St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቃችሁ የጤና ባለሙያዎች የብቃት መመዘኛ ከግንቦት 1 ቀን 04/2014 ዓ ም ይሰጣል፡፡
የፈተናው የጊዜ ሰሌዳ ይመልከቱ፡፡
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ኮሌጅ የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍል HCP በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት እገዛ 500 የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና /CATARACT SURGERY/ ከ ሰኔ 6-12/2014 ዓ.ም ለማድረግ አስቧል፡፡ ስለሆነም ይህን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ቅድመ ምርመራ፣ልየታና ምዝገባ በግንቦት ወር ባሉት ቅዳሜና እሁድ ቀናቶች ማለትም (ግንቦት 6፣7፣13፣14፣20፣21፣27፣28 ) ስለምናደርግ በኮሌጁ የስልክ አገልግሎት 976 በመደወል ለቅድመ ምርመራ፣ ልየታና ምዝገባ ቀጠሮ እንድትይዙ ስንል በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- በስልክ ቀጠሮ ያልተሰጠዉ ታካሚ ቅድመ ምርመራም፣ ልየታም ይሁን ምዝገባ ማድረግ አይችልም፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ከጣዝማ የውስጥ ደዌና ቀዶ ሕክምና ማዕከል ጋር በልብ ቀዶ ሕክምና ላይ በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡ኮሌጁ ከ300 ሺህ ዶላር ዋጋ ያለው የልብ እና ሳንባ ቀዶ ሕክምና ለማድረግ የሚያገለግል ማሽንም ከማእከሉ በድጋፍ አግኝቷል፡፡

የሥምምነቱ ዋና ዓላማ ቀጣይነት ያለው የልብ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት መስጠትና በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች በቂ ሥልጠና እንዲያገኙ አጋርነት መፍጠር ነው፡፡ ይህም አገልግሎቱን ለሕብረተሰቡ በይበልጥ ተደራሽ ያደርገዋል፡፡
በስምምነቱ ወቅት የተገኙት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ኮሌጁ ከማዕከሉ ጋር በልብ ቀዶ ህክምና በጋራ መሥራቱ መንግሥት የግሉን ጤና ተቋማት ተሳትፎ ለማሳደግ ከቀረፀው ፍኖተ ካርታ አንዱ አካል ነው ብለዋል።
ሥምምነቱ ኮሌጁ የአገልግሎት አድማሱን እንዲያሰፋ፣ በልብ ቀዶ ሕክምና በቂ የሰው ኃይል ለማፍራትና በህክምና እጦት የሚንገላቱ ወገኖችን ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ አቅም ይፈጥርለታል ብለዋል፡፡

በእለቱ ስምምነቱን ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በኩል የፈረሙትፕሮቮስቱ ዶር ወንድማገኝ ገዛኸኝ ሲሆኑ ከጣዝማ የውስጥ ደዌና ቀዶ ሕክምና ማዕከል የቦርድ ሊቀመንበሩ ዶር ፍቅሩ ማሩ ናቸው፡፡
መልካም የእናቶች ቀን!
Happy Mother's Day to all moms in the world! Your sacrifice, compassion, and care deserve to be celebrated and honored every day!
#HappyMothersDay2022
#LoveYouMom
#HappyMothersDay
#መልካም_የእናቶች_ቀን
#sphmmc
ማስታወቂያ

*************

በ2014 ዓ.ም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የሕክምና ትምህርት ለመማር የተመረጣችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ግንቦት 15 እስከ 17/2014 ዓ.ም ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

ወደኮሌጁ በምትመጡበት ጊዜ

Ø የ1ዐኛ እና 12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰርተፊኬት ዋና እና ኮፒ

Ø ከ9-12 ክፍል የተማራችሁበትን ትራንስክሪፕት ዋና እና ኮፒ

Ø 8 ፓስፖርት ሳይዝ ፎቶግራፍ

Ø አንሶላ፣ ብርድልብስ እና የትራስ ልብስ

Ø የስፖርት ልብስና ጫማ

ይዛችሁ እንድትመጡ እያስታወቅን ከላይ ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እናስታውቃለን።



ለተጨማሪ መረጀ 0118965125 / 976 መጠየቅ ይቻላል፡፡



የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ

ሬጅስትራርና አልሙናይ ማናጅመንት ዳሬክቶሬት
https://fb.watch/c-lI5LPcAd/
በካንሰር በሽታ ጉዳይ ባልደረባችን ዶር ሙሉጌታ የሰጡት መረጃ ይከታተሉ ። ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ።
ደም ግፊትዎን ሲለኩ እንዲህ ያድርጉ፡፡

• የደም ግፊታችንን በምንለካበት ወቅት አጃችን( ከንዳችን) በፍጹም በልብስ መሸፈን የለበትም፡፡
• አጃችን በልባችን ትይዩ ሆኖ ጠረጴዛ ላይ ደገፍ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
• በደም ግፊት በሚለካበት ወቅት ማውራት አይመከርም፡፡
• በጀርባችን ወንበሩን ደገፍ ብለን፣ እግራችን መሬት ላይ ሙሉ ለሙሉ መንካት አለበት፡፡
• እግርን አጣምሮ የደም ግፊት መለካት አይለኩ፡፡
• ከመለካትዎ 30 ደቂቃ ውስጥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አያድርጉ፡፡
• ሻይ ቡና ጠጥተው ወይም ሲጋራ አጢሰው ደምዎን አይለኩ፡፡

#WorldHypertensionDay17may #worldhypertensionday
የደም ግፊት ንባብ
ስለ ደም ግፊት ቁጥሮች ምን ይናገራሉ?
የደም ግፊት ሲለኩ ሁለት ቁጥሮችን ያያሉ። በተለምዶ እነዚህ ቁጥሮች የላይኛው (ሲስቶሊክ/systolic blood pressure) እና የታችኛው (ዳያስቶሊክ/diastolic blood pressure) ይባላሉ።
• የላይኛው(ሲስቶሊክ/systolic) ቁጥር የሚያመላክተው ልብ ሲመታ በደም ስር ላይ የሚያሳርፈውን የግፊት መጠን ነው።
• የታችኛው(ዳያስቶሊክ/diastolic) ቁጥር የሚያመላክተው ልብ ሲያርፍ ወይም በሁለት የልብ ምቶች መካከል በደም ስር ላይ ያለው የደም ግፊት ነው።
የከፍተኛ ደም ግፊት ምርመራ ሁለቱንም የደም ግፊት ቁጥሮች ግምት ውስጥ ያስገባል። ከሁለቱ አንዱ ወይም ሁለቱም ከፍተኛ ከሆነ ሃኪምዎ ከፍተኛ የደም ግፊት እንዳለብዎ ሊነግርዎ እና መድሃኒት ሊያዝልዎ ይችላል።(በየጊዜው የደም ግፊትዎን መጠን ሲለኩ መመዝገብ አይርሱ፡፡)
#hypertension
#WorldHypertensionDay #WorldHypertensionDay17may
ዛሬ የዓለም የደም ግፊት ሕመም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው፡፡
በሽታው ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳያሳይ ሊቆይ ይችላል። በዚህ ምክንያት አንዳንዴ የደም ብዛትድምጽ አልባው ገዳይ በሚል ስም ይጠራል። የደም ግፊት ያለበት ሰው ምልክት ባያሳይም ሰውነቱ እየተጎዳ አይደለም ማለት አይደለም። እንዲያውም ህክምና ያልተደረገለት የደም ግፊት ለተለያዩ የጤና እክሎች ሊዳርግ ይችላል። ከነዚህም መካከል የኩላሊት በሽታ፣ የአይን ህመም እና የልብ እና የደምስር በሽታዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው።ሆኖም ህሙማኑ በአብዛኛው የሚከተሉት ምልክቶች ሊታይባቸው ይችላል፡፡
• የራስ ምታት
• የአይን ብዥታ
• ራስ ማዞር
• ደረት ላይ የሚሰማ ህመም
#worldhypertensionday17may #hypertension
#WorldHypertensionDay
በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት (ፕሪክላምፕሲያ) በነፍሰ ጡር ሴቶች ላይ የሚከሰት የደም ግፊት ነው። ሕመሙ ከ20ኛው የእርግዝና በኋላ ይከሰታል ።
የአለም ጤና ድርጅት መረጃ መሠረት በዓለም ላይ በየዓመቱ 76 ሺህ እናቶች በዚሁ በሽታ ሕይወታቸው ያልፋል ።
የሕክምና ባለሙያዎች አንዲት ነፍሰጡር ሕመሙ ሲሰማት ወደ ጤና ተቋም በቶሎ መሄድ አለባት በማለት ይመክራሉ።
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ እና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በትምህርትና ስልጠና፣ በፎረንሲክ ምርመራና በጤና ዙርያ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱ በተጨማሪም የምርመራ ሥራዎችን የጋራ ለማድረግና በተመሳሳይ ሥራ ድግግሞሽ እንዳይፈጠር የሚያግዝ ነው ፡፡

ስምምነቱን በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በኩል የፈረሙት ዶር ሲሳይ ስርጉ የአካዳሚክ እና ምርምር ምክትል ፕሮቮስት ሲሆኑ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በኩል ፕሬዚዳንቱ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ ናቸው።
በዛሬው ቀን የዓለም በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ግፊት ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን በመላው ዓለም በልዮ ልዮ ትምህርታዊ ዝግጅቶች ተከብሯል ።
በዕለቱ የበሽታውን መንስኤ : አጋላጭ እና አስቀድሞ መከላከል ስለሚቻልበት ሁኔታ ትምሕርት ይሠጣል።

በሽታውን አስቀድሞ ለመከላከል መደረግ የሚገባቸው ዓበይት ነገሮች እነሆ :-

1. ሁሉም ነፍሰጡር የቅድመ ወሊድ ክትትል እንዲያደርጉ ማበረታታት ፡- የደም ግፊቱ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ትንፋሽ ሲያጥራቸዉ፤ ሲያንቀጠቅጣቸዉ እና አእምሮአቸዉን ሲያስታቸዉ ወደ ህክምና የሚሄዱ ነፍሰጡሮች በተደጋጋሚ ያጋጥማሉ፡፡ይህ ከመከሰቱ በፊት እርዳታ ማግኘት እንድትችል የቅድመ ወሊድ ክትትል ማድረግ አስፈላጊ ነዉ፡፡

2. ደም ግፊት ያለባት ለመጸነስ የምታስብ ሴት የጤና ባለሙያ በማማከር ህመሙ በጤናዋ ላይ ችግር አለመፍጠሩን ለማጣራት የቅድመ እርግዝና ምርመራ ማድረግ ይኖርባታል፡፡

3. ክብደቷ ከተገቢዉ በላይ ከሆነ ከእርግዝና በፊት መቀነስ ይኖርባታል፡፡

4. የስኳር ህመም ያለባት ሴት ከማርገዟ በፊት ህመሟን በቁጥጥር ስር ማድረግ አለባት፡፡

5. የእርግዝና ደም ግፊት የተጋለጡ እናቶችን ለመለየና የመከሰት እድሉን ለመቀነስ የቅድመ ወሊድ ክትትል በመጀመሪያ ሶስት ወር መጀመር
Join us in our biweekly ECHO session
Topic:- Liver Disease in pregnancy

Speaker:- Professor Hari Conjeevaram
Join us on time for case presentation, Q & A sessions and didactic lecture

Accredited:- 1 CEU credits

Time:- 4:00 PM

https://echo.zoom.us/meeting/register/tJ0vd-6sqDgqE93zDlc9TkTbASlHWxW4Ss-z
Monkeypox Virus Facts
Key facts
• Monkeypox is caused by monkeypox virus, a member of the Orthopoxvirus genus in the family Poxviridae.
• Monkeypox is a viral zoonotic disease that occurs primarily in tropical rainforest areas of Central and West Africa and is occasionally exported to other regions.
• Monkeypox typically presents clinically with fever, rash and swollen lymph nodes and may lead to a range of medical complications.
• Monkeypox is usually a self-limited disease with the symptoms lasting from 2 to 4 weeks. Severe cases can occur. In recent times, the case fatality ratio has been around 3-6%.
• Monkeypox is transmitted to humans through close contact with an infected person or animal, or with material contaminated with the virus.
• Monkeypox virus is transmitted from one person to another by close contact with lesions, body fluids, respiratory droplets and contaminated materials such as bedding.
• The clinical presentation of monkeypox resembles that of smallpox, a related orthopoxvirus infection which was declared eradicated worldwide in 1980. Monkeypox is less contagious than smallpox and causes less severe illness.
• Vaccines used during the smallpox eradication programme also provided protection against monkeypox. Newer vaccines have been developed of which one has been approved for prevention of monkeypox
• An antiviral agent developed for the treatment of smallpox has also been licensed for the treatment of monkeypox.
(Source: WHO)