St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.66K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
ሆስፒታሉ በክዋኔ ኦዲት ግኝቶች ተገቢውን የእርምት ማስተካከያ እንዳደረገ ተገለጸ
---------------------------
(ዜና ፓርላማ) ህዳር 5፣ 2018 ዓ.ም፤ ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ዙሪያ በነበሩበት የክዋኔ ኦዲት ግኝቶች ላይ ተገቢውን የእርምት ማስተካከያ እንዳደረገ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የክዋኔ ኦዲት ግኝቶች ላይ ማሻሻያ እንዲያደርግ በሰጠው ምክረ ሀሳብ መሰረት የእርምት ማስተካከያ ማድረጉን ለማረጋገጥ ቋሚ ኮሚቴው የመስክ ጉብኝት አድርጓል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ ለማስወገድ ኢኮስትሪል ማሽን ተተክሎ ስራ ሊጀምር ቅድመ ዝግጅቱ መጠናቀቁ በአወንታዊ የሚታይ እንደሆነ የተከበሩ ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ ገልጸዋል፡፡

ተበላሽቶ የነበረው የደረቅ ቆሻሻ ማቃጠያ መሽን በአግባቡ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት መቻሉ ከተፈቱ የክዋኔ ኦዲት ግንቶች መካከል የሚጠቀስ አንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡

በሌላ በኩል በጤና ሚንስቴር በቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ዙሪያ የህግ ማዕቀፍ ወጥቶ ተግባራዊ አለመደረጉ አሁንም በሆስፒታሎች እንደ ክዋኔ ኦዲት ግኝት የሚታይ ችግር መሆኑን የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ገልጸዋል፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ዋና ፕሮቮስ ዶክተር ሙሉቀን ተስፋዬ በበኩላቸው በሆስፒታሉ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓቱን ለማዘበን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው በክዋኔ ኦዲት ግኝቶች ዙሪያ የእርምት ማስተካከያ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

አዲሱ ኢኮስትሪል ማሽን የደረቅ ቆሻሻን ለማስወገድ የላቀ ጠቀሜታ አንዳለው የገለጹት ዶክተር ሙሉቀን፤ ፕላስቲክና መጠነኛ ብረት ነክ ቁሳቁሶችን 80 በመቶ በመቆራረጥና ከባክተሪያ ነጻ በማድረግ መልሰው ጥቅም ላይ እንደውሉ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

ዶክተር ሙሉቀን አክለውም ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ግንበታው አፈጻጸሙ 90 በመቶ መድረሱን ገልጸው፤ በሆስፒታሉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የቋሚ ኮሚቴው እገዛ አስፈላጊ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
(ዜና ፓርላማ)
Burundi’s Minister of Public Health Visits St. Paul’s Hospital Millennium Medical College

The Minister of Public Health of Burundi, Dr. Lydwine Baradahana, visited St. Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC), where she held discussions with the College Provost, Dr. Muluken Tesfaye, and Vice Provosts, Dr.Lemi Belay and Dr.Ewenet Geberehana.

Dr. Lydwine expressed her strong interest in collaborating with the College and shared plans to send Burundian medical professionals to training at St. Paul’s. She remarked that she and her team had gained valuable insights from their discussions and visit, particularly regarding the College’s medical education programs and hospital management systems.

During the meeting, Dr. Muluken highlighted that SPHMMC has been working to become a training hub for African health professionals, offering high-quality education and specialized clinical training.

As part of her visit, Dr. Lydwine toured the Center of Excellence in Reproductive Health, other medical centers, and various hospital facilities. She praised St. Paul’s leadership for its commitment to advancing healthcare through education, innovation, and regional collaboration.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Here’s everything you need to know about #Marburg, its symptoms, and how it spreads. 👇🏿

#ViralFacts
የማርበርግ ቫይረስን ለመቆጣጠር በቅንጅት እየተሰራ ነው - ዶ/ር መቅደስ ዳባ

በቅርቡ በደቡብ ኢትዮጰያ ክልል በጂንካ ከተማ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መከሰቱ በላቦራቶሪ ከተረጋገጠ ጀምሮ የአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድኖች  በሽታው ወደ ተከሰተበት አካባቢዎች ተልከው ቫይረሱን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ እየተሰራ ይገኛል ሲሉ ዶር መቅደስ ዛሬ በበሽታው ዙሪያ በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትርዋ  በመግለጫቸው መንግስት በራስ  ከፍተኛ የላቦራቶሪ አቅም በመገንባት የዘረ-መል ምርመራ ጭምር በሀገር ዉስጥ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ በዛሬዉ ዕለት ከፍተኛ የመመርመር አቅም ያለዉ ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪም ወደ ጅንካ  ከተማም ተልኳል፡፡ በተጨማሪም የአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ማእከላትና የህክምና ተቋማትን ማቋቋምና ማጠናከር ስራ ተጠናክሮ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የለይቶ ማቆያ እና ማከሚያ ማዕከላት የተቋቋመ ሲሆን÷ በሌሎች ክልሎች ደግሞ በሽታው ቢከሰት ለማከም የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል። ለእነዚህም ተቋማት የሚያስፈልጉ የሕክምና ግብአቶችና የኢንፌክሽን መከላከያ ቁሳቁሶችን ለማሟላት ጥረት እየተደረገ መሆኑን  ዶር መቅደስ  በመግለጫቸው አስረድተዋል፡፡

ሚኒስትሯ እስካሁን ድረስ 17  በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው፣ ከዚህም 3ቱ ህይወታቸው በቫይረሱ ያለፈ መሆኑን በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ኢንስቲትዩት ሪፈረንስ ላቦራቶሪ የተረጋገጠ ሲሆን  በተጨማሪም በምርመራ የተረጋገጠ ባይሆንም 3 ምልክቶች የታየባቸው ሰዎችም ህይወት  ማለፉን ሚኒስትርዋ አስረድተዋል፡፡  ሌሎች ንኪኪ የነበራቸዉ 129 ሰዎች ራሳቸዉን ለይተዉ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል። በቫይረሱ ህይወታቸዉን ላጡ ወገኖች የተሰማቸዉን ሀዘን በመግለጽ ለቤተሰቦቻቸዉና ወዳጅ ዘመዶቻቸዉ መጽናናትን ተመኘተዋል፡፡

የህብረተሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫና የቅኝትና ቁጥጥር ስራዎች እየተካሄዱ ሲሆን በሀገር ውስጥና በድንበር አከባቢ መግቢያ እና መውጫ ቦታዎች ላይ የጤና ምርመራዎች እየተጠናከሩ መሆኑን  በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት  ተገልጿል፡፡