ኮሌጃችን አዳዲስ እና ፈር ቀዳጅ የሆኑ የሕክምና ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅና ለመተግበር በሰነቀዉ ራዕይ መሠረት እነሆ አዳዲሶቹን የኒዉክሌር ህክምናና በጨረር የካንሰር ህክምናን ለመጀመር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት የተደራጀ የጨረር ህክምና(Radiation Oncology) ፤ የኒዉክሌር የምርመራና ህክምና (Nuclear Medicine) ማዕከላት በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም ባሻገር ለሀገሪቱ የመጀመሪያ ከአፍሪካ ደግሞ ከቀዳሚዎቹ አንዱ የሆነዉ የአይሶቶፕ ማምረቻ (CYCLOTRON) ግንባታ በመፋጠን ላይ ይገኛል፡፡ ይህ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነዉ ፋሲሊቲ በአለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ የቴክኒካል ትብብር ፕረግራም ፕሮጀክት የምደገፍና ለህክምና(Therapy)፣ ለምርመራና(Diagnosis) ለምርምር(Research) የሚዉሉ አይሶቶፖችን ለማምረት የሚያስችል ነዉ፡፡ በመሆኑም የሀገሪቱን የጤና አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግር ይታመናል፡፡ መጪዉ ጊዜ አስደማሚ የሆነ የጤና አገልግሎት የምንሰጥበት ይሆናል፡፡
እኔም በዚህ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሕሙማንን ለማልገል በሚሰራ ተቋም በመስራቴ ደስተኛ ነኝ፡፡ መጪዉ ጊዜ አስደማሚ የሆነ የጤና አገልግሎት የምንሰጥበት ይሆናል፡፡
እንኳን ለ75ኛ ዓመት የሆስፒታላችን የምሥረታ በዓል አደረሰን!
እጅጉ ከበደ
ሜዲካል ፊዝሲስትና የETHIO-IAEA የቴክኒክ ትብብር ፕረግራም ፕሮጀክት አስተባባሪ
#sphmmc_75thanniversary

ኮሌጁ በቀጣይ ዓመታት በሕክምና አገልግሎት፣ በትምህርት እና በምርምር የላቀ ተቋም ሆኖ እንዲወጣ አመራሩና መላው ሠራተኛ በጋራ መሥራት ይጠበቅባችኃል ፡፡ በኮሌጁ በዘመናት የተገኘውን ስኬት ማስቀጠል እና ወደላቀ ደረጃ ማሻገር ይገባል።
የልብና የካንሰር እና የንቅለ ተከላ ማዕከላት ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት ከመሰጠቱ በፊት በእናንተ ከወዲሁ ቅድመ ሥራዎች መጀመራችሁን ስመለከት ደስታ ይሰማኛል፡፡ ማዕከላቱ ስራ ሲጀምሩ በሐገር አቀፍ ደረጃ ሁነኛ አገልግሎት እንደሚሰጡ እተማመናለሁ፡፡
ከአለም አቀፍ የአቶሚክ ኤጀንሲ ጋር በትብብር የምትሠሩት ሥራ በእጅጉ የሚበረታታ ነው፡፡ የጨረር ሕክምና ፣የኒውክሌር የምርመራ ሕክምና መገንባት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ፋሲሊቲ ለሕክምና፣ለምርመር ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ የኮሌጁን ብቻ ሣይሆን የአገራችንን የጤና አገልግሎት ደረጃ ከፍ ያደርገዋል፡፡ መጪው ዘመንም መላው ኢትዮጲያውያን በዘመነ ሁኔታ የምታገለግሉበት እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር

በዓለም ላይ ለሌሎች ማገልገልን የመሰለ መልካም ሥነምግባር የለም:: በተለይ ደግሞ ለታመሙ ሠዎች በፍቅር ማገልገል ይለያል::
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ለእንዲህ አይነት የፍቅር አገልግሎት ተመስርቶ ፈር ቀዳጅ በመሆን አገልግሎቱን ላለፍት 75ዓመታት በማስቀጠሉ ልዩ አድናቆታችንን ልንቸረው ይገባል።
ተቋማችን ገና ብዙ አዳዲስ የሕክምና አገልግሎቶችን በመክፈት የትምህርት ዘርፎችን በማስፍት እና አዳዲስ የምርምር ሥራዎችን በማምጣት እያበራ ይቀጥላል።
መልካም 75ተኛ ዓመት ለምርጡ ተቋም ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ።
ዶ/ር ማኅተመ በቀለ
የጥናት እና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

ኮሌጃችን በሀገራችንም ለመጀመሪያ የሆነዉን የሪስፓራቶሪ ቴራፒ በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች ስራ አስጀመረ፡፡ይህም ኮሌጁ የሚሰጠውን የሕክምና አገልግሎት በእጅጉ ከፍ ያደርገዋል፡፡
በዛሬው ቀን እነዚህን ባለሙያዎች በይፋ ወደስራ ገብተዋል፡፡
ሪስፓራቶሬ ቴራፒስቶች በአንድ ጤና ተቋም አገልግሎታቸው ሰፊ ነው፡፡ የመተንፈስ ችግር ያለባቸዉን ታማሚች ለመለየት፣ ለመመርመርና ለማከም የተሟላ ስልጠና ያላቸው እና ብቁ የሆነ ክህሎት ያላቸው የጤና ባለሞያዎች ናቸው፡፡
በየትኛዉም እድሜ ክልል ያሉ ህሙማንን ወደ ትክክለኛ የሆነ አተነፋፈስ ስረአት እንዲመጡና እንዲኖራቸዉ ከሐኪሞችና ነርሶች እንዲሁም ከሌሎች ባለሞያዎች ጋር ይሰራሉ፡፡
በመሆኑም የሪስፓራቶሪ ቴራፒ ባለሞያ ከመጀመሪያ ምርመራ ጀምሮ ታካሚዎች ራሳቸዉን እንዲረዱ ጭምር ስለ አተነፋፈስ ያስተምራሉ፡፡ ሪሰፓራቶሬ ቴራፒሰቶች በተለያዩ ተቋማት ( ሆስፒታል፣ ክሊኒክ፤) እንዲሁም የተለያዩ ክፍሎች ( ፅኑ ህሙማን ክፍል፣ ድንገተኛ ክፍል…. )መስራት የሚችሉ ባለሞያዎች ናቸዉ፡፡
ይህ የሕክምና ቡድን ወደ ስራ ሲቀላቀል የሚያበረክተዉ አስተወፅኦ ዋና ዋናዎቹን ለመጥቀስ ያህል፡- የመተንፈሻ አካል ችግር ያለበቸዉን ህሙማን መመርመር ፣ ከሐኪሞችና ነርሶች ጋር በመሆን ስለ ህሙማን ህክምና ማቀድ ፣ የታካሚዉ ያለበትን ሁኔታ መገምገም ፣ ለመተንፈሻ አካል የሚሆኑ መዳኒቶችን መስጠት ፣ የተሰጡ የህክምና አገልግሎቶችን መመዝገብ ፣ ለመተንፈሻ አካል የሚሆኑማሽኖችን ኦፕሬት ማድረግ ፣ ለህሙማን የመተንፈሻ አካልን በተመለከተ ትምህርት መስጠት ወ .ዘ. ተ ናቸው፡፡

We are proud to work in one of the most dynamic and progressive medical institution and school in the country. It is a home away home and we are happy to be part of this vibrant community. We will continue to strive for excellence in women's health.
Happy 75th anniversary and more is yet to come.
Dr. Delayehu Bekele
Head, Department of Obstetrics and Gynecology
#sphmmc_75thanniversary
Happy 75th anniversary and more is yet to come.
Dr. Delayehu Bekele
Head, Department of Obstetrics and Gynecology
#sphmmc_75thanniversary
የሀገሪቱን የጤና ፖሊሲ አቅጣጫ በመከተል ከአመሰራረቱ ጀምሮ ድሆችን ማገልገል መርሁ ያደረገው ኮሌጃችን ካለፉት አምስት ዓመታት ጀምሮ የካንሰር ሕክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ አገልግሎቱን ይበልጥ ለማስፋፋትና ጥራቱን የጠበቀ ለማድረግ በሀገሪቱ የመጀመሪያና
ሁለገብ የሆነ የካንሰር ማዕከል በማስገንባት ላይ ይገኛል።
እኔም የዚህ ባለብዙ ሕልምና ባለ ብሩህ ተስፋ ኮሌጅ ማህበረሰብ አባል በመሆኔ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ሁላችንንም እንኳን ለ75ኛ ዓመት የአልማዝ እዮቤልዪ በዓል አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ!
ዶ/ር አብዱ አደም
የካንሰር ህክምና ስፔሻሊስት
የካንሰር ህክምና ክፍል ሀላፊ
የህክምና ጥራት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

Honourable Worksemu Mamo
Chair Person of Health, Social Development, Culture and Sport Affiars Standing Committee
St. Paulo’s Hospital and Millennium Medical College 75th Diamond Jubilee Celebration
St. Paulo’s Hospital and Millennium Medical College now has reached 75th years since its establishment was in 1939 E.C by the late Emperor Haile Selassie. Thus, on the occasion of its Diamond Jubilee it is with great pleasure and happiness to say congratulations to all the leadership, managements and workers of the Hospital and Millennium Medical College as well as to all who got medical services and treatment from the hospital. Finally, We Health, Social Development, Culture and Sport Affiars Standing Committee express our good will for the zeal of the Hospital and Millennium Medical College in the future/ in the time to come.
Honor Message from Health, Social Development, Culture and Sport Affiars Standing Committee, House of Peoples Representatives of the FDRE. #sphmmc_75thanniversary
Chair Person of Health, Social Development, Culture and Sport Affiars Standing Committee
St. Paulo’s Hospital and Millennium Medical College 75th Diamond Jubilee Celebration
St. Paulo’s Hospital and Millennium Medical College now has reached 75th years since its establishment was in 1939 E.C by the late Emperor Haile Selassie. Thus, on the occasion of its Diamond Jubilee it is with great pleasure and happiness to say congratulations to all the leadership, managements and workers of the Hospital and Millennium Medical College as well as to all who got medical services and treatment from the hospital. Finally, We Health, Social Development, Culture and Sport Affiars Standing Committee express our good will for the zeal of the Hospital and Millennium Medical College in the future/ in the time to come.
Honor Message from Health, Social Development, Culture and Sport Affiars Standing Committee, House of Peoples Representatives of the FDRE. #sphmmc_75thanniversary
We are proud to work in one of the most dynamic and progressive medical institution and school in the country. It is a home away home and we are happy to be part of this vibrant community. We will continue to strive for excellence in women's health.
Happy 75th anniversary and more is yet to come.
Dr. Delayehu Bekele
Head, Department of Obstetrics and Gynecology
#sphmmc_75thanniversary
Happy 75th anniversary and more is yet to come.
Dr. Delayehu Bekele
Head, Department of Obstetrics and Gynecology
#sphmmc_75thanniversary
በየጊዜው በለውጥ እና ለተገልጋዮች የላቀ አገልግሎት በሚሰጠው ተቋማችን ብቃት ያለው የሰው ሐይል ያስፈልገዋል፡፡በተደራጀና ዘመናዊ የሆነ የመረጃ ስርዓትን በማደራጀት ፤የላቀ አደራጃጀት በመዘርጋት የሰው ሓይሉን በሟሟላት የአገልግሎቱ አሰጣጡን የተሻለ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡
ወደፊትም በብቁ ባለሙያዎችና አደራጃጃት ምርጥ የሕክምና ኮሌጅ እንዲሆን እንሰራለን፡፡ እኔም የዚህ ትልቅ ተቋም አካል መሆኔ ትልቅ ክብር ነው፡፡
ዳንኤል ቸርነት
የሰው ሐብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክተር
#sphmmc_75thanniversary
ወደፊትም በብቁ ባለሙያዎችና አደራጃጃት ምርጥ የሕክምና ኮሌጅ እንዲሆን እንሰራለን፡፡ እኔም የዚህ ትልቅ ተቋም አካል መሆኔ ትልቅ ክብር ነው፡፡
ዳንኤል ቸርነት
የሰው ሐብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክተር
#sphmmc_75thanniversary
የክቡር ዶር አየለ ተሾመ መልዕክት
ሚኒስትር ዴኤታ-ጤና ሚኒስትር
ተቋማት ዓላማን ሰንቀው ይመሰረታሉ፤ በጉዞአቸውም ያድጋሉ፣ ይለወጣሉ፣ አንዳንድ ጊዜም የታሰበውን ግብ አሳክተውም አለያም ሳይሆንላቸው ይቀርና ይዘጋሉ አለያም ይከስማሉ! እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የተራማጅነትና እና አሻጋሪ ሃላፊነትን በሚገባ ለማሳካት ግን እድል ብቻ ሳይሆን ጠንካራ አደረጃጀትን እና ስትራቴጂክ የአመራር ጉዞን ይጠይቃል። በውስን የጤና አገልግሎት ዘርፎች የተጀመረው የ75 አመታት ጉዞአችሁ ዛሬ ላይ በአገልግሎት አሰጣጡ ብቻ ሳይሆን በመማር ማስተማርና በምርምር ስራዎችም ጭምር ፋና ወጊ ሆኖ ማየት እንደ ሃገርም ኩራት ነውና በነዚህ አመታት ሁሉ በሁሉም ዘርፍ በተለይ ደግሞ በአመራርነት አሻራችሁን ላሳረፋችሁ ሁሉ ልትኮሩ ይገባልና እንኳን አደረሳችሁ ፣ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ! በቀጣይም የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በፍጥነት ተጠናቀው የታለመላቸውን የ3ኛ እና 4ኛ ደረጃ ጤና አገልግሎት ጀምረው ህዝባችን ላይ የሚደርሰውን የጤና ጉዳትና ሞት ከመግታት ባሻገር እንደ ሃገርም ለቀጠናው የሜዲካል ቱሪዝም መዳረሻነት ህልም እንድታሳኩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንክራችሁ እንድትሰሩ ፤ በተጨማሪም በጤና ስርአት ግንባታ፣ በሰው ሃብት ልማትና ሃገር በቀል እውቀቶችን ከማስፋት አንፃር የቀሩ የቤት ስራዎችን ከመስራት አንፃር የአንበሳውን ድርሻ እንደምትወጡ በመተማመን በድጋሚ እንኳን ለ75ኛ አመት የኢዮቤልዩ በአል አደረሳችሁ በማለት በጉዞአችሁ ሁሉ እንደ ጤና ሚኒስቴርም የሚጠበቀውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ቃል እየገባሁ ነው! አመሠግናለሁ !!
ዶር አየለ ተሾመ
የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ