St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.66K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
ማስታወቂያ
በመካንነትና ከማህጸን ጋር የተያያዘ የጤና ችግር ሕክምና ማግኘት ለምትፈልጉ በሙሉ :-
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ከፍተኛ የመካንነት ሕክምና ቡድን በሐዋሣ ከተማ በመገኘት አገልግሎት ይሠጣል::
ቀን:- ከግንቦት 12-14/2018
ቦታ:- ሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል እና አላቲዮን ሆስፒታል           
የሚሰጡት የምርመራ ዓይነቶች
-    ጥንዶችን በስነተዋልዶ ጉዳዮች ማማከር
-    የወንድና የሴት የመካንነት ቅድመ ምርመራ
-    በመካንነት ዙሪያ ህክምና ጉዳይ ምክርና የህክምና አማራጮችን ማስገንዘብ
-    በIVF የሕክምና ሳይንስ ልጅ ማግኘት ያልቻሉ ጥንዶችን ስለሕክምናው ማማከር
- ለመካንነት ችግር፡- የቱቦ መዘጋት እና የማህጸን ግርግዳ መጣበቅ መንስዔ ላለባቸው
- የቆየ የማሕጸን ህመም (chronic pelvic pain) ላለባቸው
- Endometriosis  እና በውስጠኛው የማህፀን ግርግዳ ላይ ያለ የማህጸን እጢ ላለባቸው ሕክምና ይሠጣል: :   

ስለሆንም ከላይ የተጠቀሱት ሕክምና የሚያስፈልጋችሁ ወገኖች በሁለቱ ተቋማት  በመገኘት ምዝገባና ቅድመ ምርመራ  ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
ሐኪማችንን ይተዋቁ!
በግል ሕክምና ያገኙዋቸዋል!
የቅዱስ ጳወሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በመካንነት እና ስነ-ተዋልዶ ጤና ዙሪያ የሚሰጠውን ልዩ የሕክምና መርሐግብር ዛሬ በአዋሳ ከተማ ጀመረ፡፡

ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ የሕክምና አገልግሎት ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተው በንግግር የከፈቱት ዶር ለሚ በላይ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ምክትል የአካዳሚክ እና የሕክምና አገልግሎት ፕሮቮስት እንደገለጹት ይህ የሕክምና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት፣ ማኅበረሰቡ ዘንድ መካንነት እንደማንኛውም በሽታ ታይቶ ሕክምና እንዳለው ግንዛቤ መፍጠር እና በተጨማሪም ከፍተኛ የላቀ ሕክምና ለሚያስፈልጋቸው ደግሞ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሚመሩበትን የሪፈራል ሥርዓት መዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ የመካንነት ህክምና የሚሰጠው በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ ብቻ መሆኑን አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ኮሌጁ አየሰራ እንደሆነም ተገልጿል፡፡


የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሕክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙንጣሻ ብርሃኑ በበኩላቸው ፣ የመካንነት ጉዳይ በአገርና በክልል ደረጃ ከፍተኛ የሕዝብ ጤና ችግር እየሆነ መምጣቱን ጠቁመው፡ ይህ የህክምና አገልግሎት በችግሩ ዙሪያ ያሉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ለመቀየርና ግንዛቤን ለማስፋት እንዲሁም የመካንነት ችግር ላጋጠማቸው ጥንዶች ምርመራውን ለማድረግ ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍጹም ወ/ገብርኤልም ፤ ታካሚዎች ባሉበት ቦታ አገልግሎቱ መድረስ አለበት በሚል የተጀመረው ይህ መርሀግብር ፣ ተደራሽነትን ለማረጋገጥና የተቀናጀ ሕክምናን በዘላቂነት ለመቀጠል ያስችላል ብለዋል።

እስከ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆየው በዚህ ልዩ የሕክምና መርሀግብር የሥነ-ተዋልዶ ጤና ችግር ያለባቸው እና የመውለድ ችግር ያጋጠማቸው ጥንዶች በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ፣በአላቲዮን አጠቃላይ ሆስፒታል ፣አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል በመገኘት ሕክምናውን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ይህን መርሐግብር ያዘጋጀው ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ፣ከሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ እና ከአላቲዮን አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ነው፡፡
SPHMMC,Reach Another Foundation Move to Advance Pediatric Neurosurgery Care in Ethiopia

St. Paul’s Hospital Millennium Medical College and Reach Another Foundation have initiated a partnership aimed at establishing a Center of Excellence and launching a specialized fellowship program to strengthen pediatric neurosurgery care in Ethiopia.

The discussion was held between SPHMMC Provost Dr. Muluken Tesfaye and Dr. Patricia O'Neill,International prisdant of.Reachanother foundation and Dr. Yakob Seman,,Ethiopian Country director of.Reachanother foundation, focusing on expanding specialized neurosurgical services and training opportunities at the institution.

The meeting was attended by SPHMMC Vice Provost Dr. Jemal Shifa and Dr. Daniel Sebhat,Head of the Neurosurgery dept.

Discussions centered on strengthening collaboration with the Neurosurgery team at SPHMMC through advanced training, institutional partnership, and service expansion.

The two institutions also discussed a shared vision to establish a dedicated pediatric neurosurgery service capable of delivering high-quality specialized care for children with complex neurological conditions.

The partnership is expected to improve access to specialized pediatric neurosurgical services while contributing to the training of future pediatric neurosurgeons in Ethiopia and across the region.

Both institutions reaffirmed their commitment to long-term collaboration aimed at advancing pediatric neurosurgery care and medical education.