St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
የማይቀርበት!
እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሣችሁ!
የዓለም ዓቀፍ የእናቶችን ቀን በማድረግ በእንጦጦ መናፈሻ (ፓርክ) የእግር ጉዞ አዘጋጅተናል፡፡
የእናቶቻችንን ፍቅር ለመዘከር ኑ አብረን በእግር ጉዞው እንሳትፍ፡፡ የጤና ምርመራም እናድርግ! ሁላችሁም ተጋብዟችኃል! መግቢያ በነጻ!
ቀን፡ እሑድ ግንቦት 06/2015 ዓ.ም
ሰዓት፡ 1፡30-7፡300
#femtech #ethiopia #SPHMMC #womenshealth #walk #mothersday #ethiopia #startup #community #healthfair
መልካም የእናቶች ቀን! To all Mothers on this very special day, WE LOVE YOU! Happy Mother's Day from SPHMMC
We are sorry to annonce that the application for GI fellow training at SPHMMC has been postponed until further notice.
የቀጥታ ስርጭት
በወሊድ ጊዜ የሚከሰት የደም ግፊት ምንድነው በሚል ርእሰ ጉዳይ ፕሮፌሰር ድልአየሁ ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
ምን እንጠይቅልዎ? ጥያቄዎን ይላኩልን፡፡
በፌስቡክ ቀጥታ ስርጭት ቀን፡ ዓርብ ፡ ግንቦት 11/2015
ሰዓት፡ 8፡00
ይከታተሉን፡፡

Friday 2.30 PM
Q & A answering YOUR QUESTIONS about preeclampsia, Link below.
Consultant Obstetrician Gynecologist Professor DilAyehu Bekele will answer the questions you have already sent in and the NEW QUESTIONS you may have.
JOIN our live stream today at 8.30 PM GMT on our Facebook page!
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ሁለት ስመጥር አርቲስቶችን የኮሌጁ በጎፈቃድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ፡፡
በፊልም እና በትያትር ሥራዎቻቸው ታወቂ የሆኑት አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ እና ሐረገወይን አሰፋን ኮሌጁ በጎፈቃድ አምባሳደር አድርጎ ሾማዋቸዋል፡፡
ሁለቱም አርቲስቶች በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በጤና ግንዛቤ መስጫ መርሐግብሮች ላይ በመገኘት ማሕበረሰቡን በማስተማር እና በማስተባበር የተላያዩ ስራዎችን ይሰራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዚሁ ስነስርዓት ላይ አርቲስቶቹ እንደገለጹት የላቀ ስራ ለመስራት መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል፡፡
St. Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC)

Department of Obstetrics and Gynecology

Announcement for enrollment to maternal-fetal medicine, gynecologic oncology, reproductive endocrinology and infertility, family planning and Urogynecology and Reconstructive Pelvic surgery fellowship programs

The department of Obstetrics and Gynecology at SPHMMC kindly invites all qualifying candidates to apply for maternal-fetal medicine, gynecologic oncology, reproductive endocrinology and infertility, family planning and Urogynecology and Reconstructive Pelvic surgery fellowship programs for the year 2023/2024 G.C.

Background and General Information

The Department of Obstetrics and Gynecology at SPHMMC as mandated by the Academic Commission of the college has started the above-mentioned fellowship programs in different academic years. The primary goal of these fellowship programs is to produce physicians who are competent clinicians, trainers, researchers, advocates, and leaders in all issues related to respective sub-specialty disciplines and broader reproductive health

These are two years programs at the end of which candidates will become subspecialists in respective fellowship programs. The training will involve clinical attachments, deductive trainings (seminars, tutorials, online lectures, research training, and mentorship ), with possible attachments abroad (depending on the availability of resources and a competitive basis) attending various local and international relevant conferences, and taking a supervisory role in the training of residents, undergraduate medical students and related in-service trainings. Fellows are also expected to conduct high-standard research in their respective programs as part of a requirement for completion of the fellowship.

Schedule for enrollment

September 2023
Two fellowship positions are available for enrollment in each program

Admission Requirements

The candidate should be a graduate from a recognized Medical School with a Doctor of Medicine and a specialty in Obstetrics and Gynecology.
The candidate must complete a screening process for admission to be conducted by the SPHMMC Obstetrics and Gynecology department.
The candidate should produce two recommendation letters from their respective institutions.
The candidate should be registered and licensed to practice obstetrics and gynecology by the relevant authority in Ethiopia.
The candidate should have adequate mental and physical health.
Female applicants are strongly encouraged.
Queries regarding the fellowship can be addressed to Dr. Abdulfetah via email (chechera68@gmail.com) or Dr. Delayehu Bekele via email (delayehu@gmail.com)

All interested applicants can apply in person to the registrar’s office at St. Paul’s Hospital Millennium Medical College OR the office of the Department of Obstetrics and Gynecology OR by email at obgyn.sphmmc@gmail.com from May 22 until June 30, 2023. Applicants should write a letter of intent of no more than 750 words explaining why they are interested in the fellowship, how this will impact their career, and their long-term professional goals.

Applicants should submit an application letter, letter of intent, recent CV, and copy of credentials including copies of degree, student grade report, and two letters of recommendation in a sealed envelope. Application may be submitted by paper in person to the registrar directly or electronically as attached scanned documents if submitted by e-mail.
በእርግዝና ወቅት የሚከሰት ደም ግፊት ቀንን አስመልክቶ ከመንግስት እና ከግል መገኛኛ ብዙሓን ለተውጣጣጡ ጋዜጠኞች ቢቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ የተዘጋጀ የስልጠና መርሐግብር ተካሄደ፡፡
በሀገራችን ብዙ እናቶችን በሞት የሚነጥቀውን በእርግዝና ወቅት የሚከሰት ደም ግፊት በሽታ ዙሪያ ትምህርት በባለሙያዎች ተሰጥቷዋቸዋል፡፡ በስልጠናው ወቅት እንደተገለጸው ጋዜጠኖች ለሕብረተሰቡ በመገናኛ ብዙኃን አስፈላጊውን መረጃ በየጊዜው እንዲሰጡ ተጠይቀዋል፡፡
#WorldPreeclampsiaDay
ዛሬ የአለም በእርግዝና ወቅት የሚከሰት ደም ግፊት ቀን ነው፡፡በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት ወይም #preeclampsia ከዋና ዋና ከእርግዝና ጋር የተገናኙ የእናቶች እና የጨቅላ ህጻናት ሞት ምክንያቶች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ነዉ፡፡ በየአመቱ ወደ 76,000 የሚጠጉ እናቶች እና 500,000 ህጻናት ከዚሁ ህመም ጋር በተገናኘ ይሞታሉ፡፡ በሃገራችንም ከደም መፍሰስ በመቀጠል ሁለተኛ የእናቶች ሞት ምክንያት ሲሆን በአንዳንድ ሆስፒታሎች (ለምሳሌ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሜሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ) ቀዳሚ የእናቶች ሞት ምክንያት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
በሀገራችንም በእርግዝና ወቅት የሚከሰት ደም ግፊት ሳቢያ የሚሞቱ እናቶች ቁጥር ከፍተኛ ነው፡፡ ይህን ችግር ለመቀልበስ ትምህርታዊ የግንዛቤ መስጫ መርሀግብሮች ያስፈልጋሉ፡፡
በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት (ፕሪክላምፕሲያ) እርጉዝ በሆነች ወይም በአራስ ሴት አካል ዉስጥ ያሉ ክፍሎች ላይ እክል የሚፈጥር እና ከፍተኛ የደም ግፊት የሚያስከትል ህመም ነዉ፡፡ይህ በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት ከ እናቲቱ በተጨማሪ በጽንስ ላይ የተለያዩ ችግሮችን የሚያስከትል በሽታ ሲሆን በጊዜ ታዉቆ ህክምና ካልተደረገ ከፍተኛ የጤና መቃወስ ከማስከተሉ በተጨማሪ የእናቲቱንም ሆነ የጽንሱን ህይወት እስከማሳጣት ሊያደርስ ይችላል፡፡
የአለም የእርግዝና ደም ግፊት #preeclampsia ቀን በየአመቱ May, 22 የሚከበር ሲሆን በዚህ አመትም
‘Move Preeclampsia Research Forward' “በእርግዝና ደም ግፊት ላይ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮችን እናስፋ”
በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡
በሃገራችንም ለመጀመሪያ ጊዜ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሜሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ነው የተከበረው፡፡ በዚህ ዓመትም ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በኮሌጃችን እየተከበረ ይገኛል፡፡ በዚህም አከባበር በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ዉስጥ ስለ በሽታዉ ያለዉን ግንዛቤ ለመጨመር የተለያዩ መርሃ ግብሮችና በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡
#PreeclampsiaAwarenessMonth #worldpreeclampsiaday
#maternalhealthmatters #sphmmc
እርግዝና ወቅት ደም ግፊት የሚከሰተዉ መቼ ነዉ?
አብዛኛዉን ግዜ በርግዝና 2ኛዉ አጋማሽ ማለትም ከሃያ ሳምንት በኋላ ይከሰታል፡፡ልጅ ከተወለደ በኋላም ሊከሰት ይችላል፡፡ መንስኤዉ ምንድን ነዉ?
በተለያየ ጊዜ ጥናቶች ቢደረጉም አንዳንድ ሴቶች ለምን በእርግዝና ወቅት ደም ግፊት እንደሚይዛቸዉ በትክክል አልታወቀም
ወይም የዚህን በሽታ መንስኤ ለይቶ ለማወቅ አልተቻለም፡፡ነገር ግን ከዚህ በታች የተጠቀሱት ምክንያቶች ተጋላጭ ያደርጋቸዋል፡፡
Ø እርግዝና የመጀመሪያቸዉ የሆነ
Ø ከዚህ በፊት በእርግዝና ግዜ የደም ግፊት የታየባቸዉ ወይም በቤተሰብ ዉስጥ ተመሳሳይ ታሪክ ያላቸዉ
Ø ከዚህ በፊት የደም ግፊት ፤ የኩላሊት ወይም ሁለቱም በሽታ የነበረባቸዉ
Ø እድሜያቸዉ ከ 40 አመት በላይ የሆኑ
Ø እርግዝናዉ መንታ ወይም ከዚያ በላይ ሲሆን
Ø እንደ ስኳር አይነት ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸዉ
Ø ከመጠን በላይ የሰዉነት ክብደት
አንዲት ነፍሰጡር ደም ግፊት ቢኖርባት በልጇ ላይ ምን ሊያስከትል ይችላል?
Ø የልጁ ክብደት ከእርግዝና ጊዜ ጋር ሲታይ የቀነሰ ይሆናል
Ø የዉሃ ሽንት መቀነስ
Ø በእትብት በኩል ለልጁ የሚደርሰዉ ደም መቀነስ
Ø እንዲሁም ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እንዳለ ሊሞት ይችላል ምልክቶቹ ምንድን ናቸዉ?
Ø የበሽታዉ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ምንም አይነት ምልክት አይታይም፡፡ በምርመራ ጊዜ የግፊት መጨመር
(≥140/110) እና ሽንት ዉስጥ ያለዉ ፕሮቲን መጨመር ይታያል፡፡ ህመሙ አደገኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ
Ø ከባድ ራስ ምታት
Ø የእይታ ለዉጥ(የእይታ ብዥ ማለት፤ የእይታ መጋረድ)
Ø ትንፋሽ ማጠር
Ø በሆድ የላይኛዉ ክፍል ላይ ከባድ የሆነ የህመም ስሜት
Ø ከፍተኛ የደም ግፊት(≥160/110)
Ø የፊት እና የእጆች ማበጥ
በእርግዝና ወቅት የሚከሰትየደም ግፊትን ለመከላከል ምን ይደረግ?
1. ሁሉም ነፍሰጡር የቅድመ ወሊድ ክትትል እንዲያደርጉ ማበረታታት ፡- የደም ግፊቱ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ትንፋሽ ሲያጥራቸዉ፤ ሲያንቀጠቅጣቸዉ እና አእምሮአቸዉን ሲያስታቸዉ ወደ ህክምና የሚሄዱ ነፍሰጡሮች በተደጋጋሚ ያጋጥማሉ፡፡ይህ ከመከሰቱ በፊት እርዳታ ማግኘት እንድትችል የቅድመ ወሊድ ክትትል ማድረግ አስፈላጊ ነዉ፡፡
2. ደም ግፊት ያለባት ለመጸነስ የምታስብ ሴት የጤና ባለሙያ በማማከር ህመሙ በጤናዋ ላይ ችግር አለመፍጠሩን ለማጣራት የቅድመ እርግዝና ምርመራ ማድረግ ይኖርባታል፡፡
3. ክብደቷ ከተገቢዉ በላይ ከሆነ ከእርግዝና በፊት መቀነስ ይኖርባታል፡፡
4. የስኳር ህመም ያለባት ሴት ከማርገዟ በፊት ህመሟን በቁጥጥር ስር ማድረግ አለባት፡፡
5. የእርግዝና ደም ግፊት የተጋለጡ እናቶችን ለመለየና የመከሰት እድሉን ለመቀነስ የቅድመ ወሊድ ክትትል በመጀመሪያ ሶስት ወር መጀመር
በትግራይ ለሚገኘው የዶር ጸጋዬገብረ ሔር አጠቃላይ ሆስፒታል ድጋፍ ተደረገ::
ከአዲግራት 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ፋጺ ከተማ በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የዶር ጸጋዬ ገብረ ሔር አጠቃላይ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎቱን ለማስጀመር የሚያስችሉ ግምቱ 10 ሚሊዮን የሚደርስ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ፕሮቮስት ዶር ሲሳይ ስርጉ በቦታው ተገኝተው የሕክምና ቁሳቁሱን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ኮሌጁ ያደረገው ድጋፍ ሆስፒታሉን በፈጠነ መልኩ ስራ እንዲጀምር ያደርገዋል ብለዋል፡፡ በመቀጠልም የዶር ጸጋዬ ሆስፒታል መደበኛ አገልግሎቱን በሚገባ እስከሚሰጥ ድረስ የኮሌጁ ድጋፍ እንደማይለየውም ገልጸዋል፡፡
የሕክምና ቁሳቁሱን የተረከቡት የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶር ቃለክርስቶስ ግደይ ስለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ከዚህ ቀደምም በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ለደሴ ሆስፒታል እና ለአፋር ሆስፒታል ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉ ይታወቃል፡፡
We are pleased to announce that our own colleague Dr. Mebratu Eyasu (PhD in Pharmacy), recently has defended his PhD thesis successfully at Complutense University of Madrid, Madrid, Spain.

Also, we are grateful to his PhD thesis evaluation score: “Sobresaliente”, “CUM LAUDE”.
We, Saint Paul´s Community, congratulate him and wish a successful future professional career.
We are very pleased to announce that our own colleague, Dr. Seid Mohammed, was elected as the president of The Urology Society of Ethiopia (USE) during the society’s Annual Conference held in Addis Ababa.

We, St. Paul’s community, would like to congratulate Dr. Seid Mohammed and wish him an industrious term to make the USE great as it deserves.
ሕጉ ምን ይላል?

አድሜው ከ21 ዓመት በታች የሆነ ሰው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የትምባሆ ምርትን መሸጥ ወይም ከ21 ዓመት በታች በሆነ ሰው እንዲሸጥ ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡
ትምባሆ ማጨስ እና መጠቀም በተከለከሉባቸው ቦታዎች ቅጥር ግቦ ውስጥ እና በማንኛውም የጤና ተቋም፣ ትምህርት ቤት ፡ የመንግስት ተቋም እና የወጣት ማዕከላት መቶ ሜትር ዙሪያ ትምባሆ መሸጥ የተከለከለ ነው፡፡
ማንኛውም ሰው የኢንተርኔት ፣የፖስታ እና የቴሌኮምዩኒኬሽን ሽያጭን ጨምሮ ፤ ገዥ በአካል በማይገኙበት በምንም ዓይነት ሌላ ሁኔታ ተጠቅሞ የትምባሆ ምርት መሸጥ ፣ እንዲሸጥ ማስቻል ወይም እንዲህ ዓይነቱን ሽያጭ ማመቻቸት የተከለከለ ነው፡፡
የምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/11/
#WorldNoTobaccoDay #NoTobaccoDay #Tobacco #Nosmoking
 

 

Kansas University delegation led by an orthopedic trauma surgeon, Dr Archie Heddings, has been visiting SPHMMC.

The purpose of the visit was to build a strong relationship with the orthopedic department of the college and reinvigorating their institution’s relation with school of nursing, too.

The delegate met with Dr. Sisay sirgu, provost of St.Paul's Millennium medical college, and discussed ways how to further advance relationship as it is of greater value in improving the patient care, and Dr. Sisay on his part promised to work closely with the University of Kansas.

Previously, the University funded two fellowship spot for orthopedic and traumatology department of St Paul Hospital.