የጡት ካንሰር በሽታ ምንድን ነው?
የጡት ካንሰር በአብዛኛው በሴቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ወንዶችንም የሚያጠቃ የካንሰር ዓይነት ነው፡፡የጡት ካንሰርም በቅድሚያ በጡት ላይ በመከሰት በሽታው በአጭር ጊዜ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በመዛመት የከፋ ችግር ያስከትላል፡፡
ጡት በተፈጥሮ በውስጡ ወተት ለማመንጨት የሚያስችሉ በርካታ ከረጢት መሰል ነገሮች እንዲሁም እነዚህን ከጡት ጫፍ ጋር የሚያገናኙ ቱቦዎች አሉት፡፡
እነዚህ ቱቦዎች በእርግዝና ወቅት ወተት ለማመንጨት ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ የጡት ካንሰር ጅማሬው በእነዚህ ቱቦዎች ውስጥ ነው፡፡ የጡት ካንሰር ተፈጠረ የሚባለው አንድ ጤነኛ ያልሆነ ህዋስ በሰውነታችን ውስጥ ተፈጥሮ ከገደብ በላይ መራባት ሲጀምር ነው፡፡ የተራባው ህዋስም በጊዜ ሂደት ጤነኛ የነበሩ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ህብረ ህዋሳትን በማጥቃት በሽተኛ ያደርጋቸዋል፡፡
ለጡት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች
የጡት ካንሰር በብዛት ሴቶችን የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡ የሚከሰትበት ምክንያት በውል አይታወቅም፡፡ የሚከተሉት ሴቶች ግን የበለጠ ለበሽታው ተጋላጭ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
• ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ፡፡ የእድሜ መጨመር ለጡት ካንሰር አጋላጭ ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡ ፣
• ከዘር/ከቤተሰብ በጡት ካንሰር የተያዘ ካለ ለበሽታው የመጋለጥ እድል ከፍተኛ
• ካንሰር ያልሆኑ ሌሎች የጡት በሽታዎች አጋጥሞ ከነበረ፣
• የአልኮል መጠጥ የሚያበዙ ሴቶች ለጡት ካንሰር ተጋላጭ ናቸው፡፡ አልኮል መጠጥ አዘውትራ የምትወስድ ሴት አልኮል ከማይጠቀሙት ይልቅ በጡት ካንሰር የመያዝ እድሏ ከፍተኛ ነው፡፡
• የወር አበባቸውን ቀድመው/በልጅነት ያዩ ሴቶች ለጡት ካንሰር ተጋላጭ ናቸው፡፡
• ከ30 ዓመት በኋላ ልጅ የሚወልዱ ወይም ከነጭራሹ የማይወልዱ፣
የወር አበባ ማየት ከማቆም(ከማረጥ) በኋላ የሚመጣ የሰውነት ክብደት መጨመር ለጡት ካንሰር ያጋልጣል፡፡
• ከሚገባው ዕድሜ በጣም ዘግይተው ያረጡ፣
• ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ የሚያዘወትሩና ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው፣
• በስራ ገበታቸው ላይ በከፍተኛ ጨረር ውስጥ ያለምንም መከላከያ የሚሰሩ
• ሰራተኞች በበሽታው የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡፡፡
•
የጡት ካንሰር ምልክቶች
የጡት ካንሰር ሲጀምር ህመምም ሆነ ምልክቶች የሉትም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የጡት ላይ እብጠቶች ካንሰር ባይሆኑም ዋነኛው የጡት ካንሰር ምልክት ግን በጡት ላይ የሚከሰት ጠጣር እብጠት ነው፡፡ የሚከተሉት ደግሞ ተጨማሪ ምልክቶቹ ናቸው፡፡
• ከጡት ጫፍ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ መውጣት፣
• የጡት ጫፍ አካባቢዎች መቅላትና ወደ ውስጥ መሰርጎድ፣
• በጡት አካባቢና በብብት ውስጥ እብጠት መከሰትና ሙቀት ያለው መሆን፣
• የጡት ቆዳ መሸብሸ/ወደ ውስጥ መግባት ወይም እንደብርቱካን ልጣጭ ዓይን ማውጣት፣
• ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ሲታዩ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምናና ምርመራ ማድረግ ነው፡፡
የጡት ካንሰር መከላከያ ዘዴዎች
የጡት ካንሰር ተሰራጭቶ ወደ ሌላ የሰውነት አካል ከመድረሱና ከመባዛቱ በፊት ከተደረሰበት ሙሉ በሙሉ ሊድን የሚችል በሽታ ነው፡፡ በመሆኑም የጡትን ችግር በየወቅቱ ወይም በየጊዜው ለማወቅ ሴቶች በተወሰነ ጊዜ በጡታቸው ላይ የሚከሰተውን እብጠት በጥንቃቄ መመርመር ተገቢ ነው፡፡ የኸውም፣-
1. የማሞግራም ምርመራ ማድረግ
ይህ ምርመራ ጡትን ራጅ በማንሳት የሚደረግ የምርመራ ዘዴ ሲሆን አስተማማኝ የጡት ካንሰር ምርመራ ዘዴ ነወ፡፡ በመሆኑም ብዙ ሐኪሞች ማንኛዋም ሴት ከ40 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ በየዓመቱ እንዲሁም ከ20 እስከ 40 ዓመት ያሉ ደግሞ በየሦስት ዓመቱ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው ይመክራሉ፡፡
2. ሐኪም በመዳሰስ የሚያደርገው ምርመራ
ሐኪም ጋር በየስድስት ወሩ በመቅረብ፣ የሚሰማን ስሜት በመግለጽና ጡትን በማሰዳሰስ ምርመራ ማድረግም ተገቢ ነው፡፡
3. የራስን ጡት በራስ የመመርመር ዘዴ
የራስ በራስ የጡት ምርመራ በየወሩ ማድረግ ህይወትን ከሞት ለመታደግ ያስችላል፡፡ጡት በወር አበባ ምክንያት በቅርጽ፣ በመጠንና በስሜት ስለሚቀያየር ሁልጊዜ በየወሩ በተለመደ ቀን መመርመር አለበት፡፡ ይህን ማድረግ ጡት ላይ የሚከሰት ማንኛውንም ለውጥ ለማወቅ ይረዳል፡፡

ዶር ሣራ ደምሰው የተባሉ Anesthesiology ስፔሻሊቲ ተማሪ በተለያዩ ሶሻል ሚዲያ ላቀረቡት አግባብነት የሌለው ክስ የተሰጠ ምላሽ
የቀድሞ ተማሪያችን/ባልደረባችን ዶር ሣራ ደምሰው በትምህርታቸውና ተያያዥ ጉዳዮች ኮሌጃችንን በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች እና በውይይት መድረኮች ክስ አቅርበዋል፡፡ የሚመለከታቸው ተቋማትም ሕግን ተመርኩዘው ምላሽ ሰጥተዋቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ግራና ቀኙን አይተው ውሳኔ ለሰጡዋቸው ተቋማት “ይግባኝ!” ማለት ትተው፤ በዩቲዩብ አቤቱታቸውን በተከታታይ ማሰማት ጀምረዋል፡፡ከጥቂት ወራት በፊት በኢዮሐ ዩ ቲዩብ፤አሁን ደግሞ የኔታ በተባለ ዩ ቲዩብ ክሳቸውን አሻሽለው መጥተዋል፡፡የዘውዱ ሾው ዩ ቲዩብ ቻናል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘውዱ በዶክተር ሣራ ጉዳይ የሚመለከታቸውን የኮሌጁን ሁለት ኃላፊዎችን አነጋግረዋል።
እንደለመደው የየኔታ ቲዩብም በተለያዩ አስደንጋጭ ርዕስ የዶክተርዋን ጉዳይ አጀንዳው አድርጎታል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ዘገባ ብዙዎችን ሊያሳሳት ይችላል፡፡ የሚመለከታቸው እና ከአንድ ወገን ብቻ መረጃ የሰሙት በሙሉ እውነታውን እንዲያውቁት ይህን እጥርጥር (Summery) እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡
ትምህርቱ (ሙያው) - Anesthesiology and critical care ( አንስቲዚዬሎጂ እና ክሪቲካል ኬር)
ሙያው ዕለት ተዕለት ከሕሙማን በጥብቅ ያገኛኛል፡፡ የአንድን ታካሚ ከቅድመ ቀዶ ሕክምና ወቅት እና በኃላ ለሕሙማን ሕክምና መስጠትን ያጠቃልላል፡፡ በተጨማሪም ጽኑ የሕክምና ክትትል ላሉም አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
በኮሌጁ በኩላሊት ንቅለ ተከላ ጀምሮ በሌሎች ቀዶ ሕክምናዎች ወገናቸውን ማገልገል የስፔሻሊሽቲ ሐኪሞች የዘውትር ስራቸው ነው፡፡
ይህ ከህሙማኑ ሕይወት ጋር በእጅጉ የተያያዘው ትምህርትም ከፍተኛ ትጋት ያሻል፡፡ የስፔሻሊቲ ተማሪዎችም ከመምህራኖቻቸው በተጨማሪ በቀዶ ሕክምና ሐኪሞች ክትትል ይደረግባቸዋል፡፡ ተማሪዎቹ እየሰሩና እየተማሩ ይመዘናሉ፡፡
ዶር ሣራና ትምህርታቸው
ይህን የስፔሻሊቲ ትምህርት የመረጡት ዶር ሣራ ዘውትር የተለያዩ ኮርሶችን አንብበው እንደማይጨርሱ ለመምህራኖቻቸው ይናገሩ ነበር፡፡ ምክንያታቸውም ‘ በቤቴ የሚያግዘኝ የለም ’ የሚል ነው፡፡ ይሁን እንጂ መምህራኖቻቸው የስፔሻሊቲ ዘርፉ ከፍተኛ ትጋት እንደሚፈልግ ይነግርዋቸው ነበር፡፡ በተለይ ለሙያቸው መሰረት የሆኑትን Basic Pharmacology እና physiology በደንብ ካላጠኑ ታካሚዎችን በበቂ እውቀት እና ሕክምና መስጠት እንደማይችሉ ምክር ሠጥተዋቸዋል፡፡ ዶክተርዋ ግን የሲኒየሮችን ምክር ገንዘብ ማድረግ አልፈለጉም፡፡ እንዲያውም የታካሚን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል ስህተት ተገኝቶባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ከዶር ሣራ ጋር የሚሰሩ የቀዶ ሕክምና ሐኪሞች “ በሥራዋ ላይ ከፍተኛ ክፍተት አለባት ” በማለት ሪፖርት አድርገዋል፡፡
ዶክተርዋ ትምህርታቸውንም በሚገባ ማጥናትም ሆነ በሕሙማን ላይ ክትትል ማድረግ አልቻሉም፡፡ በእነዚህና በሌሎች ብዙ ምዘናዎች ከሁለተኛ ዓመት ወደ ሶስተኛ ዓመት ማለፍ አልቻሉም፡፡ ውጤታቸውን የገመገሙት የትምህርት ክፍሉ ፣ የድኅረ ምረቃ አስተባባሪና የአካዳሚክ ኮሚሽን የዶር ሣራ ውጤት በአጭሩ“ Major Academic Deficiency ነው በማለት ውሳኔ ሠጥተዋል ።
የሕንድ አገር ቆይታቸው
ኮሌጃችን በሌሎች አገራት ያለውን (በተለይ በሕንድ) በመስኩ እንዴት እንደሚሰራ ተማሪዎችን እንዲያዪ ይልካል፡፡ ይህ ማለት የሕንድ ቆይታቸው በትምህርታቻው ሥርዓተ ትምህርት መመዘኛ ውጤት ያለው አይደለም፡፡ እሳቸው ግን በሕንድ ቆይታዬ ምስክር ወረቀት እና Recommendation አግኝቻለሁ የሚሉት ለሁሉም የተሰጠ ነው፡፡ ለእሳቸው ብቻ የተሰጠ አይደለም፡፡ስብሰባ የተሳተፉበት የምስክር ወረቀት በሚከታተሉት በስፔሻሊቲ የትምህርት ዘርፍ ውጤት አይያዝም፡፡ እርሳቸው ግን በህንድ የምስክር ወረቀት በግላቸው ለተካፈሉበት የአንድ ቀን ሴሚናር አጋነው ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ ተገቢ አይደለም፡፡
የእሳቸው ክሶች
ክሶቻቸው ከተለያዩ ተቋማት እስከ ዩ ቲዩብ ቻናሎች የዘለቀ ነው፡፡ ወደፊትም ክሳቸው ሊቀጥል ይችላል፡፡ አይታወቅም፡፡ መጀመሪያ አቤቱታቸውን ያቀረቡት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ዶር ዓብይ አህመድ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ነበር፡፡ በኃላም በጤና ሚኒስቴር የሴቶች ጉዳይ እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ነው፡፡ የኮሌጁ የአካዳሚክ ፕሮቮስት እና የትምህርት ክፍሉ ተጠሪዎች በሚመለከታቸው ፊት ቀርበው በዶር ሣራ አካዳሚክ አቤቱታ እና ተዛማጅ ጉዳዮች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የዶር ሣራ ውጤታቸው Academic Deficiency እንደሆነ በየደረጃው አስረድተዋል፡፡ስለዚህ ወደ ሶስተኛ ዓመት መግባት የማይችሉ እና መድገም እንደሚገባቸው የኮሌጁ ውሳኔ መሆኑ ተገልጾላቸዋል፡፡ በኮሌጁ እና በትምህርት ክፍሉ ላይ የሚሰነዝሩት አስተያያት ሐሰት ነው፡፡ አንዳች አውነታ የለውም፡፡ የተማሪ አካዳሚክ ውጤት የሚሻሻለው ተግቶ በመስራት ብቻ ነው፡፡
አዲሱ ክሳቸው
ኮሌጁ ለሴት ተማሪዎችም ሆነ ለሰራተኞች ምቹ አይደለም በማለት አዲስ ውንጀላቸውን ዶር ሣራ ለዩቲዩብ ቻናሉ ገልጠዋል፡፡ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ኮሌጁ ለራሱ ከሚመሰከክር ሌሎች ቢመሰክሩለት ይሻል ነበር፡፡ ለማንኛውም መልሳችንን ከማስረጃ ጋር እናቀርባለን፡፡ ማስረጃ አንድ፡- ኮሌጁ ለአዲስ ለሴት የሕክምና ተማሪዎች Affirmative action ያደርጋል፡፡ ማስረጃ ሁለት፡-በፐብሊክ ሔልዝ ለሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች በየዓመቱ የነጻ ትምህርት ዕድል ይሰጣል፡፡ ማስረጃ 3፡-ከኖርዌይ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የኮሌጁ ሴቶች የሊደርሺፕ ስልጠናዎች እንዲያገኙ ያደርጋል፡ ማስረጃ 4፡- የትምሀርት ቤቶች ዲኖች፣ ምክትል ፕሮቮስት ፣ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች የአንስቲዚዬሎጂ እና ክሪቲካል ኬር ትምህርት ክፍልን ጨምሮ ሴቶች ናቸው፡፡ወደፊትም ኮሌጁ ምቹ የትምህርት እና የስራ ቦታ እንዲሆን እየተሰራ ነው፡፡ ነገር ግን Academic Deficiency ያጋጠመው ተማሪ እንዲህ ዓይነት ፍጹም ከእውነት የራቀ ነገር ቢናገር አይገርመንም፡፡እውነቱ ግን ይህ ነው፡፡
ሌሎች አማራጮች
ዶር ሣራ በኮሌጃችን ትምህርታቸውን መቀጠል ካልፈለጉ ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች እንዲዛወሩ በጤና ሚኒስቴር በኩል ተጠይቀው ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ወይም ዲፓርትመንት ቀይረው እንዲማሩ በኮሌጃችን ተጠይቀው ነበር ፡፡ አልፈለጉም፡፡ እሳቸው ትምህርታቸውን መድገም ካልፈለጉ ስራቸውን መቀጠል ይችሉ ነበር፡፡ አላደረጉትም፡፡ ከስራቸው ገበታ ባለመገኘታቸው የኮሌጁ አስተዳደር ተደጋጋሚ ማስታወቂያ አውጥቶባቸዋል፡፡ የቀሩበትን ምክንያት ባለማቅረባቸው በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን እንደለቀቁ ተቆጥርዋል፡፡
ከተማሪ ጋር የነበረ አለመግባባት
በሕንድ ቆይታቸው ወቅት ከእርሳቸው ጋር ያልተግባቡት ተማሪ ባቀረቡበት ክስ እና የሕንድ ትምህርቱን አቋርጦ በመምጣቱ ስድስት ወር ተቀጥቷል፡፡ ተማሪው ቅጣቱን ፈጽሞ ዘግይቶ ለምርቃት በቅቷል፡፡ ቅጣቱ አነሰው የሚሉ ከሆነ ከተማሪው ጋር የነበራቸውን ቅሬታ በፍርድ ቤት ሆነ በሌሎች ተቋማት መክሰስ ይችላሉ፡፡ ሌሎች ተመሳሳይ አቤቱታዎችም ካላቸው በየደረጃው ላሉ የሕግ ተቋማት ማስረዳትና ክስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

ማጠቃለያ
ዶር ሣራ ትምህርታቸውን በአግባቡ መከታተል ባለመቻላቸው Academic Deficiency አጋጥሟቸዋል፡፡ የአካዳሚክ ውጤት ደግሞ በስራ ብቻ ነው የሚቀየረው ፡፡ በዩ ቲዩብ አቤቱታን በማሰማት የአካዳሚክ ውጤት አይሻሻልም- በትጋት እንጂ፡፡

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዶር ሐይማኖት በጡት ካንሰር ዙሪያ የሰጡት ትምህርት እነሆ!
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ቦርድ በቀዶ ሕክምና የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለዶ/ር ማኅተመ በቀለ ሙለታ አፀደቀ ፡፡
ቦርዱ ጥቅምት 19/2013 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ የዶ/ር ማኅተመ በቀለን መረጃዎች ከገመገመ በኋላ በቀዶ ሕክምና የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አፅድቋል፡፡
ፕሮፌሰር ማኅተመ በቀለ ሙለታ የሕክምና ዲግሪያቸውን (MD) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ በ1997 ዓም ፣ የስፔሻሊቲ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቀዶ ህክምና በ2003 ዓም እንዲሁም የሰብ-ስፔሻሊቲ ዲግሪያቸውን በኩላሊት ንቅለ ተከላ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ በ2010ዓም አግኝተዋል። ፕሮፌሰር ማኅተመ ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ የሙያ ማበልጸጊያ አጫጭር ስልጠናዎችን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ተከታትለዋል፡፡
ፕሮፌሰር ማኅተመ በግላቸውና ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር ከ50 በላይ በምርምር የተደገፉ ጥናታዊ ፅሁፎችን በታወቁ ሀገራዊና አለምዓቀፋዊ መፅሄቶች ላይ ለህትመት አብቅተዋል፡፡
ፕሮፌሰር ማኅተመ በትምህርት ክፍላቸውና በኮሌጁ የተለያዩ ከፍተኛ ኃላፊነቶችን በመውሰድ ሃገራቸውና ሕዝባችውን አገልግለዋል፡፡ እያገለገሉም ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የድንገተኛ ሕክምና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፤ የአስተኝቶ ሕክምና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፤ የቀዶ ሕክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊ በመሆን በከፍተኛ ደረጃ ሃገራቸውንና ሕዝባቸውን አገልግዋል፡፡ ፕሮፌሰር ማኅተመ ከዚህም በተጨማሪ በርካታ የማህበረሰብ አገልግሎቶችና የሙያ ነክ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
ዛሬ በቀዶ ህክምና የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው ፕሮፌሰር ማኅተመ በአሁኑ ወቅት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ በቀዶ ህክምና ትምህርት ክፍል በሕክምና ፣በማስተማር እና የኮሌጁ የምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
The Managing Board of St. Paul's Hospital Millennium Medical College approved the promotion of Dr. Mahteme Bekele Muleta to the rank of Full professor of Surgery.
The managing board of St. Paul's Hospital Millennium Medical College on its regular meeting conducted on October 29th , 2022 has evaluated all credentials of Dr. Mahteme Bekele Muleta and approved the promotion to the rank of full professor
Professor Mahteme Bekele Muleta, has received his MD degree from Addis Ababa University in 2005 , specialty certificate in General Surgery from Addis Ababa University in 2011 and his Subspecialty certificate in transplant surgery from St. Paul's Hospital Millennium Medical college in 2018.
Prof Mahteme has also done several short term trainings and courses in country and abroad.
Professor Mahteme has published more than 50 articles in different reputable national and international journals. He gained over 2.5 times of what is expected for promotion.
Professor Mahteme has served Ethiopia at various level in his department, the college and the public. To mention few Prof Mahteme was Director of Emergency directorate, Director of In-patient director, Head of the department of surgery. Professor Mahteme has been Member of Ethiopian surgical Society executive body, did several undergraduate and post graduate external examination, prepared training materials. Professor Mahteme has served his community in all corners of Ethiopia as a clinician, academician and responsible citizen of Ethiopia.
Professor Mahteme is currently serving the college as consultant surgeon, director of research directorate and chairman of SPHMMC IRB.

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ቦርድ በጽንስና ማህፀንና ሕክምና የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለዶ/ር ድልአየሁ በቀለ ማሞ አፀደቀ።
ቦርዱ ጥቅምት 19/2015 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ የዶ/ር ድልአየሁ በቀለን መረጃዎች ከገመገመ በኋላ በጽንስና ማሕጸን ሕክምና የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አፅድቋል፡፡
ፕሮፌሰር ድልአየሁ በቀለ ማሞ የሕክምና ዲግሪያቸውን (MD) ከጎንደር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ1992 ዓ.ም ፣ የስፔሻሊቲ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በፅንስና ማህፀንና ሕክምና በ2000 ዓ.ም፣ በማህበረሰብ ጤና አጠባበቅ የማስተርስ ድግሪያቸውን ከጎንደር ዩኒቨርሰቲ በ2005 ዓ.ም፣ እንዲሁም የሰብ-ስፔሻሊቲ ዲግሪያቸውን በ Maternal Fetal Medicine ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም አግኝተዋል። ፕሮፌሰር ድልአየሁ ከእዚህ በተጨማሪ የተለያዩ የሙያ ማበልጸጊያ አጫጭር ስልጠናዎችን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ተከታትለዋል፡፡
ፕሮፌሰር ድልአየሁ በግላቸውና ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር ከ50 በላይ በምርምር የተደገፉ ጥናታዊ ፅሁፎችን በታወቁ ሀገራዊና አለምዓቀፋዊ መፅሄቶች ላይ ለህትመት አብቅተዋል፡፡
ፕሮፌሰር ድልአየሁ በትምህርት ክፍላቸውና በኮሌጁ የተለያዩ ከፍተኛ ኃላፊነቶችን በመውሰድ ሃገራቸውና ሕዝባችውን አገልግለዋል፡፡ እያገለገሉም ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የኢትዮጵያ የፅንስና የማህፀን ሐኪሞች ማህበር ፕርዝደንት እንዲሁም በኮሌጁ የድህረ ምረቃ ትምህርት ዳይሬክተር እና የፅንስና ማህፀንና ሕክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊ በመሆን በከፍተኛ ደረጃ ሃገራቸውንና ሕዝባቸውን አገልግዋል፡፡ ፕሮፌሰር ድልአየሁ ከዚህም በተጨማሪ በርካታ የማህበረሰብ አገልግሎቶችና የሙያ ነክ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
ዛሬ በፅንስና ማህፀንና ሕክምና የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው ፕሮፌሰር ድልአየሁ በአሁኑ ወቅት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ በፅንስና ማህፀንና ሕክምና ትምህረት ክፍል በሕክም ፣በማስተማር እና የትምህርት ክፍሉ ሀላፊ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
The Managing Board of St. Paul's Hospital Millennium Medical College approved the promotion of Dr. Delayehu Bekele Mamo to the rank of Full professor of Obstetrics and Gynecology.
The managing board of St. Paul's Hospital Millennium Medical College in its regular meeting conducted on 29 October 2022, has evaluated all credentials of Dr. Delayehu Bekele Mamo and approved the promotion to the rank of full professor
Professor Delayehu Bekele Mamo received his MD degree from Gondar College of Medical sciences in 2000, his specialty certificate in Obstetrics and Gynecology from Addis Ababa University in 2008, his Masters of Public Health from Gondar University in 2013, and his Subspecialty certificate in Maternal Fetal Medicine from St. Paul's Hospital Millennium Medical College in 2018.
Prof Delayehu has also done several short-term trainings and courses in the country and abroad.
Professor Delayehu has published more than 50 articles in different reputable national and international journals.
Professor Delayehu has served Ethiopia at various levels, as well as within the college and the Obstetrics and Gynecology department, and the public. To mention few Prof Delayehu was the president of the Ethiopian Society of Obstetricians and Gynecologists and he is the current Editor-in-Chief of the Ethiopian Journal of Reproductive Health. He served as a member of several technical working groups at the Ministry of Health, prepared training materials, and participated in the development of several national guidelines. He also worked as the director of postgraduate programs at the college and took part in several undergraduate and postgraduate external examinations. Professor Delayehu has served his community in all corners of Ethiopia as a clinician, academician, and responsible citizen of Ethiopia.
Professor Delayehu is currently serving the college as a consultant Obstetrician and Gynecologist and Head of the Department of Obstetrics and Gynecology.

የኮሌጃችን ባልደረቦች በተለያየ ጊዜ በተሌቭዥን ቀርበው በልዩ ልዩ የጤና ርዕሰ ጉዳይ በማስተማራቸው ፤ የምስጋና ደብዳቤ ከአዲስ ሚዲያ ተልኮላቸዋል፡፡ እናመሰግናለን፡፡
St. Paul's Hospital Millennium Medical College-Center for Professional and Institutional Development invites you to join a virtual seminar on Mass Casualty Management: Preparedness and Response.
Presenter: Dr. Desalegn Keney, Assistant Professor of EMCC
Moderator: Dr. Zelalem Getahun, Assistant Professor of EMCC
Duration: 60 minutes
Date: Friday, November 4th, 2022
Starting time: 3:00 PM (9:00 PM Local Time)
Register here:
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScBdCXwGg5gXWugfn2p0QASlE-KgwYocSqiE9A316dnZV24JQ/viewform?usp=sf_link

ለ NIMEI አመልካቾች በሙሉ
የፈተናው ቀን ነገ እሑድ
November 6th, 2022/ Tikemt 27 201 @Medhaniyalem Secondary School
መፈተኛ ቦታ:-
መድኃኒያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው። ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ይጀምራል ፡፡
የመፈተኛው ት/ቤት የሚገኘው
ከጳውሎስ ወደ ዊንጌት በሚወስደው መንገድ አደባባዩን ሳይደርሱ ነው።

All candidates who are not selected for the interview may appeal at the HSEDC office in Saint Paul hospital millennium medical college only on November 9 and November 10, 2022 after paying 200 birr as was indicated on the notice given for the entrance exam. If the bank slip is not provided their appeal will not be considered
All candidates who applied for emerging regions and did not provide the support letter from their region will be flunked from the interview.
HERE IS THE LINK TO SEE THE RESULT OF APPLICANTS:
https://sphmmc.edu.et/2022/11/09/2015-e-c-nimei-exam-result/

የኢትዮጵያ የወጣቶች ፌደሬሽን ባዘጋጀው ብሔራዊ የወጣት አምባሳደሮች የእወቅና ፕሮግራም ላይ በጤናው ዘርፍ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ዝግጅቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሶስት የኮሌጃችን የሕክምና ተማሪዎች የበጎ ፈቃድ የጤና አምባሳደር ሆነው ተመርጠዋል፡፡
የበጎ ፈቃድ የጤና አምባሳደር የሆኑት ዶ/ር የሱፍ አራጌ፣ ሮቤል በቀለ እና በቴልሄም ታደለ ናቸው፡፡ እንኳን ደስ ያላችሁ!
!

We are pleased to announce that Sumeya Nahwi elected as the President of EMSA ( Ethiopian Medical Students Association) St. Paul's branch for the term 2022/2023.
We believe that Sumeya is a dedicated and passionate PC II student who will work for the betterment of the association and works toward improving the integrity of students within the college’s community. We believe that the St. Paul's Community will benefit from the new energy she brings to EMSA.
The SPHMMC community would like to congratulate Sumeya on her appointment as the president and wish her and her team a successful term.