ልጅዎ የመስማት ችግር እንዳለበት ለማወቅ እነዚህን ምልክቶች ልብ ይበሉ።
# ከ1 ዓመት እድሜ በታችየሆኑ ለማንኛውም ድምጽ ምላሽ አለመስጠት
# ከ 1-2 ዓመት ቀላል ትዕዛዝ አለመቀበል
# ከ 7 ወር እስከ 1 ዓመት ስማቸው ሲጠራ አለመዞር
# ከ 3 ዓመት በታች ግልጽ የሆነ የንግግር እና የቋንቋ መዘግየት
#WorldHearingDay2023 #HearingCare #safelistening

የመስማት ችግር እንዳይገጥምዎ ማድረግ የሌለብዎ ነገሮች
1.በእንጨት ወይም ሹል ነገር በጆሮዎ ውስጥ መክተት አይገባም
2. የመዳመጫ ቁሳቁሶቹን አይዋዋሱ
3. ለከፍተኛ ድምጽ አይጋለጡ
4. በቆሻሻ ውሃ ውስጥ አይዋኙ ወይም አይታጠቡ
#WorldHearingDay2023 #HearingCare #safelistening
1.በእንጨት ወይም ሹል ነገር በጆሮዎ ውስጥ መክተት አይገባም
2. የመዳመጫ ቁሳቁሶቹን አይዋዋሱ
3. ለከፍተኛ ድምጽ አይጋለጡ
4. በቆሻሻ ውሃ ውስጥ አይዋኙ ወይም አይታጠቡ
#WorldHearingDay2023 #HearingCare #safelistening
A memorandum of understanding (MoU) has been signed between St. Paul's Millennium Medical College ( SPHMMC) and Jimma University Medical Center (JUMC)
The MoU aims to facilitate collaboration in clinical services, education, research and community services.
The MoU will bring the years long collaboration of the two institutions to a new chapter.
The MoU was signed by SPHMMC Provost Dr. Sissy Sirgu, JUMC CEO, Dr Ahmed Zeynudin, in a ceremony held at SPHMMC's Provost meeting hall.

የኩላሊት ህመምን ለመከላከል የሚያግዙ
8 ወርቃማ ህጎች
1 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ፣ንቁ ይሁኑ
2 ጤናማ አመጋገብ ይከተሉ
3 የደምዎን ስኳር መጠን ይለኩ እና ይቆጣጠሩ
4 የደም ግፊትዎን ይለኩ እና ይቆጣጠሩ
5 ተገቢውን ፈሳሽ ይውሰዱ
6 ሲጋራ አያጭሱ
7 የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን አዘውትሮ ከመውሰድ መቆጠብ
8 የኩላሊትዎን ጤነኝነት ማስመርመር፣በተለይም
የስኳር ህመም ካለብዎት
ከፍተኛ የደም ግፊት ካለብዎት
ከመጠን በላይ ውፍረት ካለብዎትበቅርብዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ ይመርመሩ፡፡
#kidneyhealthforall #WorldKidneyDay2023 #KidneyDisease #NephroticSyndrome

የኩላሊት ህመም ምልክቶች
• የእግር እና የቁርጭምጭሚት ማበጥ፣
• የድካም ስሜት
• ትኩረትን የመሰብሰብ ችግር፣
• የምግብ ፍላግት መቀነስ እና
• አረፋ የሚመስል (የቀላቀለ) ሽንት የተወሰኑት ናቸው፡፡
#KidneysMatter #WorldKidneyDay2023
• የእግር እና የቁርጭምጭሚት ማበጥ፣
• የድካም ስሜት
• ትኩረትን የመሰብሰብ ችግር፣
• የምግብ ፍላግት መቀነስ እና
• አረፋ የሚመስል (የቀላቀለ) ሽንት የተወሰኑት ናቸው፡፡
#KidneysMatter #WorldKidneyDay2023
👉🦴የአጥንት ቅኝት (Bone scan) ምንነትና አስፈላጊነት፡
ይህ የአጥንት ምርመራ የአጥንትዎን ጤና ለመገምገም የሚረዳ ምርመራ ነው።
የምርመራው አሰራር ሂደቱን ስንመለክት፡ አነስተኛ መጠን ያለው ጨረር አመንጪ ንጥረ ነገር በመርፌ ወደ ደም ስርዎ ውስጥ በማስገባት ከውጭ በሚገኝ ጨረር ለቃሚ መሳሪያ (SPECT or SPECT/CT) አማካኝነት ስርጭቱን በምስል በመከታተል የሚደረግ ምርመራ ሲሆን። ወደ ሰውነት የገባው ንጥረ ነገር ወደ አጥንቶችዎ በመጓዝ ችግር ያለባቸው ቦታዎችን ያጎላል። ቅኝቱ ወደ 30 ደቂቃ ያክል ይወስዳል እና ምንም አይነት ህመም የለውም።
መላውን የሰውነት አጥንት በመቃኘት የሚከተሉትን ጨምሮ የተለያዩ የአጥንት በሽታዎችን ለመመርመር ይረዳል፡-
o ስብራት (fracture)
o የመገጣጠሚያ ህመም (Arthritis)
o የፓጄትስ የአጥንት በሽታ (Paget’s disease of bone)
o ከአጥንት ለሚነሳ ካንሰር (Primary bone tumor)
o ከተለየ ቦታ ወደ አጥንት ለተሰራጨ ካንሰር (Metastatic tumor to the bone) እና
o የአጥንት፣ የመገጣጠሚያዎች ወይም ሰው ሰራሽ የመገጣጠሚያዎች ቅየራ ኢንፌክሽንኖችን (bone, joint and prosthetic joint infections)
👉ከምርመራው በፊት ቅድመ ዝግጅቱ ምን ይመስላል?
ከምርመራው በፊት, ለተወሰነ ጊዜ መጾም ያስፈልግዎታል.
ታካሚዎች ማንኛውንም አለርጂዎች, የቅርብ ጊዜ ቀዶ ጥገናዎች እና የሚወስዱትን ወቅታዊ መድሃኒቶች ለሐኪማቸው ማሳወቅ አለባቸው
እርጉዝ ወይም የሚያጠቡ እናቶች ከሆኑ ማሳወቅ አለባቸው
👉ከምርመራ በኋላ ፡
መብላት እና መድሃኒቶችን መውሰድን ጨምሮ መደበኛ እንቅስቃሴዎችዎን መቀጠል ይችላሉ። ራዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገሩን ከሰውነት ስርአትዎ ለማስወጣት እንዲረዳዎ ብዙ ፈሳሽ እንዲጠጡ ሊጠየቁ ይችላሉ።
👉የአጥንት ቅኝት ምርመራን በማድረግ ወደ አጥንት የተሰራጨ የካንሰር በሽታን ቀደም ብሎ ማወቁ ፈጣን ሕክምና እንዲጀመር በማድረግ በታካሚው ላይ አወንታዊ ውጤትን ማየት ያስችላል። ከዚህም በተጨማሪ ለተለያዩ የካንሰር ዓይነቶች የሚሰጡ ሕክምናዎች የሚያሳዪትን ምላሾችን ለመገምገም ይረዳል። ወደ አጥንቶች ሊሰራጩ ከሚችሉት በጣም የተለመዱ የካንሰር ዓይነቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
የፕሮስቴት ካንሰር
የጡት ካንሰር
የሳምባ ካንሰር
የታይሮይድ ካንሰር
የኩላሊት ካንሰር
የኮሎሬክታል ካንሰር እና
የጣፊያ ካንሰር
በዶ/ር ሔኖክ ተስፋዬ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
የኒውክለር ህክምና ስፔሻሊስትና
ረዳት ፕሮፌሰር

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ
ለክሊኒካል ነርስ ( ፍሎቦቶሚስት ) አመልካቾች በሙሉ
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥር 9ቀን 2015ዓ.ም ቋሚ ቅጥር ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ያመለከታችሁ በሙሉ ማክሰኞ መጋቢት 12 ቀን 2015ዓ.ም በ3፡00 ሰዓት ተገኝታችሁ ለጽሑፍ ፈተና ለመቅረብ ዕጣ እንድታወጡ እየገለጽን በዕለቱ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ይዛችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
ከሠላምታ ጋር

የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር በ59ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤው ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለሰጡ ሁለት ሐኪሞች የህይወት ዘመን ሽልማትን አበረከተ።
ዶክተር ይርጉ ገብረህይወት በወንድ ጾታ እንዲሁም ዶክተር ተቋም ደበበ ደግሞ በሴት የህይወት ዘመን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ተሸላሚዎቹ በ ሙያቸው የተሻለ የሕክምና አገልግሎት እንደሰጡ በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
ማህበሩ ከህይወት ዘመን ሽልማት በተጨማሪ ዶክተር ትህትና ንጉሴን በሴት ወጣት ተጽዕኖ ፈጣሪ ሐኪም በሚል ሲሸልም ዶክተር ፈቀደ አግዋርን ደግሞ በወንድ ወጣት ተጽዕኖ ፈጣሪ ሐኪም በማለት ሸልሟል።
አዲስ ህይወት የማገገሚያ ማዕከል ደግሞ የዓመቱ ምርጥ የጤና ተቋም በሚል ዕውቅና ተሰጥቶታል።
ሽልማቱን የጤና ሚንስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ተግባር ይግዛው ሰጥተዋል ። ።

የቲቢ በሽታ ምንድን ነው?
የቲቢ በሽታ በአገራችን በተለምዶ የሳንባ ነቀርሳ የሚባለው በሽታ ነው፡፡ ቲቢ የተባለውን የአሁኑን ሲያሜ ያገኘው ቲዩበርክሎሲስ ተብሎ ከሚጠራው የበሽታው የእንግሊዘኛው ቋንቋ አህጽሮተ-ቃል ነው፡፡ መንስኤውም አልፎ አልፎ እንደሚነገረው ብርድ ወይም ንፋስ ሳይሆን ረቂቅ በሆነው “ማይኮባክቴሪያም ቲዩበርክሎስስ” የተባለ ባክቴሪያ ነው፡፡ ቲቢ “ማይኮባክቴሪያም ቦቪስ” በተባለ ባክቴሪያ የተጠቁ የቤት እንስሳት ወተት ሳይፈላ ቢጠጣ ከእንስሳት ወደ ሰው ሊተላለፍ እንደሚችልም ተረጋግጧል፡፡
ቲቢ የትኛውን የኅብረተሰብ ክፍል ያጠቃል?
ቲቢ ዕድሜን፣ ፆታን፣ ዘርንና ቀለምን ሳይለይ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል የሚያጠቃ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ምንም እንኳን በሽታው ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች ቢያጠቃም በበሽታው በበለጠ የሚጠቁት በአምራች ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙና የቤተሰብ ኃላፊ የሆኑ ዜጎች ናቸው፡፡
በተያያዘም ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት፣ አረጋዊያን፣ የሰውነት መከለከያ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ለምሳሌ ኤች አይ ቪ፣ የካንሠር እና የስኳር ሕሙማን፣ የምግብ እጥረት ያለባቸው፣ በአክታ ምርመራ ቲቢ እንዳለባቸው ከተረጋገጠ ሕሙማን ጋር አብረው የሚኖሩ እንዲሁም በተጨናነቁና በተፋፈጉ ቦታዎች የሚኖሩ/የሚሠሩ/የሚሰባበሱ ሰዎች እንዲሁም የአልኮንና የትምባሆ ሱሰኞችም ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡
የቲቢ በሽታ እንዴት ይተላለፋል?
ቲቢ የሚተላለፈው በአብዛኛው በትንፋሽ አማካኝነት ነው፡፡ ይኸውም አንድ በሳንባ ቲቢ የተያዘ ሕመምተኛ በሚስልበት፣ በሚያስነጥስበት፣ በሚተፋበት፣ ወይም በሚናገርበት ወዘተ... ወቅት የቲቢ በሽታ አምጪ ባክቴሪያን የያዙ የአክታ ብናኞች ወደ አየር ስለሚረጩና ብናኞችም በአቅራቢያው ያሉ ሰዎች አየር ወደ ውስጥ በሚተነፍሱበት ጊዜ በቀላሉ ወደ ሳንባው ውስጥ ገብተው ለማጥቃት ዕድል ስለሚያገኙ ነው፡፡
የቲቢ በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
የቲቢ በሽታ ሰማኒያ ከመቶ የሚሆነውን የሚያጠቃው ሳንባን በመሆኑ የሳንባ ቲቢ በሽታ ዋናው ምልክት ሁለት ሳምንትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ የዘለቀ ሳል ነው፡፡ ሳሉ አክታ ያለውና ደም የቀላቀለ ወይም ያልቀላቀለ ወይም ደረቅ ሊሆን ይችላል፡፡ ሕመምተኛው ከሳሉ በተጨማሪ በደረቱ አካባቢ የውጋት ስሜት፣ መጠነኛ የሆነ ትኩሳት፣ ሌሊት በመኝታ ጊዜ ማላብ፣ የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስና የሰውነት መድከም የመሳሰሉ አጠቃላይ የሆኑ ምልክቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ የበሽታም ምልክቶች እንደተጠቃው የሰውነት ክፍል ዓይነት ይለያያሉ፡፡
የቲቢ በሽታን ማዳን ይቻላል?
ቲቢ መድኃኒት ስለአለው በአግባቡ ከታከሙት የሚድን በሽታ ነው፡፡ የበሽታው ምርመራም
ሆነ ሕክምና በመንግሥታዊና ሕክምናውን እንዲሰጡ በተፈቀደላቸው የግል ጤና ተቀቋማት በነፃ ማግኘት ስለሚቻል ማንኛውም ሰው የበሽታው ምልክቶች ሲታዩበት አገልግሎቱን ወደሚሰጥ ጤና ድርጅት መሄድ ይኖርበታል፡፡ የቲቢ መድኃኒት በታዘዘው መጠንና ጊዜ ባይወሰድ ችግር ያስከትላል፡፡ ስለሆነም ሕመምተኛው የታዘዘለትን መድኃኒት ሳያቋርጥ በየቀኑ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡ ሕክምናው ከተቋረጠ ግን የበሽታ መንስኤ የሆነው ባክቴሪያ የፀረ-ቲቢን መድኃኒቶችን በመላመድ በመደበኛው የቲቢ ሕክምና ዘዴ መዳን የማይችል የቲቢ ዓይነት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
መድኃኒት የተላመደ ቲቢ ምንድን ነው?
መድኃኒትን የተላመደ ቲቢ በሽታ መድኃኒት ያልተላመደ ቲቢን ለማከም የሚያገለግሉ መድኃኒቶችን የተላመደ የቲቢ በሽታ ዓይነት ነው፡፡ በሽታው የሚከሰተው ታካሚዎች መድኃኒቶችን በታዘዘው መሠረት ካላመውሰድና የክትትል ጉደለት ቢሆንም በሽታው መድኃኒት እንዳልተላመደው ቲቢ ሁሉ በትንፋሽ አማካይነትም ይተላለፋል፡፡ መድኃኒት ያልተላመደውም ሆነ መድኃኒት የተላመደ ቲቢ ዓይነቶች መንስኤያቸው፣ መተላለፊያ መንገዶቻቸውና ምልክቶቻቸው ተመሳሳይ ቢሆኑም መድኃኒትን ለተላመደ ቲቢ ሕክምና የሚሰጡ መድኃኒቶች ዓይነትና ብዛት እንዱሁም ሕክምናው የሚፈጅበታ ጊዜ ይለያል፡፡ ይሁን እንጂ መድኃኒትን የተላመደው ቲቢም በአግባቡ ከታከሙት መዳን ይችላል፡፡
የቲቢ በሽታን መከላከል ይቻላል?
መድኃኒት ያልተላመደውንም ሆነ መድኃኒት የተላመደ ቲቢን መከላከል ይቻላል፡፡ ስለሆነም የቲቢ ሕሙማን፣ ቤተሰቦቻቸውና በአጠቃላይ ሕብረተሰቡ የግልና የጋራ ኃላፊነታቸውንና ድርሻቸውን በታማኝነት ቢወጡ የበሽታው የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ እንደሚፋጠን ይታመናል፡፡

A courageous Physician Women has been recognized as the heroine of the year at the 17th TRAC Annual TB Research conference held in Gondar. The woman goes by the name, Dr. Mahelet Tesfaye, has been doing marvelous professional deed for her country and cherished citizenry. Following the untold responsibility she has effectively discharged, Dr. Mahelet is well acknowledged and demonstratively bestowed.
She received an award for her great commitment in due course of saving the lives of two Pre-XDR TB and DR -TB patients with complications; this is quite extraordinary achievement.
Dr. Mahelet, a cardiothoracic surgeon, has provided two young patients—coming from Butajira and Jimma towns—who have been suffering from drug resistant TB for years, with bright hope.
The patient from Jimma had a destroyed bronchestic lung due to DR-TB disease, whereas the one from Butajera has had bacilli multiply inside cavity and contaminate the healthy tissues inside.
The only solution for saving the two patients was recommended lung surgery. However, there is no operation theatre in Ethiopia, and the country designed to conduct peration for such patients with infectious disease.
Dr. Mahelet conducted the most wanted surgery for her Jimma resident patient. She removed his lung affected tissues, and she removed the Butajira patients bacilli multiply inside cavity and contaminate the healthy tissue as his lung parts were the most affected ones. Ethiopia did rescue the lives of patients. Now, both are in a very good state of health and recovery.
Dr. Mahelet is consultant cardiothoracic surgeon and assistant professor at Black Lion Comprehensive Specialized Hospital.
She received an award from Health Minister, Dr.Lia Tadesse, for her extraordinary deed and selfless commitment to save the lives of fellow citizens.
Congratulations! Dr. Mahelet!