St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
Announcement

written examination for all MPH applicants, both regular and weekend, will be on October 15,22.

Note the following points before coming:

1. Place of examination: Medhanialem general secondary school, located just next to Medhanialem roundabout. (Gulele)
2. To bring a valid Identification card.
3. Examination start time: morning 3:30 AM local time.
4. Only those who have passed the primary screening will be allowed to site for examination: check your names on the will be posted list.
5. To communicate the registrar in person for any complaint between Oct, 7,22. and oct,10,22.
የሐዘን መግለጫ
የኮሌጃችን የፋርማሲ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ፋንታነሽ አብርሐም ባጋጠማቸዉ የድንገተኛ ህመም ዛሬ በ26/01/2015 ዓ›ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ፡፡
የኮሌጃችን ማህበረሰብ ለቤተሰቦቻቸዉና ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉ መፅናናትን ይመኛል ፡፡
በአዲስ አበባ ከሚገኙ ከአስራአንድ የመንግስት ሆስፒታሎች የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በስራ ቦታ በመገኘት አገልግሎት አሰጣጥን ተመልክተዋል፡፡በተጨማሪም የኮሌጁ አገልግሎት አሰጣጥንም ገምግመዋል፡፡
በዚህ የልምድ ልውውጥ ወቅት የተገኙት የጤና ሚኒስት ዴኤታ ዶር አየለ ተሾመ እንደገለጹት እንዲህ ዓይነቱ መርሐግብር የእርስ በእርስ መማሪያ መድረክ ነው ብለዋል፡፡በመቀጠልም የአስተዳደር እና የሆስፒታል መሪዎች ብቃትና ውጤታማነት ወደ መሬት ወርዶ መታየት አለበት ብለዋል፡፡
በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ የ system bottleneck focused reform ትግበራ ያለበትን ደረጃ እና የሥራ ሂደቶች ጠንካራ ጎን በማመስገን ሊሻሻሉ የሚገቡ ጉዳቶች ላይ ጥቆማ ተሰጥቷል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶር አየለ በአጠቃላይ ስለ ጉብኝቱ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ በሠጡት አስተያየት እንደገለጹት የኮሌጁ አመራሮች ፣ መላው ሠራተኛና በተለይም ስፔሻሊት ሐኪሞችና እና ነርሶች የሪፎርሙን አስፈላጊነት በመረዳት ለተግባራዊነቱ እያሳዩት ያለው ተነሳሽነት በሁሉም የሪፎርሙ ፓኬጆች ትግበራ ላይ አስደናቂ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል፡፡
#system_bottleneck_focused_reform
Pease find the list of applicants who are selected for written examination after primary document screening.

you are advised to communicate the registrar, in person, if your name is not on the list till October 12,22.

https://sphmmc.edu.et/2022/10/06/to-all-public-health-applicants/
Medical Microbiology MSC. Applicants Screening

1. Time table for exam
• Written exams will be administered on October 13, 2022
• Time: 2:00pm (afternoon)
• Place: Administration building 1st floor
2. All ineligible applicants may submit the missing documents to the main registrar office, till Friday October 7, 2022, 11:30am.
MSc medical microbiology applicants screened for the written exam (Please find a link below)
https://sphmmc.edu.et/2022/10/06/medical-microbiology-msc-applicants-screening/
ሀገር አቀፍ የሐኪሞች ስፔሻሊቲ ስልጠና /ERMP/ ማስታወቂያ
_______

የህክምና ዶክትሬት ዲግሪ ላላችሁና የስፔሻሊቲ ስልጠና መውሰድ ለምትፈልጉ በሙሉ፡-
የጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በ2015 የትምህርት ዘመን፤ በ22 የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች አመልካቾችን በብሄራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና መግቢያ ፈተና አወዳድሮ ለማሰልጠን ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡ በመሆኑም ፍላጎት ባላችሁ የስፔሻሊቲ ትምህርት ዘርፍ ላይ በጤና ሚኒስቴር ድረ-ገፅ (www.moh.gov.et/ermp) መመዝገብና መወዳደር እንደምትችሉ አውቃችሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን የምዝገባ ጊዜውም ከጥቅምት 7-21 ቀን 2015ዓ.ም /October 17-31/2022/ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የፈተና ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን በተመለከተ ከላይ በተጠቀሰው ድረ-ገፅ ላይ ወደፊት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
ምዝገባውን ከመጀመራችሁ በፊት ዝርዝር መረጃዎችንና መመሪያዎችን እንድትመለከቱ እናሳስባለን፡፡

የጤና ሚኒስቴር እና የትምህርት ሚኒስቴር !!!
የአእምሮ ጤናንለመጠበቅ የሚረዱ 5 ነገሮች!
Notice for eligible candidates interested to join New Innovative Medical Education Initiative (NIMEI) schools administered by Ministry of Health
Ministry of health has delegated Saint Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC) to administer the National New Innovative Medical Education Initiative (NIMEI) Entrance exam based on to the New Innovative Medical Education Initiative (NIMEI) curriculum Admission Policy.

The registration as well as dissemination of results will be online, on the official pages of Ministry of Health official website and Facebook page; and SPHMMC official website, Facebook page and Telegram. Paper based or face to face application is not available. Please use this link to proceed: https://sphmmc.edu.et/2022/10/13/announcement-for-eligible-candidates-interested-to-join-nimei-schools/
የኔታ የተባለ ዩ ቲዩብ ባስተላለፈው የተሳሳተ ዘገባ የተሰጠ መግለጫ

በየኔታ ዩቱብ ቻናል ላይ የሚሰሩት አቶ ተክለሐይማኖት አዳነ የተባሉ ግለሰብ የኮሌጃችንን የፎረንሲክ ሕክምና ምንነት እና አገልግሎት አሰጣጥ በወጉና በአግባቡ ሳይረዱ የተሳሳተ እና ተገቢ ያልሆነ መረጃ ለሕዝብ አሰራጭተዋል፡፡

በይሆናል እና በዘፈቀደ የራሳቸውን ያልተገባ ምልከታም ጨምረው አካተዋል፡፡ይህም የእሳቸው የዩቱብ ተከታዮች የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲወስዱ አድርጓል፡፡

በእውነት የምርመራ ጋዜጠኝነት መስራት ከፈለጉ የተደራጀ መረጃ ከሚመለከታቸውና ባለሙያዎችና ኃላፊዎች ማግኘት ይችሉ ነበር፡፡ ግን አላደረጉም፡፡ ኮሌጃችን በጤና ዙሪያ እና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በወር በአማካይ በቁጥር 15 የሚደርሱ ጥያቄዎች ይቀርቡልናል፡፡ ሁሉንም እናስተናግዳለን፡፡ይህም ለማንኛውም ከሚዲያ የሚቀርቡልን ጥያቄዎች በራችን ክፍት እንደሆነ ማሳያ ነው፡፡

እርሳቸው ግን የፈለጉት ባለሙያዎቻችን ቀደም ብሎ ሳይነግሯቸው በድንገቴ በስልክ መረጃ ጠይቀዋል፡፡ ይህም አግባብ ነው ብለን አናምንም፡፡ የሚመለከተውን ቀጠሮ አስይዘው እና በቦታው ተገኝተው መረጃ አልሰበሰቡም፡፡ በሰሩት የዩ -ቲዩብ ቪዲዮአቸው እንደተረዳነው ስለፎረንሲክ ሜዲሲንና ተያያዥ ጉዳዮች ለሕዝብ ለማሰተማር( ለማስረዳት) በቂ እውቀት መረጃ ሳይኖራቸው በስማ በለው የተሳሳተ እና ያልታረመ መረጃቸውን ለቀዋል፡፡ መረጃን ለማግኘት ስለሚቀርቡ ጥያቄዎች አስመልክቶ በነጋሪት ጋዜጣ በወጣው የመገናኛ ብዙሀን እና ነጻነትን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 590/2000 ተላልፈውታል፡፡( በዚሁ አዋጅ መረጃ ለማግኘት ስለሚቀርቡ ጥያቄዎች የተደነገገውን ይመልከቱ፡፡)

ኮሌጁ የአስከሬን ምርመራ ማድረግ ከጀመረበት ካለፉት 10ዓመታት ጀምሮ ʻ የቤተሰቤን አሰከሬን ማግኘት አልቻልኩም ʻ ብሎ ቅሬታ ያቀረበ ግለሰብ የለም፡፡ ከሕጋዊ ተቋምም አንዳች ክስ አልቀረበም፡፡

ለሕክምና ወደ ኮሌጃችን የመጡ ታካሚዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ አስከሬናቸው ለቤተሰብ ይሰጣል፡፡ ቤተሰብ የሌለው አስከሬን ግን እስከ ሁለት ወር ጠያቂ እስኪመጣ ድረስ ይጠበቃል፡፡ ከሕግ ጋር ተያያ ዥነት ያለው ምርመራ ውጤቱ ለፖሊስ ይሠጣል። ወደ ምርመራ ማዕከላችን ተልከው በቀነ ገደቡ ያልተወሰደ አስከሬን በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በኩል ወደ ዘላቂ ማረፍያ ይላካሉ። ማንኛውም አስከሬን የራሱ መረጃ በኤሌክተሮኒክስና በፋይል ተሰንዶ ይቀመጣል፡፡ ይህም ጠያቂ ሲመጣ በቀላሉ መለየትና ማወቅ ያስችላል፡፡

በሕክምና ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ የሚሰጠውን የአናቶሚ ኮርስ ለማስተማር በኬሚካል የተዘጋጀ አስከሬን (cadaver) በመጠቀም ማስተማር ከ 500 ዓመታት በላይ ሲሰራበት የቆየ ተግባር ነው፡፡ የሕክምና ትምህርት ያለ cadaver ማስተማር የማይቻል ሲሆን፤ ተማሪዎች ለሕሙማን ሕክምና ለመስጠት ከመብቃታቸው በፊት በአስከሬን ላይ በጥልቀት ጥናትና ምርምር ማድረግ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህ የማስተማሪያ መንገድ በኢትዮጲያ ባሉ አንጋፋ የሕክምና ትምህርት ቤቶች ከምሥረታቸው (60 ዓመት በላይ) ጀምሮ የነበረና ወደ ፊትም የሚቀጥል ነው፡፡

በ2005 ዓም የጤና ሚኒስቴር በመላው ኢትዮጵያ 33 አዲስ የሕክምና ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ሲያደርግ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች በ cadaver እጥረት የመማር ማስተማሩ ሂደት ከፍተኛ ችግር ተከስቶ ነበር ፡፡ ኮሌጃችን ይህን ችግር ለመፍታት ለጤና ሚኒስቴር ፕሮፖዛል በማቅረብ በሕግ አግባብ የታገዘ ጠያቂ የሌላቸውን አስከሬኖች በማዘጋጀት ለሌሎች የሕክምና ትምህርት ቤቶች ማስተላለፍ የሚቻልበትን ድጋፍ አግኝቷል፡፡ አንድ አስክሬን ለሕክምና ትምህርት እንዲውል ለማድረግ ቢያንስ 30,000 ( ሰላሳ ሺህ ብር) የሚያወጡ የተለያዩ ኬሚካሎችን መጠቀም የግድ ይላል ፡፡ አስከሬኖቹ ለማስተማሪያ ወደ ሌላ ኮሌጅ ሲተላለፉ የሚጠየቀው ክፍያ ኮሌጁ ያወጣውን ወጪ እንዲጋሩ ለማድረግ ነዉ፡፡ ይህ ገንዘብም ከኮሌጆቹ በቀጥታ ወደ መንግስት ካዝና የሚገባ ነው፡፡ አቶ ተክለሐይማኖት አስከሬን ተቸበቸበ የሚሉት ይሀንን ነው፡፡ ለትክክለኛ መረጃ ያለው የምርመራ ጋዜጠኝነት ሥራን መስራት ቢፈልጉ ኑሮ የተደራጀ መረጃ ያገኙ ነበር፡፡ በሕክምና ዘርፍ ምንም መነሻ ዕውቀት ሳይኖራቸው በመሠለኝና በይሆናል መረጃቸውን በአየር አውለውታል፡፡ የጤና ነክ ጉዳዮች ላይ መረጃ ለመስጠት አስቀድሞ ነገሩን ከስር መሰረቱ መረዳት ያፈልጋል፡፡ የጤና ጉዳይ ሳይንስ ነው፡፡ የጤና ጉዳዮች ለዩቲዩብ ገንዘብ ለማግኘት የሚሰራ አይደለም፡፡ ሕዝብን ለማስተማር እንጂ፡፡ በአስተማማኝ መረጃ በማቅረብ ሕብረተሰቡ በወጉ እንዲረዳው ያስፈልጋል፡፡

'ዘጋቢውም' ሆነ የዩቱዩብ ቻናሉ የጤናን ጉዳይ በኃላፊነት ተሰምቷቸው የማይሰሩ መሆኑን ይህ የሰሩት ሪፖርት ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ ላለፉት 75 ዓመታት የኢትዮጵያን ሕዝብ ያገለገለን ተቋም ካለትክክለኛ ማስረጃ መልካም ስምና ዝናውን ማጉደፍ በሕግ ያስጠይቃል፡፡ ይህም የየኔታ ዘገባ የሕክምና ትምህርት አሰጣጥና በመስኩ የሚደረገውን የአገልግሎት አሰጣጥ በእጅጉ ይጎዳዋል፡፡ይህ ካለበቂ መረጃ እና የጋዜጠኛ ቅድመ ዝግጅት ያልተሰራ ዘገባ ከዩቲየብ ቻናሉ እንዲወርድ እና የይቅርታ ማሰተባበያ እንዲሰጡ በአጽንኦት እየጠየቅን፤ ይህ የማይደረግ ከሆነ ግለሰቡንም ሆነ የኔታ ቲዩብን የሐሰት ዘገባ አቅደው በመስራታቸው ወደ ሕግ የምናቀርባቸው መሆኑን እንገልጻለን፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ።
የቢጫ ወባ ክትባት ጀምረናል! በአገልግሎቱ ይጠቀሙ፡፡
Dear Nimei applicants,
Since the number of students registered for NIMEI so far is below expected margin, we extend the the final registration date and exam date as follows;

The final date for registration is: November 2nd, 2022/ Tikemt 23 2015
The examination date: November 6th, 2022/ Tikemt 27 201


Warmly,
የጡት ካንሰር በሽታ ምንድን ነው?
የጡት ካንሰር በአብዛኛው በሴቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ወንዶችንም የሚያጠቃ የካንሰር ዓይነት ነው፡፡የጡት ካንሰርም በቅድሚያ በጡት ላይ በመከሰት በሽታው በአጭር ጊዜ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በመዛመት የከፋ ችግር ያስከትላል፡፡

ጡት በተፈጥሮ በውስጡ ወተት ለማመንጨት የሚያስችሉ በርካታ ከረጢት መሰል ነገሮች እንዲሁም እነዚህን ከጡት ጫፍ ጋር የሚያገናኙ ቱቦዎች አሉት፡፡
እነዚህ ቱቦዎች በእርግዝና ወቅት ወተት ለማመንጨት ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ የጡት ካንሰር ጅማሬው በእነዚህ ቱቦዎች ውስጥ ነው፡፡ የጡት ካንሰር ተፈጠረ የሚባለው አንድ ጤነኛ ያልሆነ ህዋስ በሰውነታችን ውስጥ ተፈጥሮ ከገደብ በላይ መራባት ሲጀምር ነው፡፡ የተራባው ህዋስም በጊዜ ሂደት ጤነኛ የነበሩ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ህብረ ህዋሳትን በማጥቃት በሽተኛ ያደርጋቸዋል፡፡
ለጡት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች
የጡት ካንሰር በብዛት ሴቶችን የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡ የሚከሰትበት ምክንያት በውል አይታወቅም፡፡ የሚከተሉት ሴቶች ግን የበለጠ ለበሽታው ተጋላጭ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

• ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ፡፡ የእድሜ መጨመር ለጡት ካንሰር አጋላጭ ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡ ፣
• ከዘር/ከቤተሰብ በጡት ካንሰር የተያዘ ካለ ለበሽታው የመጋለጥ እድል ከፍተኛ
• ካንሰር ያልሆኑ ሌሎች የጡት በሽታዎች አጋጥሞ ከነበረ፣
• የአልኮል መጠጥ የሚያበዙ ሴቶች ለጡት ካንሰር ተጋላጭ ናቸው፡፡ አልኮል መጠጥ አዘውትራ የምትወስድ ሴት አልኮል ከማይጠቀሙት ይልቅ በጡት ካንሰር የመያዝ እድሏ ከፍተኛ ነው፡፡
• የወር አበባቸውን ቀድመው/በልጅነት ያዩ ሴቶች ለጡት ካንሰር ተጋላጭ ናቸው፡፡
• ከ30 ዓመት በኋላ ልጅ የሚወልዱ ወይም ከነጭራሹ የማይወልዱ፣
የወር አበባ ማየት ከማቆም(ከማረጥ) በኋላ የሚመጣ የሰውነት ክብደት መጨመር ለጡት ካንሰር ያጋልጣል፡፡
• ከሚገባው ዕድሜ በጣም ዘግይተው ያረጡ፣
• ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ የሚያዘወትሩና ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው፣
• በስራ ገበታቸው ላይ በከፍተኛ ጨረር ውስጥ ያለምንም መከላከያ የሚሰሩ
• ሰራተኞች በበሽታው የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡፡፡
•


የጡት ካንሰር ምልክቶች

የጡት ካንሰር ሲጀምር ህመምም ሆነ ምልክቶች የሉትም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የጡት ላይ እብጠቶች ካንሰር ባይሆኑም ዋነኛው የጡት ካንሰር ምልክት ግን በጡት ላይ የሚከሰት ጠጣር እብጠት ነው፡፡ የሚከተሉት ደግሞ ተጨማሪ ምልክቶቹ ናቸው፡፡
• ከጡት ጫፍ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ መውጣት፣
• የጡት ጫፍ አካባቢዎች መቅላትና ወደ ውስጥ መሰርጎድ፣
• በጡት አካባቢና በብብት ውስጥ እብጠት መከሰትና ሙቀት ያለው መሆን፣
• የጡት ቆዳ መሸብሸ/ወደ ውስጥ መግባት ወይም እንደብርቱካን ልጣጭ ዓይን ማውጣት፣
• ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ሲታዩ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምናና ምርመራ ማድረግ ነው፡፡

የጡት ካንሰር መከላከያ ዘዴዎች
የጡት ካንሰር ተሰራጭቶ ወደ ሌላ የሰውነት አካል ከመድረሱና ከመባዛቱ በፊት ከተደረሰበት ሙሉ በሙሉ ሊድን የሚችል በሽታ ነው፡፡ በመሆኑም የጡትን ችግር በየወቅቱ ወይም በየጊዜው ለማወቅ ሴቶች በተወሰነ ጊዜ በጡታቸው ላይ የሚከሰተውን እብጠት በጥንቃቄ መመርመር ተገቢ ነው፡፡ የኸውም፣-

1. የማሞግራም ምርመራ ማድረግ
ይህ ምርመራ ጡትን ራጅ በማንሳት የሚደረግ የምርመራ ዘዴ ሲሆን አስተማማኝ የጡት ካንሰር ምርመራ ዘዴ ነወ፡፡ በመሆኑም ብዙ ሐኪሞች ማንኛዋም ሴት ከ40 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ በየዓመቱ እንዲሁም ከ20 እስከ 40 ዓመት ያሉ ደግሞ በየሦስት ዓመቱ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው ይመክራሉ፡፡

2. ሐኪም በመዳሰስ የሚያደርገው ምርመራ
ሐኪም ጋር በየስድስት ወሩ በመቅረብ፣ የሚሰማን ስሜት በመግለጽና ጡትን በማሰዳሰስ ምርመራ ማድረግም ተገቢ ነው፡፡
3. የራስን ጡት በራስ የመመርመር ዘዴ

የራስ በራስ የጡት ምርመራ በየወሩ ማድረግ ህይወትን ከሞት ለመታደግ ያስችላል፡፡ጡት በወር አበባ ምክንያት በቅርጽ፣ በመጠንና በስሜት ስለሚቀያየር ሁልጊዜ በየወሩ በተለመደ ቀን መመርመር አለበት፡፡ ይህን ማድረግ ጡት ላይ የሚከሰት ማንኛውንም ለውጥ ለማወቅ ይረዳል፡፡