St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
ማስታወቂያ

ኮሌጃችን በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ከዚህ በታች በተገለጸው የትምህርት ፕሮግራም ለ2013ዓ.ም ትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የመመዝገቢያ መስፈርቶች እና ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን የምታሟሉ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡
1. ስልጠና የሚሰጥበት የትምህርት መስክ፣
በMasters in Medical Microbiology (Regular Programme/በመደበኛ ፕሮግራም)
2. የመመዝገቢያመስፈርት፣
2.1 Masters in medical Microbiology:
እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም የመጀመሪያ ዲግሪ በ(Laboratory Technology, Medicine Veterinary Medicine and Biology) ያለው ወይም ያላት

ተጨማሪ መስፈርቶች
ሀ. ከተመረቀ/ች በኃላ ቢያንስ ሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ላት/ እና ከሚሰሩበት መሰሪያ ቤት የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፣
ለ. ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ Official Transcript ማቅረብ የሚችል/የምትችል/፣
ሐ.ኮሌጅ የሚያዘጋጀውን የቃል /Interview/እና የፁሑፍ /written/ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል/፣
መ. በስፖንሰርሺኘ የሚማሩ ተማሪዎች የስፖንሰርሺኘ ደብዳቤ ከሚሰሩበት መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ፣
ሠ. ሁለት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡-
 አንድ አሁን ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት እንዲሁም፡-
 አንድ ከተማሩ ዩኒቨርስቲ ከአስተማሪዎቻቸው የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
3. የመመዝገቢያ ሁኔታ፡-
ኮሌጁ ለፕሮግራሙ ባዘጋጀው ሊንክ አማካይነት መመዝገብ ይችላሉ፡፡ (online registration at http://197.156.83.153/admissionpost/)
ማሳሰቢያ፡-ምዝገባው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በሚዲያ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ 10/አሥር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲሆን በተጨማሪም የመመዝገቢያ የማይመለስ200 (ሁለት መቶ ብር) መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
• የ መግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ወደ ፊት በኮሌጁ ማህበራዊ ገጽ ይገለፃል፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0118 96 51 25

ሪጅስትራር ጽሕፈት ቤት
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
Nov. 8 is the International Day of #Radiology, but radiology makes a world of difference every day #InternationalDayofRadiology 2020- Best wishes to everyone on the World Radiology day.
#IDoR2020
#radiography #radiology
Why I became a radiologist?

My name is Dr Ashenafi Regasa, MD, Radiologist. currently working in St.Peter's Specialized
Hospital .
When I was practicing medicine at Gonder College of medicine and health science as an intern,
during my pediatric attachment, lencountereda child with diagnosis of disseminated TB to
lung, pleura and pericardium. He stayed inthe ward for more than two months with on and off
type of shortness of breath and fever. I tried to figure out the management of the case and
consulted a senior radiologist and gave me clear picture of huge pericardial fluid with help of
chest x -ray and chest ultrasound, and told me actually to do therapeutic pericardial tap by
locating where to pierce. By that time the patient was critical, and I did the tap successfully
since it is huge and occupied almost the whole chest, drained abscess from pericardial space
and the child got relief for the moment. Then l go back to the radiologist and we did guided
pericardial abscess drainage but it recurred then l consulted a surgeon for pericardiotomy and
he was operated, discharged with complete resolution of symptoms
And another case came with malnutrition who is an eight months old child first born to the
parents who made me to think unlikely to be from poor feeding. The child has repeated
vomiting as the mother told me. So we sent for neck x - ray which actually showed neck mass.
Then we decided to do CT with senior consultation and teratoma was the diagnosis which for
she had surgical rermoval of the mass, the child got improved gained weight and discharged.
With those two cases and many others I started really getting interested in radiology since it
has pivotal role for patients diagnosis and guidance for their rational management.
she naasurgical removl.

With those two cases and many others I started really getting interested in radiology since it
has pivotal role for patients' diagnosis and guidance for their rational management
with those inspirational igniting reasons, as well as for the following reasons decided to be
radiologist.
These are
The wide scope and advancing technological aspect of ft.
The inter-disciplinery discussions and consultations will have advantagein building up of
knowledge
The less invasive guided diagnostic and therapeutic procedures
Since you study entire body, you will have holistic approach for patient's problem.
#IDoR2020
#SPHMMC
የኢትዮጵያ ራዲግራፈሮች እና ራዲሎጂክ ቴክኖሎጂሰቶች ማህበር ለሁሉም ራዲዮግራፈሮች እና ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂስቶች እንድሁም ለሁሉም ጤና ሙያተኞች እንኳን ለአለም ራዲሎጂ ቀን አደረሳችሁ እያለ በዚህ አስቸጋሪ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ጊዜ ከማንም በላይ ለማህበረሰባችሁ ቅድሚያ ሰጥታችሁ እያደረጋችሁት ላላችሁት ዘመን የማይሽረው አኩሪ ተግባር አለማመስገን ንፉግነት ነው፡፡ በዚህም ታላቅ ኩራት ሊሰማችሁ ይገባል፡፡

የሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ ሙያ በሀገራችን ኢትዮጵያ በድፕሎማ ደረጃ ከተጀመረ ከ 50 አመት በላይ ያስቆጠረ እና በድግሪ ደረጃ ከተጀመረ ከ 15 አመት በላይ ሆኖታል፡፡ ሙያውም በሀገራችን የጤና ስርአት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡ በተለይም ዘመናዊ የራዲሎጂ መሳሪያዎችን ማለትም  የራጅ፣ አልትራሳውንድ፣ ሲቲ ስካን፣ ኤም. አር. አይ እና የመሳሰሉትን በመጠቀም በሽታዎችን በቀላሉ መለየት በመቻሉ ለህክምናው የጀርባ አጥንት ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡ ከዚህም ባለፈም የራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ ሙያተኞች እስከ ገጠሩ የሀገራችን ክፍል በመግባት የራዲዮሎጂ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ የእናቶች እና ህፃናትን ሞት በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማደረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜም የራዲዮሎጂ መሳሪያዎች እጂግ አየዘመኑ በመምጣታቸው የራዲዮሎጂ አገልግሎቱም በከፍተኛ ሁኔታ በመሻሻል ላይ ይገኛል፡፡ የራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ ሙያተኞችም በትምህርት እና በልምድ ባገኙት የዳበረ ዕውቀት ማህበረሰባቸውን በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ ሙያተኞቹን በትምህርት ደረጃ እራሳቸውን እንዲያሻሻሉ ቢደረጉ (ማለትም በሁለተኛ እና ሶስተኛ ድግሪ ቢማሩ) ማህበረሰቡን ከዚህ በበለጠ ሁኔታ በጥራት እና ተደራሽነት ማገልገል ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ራዲግራፈሮች እና ራዲሎጂክ ቴክኖሎጂሰቶች ማህበርም በሀገራችን የድህረ-ምረቃ ትምህርት እንዲጀመር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ በመስራት ለይ ይገኛል፡፡ ይህም በቅርቡ እንደሚሳካ ማህበሩ ያምናል፡፡

በድጋሜ እንኳን ለአለም አቀፍ ራዲዮሎጂ ቀን አደረሳችሁ፡፡

 

የኑስ ሞላ

የማህበሩ ፕሬዚደንት
የልጆች የሳምባ ምች(ኒሞኒያ) ምንድነው?

ብዙ ጊዜ እናቶች ልጄን ብርድ መታው እና በጣም ያስላል ይላሉ:: እውነት ብርድ የሚባል የልጆች በሽታ አለ?? ይሄንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት እስኪ ስለ ሳምባ ምች የተወሰነ ነገር ልበል::
ሳምባ ምች(ኒሞኒያ ) ማለት የሳምባችን የታችኛው እና የመጨረሻው ክፍል መቆጣት እና መታመም ነው:: እንደሚታወቀዉ ሳምባችን ለሰውነታችን ኦክስጅን የሚባለውን ጠቃሚ አየር የምናስገባበት እና ካርቦንዳይ ኦክሳይድ የሚባለውን የተቃጠለ አየር የሚናስወግድበት አካላችን ሲሆን ይህ አካል ደሞ ኒሞኒያ በሚባለው በሽታ ሲጠቃ ሳምባችን ዉስጥ ያሉ ህዋሳት በከፍተኛ መጠን ስለሚቆጡ አየር የሚቀያየርበት የሳምባ ቅንጣት አካላት(Alveolus) በፈሳሽ ነገር ይሞላል በዚህም ምክንያት ሰውነታችን በቂ የሆነ ኦክስጅን አያገኝም:: የልጆች ሳምባ ደሞ በደምብ ያልዳበረ እና ጠባብ ስለሆነ በወቅቱ ካልታከመ እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል::
እንደ ዓለም የጤና ድርጅት(WHO) መረጃ መሰረት በ2017 ብቻ በዓለም ላይ 808,694 እድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት በሳምባ ምች ምክንያት ህይወታቸውን አተዋል:: ይህም ከአጠቃላይ የልጆች ሞት 15% ይይዛል ::
ሳምባ ምች(ኒሞኒያ) መንስኤው ምንድነው?
ይህ በሽታ ብዙ ጊዜ በአይን በማይታዩ የበሽታ አምጭ ጀርሞች ማለትም በቫይረስ, በባክቴርያ, በፕሮቶዝዋ አልፎ አልፎም በፓራሳይት አማካኝነት ሊመጣ ይቻላል:: ከነዝህም ዉስጥ በአብዛኞቹ ጀርሞች በሳል ወይም በንጥሻ ወቅት በትንፋሽ የሚተላለፉ ናቸው:: ከነዚህ በሽታ አምጭ ጀርሞች በተጨማሪም ኒሞኒያ በተለያዩ ኬሚካሎችም ሊመጣ ይቻላል::ለምሳሌ የጨጓራ አሲድ በድንገት ወደ ሳምባ ከገባ ኒሞኒያ ሊያስከትል ይችላል:: ከ 5 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ላይ የሳምባ ምች ብዙ ጊዜ መንስኤው ቫይረሶች ሲሆኑ የሚጀምረውም ከጉፋን መሰል ምልክቶች ነው::

ልጆችን ለሳም ባምች(ኒሞኒያ) የሚያጋልጡ ነገሮች
1.የላይኛው የትንፋሽ አካላት ኢንፌክሽን ለምሳሌ ጉፋን፤ የቶንሲል ኢንፌክሽን እና የመሳሰሉት
2. ቤት ዉስጥ የሚጨሱ ማንኛዉም የጭስ አይነቶች ለምሳሌ የሲጋራ የከሰል እና የእንጨት ጭሶች በሀገራችን በከፍተኛ መጠን ብዙ ህፃናትን ለሳምባ ምች እያጋለጣቸው ይገኛል::
3. ዝቅተኛ የበሽታ መከላከል አቅም(በምግብ እጥረት ወይም በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት)
4. በጣም ተጠጋግቶ መኖር እና በቂ የሆነ የአየር ዝውውር በሌለበት ቤት እና አካባቢ መኖር
5. የሳምባ የተፈጥሮ ችግሮች
6. የቫይታሚን ዲ እጥረት(ሪኬትስ)፦ በተለይ ፀሐይ በደምብ ያልሞቁ ህፃናት ለሳምባ ምች ተጋላጭ ናቸው::
ምልክቶቹ ምንድናቸው?
ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
ትንፋሽ ማጠር እና ለመተፈስ መቸገረ
ትኩሳት
ማቃሰት
ትውከት
የደረት ውጋት ወይም ህመም
ህፃናት ሲተነፍሱ የታችኛው ደረት ክፍል ወደ ዉስጥ ግብት ግብት ማለት ናቸው::
ልጆት ላይ እነዚህ የተጠቀሱት ምልክቶች ካሉ ባፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መውሰድ እና ማሳከም ይኖርቦታል::
ልጆች ሳምባምች(ኒሞኒያ) እንዳይዛቸው ምን እናድርግ መከላከያ መንገዶችስ ምንድናቸው?
ክትባት
ቤት ዉስጥ ማንኛዉም ጭስ አለማጨስ
ቤት ዉስጥ በቂ የ አየር ዝውውር እንዲሮር ማድረግ
የተመ ጣ ጠ ነ ምግብ መመገብ
እስከ 6 ወር ያሉ ህፃናት የእናት ጡት ወተት ብቻ እንዲወስዱ ማድረግ
ልጆች የፀሀይ ብርሃን በበቂ ሁኔታ እንዲያገኙ ማድረግ
ልጆችን ጉፋን ከያዛቸዉ ሰዎች በተቻለ መጠን ማራቅ
በመጨረሻም ብርድ የሚባል በሽታ አለ ወይስ የለም? ለሚለው ጥያቄ በ አ ጭ ሩ በ ዘመናዊ ሕክምና ዉስጥ ብርድ የሚባል ነገር የለም! አንዳንድ ሰዎች ብርድ የሚለው ቃል ከሳምባ ምች(ኒሞኒያ) ጋር ሲያምታቱ ይታያል ይሄ ትክክል አይደለም ቀዝቃዛ አየር የሳምባ ምች አያመጣም! በርግጥ ቀዝቃዛ አየር ሊያነሳሳቸው የሚችሉ በሽታዎች ይኖራሉ ለምሳሌ የአፍንጫ ወይም የሳይነስ አለርጂ እና የ መሳሰሉት:: ለማንኛዉም ማህበረሰቡ ብርድ የሚለውን ቃል ከምን ከምን ጋር እንደሚያይዘው ጠለቅ ያለ ምርምር ይጠይቃል ብዬ አምናለሁ::
ቸር እንሰንብት !!
ለሀገራችንም ቸር ወሬ ያሰማን !!

ዶክተር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም)
PICTURE: UNICEF
ዛሬ ዕለቱ ህዳር 8 የዓለም የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የሚወለዱ ህጻናት ቀን ነው፡፡ እኛም ቀኑን አስመልክተን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለንነባባችሁ እንዲህ አዘጋጅተናል፡፡ መልካም ንባብ፡፡
የመወለጃ ቀን ሳይደርስ መወለድ ማለት ምን ማለት ነው?

አንድ ህፃን የእርግዝና 37ኛ ሣምንት ከመጠናቀቁ በፊት ከተወለደ የመወለጃ ቀኑ ሳይደርስ ተወልዷል ይባላል፡፡

የችግሩ ስፋት ምን ያህል አሳሳቢ ነው?

በዓለም፡

• በየዓመቱ ከ 15 ሚሊየን በላይ ህፃናት የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ ይወለዳሉ፡፡

• በየዓመቱ ከ 1 ሚሊየን በላይ የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የተወለዱ ህፃናት ይሞታሉ፡፡

• የመወለጃ ቀን ሳይደርስ መወለድ ለተለያዩ የአካልና የአዕምሮ ጉዳቶች ይዳርጋል፡፡

• የመወለጃ ቀን ሳይደርስ መወለድ እድሜያቸው ከ 1 ወር በታች ለሆኑ ህፃናት ቁጥር አንድ ሞት ምክንያት ነው፡፡

• በዓለም ላይ የመወለጃ ቀን ሳይደርስ መወለድ እየጨመረ ነው፡፡

• ዝቅተኛ የገቢ መጠን ባላቸው ሀገራት ውስጥ የመወለጃ ቀናቸው፡ሳይደርስ የተወለዱ ህፃናት ከፍተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ ከተወለዱት ጋር ሲነፃፀር የመሞት እድላቸው 10 እጥፍ ነው፡፡

በኢትዮጵያ፡

• በዓመት 320,300 ህፃናት የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ ይወለዳሉ::

• ከ10 በሕይወት ከሚወለዱ ህፃናት አንዱ የመወለጃ ቀኑ ሳይደርስ ይወለዳል፡፡

• የመወለጃ ቀን ሳይደርስ መወለድ እድሚያቸው ከ 1 ወር በታች ለሆኑ ህፃናት ቁጥር አንድ የሞት ምክንያት ነው፡፡

ምክንያቱ?

የመወለጃ ቀን ሳይደርስ መወለድ በአብዛኛው ምክንያቱ በውል አይታወቅም፡፡ ብዙ መውለድ፣ የስኳር ህመም፣ በቤት ውስጥ በከሰል ወይም በእንጨት ማብሰል፣ የደም ግፊት እና ሌሎች ህመሞች አጋላጭ ሁኔታዎች ናቸው ተብሎ ይታመናል፡፡

መከላከል ይቻላልን?

የቤተሰብ እቅድ መጠቀም፣ ሴቶችን ማብቃት እና የቅድመ-ወሊድ ክትትል ማድረግ የመወለጃ ቀን ሳይደርስ የመወለድን እድል ይቀንሳል::

የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የተወለዱ ህፃናትን ሊያጋጥሙአቸው የሚችሉ ዋና ዋና ችግሮች ምን ምን ናቸው?

አስፈላጊው እንክብካቤ በወቅቱ ካልተደረገላቸው የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የተወለዱ ህፃናት ለሚከተሉት ችግሮች ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡
የሰውነት ሙቀት፡ የሰውነታቸውን ሙቀት መጠበቅ ስለማይችሉ በቀላሉ በቅዝቃዜ ምክንያት ለህልፈተ- ሕይወት ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡

መጥባት፡ ጡት ለመጥባት ሊቸገሩ ስለሚችሉ ተጨማሪ እገዛ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡ ስለዚህ የእናት ጡት ወተትን አልቦ በስኒ በማጠጣት ችግሩን መቅረፍ ይቻላል፡፡

ህመም፡ በአብዛኛው በሽታን የመከላከል አቅማቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ ስለዚህ በቀላሉ በህመም ይጠቃሉ፡፡

አዕምሮ፡ በቀለሉ የአዕምሮ ጉዳት ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ አይን፡ የአይን ብርሃንን የማጣት ጉዳት ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡

የመተንፈሻ አካላት ችግር፡ የሳንባ አለመዳበርን ተከትሎ የሚከሰት የአተነፋፈስ ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡

ሞት እና ጉዳትን መቀነስ ይቻላል?

አዎ! ቀላልና ከፍተኛ ቴክኖሎጂ በማይጠይቅ ህክምና እና እንክብካቤ 75 በመቶ የመወለጃ ቀን ሳይደርስ ከመወለድ ጋር የተያያዘ የህጸናት ሞትን ማስቀረት ይቻላል ፡፡ ቁልፍ እርምጃዎች የሚከተከሉትን ያካትታሉ፡፡

• በጤና ተቋማት መውለድ፣

• የቅድመ ወሊድ እና የድህረ ወሊድ ክትትል ማድረግ፣

• ለጨቅላ ህጻናት ህመሞች በአፋጣኝ ህክምና መሻት፣

• በጤና ባለሙያ የታዘዘን ህክምና እና እንክብካቤ በአግባቡ መተግበር

የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የተወለዱ ህጻናት በወደፊት ሕይወታቸው ስኬታማ ሊሆኑ ይችላሉ?
አዎ ! ምክንያቱም እነ አይዘክ ኒውተን (የሂሳብ፤ የፊዚክስ እና የስነ ከዋክብት ተመራማሪ)፤ አልበርት እንስተይን (የፊዚክስ ተመራማሪ) ስቲቪ ወንደር (ዘፋኝ፤ የዘፈን ግጥም ደራሲ እና አዘጋጅ) እና ቻርልስ ዳርዊንን የመሳሰሉ አንቱ የተባሉ የአለማችን ስኬታማ ሰዎች የተወለዱት የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ ነበር፡፡

መረጃውን ሼር ያድርጉ! ሼር!ሼር!
Tuberculosis
Key facts

A total of 1.4 million people died from TB in 2019 (including 208 000 people with HIV).

Worldwide, TB is one of the top 10 causes of death and the leading cause from a single infectious agent (above HIV/AIDS).

In 2019, an estimated 10 million people fell ill with tuberculosis(TB) worldwide. 5.6 million men, 3.2 million women and 1.2 million children. TB is present in all countries and age groups. But TB is curable and preventable.

In 2019, 1.2 million children fell ill with TB globally. Child and adolescent TB is often overlooked by health providers and can be difficult to diagnose and treat.

In 2019, the 30 high TB burden countries accounted for 87% of new TB cases. Eight countries account for two thirds of the total, with India leading the count, followed by Indonesia, China, the Philippines, Pakistan, Nigeria, Bangladesh and South Africa.

Multidrug-resistant TB (MDR-TB) remains a public health crisis and a health security threat. A global total of 206 030 people with multidrug- or rifampicin-resistant TB (MDR/RR-TB) were detected and notified in 2019, a 10% increase from 186 883 in 2018.

Globally, TB incidence is falling at about 2% per year and between 2015 and 2019 the cumulative reduction was 9%. This was less than half way to the End TB Strategy milestone of 20% reduction between 2015 and 2020.

An estimated 60 million lives were saved through TB diagnosis and treatment between 2000 and 2019.

Ending the TB epidemic by 2030 is among the health targets of the United Nations Sustainable Development Goals (SDGs).
( Source: WHO)
የጸረ ተሕዋሲያን መድሀኒቶችን በሐኪም ሲታዘዝልዎ ብቻ ይጠቀሙ!
ቢሻልዎትም እንኳን የታዘዙልዎትን መድሀኒት አያቋርጡ!
ሐኪም ካዘዙልዎ መድሀኒት ውጪ አይውሰዱ!
የስኳር ሕመም

የስኳር ሕመም በደም ውስጥ የሚፈጠር ፡ ከልክ በለፈ የስኳር መጠን ሳቢያ የሚከሰት ነው፡፡ በሽታው የሚከሰተው ሰውነታችን ኢንሱሊን ማምረት ሳይችል ሲቀር ነው፡፡ አሊያም ሰውነታችን ኢንሱሊኑን መጠቀም ሲያቅተው ነው፡፡ እንዲህ በሚሆንበት ወቅት በደም ዝውውር ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከፍ ይላል፡፡
የስኳር ሕመም ዓይነቶች
ዓይነት 1 የስኳር ሕመም
ይህ የስኳር ሕመም በአብዛኛው የሚታየው በሕጻናትና ወጣቶች ላይ ነው፡፡ በዚህ ህመም ቆሽት ኢንሱሊን ማምረት ያቆማል፡፡ ስኳር ያለው በደም ዝውውሩ ስርዓት ብቻ ነው፡፡ ወደ ሕዋሳት አይደረስም፡፡ስለዚህ የረሀብ ስሜት ፡ ከፍተኛ የውሀ ጥም ፡ድካም እና መጠኑ የበዛ ሽንት መታየቱ አይቀሬ ነው፡፡መፍትሄው ኢንሱሊንን በመርፌ መውሰድ ይሆናል፡፡
ዓይነት 2
ይህ የስኳር ህመም ዓይነት በብዛት የሚታይ ነው፡፡በአብዛኛውም በአዋቂ እድሜ ክልል በብዛት ይከሰታል፡፡ የበሽታው መነሾ ሰውነትኢንሱሊንን ለማምረት ወይም የተመረተውን ለመጠቀም የሚያስችለው የሰውነት ስርዓቶችበሚዛቡበት ወቅት ነው፡፡
ዓይነት 2 ስኳር ህመም ያለባቸው ሕሙማን ኢንሱሊንን ሕዋሶቻችው የሚቀበሉበት ሁኔታ ይቀንሳል፡፡ አልያም ስኳርን ወደ ውስጣቸው ለማስገባት የሚፈልጉት ኢንሱሊን እጅግ ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ወደ ሕዋሳቱ መግባት የነበረበት ስኳር በደም ዝውውር ውስጥ እየተከማቸ ሲሄድ ከፍተኛ የጤና ጉዳቶችን ማስከተል ይጀምራል፡፡
ለዓይነት 2 የስኳር ህመም የሚያጋልጡ ሁኔታዎች
• ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያለማድረግ
• ከመጠን ያለፈ ውፍረት
• በእድሜ መግፋት
• የቅርብ ቤተሰብ ውስጥ የስኳር ሕመም ያለ እንደሆነ
• የደም ግፊት እና ሌሎች ጉዳዮች

በእርግዝና የሚከሰት የስኳር ሕመም
ይህ ሕመም ነፍሰ ጡር የሆኑ እናቶች ላይ ይከሰታል፡፡

ሌሎች የስኳር የሕመም ዓይነቶች
ከተለያዩ ህመሞችና መድሐኒቶች እንደ (Stroid) ስትሮይድ በመጠቀም የሚመጣ ነው፡፡
t.me/spmmc

በቁጥጥር ስር ያልዋለ የስኳር ህመም ሊያመጣቸው የሚችላቸው የጤና ችግሮች:-

በቁጥጥር ሥር ያልዋለ የስኳር ሕመም መዘዙ ብዙ ነው። የሐኪም ምክር መስማትና ክትትል ማድረግ ችግሩን ይቀንሰዋል። እስቲ ሕመሙ የሚያመጣውን የጤና ችግር እንመልከት።

የኩላሊት ጉዳት ፡- ኩላሊት ቆሻሻን የሚያጣራበት ክፍል በመጉዳት ኩላሊት ስራ እንዲስተጓጎልና ብሎም አንዲቆም ያደርጋል፡፡

የነርቭ ጉዳት ፡-ለነርቭ ምግብ የሚያቀብሉትን ጥቃቅን የደም ስሮችን በመጉዳት የነርቮች ስራ መስተጓጎል ያመጣል። በተለይ በእግር እና በእግር ጣቶች ጫፎች ላይ የሚገኙት ነርቮች እንዲጎዱ በማድረግ የእግር ጉዳት ቁስል እና ጉዳቱ ሲብስ ደግሞም ለእግር መቆረጥ ሊዳርግ ይችላል፡፡

የዓይን ጉዳት ፡- ለዓይናችን ምግብ የሚያቀብሉትን ጥቃቅን የደም ስሮችን በመጉዳት ዓይናችንን ብርሃኑን እንዲያጣ ሊያደርግ ይችላል፡፡ሞራ ለመሳሰሉ የዓይን እክሎች ሊያጋጥም ይችላል፡፡

የልብ ሕመም ፡-በቁጥጥር ስር ያልዋለ የስኳር ህመም የልብ እና ተያያዥ ችግሮችን በተለይም የልብ ድንገተኛ እና በሂደት የሚመጣ ድካም እና ከፍተኛ የደም ግፊት ለመሳሰሉ ችግሮች በከፍተኛ ሁኔታ ያጋልጣል፡፡

የደም ቧንቧዎች መጥበብ ፡-የደም ቧንቧዎች ቁጥጥር ስር ባልዋለ የስኳር መጠን የሚመጡ ችግሮች ምክንያት ይጠባል፡፡በዚህም የተነሳ ደም እንደልብ በሰወነታችን ለመዘዋወር አይችልም ፡፡

ስትሮክ፡-በጭንቅላታችን ውስጥ ያለው የደም ቧንቧ ቁጥጥር ስር ባልዋለ ስኳር የተነሳ በሚከሰቱ ችግሮች እጅግ ጠቦ በሚዘጋበት ወይም በሚጎዳበት ጊዜ ለጭንቅላታችን ህዋሳት የሚደርሰው ኦክስጂን እያነሰ ይሄድ እና ስትሮክ ተብሎ ለሚመጣው የጤና ችግር የመጋለጥ አጋጣሚዎችን ይጨምራል፡፡ይኸውም በደም መፍሰስ ወይም መርጋት የሚመጣ ችግር ነው፡፡

(እባክዎ አንብበው ሼር ያድርጉ)
የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መውሰድ የሌለባት ሴት

በዚህ ፅሁፍ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች የሚለው የሚወክለው (COC) ሁለቱንም ሆረሞኖች(Estrogen and progestrone) የያዘውን የወሊድ መቆጣጠሪያ ይሆናል

ይህንን ዘዴ መጠቀም የሌለባቸው ሴቶች በሁለት ከፍለን እንያቸው።
ፈፅሞ መጠቀም የሌለባት
1. ከዚህ በፊት ስትሮክ(stroke) እና ተያያዥ ተሆነ የልብ ህመም፣ የደም መርጋት የነበረባት
2. የጉበት እጢ ወይም የጉበት ህመም
3. የጡት ካንሰር ወይም የመራቢያ አካላት ካንሰር
4. የታወቀ ወይም የሚጠረጠር እርግዝና ካላት ፈፅሞ መውሰድ የለባትም

ባትጠቀም እጅጉን ይመከራ

1. ከፍተኛ የሆነ እራስ ምታት ያለባት
2. የደም ግፊት፣ የስኳር ህመም፣ በቤተሰብ ውስጥ ጠንካራ የሆነ የስኳር ህመም ካለ
3. የሃሞት ከረጢት ህመም ወይም በኦፕሪሽን ተቆረጦ የወጣ ከሆነ
4. በህክምና ተመርምሮ ያልታወቀ ከማህጸን ደም መድማት ካላት ይህንን የወሊድ መቆጣጠሪ ባትጠቀም እጅጉን ይመከራል።

ጽሑፉን ከወደዱት(Like) በማድረግ ለሌሎችም (share)ያድርጉት፡፡
ቸር እንሰንብት
(ዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ )
ስፔሺያሊስት)
########################################################
የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች ተጨማሪ ጥቅም
th.me/spmmc

የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች(combined oral contraceptives) ካልተፈለገ እርግዝና ከመከላከላቸውም በተጨማሪ ሌሎች ጥቅሞች አሏቸው። እነዚህ በተለምዶው ፒልስ በሚል ስም የሚጠሩ ሲሆን በተለያየ የምርት ስያሜ ገበያ ላይ ይገኛሉ። ተጨማሪ ጥቅሞቻቸውም፤

ይከላከላሉ
· ከእንቁላል ማመንጫ፡ የማህጸን እና የትልቁ አንጀት ካንሰርን
· የጡት እና የእንቁላል ማመንጫ እጢወችን (benign)
· የአጥንት መሳሳትን

ይቀንሳሉ
· ከማህጸን ውጭ የሚከሰት እርግዝናን
· የውስጥ የመራቢያ አካላት ኢንፌክሽንን
· የደም ማነስን
· የወር-አበባ መዛባትን እና ህመምን
· ብጉርን

ጽሑፉን ከወደዱት(Like) በማድረግ ለሌሎችም (share)ያድርጉት፡፡
(በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)

ቸር እንሰንብት
በወር አበባ ዑደት እርግዝናን መከላከል

የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዶች ተፈጥሮአዊ እና ዘመናዊ በመባል ይከፈላሉ። ተፈጥሮአዊ ከሚባሉተ ውስጥ የቀን መቁጠሪያን በመጠቀም እርግዝና ሊፈጠር የሚችልበትን ቀኖች ላይ ከግንኙነት በመታቀብ መከላከል አንዱ ነው።

አጠቃቀሙ

1. ባለፉት 6 ወራት ውስጥ የወር አበባ የመጣበትን ቀናት ማየት
2. ከቀኖች ውስጥ ቶሎ ከመጣበት ቀን ላይ 21 መቀነስ
3. ከቅናሹ የተገኘው ውጤት ግንኙነት የሚቆምበትን ቀን ያመለክታል
4. የማህጸን ጤናማ ፈሳሽ በዚህ ወቅት ይቀጥናል
5. ፈሳሹ መወፈር ከጀመረ ከ3 ቀን በኃላ ግንኙነት መጀመር ይቻላል

የመከላከል ብቃት

1. እንደየስው ጥንቃቄ ይለያያል (3-80%)
2. የወንድ አጋሮችንም ተባባሪነት ይጠይቃል
3. አንዳንድ የወንድ የዘር ፍሬዎች 5-7 ቀን የሴት አካል ውስጥ ሊቆዩ ይችላሉ።

ምሳሌ
ያለፉት 6 ወራት የወር አበባ የመጣበት ቀናት፡ 27ኛ፡28ኛ፡29ኛ፡27ኛ፡28ኛ፡29ኛ ቢሆን
ትንሹ 27 ስለሆነ 27-21= 6። የወር አበባ ከመጣ ከ6ኛ ቀን ጀምሮ ግንኙነት መቆም አለበት ማለት ነው።

ጽሑፉን ከወደዱት(Like) በማድረግ ለሌሎችም (share)ያድርጉት፡፡
(በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)
Did you know that diabetes can lead to complications such as:

🔴 Stroke
🔴 Blindness
🔴 Heart attack
🔴 Kidney Failure
🔴 Amputation
🔴 Loss of limbs
🔴 Loss of life
የስኳር ሕመም መከላከያና መቆጣጠሪያ መንገዶች
1. የሰውነትዎ ክበደት ጤናማና ልከኛ ይሁን፡፡
2. የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎን እለት ተእለት ይጨምሩ፡፡ ቢቻልዎ በየቀኑ ለ30 ደቂቃ ላብ የሚስወጣ እንቅስቃሴ ማድረግ የሰርክ ተግባርዎ ይሁን፡፡ ስለአካል እንቅስቃሴዎ ሀኪምዎን ያማክሩ፡፡
3. ፍራፍሬ ፡ ቅጠላቅጠል እና የእህል ውጤቶችን አዘውትረው ይመገቡ፡፡ በደምዎ ውስጥ ያለውን ስኳር ለመቆጣጠር የሐይል ሰጪ ምግቦችን መጠን ላይ ሊኖራቸው የሚችለውን አስተዋጽኦ ያገናዝቡ፡፡
4. ጭንቀት የስወግዱ፡፡ በጭንቀት ወቅት የሚፈጠሩ ንጥረ -ቅመሞች በኢንሱሊን ምርትና በስራ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አላቸው፡፡
5. ሲጋራ አያጭሱ፡፡
6. የታዘዘልዎትን መድሓኒት በትክክልና በወቅቱ ይውሰዱ፡፡
7. የስኳር ህመም የጎንዮሽ ጉዳት መኖር አለመኖሩን ለማወቅ ከሀኪምዎ ጋር ይነጋገሩ፡፡
8. በደምዎ ውስጥ የሚኖረውን ስኳር በሚገባ ለመቆጣጠር ቁርጠኛ ይሁኑ፡፡፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የስኳር ህመም እና የኮቪድ-19 በሽታ
t.me/spmmc
አንድ ግለሰብ የስኳር ህመም ቢኖርበት በቀጥታ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ተጠቂ አይሆንም፣ ነገር ግን የስኳር ህመም በተለይም በቁጥጥር ስር ያልዋለ ከሆነ ለከፋ የኮሮና በሽታ ሊዳርግ ስለሚችል ታካሚዎች ተገቢውን ህክምናና ክትትል እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡
በተለይም ከስኳር ህመም ጋር ተደራራቢ የጤና ችግር እንደልብ ህመም፣ደም ግፊት፣ አስም ያለባቸው ታካሚዎች ለከባድ ህመም ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ የኮሮና ቫይረስ ህመም የስኳር ቁጥጥሩን ሊያውክ ይችላል፡፡
በተለይ በአይነት አንድ የስኳር ህሙማን ላይ መርዛማ አሲዶችን በመጨመር የሚከሰትን ድንገተኛ የስኳር መጨመር ሁኔታን (DKA) ሊያስከትል ይችላል፡፡ የኮሮና በሽታ ሲጠና በሰውነት ውስጥ የደም መርጋትና መዛባትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር እንደ አዲስ የስኳር ህመም የሚገኝባቸው ሰዎች እየጨመረ በመምጣቱ ምናልባት ቫይረሱ ኢንሱሊን የሚያመርቱ ቆሽት ውስጥ ያሉ ህዋሶች ሊያጠቃ ይችላል የሚሉ ሳይንሳዊ መላምቶች እየወጡ ይገኛሉ፡፡
አንድ የስኳር ታካሚ በኮሮና የተያዘ እንደሆነ ለቫይረሱ በሚመከረው መልኩ እራሱን ከመንከባከብ በተጨማሪ ስኳሩን መከታተል፣ መድሃኒቱን በአግባቡ መውሰድ፣ ሀኪሙን ማማከር እንደአስፈላጊነቱ የሚሰጡትን የመድሃኒት ማስተካከያና ምክር መተግበር አለበት፡፡
የከባድ የኮሮና ህመም ምልክቶች ትንፋሽ ማጠር፣ደረት መጫንና፣ ራስ መሳት ከታየ በአስቸኳይ በራስ ወይም በቤተሰብ አባል ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የህክምና እርዳታ ማግኝት ያስፈልጋል፡፡
የኮቪድ-19 በሽታ በስኳር ህሙማን ላይ የሚያስከትለው የጤና እክል የጠነከረ ሊሆን ስለሚችልና በሽታውን የሚያድን እስከ አሁን የተረጋገጠ መድሃኒትም ስለሌለ አዘውትሮ እጅን በሳሙና ውሃ በመታጠብ፣ አልኮል ያላቸውን የጀርም ማፅጃ በመጠቀም፣የአፍና የአፍንጫ ጭንብሎችን በመጠቀም ርቀትን በመጠበቅ፣ ያለአስፈላጊ ጉዞዎችንና ንክኪዎችን በማስቀረትና፣ ተገቢውን ጥንቃቄዎች በሙሉ በማድረግ ከበሽታው ራስን፣ቤተሰብንና ማህበረሰብን ይጠብቁ፡፡