St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.66K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ: :
                
                 ኢድ- ሙባረክ!
                መልካም በዓል!
    
Eid al-Fitr celebrations held with patients today.
St. Paul’s pediatric surgeons graduate in 2026: Dr. Beza Degmu, Dr. Raji Amsalu, and Dr. Ayenesh Yehune.
የዓለም ቲቢ ቀን በየዓመቱ መጋቢት 15 ቀን “ March 24” ይከበራል፡፡ የዓለም ቲቢ ቀን በየዓመቱ የሚከበርበት ዋና ምክንያት በሽታው ዛሬም በሰው ዘር ላይ ከፍተኛ ሕመምና ሞት እያስከተለ መሆኑን ለማስገንዘብና የቲቢ በሽታን ለመቆጣጠር የሚከናወኑትን ሁሉን አቀፍ ተግባራት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በተጠናከረ መልክ እንዲቀጥል ለማስቻል ነው፡፡ ዕለቱ መጋቢት 15 ቀን እንዲሆን የተመረጠውም የዛሬ 140 ዓመት “March 24, 1882” ታዋቂው ጀርመናዊ ተመራማሪ ዶ/ር ሮበርት ኮች፣ “ማይኮባክቴሪያም ቲዩበርክሎስስ” ተብሎ የሚታወቀውን የቲቢ በሽታ መንስኤ ማግኘቱን ለዓለም ያበሰረበትን ቀን ለማስታወስ ሲባል ነው፡፡ ይህንኑ ቀን ታሳቢ በማድረግ በበሽታው ቁጥጥር ላይ ትኩረት የሚሰጡ መልዕክቶች እንደመሪ ቃል ተወስደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች የሚከናወኑ ሲሆን ዘንድሮም የዓለም ቲቢ ቀን ከዓመታዊ የቲቢ ምርምር ጉባኤ ጋር በመቀናጀት “አዎ! ቲቢን ለማጥፋት እንችላለን!በመንግስት መሪነት: በሕዝባችን ኃይል!!” በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል::
የቲቢ በሽታ ምንድን ነው?

የቲቢ በሽታ በአገራችን በተለምዶ የሳንባ ነቀርሳ የሚባለው በሽታ ሲሆን ቲቢ የተባለውን የአሁኑን ሲያሜ ያገኘው ቲዩበርክሎሲስ ተብሎ ከሚጠራው የበሽታው የእንግሊዘኛው ቋንቋ አህጽሮተ-ቃል ነው፡፡ መንስኤም አልፎ አልፎ እንደሚነገረው ብርድ ወይም ንፋስ ሳይሆን ረቂቅ የሆነና ቀደም ሲል እንደተገለጸው “ማይኮባክቴሪያም ቲዩበርክሎስስ” የተባለ ባክቴሪያ ነው፡፡ ቲቢ “ማይኮባክቴሪያም ቦቪስ” በተባለ ባክተሪያ የተጠቁ የቤት እንስሳት ወተት ሳይፈላ ቢጠጣ ከእንስሳት ወደ ሰው ሊተላለፍ እንደሚችልም ተረጋግጧል፡፡

ቲቢ የትኛውን የኅብረተሰብ ክፍል ያጠቃል?

ቲቢ ዕድሜን፣ ፆታን፣ ዘርንና ቀለምን ሳይለይ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል የሚያጠቃ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ምንም እንኳን በሽታው ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች ቢያጠቃም በበሽታው በበለጠ የሚጠቁት በአምራች ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙና የቤተሰብ ኃላፊ የሆኑ ዜጎች ናቸው፡፡

በተያያዘም ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት፣ አረጋዊያን፣ የሰውነት መከለከያ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ለምሳሌ ኤች አይ ቪ፣ የካንሠር እና የስኳር ሕሙማን፣ የምግብ እጥረት ያለባቸው፣ በአክታ ምርመራ ቲቢ እንዳለባቸው ከተረጋገጠ ሕሙማን ጋር አብረው የሚኖሩ እንዲሁም በተጨናነቁና በተፋፈጉ ቦታዎች የሚኖሩ/የሚሠሩ/የሚሰባበሱ ሰዎች እንዲሁም የአልኮንና የትምባሆ ሱሰኞችም ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡

የቲቢ በሽታ እንዴት ይተላለፋል?

ቲቢ የሚተላለፈው በአብዛኛው በትንፋሽ አማካኝነት ነው፡፡ ይኸውም አንድ በሳንባ ቲቢ የተያዘ ሕመምተኛ በሚስልበት፣ በሚያስነጥስበት፣ በሚተፋበት፣ ወይም በሚናገርበት ወዘተ... ወቅት የቲቢ በሽታ አምጪ ባክቴሪያን የያዙ የአክታ ብናኞች ወደ አየር ስለሚረጩና ብናኞችም በአቅራቢያው ያሉ ሰዎች አየር ወደ ውስጥ በሚተነፍሱበት ጊዜ በቀላሉ ወደ ሳንባው ውስጥ ገብተው ለማጥቃት ዕድል ስለሚያገኙ ነው፡፡

የቲቢ በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የቲቢ በሽታ ሰማኒያ ከመቶ የሚሆነውን የሚያጠቃው ሳንባን በመሆኑ የሳንባ ቲቢ በሽታ ዋናው ምልክት ሁለት ሳምንትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ የዘለቀ ሳል ነው፡፡ ሳሉ አክታ ያለውና ደም የቀላቀለ ወይም ያልቀላቀለ ወይም ደረቅ ሊሆን ይችላል፡፡ ሕመምተኛው ከሳሉ በተጨማሪ በደረቱ አካባቢ የውጋት ስሜት፣ መጠነኛ የሆነ ትኩሳት፣ ሌሊት በመኝታ ጊዜ ማላብ፣ የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስና የሰውነት መድከም የመሳሰሉ አጠቃላይ የሆኑ ምልክቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ የበሽታም ምልክቶች እንደተጠቃው የሰውነት ክፍል ዓይነት ይለያያሉ፡፡



የቲቢ በሽታን ማዳን ይቻላል?

ቲቢ መድኃኒት ስለአለው በአግባቡ ከታከሙት የሚድን በሽታ ነው፡፡ የበሽታው ምርመራም
ሆነ ሕክምና በመንግሥታዊና ሕክምናውን እንዲሰጡ በተፈቀደላቸው የግል ጤና ተቀቋማት በነፃ ማግኘት ስለሚቻል ማንኛውም ሰው የበሽታው ምልክቶች ሲታዩበት አገልግሎቱን ወደሚሰጥ ጤና ድርጅት መሄድ ይኖርበታል፡፡ የቲቢ መድኃኒት በታዘዘው መጠንና ጊዜ ባይወሰድ ችግር ያስከትላል፡፡ ስለሆነም ሕመምተኛው የታዘዘለትን መድኃኒት ሳያቋርጥ በየቀኑ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡ ሕክምናው ከተቋረጠ ግን የበሽታ መንስኤ የሆነው ባክቴሪያ የፀረ-ቲቢን መድኃኒቶችን በመላመድ በመደበኛው የቲቢ ሕክምና ዘዴ መዳን የማይችል የቲቢ ዓይነት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

መድኃኒት የተላመደ ቲቢ ምንድን ነው?

መድኃኒትን የተላመደ ቲቢ በሽታ መድኃኒት ያልተላመደ ቲቢን ለማከም የሚያገለግሉ መድኃኒቶችን የተላመደ የቲቢ በሽታ ዓይነት ነው፡፡ በሽታው የሚከሰተው ታካሚዎች መድኃኒቶችን በታዘዘው መሠረት ካላመውሰድና የክትትል ጉደለት ቢሆንም በሽታው መድኃኒት እንዳልተላመደው ቲቢ ሁሉ በትንፋሽ አማካይነትም ይተላለፋል፡፡ መድኃኒት ያልተላመደውም ሆነ መድኃኒት የተላመደ ቲቢ ዓይነቶች መንስኤያቸው፣ መተላለፊያ መንገዶቻቸውና ምልክቶቻቸው ተመሳሳይ ቢሆኑም መድኃኒትን ለተላመደ ቲቢ ሕክምና የሚሰጡ መድኃኒቶች ዓይነትና ብዛት እንዱሁም ሕክምናው የሚፈጅበታ ጊዜ ይለያል፡፡ ይሁን እንጂ መድኃኒትን የተላመደው ቲቢም በአግባቡ ከታከሙት መዳን ይችላል፡፡

የቲቢ በሽታን መከላከል ይቻላል?

መድኃኒት ያልተላመደውንም ሆነ መድኃኒት የተላመደ ቲቢን መከላከል ይቻላል፡፡ ስለሆነም የቲቢ ሕሙማን፣ ቤተሰቦቻቸውና በአጠቃላይ ሕብረተሰቡ የግልና የጋራ ኃላፊነታቸውንና ድርሻቸውን በታማኝነት ቢወጡ የበሽታው የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ እንደሚፋጠን ይታመናል፡፡





የቲቢ በሽታን መከላከል ይቻላል?

መድኃኒት ያልተላመደውንም ሆነ መድኃኒት የተላመደ ቲቢን መከላከል ይቻላል፡፡ ስለሆነም የቲቢ ሕሙማን፣ ቤተሰቦቻቸውና በአጠቃላይ ሕብረተሰቡ የግልና የጋራ ኃላፊነታቸውንና ድርሻቸውን በታማኝነት ቢወጡ የበሽታው የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ እንደሚፋጠን ይታመናል፡፡
Class of 2026: Obstetrics and Gynecology Graduates of St. Paul’s Hospital Millennium Medical College 🎉 Congratulations!
Today is World TB Day.

Tuberculosis #TB is an infectious disease caused by bacteria that mostly affects the lungs.

It spreads through the air when people with TB cough, sneeze or spit.

TB is preventable and curable 👇🏿
World TB Day, falling on March 24th each year, is designed to build public awareness that tuberculosis today remains a global epidemic, causing the deaths of 1 300 000 people each year. It commemorates the day in 1882 when Dr Robert Koch astounded the scientific community by announcing that he had discovered the cause of tuberculosis, the TB bacillus. At the time of Koch's announcement in Berlin, TB was raging through Europe and the Americas, causing the death of one out of every seven people. Koch's discovery opened the way towards diagnosing and curing TB. It is a humanity failure that 144 years later, this airborne disease remains the biggest infectious diseases killer.
SPHMMC Moves to Establish Regional Hub for Cleft Care Services
Hosts African delegation to boost collaboration

St. Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC) has hosted a high-level delegation to strengthen regional collaboration and advance cleft care services across Africa.

The SPHMMC Provost, Dr. Muluken Tesfaye, and Vice Provost, Mr. Jemal Shifa, Dr.Lemi Belay and Dr.Ewenet G.Hana held discussions with the visiting delegation on enhancing institutional partnerships and expanding regional collaboration. The delegation, led by Klara Jancarova, Senior Director of Global Operations, and Abiy Semunigus, Sub-Saharan Regional Director, included representatives from Kenya, Ghana, Tanzania, Malawi and Mozambique.

During the visit, participants exchanged best practices and discussed ongoing initiatives. Discussions also emphasized making SPHMMC a center of excellence for cleft care and a regional hub for training and service delivery.

The delegation also toured the hospital to observe ongoing clinical services.