St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
በ LTV Medical ፕሮግራም ላይ ዶር ዮርዳኖስ ኤርሚያስ ስለ መጥፎ አፍ ጠረን መግለጫ ሰጥታለች። እናመሠግናለን ።
ዛሬ(ረቡዕ ህዳር 04/2012 ዓ.ም) የአለም የስኳር ህመም ቀን ነው፡፡በየአመቱ በተለያዩ በግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብሮች ይከበራል፡፡ በዚህ ዓመትም “የስኳር ህመም ቤተሰቤን ይመለከታል” “Family and Diabetes” በሚል መሪ ቃል ለ29ነኛ በሀገራችን ይከበራል፡፡
በዓለም ላይ 425 ሚሊዮን ህዝብ ከስኳር ህመም ጋር ይኖራል፡፡ ከነዚህም አብዛኞቹ ሁለተኛዉ ዓይነት የስኳር ህመም (type2 diabetes) ነዉ፡፡ ከዓይነት 1 የስኳር (type1 diabetes) ህመም ጋር የሚኖሩ ልጆችና ወጣቶች ቁጥርም በዓለም ላይ በሶስት በመቶ እየጨመረ መሆኑንም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የስኳር ህመም በኢትዮጵያ ምን ይመስላል፡-

በአገራችንም ካለው አጠቃላይ ሕዝብም 3 በመቶ በላይ ከስኳር ህመም ጋር እንደሚኖር ይገመታል:: ከዚህ ቁጥር 90 በመቶ የሚሆነው ዓይነት ሁለት የስኳር (type2 diabetes) ህመም የሚባለው ሲሆን ይህም አስፈላጊው እርምጃዎች ከተወሰዱ በአብዛኛው መከላከል የሚቻል ነው::
የስኳር ህመም በአገራችን ስርጭቱ አስጊ እየሆነ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ጉዳዩን በይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ ሳያመን የጤና ምርመራ የማድረግ ባህላችን አነስተኛ በመሆኑ ከስኳር ህመም ጋር እየኖርን እንኳን መሆኑን ማወቅ ባለመቻሉ በአገራችን አብዛኛው ከስኳር ህመም ጋር የሚኖሩ ሰዎች በምርመራ የጤና ሁኔታቸውን ያላወቁ ናቸው:: ስለሆነም በቁጥጥር ሥር ያልዋለ የስኳር ህመም ልብን፣ ዓይንን፣ኩላሊቶችን፣ ነርቮችንና የደም ቱቦዎችን ተግባር መጉዳትና ተግባራቸውን በማስተጓጎል ከባድ የጤና ቀውስ ያስከትላል፡፡
የተለያዩ ሁኔታዎች ለስኳር ህመም ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡ በተለይ ለአይነት ሁለት የስኳር አይነት የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ጤናማ ያልሆኑ የአኗኗር ዘይቤዎች ናቸው፡፡ለምሳሌ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያለማድረግ፤ ከመጠን ያለፈ ውፍረት፤ በእድሜ መግፋት፤ የቅርብ የቤተሰብ አባል ከህመሙ ጋር መኖር (ለዓይነት አንድ የስኳር ህመም)፤የደም ግፊት እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡

የስኳር ህመምን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል በተለይ ሁለተኛውን ዓይነት የስኳር ህመም በከፍተኛ ደረጃ (80%) ልንከላከል እንደምንችል የአለም አቀፍ የጤና ድርጅት መረጃ ይጠቁማል፡፡ ስለሆነም ህብረተሰባችን እንደየአቅሙ ጤናማ አኗኗር እንዲከተል፣በተቻለ መጠን እንቅስቃሴ የተሞላበት አኗኗር እንዲያዘወትር፣በየአካባቢው የሚያገኛቸውን ፍራፍሬዎችና ቅጠላቅጠሎች የዘወትር ምግቡ ውስጥ እንዲጨምር እንዲሁም በተቻለ መጠን ህመም ቢሰማም ባይሰማም በዓመት አንድ ጊዜ አጠቃላይ የጤና ምርመራ ማድረግ በኋላ ከሚመጡ ጤናን ለአደገኛ ጉዳት ከሚዳርጉ ውስብስብ ችግሮች ራስን ለመጠበቅ ያስችላል::
የየስኳር በሽታ ምልክቶች
ቢያውቋቸው ፡
ተደጋጋሚ ሽንት ይኖራል፣ውሃ አብዝቶ ይጠማዎታል፣ ከሌላው ጊዜ በተለየ የረሃብ ስሜት ይሰማዎታል፣በጣም የድካም ስሜት ይሰማዎታል፡፡አጥርቶ አለማየት (ብዥታ)ይከሰታል፣ ቁስል ቶሎ አይድንም ፣ያልተጠበቀ ክብደት መቀነስ ይከሰታል እና የእግር እና የእጅ ጣት መደንዘዝ ያጋጥማል፡፡
እንደዚህ አይነት ስሜት ሲሰማዎት በአቅራቢያዎት ወዳለው ሆስፒታል ወይም ክሊኒክ ምርመራ ማድረግ ይገባዎታል፡፡
The CMANA yearly Gala.
Award of the faithful servant given to Mervat Shenouda for her exceptional devotion volunteering in Ethiopia
With the people.
For the people.
CMANA
(Coptic Medical Association North America)
We at saint pauls are proud and blessed with our dearest mervouta!! Well deserved!!
We are pleased to announce that Dr.Bethel Dereje of SPHMMC certified by German Society of for Gynecological Oncology (AGO) as Gynecologic Oncologist. Congratulations!
St Paul's Hospital Millennium Medical College, Department of Ophthamology, in collaboration with Himalayan Cataract Project conducted annual outreach program at Dubti General Hospital, Afar regional state, on 19-25 November 2019.
A total of 2283 patients were screened and treated: 260 sight restorative cataract surgery performed
የጡት ማጥባት ላንቺ እና ለልጅሽ!

ጡት ማጥባት ለልጅሽ

1. ከብዙ ኢንፌክሽኖች ይከላከላል። ለምሳሌ; የሳንባና የጆሮ ኢንፌክሽን፣ የማጅራት ገትር፣ የሆድ ቫይረስ
2. ከአለረጂክ ይከላከላል።
3. ብሩህ አዕምሮ እዲኖራቸው ያደርጋል
4. ከመጠን በላይ ውፍረትን በመከላከል አስተማማኝ እድገት እንዲኖራቸው ያደርጋል
5. በህፃናት ላይ የሚከሰትን ካንሰር መጠንን ይቀንሳል
6. ድንገተኛ የሆነ የጨቅላ ህፃናትን ሞት ይቀንሳል

ጡት ማጥባት ላንቺ

7. በእርግዝና ወቅት ያደገው ማህጸን ቶሎ ወደቦታው ስለሚመለስ የሚፈሰው የደም መጠን ይቀንሳል
8. ከልጅሽ ጋር የሚኖረው ፍቅር ይጨምራል
9. ከወሊድ በኃላ ቶሎ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል
10. እድሜ ሲገፋ የሚፈጠረውን የስኳር በሽታ ይቀንሳል
11. ከጡት እና ከእንቁላል ማምረቻ ካንሰር ይከላከላል
12. ወጪ ቆጣቢ ነው።

ጽሑፉን ከወደዱት(Like) በማድረግ ለሌሎችም (share)ያድርጉት፡፡
(በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)
We have held discussion on traffic accidents with representatives of the community discussion. It is well known that traffic accidents are increasing in our country. We have also carried out awareness raising programs on the issue. (AaBET Hospital, which is a branch of our college, is known for treating victims of traffic accidents.)
#WorldDayofRemembranceforTrafficVictims
የአልትራሣውንድ ጥቅም ከእናቶች ጤና አንጻር
*********************************

አልትራሣውንድ በአሁኑ ወቅት አልትራሣውንድ በድንገተኛ ክፍልና በተለያዩ አፋጣኝ የህክምና ድጋፍ ለሚያስፈልጓቸው ህሙማን አገልግሎት ለመስጠት ጠቃሚ መሳሪያነው፡፡ይሰጣል፡፡
አልትራሣውንድ የእርግዝና ምዕራፎችን ለመከታተል ጉልህ ሚናን አለው፡፡ለአብነትም፡-
በተለይ .በመጀሪመያው የእርግዝና ምዕራፍ ወቅት / ከ1-3ኛው ወር/
1. ትክክለኛ እርግዝና መኖሩንና ፅንስ መፈጠሩን ለማረጋገጥ
2. የተፈጠረው ፅንስ እድሜው ምን ያህል እንደሆነ ለመገመት
3. እርግዝናው በማህፀን ውስጥ ወይም ከማህፀን ውጪ መፈጠሩንና አለመፈጠሩን ለማረጋገጥ ይረዳል፡፡ ምክንያቱም ከማህፀን ውጪ የሚፈጠር እርግዝና ለእናትየው ጤንነት አስጊ በመሆኑ በአፋጣኝ እርምጃ ለመውሠድና የእናትየውን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል፡፡
4. የፅንሱን የልብ ምት ለማረጋገጥና በህይወት መኖሩን ለማየት
5. በአጠቃላይ እርግዝናው ትክክለኛና ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ መቀጠሉን ለማረጋገጥ ያስችላል፡፡ በሁለተኛው የእርግዝና ምዕራፍ ወቅት /
አቀማመጡን ከማህፀን በር አንፃር ለመገምገም - የፅንሱን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር - የፅንሱን እድገት ለመከታተልና በማህፀን ውስጥ መታፈንን፣ የእድገት መቋረጥ ወይም መቀነስ እንደሌለ ለማወቅ - የእናትየው ማህፀንና አካባቢው በአግባቡ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ለማወቅና የተከሠተ ችግር ካለ አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ይረዳል፡፡
በአጠቃላይ አልትራሣውንድ በእርግዝና ወቅት ከ12ኛው ሣምንት በኋላ የፅንሱን ፆታ ለመለየት ብሎም የሚወለድበትን ቀን ለመገመት ያስችላል፡፡