመም ፣ አጠቃላይ የሰውነት ህመም ፣ እና የእግር ማሳከክ እና ህመም በኩላሊት ህመም ውስጥ ተደጋጋሚ የሚታዩ ምልክቶች ናቸው። በልጆች ላይ ደግሞ በሚገባ አለማደግ ፣የቁመት ማጠር እና የእግር አጥንት ቀጥ አለማለት የህመሙ መኖር ማሳያ ነው፡፡
ብዙ ጊዜ የሚታዩ ምልክቶች
1. የሽንት መጠን መቀነስ የኩላሊት ህመሞ በጣም የተለመደ ነው።
2. በመሽናት ወቅት የሚያቃጥል ስሜት ፣ በተከታታይ መሽናት (ያልተለመደ ድግግሞሽ) እንዲሁም ደም ወይም መግል በሽንት ውስጥ ማየት እና የሽንት ቧንቧ ህመም በሽታውን የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው።
3. የሽንት ፍሰት መዘጋት ሽንትን ለማውጣት ችግር ይሆናል፡፡ ምንም እንኳን አንድ ሰው ከላይ ከተዘረዘሩት ምልክቶች መካከል የተወሰኑት ሊያሳይ ቢችልም የግድ ሰውዬው በኩላሊት ህመም ተይዟል ማለት ግን አይደለም። ሆኖም እንደዚህ አይነት ምልክቶች ባሉበት ሁኔታ ሐኪምን ማማከር እና የኩላሊት ህመም እና ሌሎች ህመሞች መኖር ወይም አለመኖራቸውን በደም እና በሽንት ናሙና ምርመራዎች ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
ማስታወቂያ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2014ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሕክምና ትምህርት ለመማር መስፈርቶች የሚያሟሉ አመልካቾች ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡
ለማመልከት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፤
1. በ2014ዓ.ም በመደበኛ ትምህርት ፕሮግራም 12ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀ/ያጠናቀቀች
2. በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና፤ 1) ሲቪክስ ውጤት ለተያዘላቸዉ ከ700 ያገኙትን ወደ 600 ከቀየሩ በኋላ 2) ሲቪክስ ውጤት ያልተያዘላቸው የሲቪክስ ውጤቱን ቀንሠው በሚያገኙትን ዉጤት መሠረት
• ከስር ከተዘረዘሩት ክልልና ዞኖች ውጪ ያሉ ሁሉም ክልሎች -
 ለወንድ 475 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያለው
 ለሴት 460 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላት
• ለአፋር ክልል፣ ለቦረና ዞን(ኦሮሚያ ክልል)፣ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ለጋምቤላ ክልል፣ ለሱማሌ ክልል፣ ለደቡብ ኦሞ ዞን(ደቡብ ክልል)፣ ለዋግ እምራ ዞን( አማራ ክልል) እና ለምእራብ ኦሞ ዞን(ደቡብ ክልል)
 ለወንድ 450 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያለው
 ለሴት 440 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላት
3. ከ9ኛ-12ኛ ክፍል አማካይ የትራንስክሪፕት ውጤት 80% እና ከዚያ በላይ የሆነ
ማሳሰቢያ
1. ማመልከት የሚቻለው Online ብቻ ነው፡፡
2. የማመልከቻ ጊዜው ከመጋቢት 5 - መጋቢት 11 , 2014ዓ.ም ድረስ ብቻ ነው
3. ለተጨማሪ ዝርዝር መረጃ የኮሌጁን ብይነ መረብ www.sphmmc.edu.et/ Official Facebook page/ Telegram page ይጎብኙ ወይንም የኮሌጁን ሬጅስራር ቢሮ ይደውሉ፤
• ስልክ ፡- 251 118 96 5125