የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የክረምት በጎ ፈቃድ የነፃ ጤና ምርመራና የሕክምና አገልግሎት መርሃ ግብር ዛሬ በይፋ አስጀመረ፡፡
ለአንድ ሳምንት በሚቆየው የጤና ምርመራ የተከፈተው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፡ የጤና ሚኒስትርዋ ክብርት ዶር መቅደስ ዳባ እና የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት አስቀድሞ የጤና ምርመራ አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ የብዙኃን ዜጎችን ሕይወት ለመታደግ ያስችላል ብለዋል፡፡ በተከታይ የሚደረጉ የክረምት የበጎ ፈቃድ ስራዎች ከጤናው አገልግሎት ባሻገር የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው፤ የጤናው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችን የጤና አገልግሎት ተደራሽነት በማስፋት በሽታን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ ሁነኛ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።
በጤና ምርመራ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት በማስፋት ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አስቀድሞ የ መከላከል ስራዎችዎችን በመስራት ውጤታማ መሆን መቻሉን ገልጸዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ በዚህ ክረምት በሚካሄዱ የጤና ምርመራ መርሀግብር ከ20 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ዛሬ ያስጀመረው የነጻ የጤና ምርመራ መርሀ ግብር እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓም ድረስ ይቆያል፡፡

ሁለተኛ ቀን፡
ዛሬም ነጻ የጤና ምርመራው ቀጥሏል፡፡ ምርመራዎቹ በሙሉ በሐኪሞች በታዘዙ ልዩ ልዩ ተጨማሪ ምርመራዎችም የሚታገዝ ነው፡፡
ታዲያ ለምን የጤና ምርመራዎን አያደርጉም?
ይምጡ!