St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
St. Paul Millennium Medical College’s staff have today acknowledged the former Health Minister for the remarkable deed she did during her stay in the ministerial position.
All employees wish her a happy future!
የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች በራሳቸው ተነሳሽነት ለሪፈራል ሕክምና ወደ ኮሌጃችን መጥተው ለሚታከሙ እናቶች በሙያቸው አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር መድሐኒት በመግዛት፡ የትራንስፖርት ወጪ በመሸፈን እና ሌሎች ከሕክምናቸው ጋር ተያያዥ ባላቸው ጉዳዮች የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡
ላለፉት ሁለት ዓመታት ከሐኪሞቹ በየወሩ በሚሰበሰብ ገንዘብ በጣም ችግር ያለባቸው እናቶች፤ በሕክምና ላይ እስካሉ ድረስ አስፈላጊው ድጋፍ ሲደረግላቸው ነበር፡፡ይሁን እንጂ አገልግሎቱን የሚፈልጉ እናቶች ቁጥራቸው በመጨመሩ ሌሎች ወገኖችም በዚህ በጎ ተግባር እንዲሳተፉ አስፈልጓል፡፡ ብዙ እናቶችን ለመርዳት ቅን ልብ ባላቸው ባልደረቦቻችን የተቋቋመው ይህ ሕብረት አሁን በመንግስት እውቅና አግኝቶ ለመንቀሳቀስ ተመዝግቧል፡፡ ይህም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ብዙ እናቶችን ለመርዳት ያስችላል፡፡
ወደፊት ሐኪሞቹ እንደሚናገሩት ከሆነ እቅዳቸው ሰፊ ነው፡፡ ለአብነትም ከሚጠቀሱት መካካል ሆስፒታል ድረስ መጥተው መታከም ለማይችሉ ያሉበት ድረስ በመሔድ አገልግሎት መስጠት፣ሴቶች የቅድመ ሕክምና ምርመራ እንዲያደርጉ መስራት፣የእናቶች ማቆያ መገንባትና ሌሎች ስራዎችንም ያካትታል፡፡
በትናትናው ዕለት ይህ በጥቂት ሐኪሞች የተጀመረው ሕብረት ʺሔዋን የሴቶች ጤና ድጋፍ በጎ አድራጎት ድርጅትʺ በሚል ሰያሜ ተመስርቷል፡፡ ኑ አብረን ብዙ እናቶችን እንርዳ ይሏችኋል፡፡
Re-Announcement
Re-Announcement

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2016 ዓ.ም Neonatal Nursing የነርሲንግ ፖስት ቤዚክ ስፔሻሊቲ ፣ ለመማር የምትፈልጉ እና መስፈርቱ የምታሟሉ ከ18/06/2016- 23/06/2016 ዓ.ም ሬጅስትራል ቢሮ እንድትመዘገቡ እናሳወቃለን፡፡

የመመዝገቢያ መስፈርቶች፣
በነርሲንግ ዲፕሎማ ደረጃ 4 የተመረቀች/የተመረቀ መወዳደር ይችላሉ፣
የሚድዋይፍሪ ዲፕሎማ ደረጃ የተመረቀች /የተመረቀ በጨቅላ ህፃናት ነርሲንግ መመዝገብ ይችላል፣
ከመስሪያ ቤታቸው የስፖንሰር ሺፕ ደብዳቤ ማምጣት የሚችል/የሚትችል ወይም ከፍሎ መማር የሚችል ፡፡
ኮሌጅ የሚያዘጋጀውን የቃል እና የፁሑፍ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል፣
ሙሉ ጤነኛ የሆነ/የሆነች
አንድ ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ ያላት
የቃል እና የፁሑፍ ፈተና በ 24/6/2016 ዓ/ም
ማሳሰቢያ፡

1.አስፈላጊውን ዶክመንት ያላሟላ ፈተናው ላይ እንደማይቀመጥ በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡

2.ኮሌጁ ማደሪያና ምግብ አያዘጋጅም

የትምህርት ማስረጃ online መግባት አለበት፡፡
‘ ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር 251 -112 -75-60-89 በሥራ ሰዓት ይደወሉ ወይም አካል መገኝት ይችላሉ ፡፡
We are pleased to announce that we have been selected as a host to organize the upcoming 18th Tuberculosis Research Advisory Council (TRAC) and the 2024 World Day events. Both the Scientific conference and Awareness events will be held in the EPHI Conference Hall from March 21-24/2024
Exhilarating presentations, round table discussions, High-level meetings, and Awareness raising events will be on the stage. #endtb #YesWeCanEndTB #WorldTBDay #tuberculosis #EndTBDialogues #makeadifference
#FindallTB #TreatAllTB #PreventAllTB #EndTB
እንኳን ለ128ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!
ADWA, The great African Victory Over Colonialism.
በወሊድ ወቅት ደም ለሚያስፈልጋቸው እናቶች ደም እንለግስ!
ቀን፡ የካቲት 28-29/2016
ቦታ፡ በኮሌጁ 5ኛ በር አካባቢ
የ128ኛው የአድዋ ድል በዓል  ምክንያት በማድረግ የጤና ሚኒስትርዋ - የዶር መቅደስ ዳባ መልዕክት።
___

የአድዋ ድል ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር ቀኝ ገዢዎች በጥቁር ሕዝብ ተሸንፈው ኢትዮጵያውያን ለአፍሪካ ነፃነት አዲስ ምዕራፍ የከፈቱበት ታሪካዊና የአሸናፊነት ተምሳሌት ነው።

ጀግኖች አባቶቻቸን በዱር በገደሉ ተዋድቀው፣ በጦር በጋሻ ተወግተው፣ ሀገር ለማጽናት፣ ትውልድ ለማስቀጠል፣ ዘርና ቋንቋ፣ ሳይከፋፍላቸው በአንድ ላይ ተመው ድልን ባይቀናጁ፣ ዛሬ ኢትዮጵያ የምትባለውን አገር ማየት ባልቻልንም ነበር።

በሀገራዊ ፍቅርና ጀግንነት ታሪክ ሰርተው፣ ኢትዮጵያዊ እሴትን ገንብተው፣ የጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነውን የድል ታሪክ፣ በደማቅ ጽፈው አልፈዋል፡፡

አሁንም አባቶቻችን የዛሬ 128 ዓመት ሀገራቸውን ለመታደግ ፣ አንድ ሆነው እንደዘመቱ፣ ዛሬም ህብረተሰባችን ጤናው የተጠበቀና አምራች እንዳይሆን በተለያዩ ግዜ እየገጠሙ ያሉ እንደ ወረርሽኝ፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በአንድ ላይ መዝመት ይጠይቀናል፡፡ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በየድርሻው ሃላፊታቸውን በብቃት ሲወጡ፣ ድምር ውጤቱ ሀገርን ይታደጋል፡፡

በዚሁ አጋጣሚ በየጤና ተቋማቱ ህሙማንን በማከም ቀን ከሌት እየለፋችሁ የምትገኙ የጤና ባለሙያዎች፣ በአጠቃላይ በጤናው ዘርፍ የተያዙ እቅዶች እንዲሳኩ ብርቱ ጥረት እያደረጋችሁ የምትገኙ በየደረጃዉ ያላችሁ አመራሮችና ባለሙያተኞች፣ ባለድርሻ አካላት፣ አጋር ድርጅቶችና ሲቪክ ማህበራት ሁሉ እያመሰገንኩ አባቶቻችን በበርካታ ባልተመቹ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው ትልቁ ሀገራዊ ተልዕኮዋቸው ላይ ትኩረት አድርገው በመታገላቸው፣ ዛሬ የምንዘክረውን ድል እንዳስገኙልን ሁሉ፣ በጤናው ዘርፍ የያዝናቸውን ትላልቅ ግቦች አሳክተን ህብረተሰባችንን ጤናማና አምራች ለማድረግ በምናደርገው ርብርብ በጋራ በመቆም  የጤና ግቦቻችንን ለማሳካት አብረን እንድንተጋ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

ዶ/ር መቅደስ ዳባ
የጤና ሚኒስትር
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
ደም እንለግስ !

" በወሊድ ወቅት ደም ለሚያስፈልጋቸው እናቶች ደም እንለግስ " ሲል የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ጥሪ አቅርቧል።

የሕክምና ኮሌጁ ለቲክቫህ ቤተሰቦች በላከው አጭር መልዕክት የፊታችን የካቲት 28 እና 29 ቀን 2016 ዓ/ም በኮሌጁ 5ኛ በር አካባቢ የደም ልገሳ እንደሚደረግ ጠቁሟል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ አሁን ላይ በወሊድ ወቅት ለእናቶች የሚሆን ደም በጣም እየተፈለገ እንደሆነ ተረድቷል።

ሁሉም የሚችል የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል ፤ በሁለቱ ቀናት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በመገኘት ደም እንዲለግስ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ቦታውን ለማታውቁ Google Map ተጠቀሙ።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
60 በመቶ የሚሆነውን የሕጻናት የመስማት ችግሮች በእነዚህ መንገዶች መከላከል ይቻላል፡፡
1. በማስከተብ
2. የጆሮ ንጽሕናን በመጠበቅ
3. ለከፍተኛ ድምጽ ባለመጋለጥ
4. ኢንፌክሽን አለመኖሩን በምርመራ በማረጋገጥ
#WorldHearingDay #hearingcare
Celebrating 1-year milestone of YeneHealth Care Women Deserve Seminar Series!

As Women's History Month, our one-year anniversary is dedicated to celebrating women's success with a special tributes to remarkable women.
Plus, get ready for exciting giveaways from Boston's Day Spa!

The event will be held at the US Embassy from 2:00 PM - 4:00 PM supported by the US Embassy, St.Paul's Hospital Millennium Medical College and Boston's Day Spa.

To attend this event:
1) Please remember you must register in advance using the link below
2) Bring your ID with you to enter the program
3) Leave all electronics except your cell phone at home. (laptops, tablets etc. are not allowed in the Embassy.). They will not let you in if you bring those devices.

Register for the event here: https://forms.gle/QLDZEwPEh1eYCKEt6
Register for Satchmo Center Entrance: https://bit.ly/SatchmoCenterMembership
Both registrations are mandatory.

#YeneHealth #CareWomenDeserve  #1yearanniversary #celebratingwomen
ነገ በጠዋት እንገናኝ! ደም እንለግስ!