St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.69K photos
39 videos
23 files
584 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
ቃለመጠይቅ ፈተና  ማስታወቂያ

 

            ለአንስቴዝዮሎጂ ፕሮፌሽናል  ፈተና የወሰዳችሁ በሙሉ  

       የካቲት 18 ቀን 2015ዓ.ም የአንስቴዝዮሎጂ ፕሮፌሽናል ወስዳችሁ 50 ፐርሰንት በላይ ያመጣቹ የቃለመጠይቅ ፈተና የሚሰጠው አርብ የካቲት 24, 2015ዓ.ም በ3፡00ሰዓት በኮሌጁ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
የፈተና ጥሪ
ለ Oral and maxillofacial surgery Speciality በ ድህረ ምረቃ ፕሮግራም ለመማር የተመዘገባቹ አመልካቾች በሙሉ የጽሁፍ ፈተና የሚሰጠው ማክሰኞ የካቲት 21, 2015 ስለሆነ በትምህርት ክፍሉ ከ ጠዋቱ 3:00 ሰዓት እንድትገኙ እናሳስባለን::
የጥርስ ህክምና ት/ት ክፍል
የፈተና ማ ስ ታ ወ ቂ ያ
ለነርስ ፕሮፌሽናል አመልካቾች
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥር 9ቀን 2015ዓ.ም ቋሚ ቅጥር ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ያመለከታችሁ ከ2013ዓ.ም ጀምሮ የተመረቃችሁ የጽሑፍ ፈተና የሚሰጠው ቅዳሜ የካቲት 25 ቀን 2015ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በመድኃኒያለም መሰናዶ ትምህርት ቤት በመሆኑ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ ለጽሑፍ ፈተና እንድትገኙ እናሳስበላን፡፡
ፈተና ተጀምሮ 30 ደቂቃ በላይ ዘግይቶ የሚመጣ ተፈታኝ የማንፈትን መሆኑን አስቀድመን እናሳስባለን፡፡
https://sphmmc.edu.et/.../written-exam-announcement-for.../
የፈተና ማ ስ ታ ወ ቂ ያ
ለነርስ ፕሮፌሽናል አመልካቾች
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥር 9ቀን 2015ዓ.ም ቋሚ ቅጥር ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ያመለከታችሁ ከ2013ዓ.ም ጀምሮ የተመረቃችሁ የጽሑፍ ፈተና የሚሰጠው ቅዳሜ የካቲት 25 ቀን 2015ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በመድኃኒያለም መሰናዶ ትምህርት ቤት በመሆኑ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ ለጽሑፍ ፈተና እንድትገኙ እናሳስበላን፡፡
ፈተና ተጀምሮ 30 ደቂቃ በላይ ዘግይቶ የሚመጣ ተፈታኝ የማንፈትን መሆኑን አስቀድመን እናሳስባለን፡፡
https://sphmmc.edu.et/.../written-exam-announcement-for.../
የሕክምና ትምህርት ለመማር ባለፈው ሳምንት የጽሑፍ ፈተና ተፈትናችሁ ፡ በውጤታችሁ መሰረት ለቃለመጠይቅ ያለፋችሁ ተማሪዎች ስማችሁን ማስፈንጠሪያውን በመጫን ማየት ትችላላችሁ፡፡ መልካም ዕድል!
https://sphmmc.edu.et/.../announcement-for-new-medical.../
ማ ስ ታ ወ ቂ ያ
የሕክምና ትምህርት ለመማር ባለፈው ሳምንት የጽሑፍ ፈተና ተፈትናችሁ ፡ በውጤታችሁ መሰረት ለቃለመጠይቅ ያለፋችሁ ተማሪዎች ስማችሁን ማስፈንጠሪያውን በመጫን ማየት ትችላላችሁ፡፡ መልካም ዕድል!
https://sphmmc.edu.et/.../announcement-for-new-medical.../
ልጅዎ የመስማት ችግር እንዳለበት ለማወቅ እነዚህን ምልክቶች ልብ ይበሉ።
# ከ1 ዓመት እድሜ በታችየሆኑ ለማንኛውም ድምጽ ምላሽ አለመስጠት
# ከ 1-2 ዓመት ቀላል ትዕዛዝ አለመቀበል
# ከ 7 ወር እስከ 1 ዓመት ስማቸው ሲጠራ አለመዞር
# ከ 3 ዓመት በታች ግልጽ የሆነ የንግግር እና የቋንቋ መዘግየት
#WorldHearingDay2023 #HearingCare #safelistening
የመስማት ችግር እንዳይገጥምዎ ማድረግ የሌለብዎ ነገሮች
1.በእንጨት ወይም ሹል ነገር በጆሮዎ ውስጥ መክተት አይገባም
2. የመዳመጫ ቁሳቁሶቹን አይዋዋሱ
3. ለከፍተኛ ድምጽ አይጋለጡ
4. በቆሻሻ ውሃ ውስጥ አይዋኙ ወይም አይታጠቡ
#WorldHearingDay2023 #HearingCare #safelistening
A memorandum of understanding (MoU) has been signed between St. Paul's Millennium Medical College ( SPHMMC) and Jimma University Medical Center (JUMC)

The MoU aims to facilitate collaboration in clinical services, education, research and community services.

The MoU will bring the years long collaboration of the two institutions to a new chapter.

The MoU was signed by SPHMMC Provost Dr. Sissy Sirgu, JUMC CEO, Dr Ahmed Zeynudin, in a ceremony held at SPHMMC's Provost meeting hall.
የኩላሊት ህመምን ለመከላከል የሚያግዙ
8 ወርቃማ ህጎች
1 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ፣ንቁ ይሁኑ
2 ጤናማ አመጋገብ ይከተሉ
3 የደምዎን ስኳር መጠን ይለኩ እና ይቆጣጠሩ
4 የደም ግፊትዎን ይለኩ እና ይቆጣጠሩ
5 ተገቢውን ፈሳሽ ይውሰዱ
6 ሲጋራ አያጭሱ
7 የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን አዘውትሮ ከመውሰድ መቆጠብ
8 የኩላሊትዎን ጤነኝነት ማስመርመር፣በተለይም
የስኳር ህመም ካለብዎት
ከፍተኛ የደም ግፊት ካለብዎት
ከመጠን በላይ ውፍረት ካለብዎትበቅርብዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ ይመርመሩ፡፡
#kidneyhealthforall #WorldKidneyDay2023 #KidneyDisease #NephroticSyndrome
የኩላሊት ህመም ምልክቶች
• የእግር እና የቁርጭምጭሚት ማበጥ፣
• የድካም ስሜት
• ትኩረትን የመሰብሰብ ችግር፣
• የምግብ ፍላግት መቀነስ እና
• አረፋ የሚመስል (የቀላቀለ) ሽንት የተወሰኑት ናቸው፡፡
#KidneysMatter #WorldKidneyDay2023
👉🦴የአጥንት ቅኝት (Bone scan) ምንነትና አስፈላጊነት፡

 ይህ የአጥንት ምርመራ የአጥንትዎን ጤና ለመገምገም የሚረዳ ምርመራ ነው።
 የምርመራው አሰራር ሂደቱን ስንመለክት፡ አነስተኛ መጠን ያለው ጨረር አመንጪ ንጥረ ነገር በመርፌ ወደ ደም ስርዎ ውስጥ በማስገባት ከውጭ በሚገኝ ጨረር ለቃሚ መሳሪያ (SPECT or SPECT/CT) አማካኝነት ስርጭቱን በምስል በመከታተል የሚደረግ ምርመራ ሲሆን። ወደ ሰውነት የገባው ንጥረ ነገር ወደ አጥንቶችዎ በመጓዝ ችግር ያለባቸው ቦታዎችን ያጎላል። ቅኝቱ ወደ 30 ደቂቃ ያክል ይወስዳል እና ምንም አይነት ህመም የለውም።
 መላውን የሰውነት አጥንት በመቃኘት የሚከተሉትን ጨምሮ የተለያዩ የአጥንት በሽታዎችን ለመመርመር ይረዳል፡-
o ስብራት (fracture)
o የመገጣጠሚያ ህመም (Arthritis)
o የፓጄትስ የአጥንት በሽታ (Paget’s disease of bone)
o ከአጥንት ለሚነሳ ካንሰር (Primary bone tumor)
o ከተለየ ቦታ ወደ አጥንት ለተሰራጨ ካንሰር (Metastatic tumor to the bone) እና
o የአጥንት፣ የመገጣጠሚያዎች ወይም ሰው ሰራሽ የመገጣጠሚያዎች ቅየራ ኢንፌክሽንኖችን (bone, joint and prosthetic joint infections)

👉ከምርመራው በፊት ቅድመ ዝግጅቱ ምን ይመስላል?

 ከምርመራው በፊት, ለተወሰነ ጊዜ መጾም ያስፈልግዎታል.
 ታካሚዎች ማንኛውንም አለርጂዎች, የቅርብ ጊዜ ቀዶ ጥገናዎች እና የሚወስዱትን ወቅታዊ መድሃኒቶች ለሐኪማቸው ማሳወቅ አለባቸው
 እርጉዝ ወይም የሚያጠቡ እናቶች ከሆኑ ማሳወቅ አለባቸው

👉ከምርመራ በኋላ ፡

 መብላት እና መድሃኒቶችን መውሰድን ጨምሮ መደበኛ እንቅስቃሴዎችዎን መቀጠል ይችላሉ። ራዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገሩን ከሰውነት ስርአትዎ ለማስወጣት እንዲረዳዎ ብዙ ፈሳሽ እንዲጠጡ ሊጠየቁ ይችላሉ።

👉የአጥንት ቅኝት ምርመራን በማድረግ ወደ አጥንት የተሰራጨ የካንሰር በሽታን ቀደም ብሎ ማወቁ ፈጣን ሕክምና እንዲጀመር በማድረግ በታካሚው ላይ አወንታዊ ውጤትን ማየት ያስችላል። ከዚህም በተጨማሪ ለተለያዩ የካንሰር ዓይነቶች የሚሰጡ ሕክምናዎች የሚያሳዪትን ምላሾችን ለመገምገም ይረዳል። ወደ አጥንቶች ሊሰራጩ ከሚችሉት በጣም የተለመዱ የካንሰር ዓይነቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
 የፕሮስቴት ካንሰር
 የጡት ካንሰር
 የሳምባ ካንሰር
 የታይሮይድ ካንሰር
 የኩላሊት ካንሰር
 የኮሎሬክታል ካንሰር እና
 የጣፊያ ካንሰር

በዶ/ር ሔኖክ ተስፋዬ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
የኒውክለር ህክምና ስፔሻሊስትና
ረዳት ፕሮፌሰር
The EPS has acknowledged our colleague, Sr. Zewdinesh Woldie, for her outstanding contributions to the field of Pediatrics and child health nursing services in Ethiopia. The college community thus would like to congratulate you; your being acknowledged is our pride, too!
ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

ለክሊኒካል ነርስ ( ፍሎቦቶሚስት ) አመልካቾች በሙሉ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥር 9ቀን 2015ዓ.ም ቋሚ ቅጥር ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ያመለከታችሁ በሙሉ ማክሰኞ መጋቢት 12 ቀን 2015ዓ.ም በ3፡00 ሰዓት ተገኝታችሁ ለጽሑፍ ፈተና ለመቅረብ ዕጣ እንድታወጡ እየገለጽን በዕለቱ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ይዛችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

ከሠላምታ ጋር